March 17, 2015
12 mins read

ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በማስመልከት በተለያዩ ድረገጽ እና የዜና አውታሮች ላይ የህዝብን ንቃተ ህሊና ሊይጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በተለይም ደግሞ ፍትህ፣ነጻነት፣እኩልነትን አስመልክቶ እንዲሁም ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት የቀረውንና የኢትዮጵያዊያንን አዕምሮ በያዘው የሀገራችን ምርጫ ዙሪያ መነጋገሩ፣ መከራከሩ እና  ከምርጫው በፊት  መስተካከል የሚገባችውን ነገር ማውሳቱ የሰሞኑ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል። በርግጥ የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የተሰበረበት እና እስከአሁንም ድረስ የኢትጵያ ህዝብ ስብራት ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል። በመሆኑም እንደ እኔ እምነት ፍትህ ከሌለበት ሀገር ከፊታችን ካለው ምርጫ ምንም ይፈጠራል ብዬ የምጠብቀው ነገር ባይኖርም ግን ጥቂት የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምርጫውን አስመልክቱ እየሰሩት ያለው ቅስቀሳ እና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን መንግስት ከስልጣኑ በማውረድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየከፈሉት ያለው መስዋትነትና ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ ።  እርግጥ ነው ከሁሉም አቅጣጫ የሚስተጋባው የኢትዮጵያዊ ድምጽ ሀገርን ከመውደድ እና ለሀገር ነጻነት እንዲሁም ሉአላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት እስከሆነ ድረስ ትግሉ ይፋፋም ይቀጥል ያስብላል።

ፍትህ የሰፈነበት ምርጫ ሊካሄድ የተገባ መሆኑን ሁላችንም እንስማማበታለን። የሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ናፍቆት ሰላም የሰፈነባት ሀገር ላይ ምርጫው የህዝብ እንዲሆን ነው። ይህም ህልም በምድራችን ላይ ተጨባጭ ይዞታ ኖሮት  ተግባራዊ ቢሆን ሀገራችን ምን አይነት ቅርጽ ሊኖራት እንደሚችል ማሰብ ከባድ አይደለም። ስለሆነም በአሁን ወቅት   በምድሪቷ ላይ እየገነነ የመጣው ግፋዊ  አገዛዝ ወደበለጠ ደረጃ ደርሶ እጅግ ከመክፋቱ በፊት የትውልድ ሁሉ ናፍቆት የሆነውን እኩልነት እና  ህዝብ ለብዙ ጥፋት ታልፎ በተሰጠበት እንዲሁም ከሀገሪቷ ፊት ለፊት ታላቅ የሆነ ክስረት ተጋርጦ ባለበት የአምባገነን ስርዐት ዘመን የሰከነና የተረጋጋ ህይወትን በኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት ታላቅ የሆነ ርብርቦሽ ያስፈልጋል።

ይህንን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘቀጠ የፓለቲካ ስርዐት ወደኋላ ከተጎተተበት ኢፍትሐዊ አሰራሩ ተናጥቆ ለማውጣት እና የሰለጠኑ ሀገራት ወደደረሱበት የነጻነትና እና የእኩልነት ክልል ለማድረስ ከጨዋታ ውጪ የተደረጉት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ከማንኛውም የእድገት  እንቅፋቶች የጸዳ አላማ ያላቸው ሀገር ወዳዶች የተዘጋባቸው በር ክፍት ሆኖ  በሁሉም ሀገራዊ አቅጣጫ ጉዳይ ላይ ለምድራቸው የሚቻላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ በተለይም ደግሞ ከፊት ለፊታችን በወያኔ ቁጥጥር ስር ያለው ምርጫ በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሊሂቃን እድሉ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ ማድረግ ተመራጭነት አለው። ይህን መሰሉ ተግባር በምድሪቷ ላይ የጸና እስከሚሆን ድረስ  እንዲሁም የገዥውን ቡድን እድሜ መቀጠል ፣ የተመዘበሩ ኮሮጆዎች እና የምርጫ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ወቅታቸውን እየጠበቁ ያለፈውን ልማዳቸውን ለመድገም የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በሁሉም አቅጣጫ መታገል እንደሚገባን እና ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽ እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በስተቀር በሌላ መንገድ ወያኔን ማክሸፍ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል።

እውነታውን በመሸፋፈን  ወያኔ በምግብ ራሳችንን ችለናል እያለ  በሚቀልድበት በዚህ የረሀብ ዘመን ዘወትር ሽቅብ እየወጣ ሰማይ ለመንካት እየተመነጠቀ ስላለው የኑሮ ውድነት ህዝቡም ሲያወራ ወያኔም ስለ ‹‹11%›› እድገት ሲደሰኩር፣ ህዝብ ስለ ስራ-አጥነት እና  እርዛት ሲያወራ ወያኔ ‹‹ስለኢንቨስትመንት መስፋፋት›› ሲያብራራ፣ ህዝብ ስለረሃብ ሲያወራ መንግስት ‹‹ስለጥጋብ›› መፈክሩን ሲያሰማ ፤ ህዝብ ስለዳቦ ሲጮህ የወያኔ መንግስት ‹‹ስለመሰረተ ልማት›› እያወሩ እርስ በርስ መግባባት ተስኗ ቸው 23ኛ አመት ዐመት አልፎ ተጋምሷል ። ይህ ያላቻ ጋብቻ ይባላል። በድግሳቸው ቀን  አንዱ የደስታ ሌላኛው የሃዘን ሻማ በማብራት አክብረው አሳልፈዋል፡፡ ከእንደዚህ አይነት ስርዓት አልባ ገዢ ጋር ፍቺ ብቸኛ አማራጭ ነው። ምርጫውም ፍትሀዊ እና የህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያዊያን የሚያመጣው ምንም አይነት ፈውስ እንደሌለው የታወቀ ይሁን። ይልቁኑም የከዚህ በፊቱን ውሸት እና ማስመሰል ረቀቅ ባለ ማደናገሪያው ለመድገም እየተሯሯጠ መሆኑ ግልጽ በሆነበት በዚህ ወቅት አምባገነኑን ወያኔን ከምርጫው ውጭ ለማድረግ በየትኛው ጎዳና ብንሔድ በትግላችን ግቡን እንደምንመታ  እና የተለያዩ የትግል ልምድ ስልቶች ልውውጥ አድርገን ሀይላችንን በማጠናከር በአንድ የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽን  የሁላችን ምርጫ ይሁን በማለት መነሳት አለብን።

የኔ የግል ምልከታዬ በአሁን ሰአት ሀገራችን ባለችበት ደረጃ የትግላችን ኢላማ እና መድረሻው መሆን የተገባው አስቀድሞ በሐስት የወያኔ ነቢያቶች ለተነበዩለት   ምርጫ ተባባሪ ሆኖ በመሰለፍ አምባገነኑ አገዛዝ እንዲቀጥል አስተውጽኦ ማበርከት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወስነውሀገር የምትተዳደርበት ልማታዊ የሆነ ህግ በምድሪቷ ላይ የበላይ እንዲሆን የዜጎች እኩልነት እና ሰብዓዊነት የሚከበሩባቸው ስርዓት በማስፈን ወያኔ በጭቆና የተቆጣጠርውን ስልጣን በመቀማት የህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ  ፍጹም የሆነ ብሩህ ተስፋ የሚታየባትን ኢትዮጵያን መፍጠር  ነው።

መቼውንም ቢሆን ወያኔ ለነጻ ፍትሀዊ ምርጫ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነት ለምን አልቆመም ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ይህ ቡድን “ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ምንጊዜም ቅኝቱ እንብላ እንብላ ነው” እንዲሉ ከፅንሰቱም ፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርዓት መልካም የሆነ አስተዳደር መጠበቅ የሚታሰብ አይደለምና እንደገና ሌላ ምዝበራ በሀገርችን ላይ ከመፈፀሙ በፊት ምርጫው ጋር ሳንደርስ በፊት የህዝባዊ አመፅ ትግልን በመምረጥ ወደ ውጤት እንጓዝ።  ምርጫው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመርጠው እና የሚወዳደረው እንጂ ለተሳትፎ ብቻ ብቅ ብሎ በወያኔ ሻጥር የሚሸነፍበት ሊሆን አይገባም።
ለውጥ የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙኃኑ ሲባል የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሐትን አስወግደን በቂ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው መንገድ ወያኔን ማስወገድ  ይቻላል፡፡ ለውጥ የሚመጠበትን መንገድ ፈርቶ እና ህዝባዊ አምፅን  ተቃውሞ  ለውጥን መጨበጥ ዘበት ነው፡፡ ‹‹መፍራት ያለብን ፍርሐትን ራሱን ነው›› እንዲሉ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፡ የትኛውንም ወደኋላ የሚጎትተንን ፍርሀት ትተን ድጋሚ በምርጫው ከመጭበርበራችን በፊት አስቀድመን በህዝባዊ አመጽ መታገንልን እንምረጥ። ከምርጫው በፊት የኢትዮጵያውያን ምርጫ  በህዝባዊ አመጽ ትግል ለዘመናት በአንባገነንነት በስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን በማሰር ፣ በመግደል ላይ ያለውን አረመናዊ መንግስት ከስልጣን ላይ ማውረድ ይሆን ነው  መልዕክቴ ።
[email protected]

የሕዝብ ትግል ያቸንፋል !!!

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop