June 4, 2014
5 mins read

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት

ለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሕዝብን መብት በመቀማትና አፍኖ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግሥት ዜጐች በአገራቸው ውስጥ በመዘዋወር ሰርተው እንዳይኖሩ ያገደ ብቻ ሳይሆን በተወለዱበትና እየኖሩበት በአለው ቀያቸውም የገዠው ፓርቲ አባል ካልሆኑ ወይም ደግፈው ካልቆሙ ይሰደዳሉ፣ ይበታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም ንብረታቸውን ይቀማሉ፡፡ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ደግሞ ጫናው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ በዚሁ መመሪያቸው መሠረትም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከልም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህልም፡-


1. በደቡብ ክልል በሰሜንአሪ ወረዳ በጉዛ ዚፍቲ ቀበሌያት የሚኖር ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቻውን ተጠቅመው በመኢአድ ጥላ ሥር ስለተደራጀና ጽ/ቤት ስለከፈቱ ብቻ ሦስት (3) አመራሮቻቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍትህም ተከልክለው ሰሚ አካል ሊያገኙም አልቻሉም፡፡


2. በጐፋ ልዩ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አመራሮችና አባላት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ስለተደራጁ ብቻ ከፍተኛ ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፤ የፓርቲው መታወቂያቸውንም እንዲነጠቁ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜም አስራ ሁለት (12) የመኢአድ አባላት በሳውላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


3. በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ የመኢአድ የወጣቶች የአመራር አባል በጩቤ ተወግተው ለፍትህ አካላት አቤት ቢሉም መልስ አጥተው በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡
4. በአማራ ክልላዊ መንግስት በአንካሻ ወረዳ የሚገኙ የመኢአድ አመራር በኢህአዴግ ካድሬዎች ተደብድበው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ ማለትም ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በጐንደር ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የብዙ ዜጎች ሕይወት እንዲጠፋ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ዜጎችም ከቤታቸው እየታፈኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንዲወሰዱ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡


5. በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአደረጉት ግጭት ምክንያት ብዙ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተው፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡


ይህ የሚያሳየን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የማስተዳደር ስልት ችግሩን በዘዴ በመፍታትና በማግባባት ሳይሆን ኃይልን በመጠቀም ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ነው፡፡
በአጠቃላይ እንደዚህ ያሉ የከፉ የሰብአዊ መብት ረገጣ አገር ተረካቢውን ወጣት ምሁር ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡


ስለዚህ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመቃወምና ከተበዳዮች ጐን የቆመ መሆኑን ለማሳየት “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር በመላ አገሪቱ ሕዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ከዜጎች ጐን የቆመ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት ሰላማዊ ሰልፎችን አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረትም እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በጐፋ ልዩ ዞን በሳውላ ከተማ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አድርጓል፡፡


ስለዚህም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት ሲል ከጐናችን እንዲሰለፍ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop