May 3, 2013
16 mins read

“አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም በእውነትህ ኮርተህ ሙት!” ሰርካለም ፋሲል

እስክንድር ነጋ
“አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም በእውነትህ ኮርተህ ሙት!” ሰርካለም ፋሲል 1

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረ ኪዳን እንደሚከተለዉ የዛሬዉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሎና አሳዛኝ ክስተት እንደሚከተለዉ አስቀምጦታል፡

የእነአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ነገር

በጠቅላይፍ/ቤት
ወሰንሰገድገብረኪዳን

“ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች” – አዝማሪ

ሌሊት ሌሊት እንደ “ዳዊት ደጋሚ” ስለማመሽ ጠዋት ጠዋት ተጋድሜ ማርፈድ ልማዴ ነበር፡፡ ዛሬ ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ  26 ቀን 2005 ዓም፣  ካለወትሮዬ በጠዋት ከዕንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ እናም ወደ ጠቅላይ ፍ/ ቤት አመራሁ። ዕለቱን እያሰ ብኩ፡፡

የዛሬው ሐሙስ በክርስትና አማኞች ዘንድ በተለየ መልኩ የሚታሰብ ቀን ነው፡፡ ክርስቶስ ትህትናን በተግባር ያስተማረበት ቀን ነው፡፡የሐዋርያዎቹን እግር ዝቅ ብሎ ያጠበበት ቀን፡፡ በልማድም ቢሆን ሐሙስ የቀን ቅዱስ ነው ይባላል፡፡ ስለዚህም ከእነ አንዱአለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይግባኝ ማመልከቻ “የተቀደሰ”  ዜና እሰማለሁ የሚል ሃሳብ ተሞልቼ ነበር  6 ኪሎ ወደሚገኘው ጠ/ፍ ቤት በእግሬ ያቀናሁት፡፡

በእግሬ ያመራሁት ተከሳሾቹ ከማረሚያ ቤት የሚመጡት አርፍደው ነዉ በሚል እሳቤ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጠዋቱ  3  ሰዓት ላይ እስረኞቹ ችሎት ገብተው ተቀምጠዉ ነበር፡፡ ወዲያው ከእስረኞቹ ውጪ ችሎቱን ለመከታተል የመጡ ሁሉ ከክፍሉ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ችሎቱ ውስጥ አንዱአለም አራጌ እና እስክንድር ነጋ እንዲሁም በሌላ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች 3  እስረኞች ከአጃቢዎች ቀሩ፡፡ በእነ አንዱአለም መዝገብ ተከሰው ይግባኝ የጠየቁት ሌሎች እስረኞች በስፍራው አልታዩም፡፡ እኛ ኮሪደር ላይ ተሰባስበን ለምን ሌሎቹ እስረኞች እንዳልመጡ እየተወያየን ደቂቃዎች በደቂቃዎች ላይ ነጎዱ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች ”

3 ሰዓት ከ50  ደቂያ ሲል ናትናኤለ መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)  አንድ አንድ እጃቸውን በካቴና ታስረው ከውጪ ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ኮሪደር ላይ ችምችም ብሎ በሚጠብቃቸው ሰው መሃል እያለፉ አንዱ በግራ እንዱ በቀኝ እጁ እየጨበጡኝ አልፈው ወደ ችሎት ገቡ፡- በፖሊስ ታጃበው፡፡ 3  ሰዓት ከ55  ደቂቃ፤ ዳኞች ወደ ችሎት ገብተው ቦታቸውን ያዙ፡፡ ወዲያው ታዳሚ እንዲገባ ፈቀዱ፡፡ ጥቂት ለችሎቱ በር በቅርበት የቆሙ ታዳሚዎች ገቡ፡፡ የደሃ ሳሎን የምታክለው(ደሃ ሳሎን አለው እንዴ?)

ችሎቷ ወዲያው ጢም አለች፡፡ 4 ሰዓት የግራ ዳኛው አንድ እስረኛ ጠሩ፡፡ እናም ውሳኔያቸውን በቃል ቅልብጭ አርገው ተናገሩ – በነፃ፡፡ በሌላ ክስ የታሰረውን ሁለተኛ ተከሳሽ ጠሩ – በነፃ፡፡ እኔ ከጠቀመጥኩበት ወንበር ጀርባ ያሉ ሁለት ሴቶች ወደመሬት ተደፍተው በደስታ አለቀሱ፡፡ መደሰት እንጂ ማዘን አይገባም ብለን ገፋፍተን “አስወጣናቸው፡፡”  የቀጣዩን የእነ እስክንድርን መዝገብ ውሳኔ ለመስማት እየቋመጥን፡፡

“ሀገሬን ሀገሬን -የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች”

የመጀመሪያዎቹ መዝገቦች ፍርድ ሲነበብ እኔ በዚያች ጠባብ አዳራሽ ውስጥ ተደራርቦ የተቀመጠውን ሰው ሆን ብዬ ቆጠርኩ፡፡ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ቦታ አጥታ ከእኔ ጋር አንድ ወንበር ተዳብላ ተቀምጣለች፡፡ ሌሎችም ሰዎች እንደዛው፡፡ ብቻ በዚያች ጠባብ ችሎት ውስጥ ከተሳሾች፣ ከጠበቆች፣ ከእስረኞችና ከችሎት አስከባሪዎች ውጭ 48 ሰው ታፍጓል፡፡ ሌላው ሰው በቦታ ጥበት ኮሪደር ላይ ተኮልኩሏል፡፡ የመሃል ዳኛው ከፊት ለፊታቸው ተደጉሶ የተቀመጠውን ፋይል እየነካኩ በለሠለሰ አንደበት

“እንግዲህ እናንተ ፍ/ቤቱን … ውሳኔ መቀበል አለባችሁ አሉ፡፡

በአንድ ወንበር ላይ ተፋፍገን የተቀመጥነው እኔና ሰርካለም እርስ በርስ ተያየን፡፡ ዳኛው ቀጠሉ“በዚህ መዝገብ የቀረበው ክስ በባህሪው ከሌሎች መዝገቦች የሚለይና ውስብስብነት ያለው ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 652/2001 በመሆኑ፣ ሕጉ የተቃኘበትን መርህ መቃኘትን” እንደሚጠይቅ አብራሩ፡፡

በዚህ መሰረት በአምስት የይግባኝ ፋይሎች የቀረቡትን አቤቱታዎች ተያያዥነት ያላቸው በመሆናቸው ፍ/ቤቱ በአንድ ላይ በጥልቀት መርምሮ ዉሳኔ መስጠቱንና ገለፁ፡፡ በቅድሚያ የአቃቤ ሕግን ክስ፣ ቀጥሎም የይግባኝ ባዮችን አቤቱታ፣ ከዚያም በከሳሽና በተከሳሽ ወገኖች የቀረቡትን ምስክሮችና ማስረጃዎችን ይዘት በመመርመር ፍ/ቤቱ የሰጠውን ትንታኔና ውሳኔ በንባብ እንደሚያሙ አሳውቁ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን- የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች”

ከእኔ በስተቀኝ የተቀመቡት ዕድሜአቸው ወደ ሰባዎቹ የሚጠጋ ጎስቋላ እናት ዳኛው የሚያነቡትን ነገር በቅጡ የተረዱት አይመስሉም፡፡ አንዴ ወደ እኛ፣ አንዴ ወደተከሳሶቹ እየተንጠራራሩ ያያሉ፡፡ እንደዘበት ሸብ ያደረጉት ሻሻቸውን አልሮ የወጣውን ሽበታቸው እየደባበሱ ቁና ቁና ይተነፍሳሉ፡፡ ገፅታቸው ላይ አንዳች ድካምና የሕመም ስሜት የሚነበብባቸው እኚህ እናት ምቾት አልተሰማቸውም፡፡ ዳኛው ንባባቸውን ከጀመሩ ድፍን አንድ ሰዓት አልፏል፡፡ ድንገት ወደቀኝ ዞር ስል ሴትዮዋ የሆነ ስሜት ስልም ሲያደርጋቸው አየሁ፡፡

ሰርካለምን በክርኔ ጎሽመ አድርጌ ወደሴትየዋ ጠቆምኳት፡፡ እጆቺን በእኔ ላይ አሸጋግራ “አይዞዎት”  እያለች ጎናቸውን ጨመቅ ጨምቅ፣ አሸት አሸት አደረገቻቸው፡፡ ወዲያው የእፎይታ ትንፋሽ በረዥሙ ተንፍሰው “ነቃ”  አሉ፡፡ የክንፈሚካኤል እናት መሆናቸውን ነገረችኝ እየደባበሰቻቸው፡፡ የእስረኛ ቤተሰቦች ከመላመድ ብዛት እርስ በርስ የሚበረታታበት ሕክምና መሆኑ ነው፡- አልኩ ለራሴ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን- የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች”

ዳኛው ንባባቸውን አላቋረጡም፡፡“ አንዱአለም አራጌን በሚመለከት፡- ሕገመንግስታዊ መብትን ሽፋን አድርጎ በመጠቀም፣ ከግቦት 7 ጋር ለሽብር ተግባር በመመሳጠር፣ ወጣቶችን ለሽብር ተግባር በማደራጀት፣ ለሽብር በመምራት… ወዘተ ናትናኤል መኮንን፡-እንዲሁ ወጣቶችን ወኪል አስተባባሪ በመሆን…. ክንፈሚካኤል ደበበ በህኑዕ የግንቦት 7  አባለ በመሆን፣ በማሴር…. እስክንድር ነጋ በሕገመንግስቱ ለዜጎች የተሰጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሽፋን በማድረግ የግንቦት ሰባትን ዓለማ ለማስፈፀም፣ በስብሰባና በፅሁፍ ሕዝብን ለአመፅ በመቀስቀስ፣ ለኢሳት መረጃ በማቀበል፣ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔ አለም ጋር በመመሳጠር..ወዘተ”  መከሰሳቸውን መረጃና ምስክር የቀረበባቸው መሆኑን አተቱ፡፡

ሁሉም ተከሳሾች በተራ ቁጥር 1  በቀረበባቸው ክስ የሥር ፍ/ቤት ያሳለፈውን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚነቀፍ ሆኖ እንዳላገኘው ገለፁ፡፡ ሁለተኛው ክስ በአንደኛው ክስ ስር የሚጠቃለል በመሆኑ መሻሩንም አክለው አሳወቁ፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በ1ኛ እና በእራተኛ ክስ ጥፋተኛ ተብለው የተወሰነባቸው ውሳኔ የሕግ ስህተት እንደሌለበት አሳወቁ፡፡ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው የተገኙበት አንቀፅ 17  እና 18  ዓመት እስራት በአጠቃላይ ድምር ወደ 34  ዓመት እስራት የሚደነግጉ ቢሆንም፣ በሃገሪቱ ከ25  ዓመት በላይ እስር ስለማይፈቀድ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲፀና መወሰኑን ገለፁ፡፡ይሁን እንጂ የሥር ፍ/ቤት ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)  ፍ/ቤት በመድፈር በተጨማሪነት የተላለፈበት የ5 ዓመት እስር እንዲሻር ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡

“ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች ”

የፍርዱ ውሳኔ ምንም ለውጥ እንዳላመጣ ቀድማ የተረዳችው ሰርካለም ፋሲል “እስክንድር ወንጀለኛ ነው ከተባለ፣ ወንጀሉ ሃገሩን መውደዱ ነው” ብለህ ፅፍ አለችኝ -በንዴት። “ግንቦት 7  የእስክንድርን እጅ የመጠምዘዝ ኃይል የለውም”  አለችኝ በቁጭት፡፡

ችሎቱ ውሳኔውን አሳውቆ ዳኞች እንደተነሱ፣ ተከሳሾች ከፍርድ ሳጥን እየወረዱ ባለ እስክንድር እልሀ በተናነነቀው ስሜት ጮክ “አትጠራጠሩ እውነት ተደብቃ አትቀርም”  አለ፡፡ ናትናኤል “የተከራከርነው ፍትህ እናገኛለን ብለን አይደለም፤ ፍትህ ወዳድ ስለሆንን ነው” አለ፡፡ አበበ ቀስቶ “ ለማንኛውም እዚህ መጥታችሁ በእናንተ ኮርተናል”  ሲል በችሎት የሰገኘውን ሰው አመሰገነ፡፡ “አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም ሙት፣ በእውነትህ ኮርተህ ሙት!”  አለች ሰርካለም እንባ እየተናነቃት፡፡ ወዲያው ፖሊሶች ታዳሚውን እየገፋፉ ከችሉት አስወጡ፡፡ በሌላኛው በር አንዱአለምና እስክንድርን አንድ ላይ፣ ክንፈሚካኤል እና ናትናኤልን በአንድ ላይ በካቴና አስረው፡- ወደ ቃሊቲ፡፡“

“አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም ሙት፣ በእውነትህ ኮርተህ ሙት!”  አለች ሰርካለም እንባ እየተናነቃት። ወዲያው ፖሊሶች ታዳሚውን እየገፋፉ ከችሉት አስወጡ፡፡ በሌላኛው በር አንዱአለምና እስክንድርን አንድ ላይ፣ ክንፈሚካኤል እና ናትናኤልን በአንድ ላይ በካቴና አስረው፡- ወደ ቃሊቲ፡፡

አይዞዎት እማማ፤ ወደፊት የሚመጣው አይታወቅም አልኳቸው ” የክንፈሚካኤልን እናት፡፡ በእኔ ቤት ማፅናናቴ ነው፡፡“ አዎ የሚመጣው አይታወቅም፣ ይኼስ ይመጣል ብሎ ማን አሰበ፡፡ እናንተ ወጣቶች ራሳችሁ አይ ዞአችሁ፡፡ ታሰሩ፡፡ አይዞአችሁ፡፡ ግን አትሙቱ”  አሉኝ የክንፈ እናት፡፡“

አይዞአችሁ ታሰሩ!  ግን አትሙቱብን!”  የእኚያን እናት አባባል እያላመጥኩ ከዳኝ፡፡ እንባዬ መጣ፡፡ ዓዓይኔን እንዳያዩ ፊቴን አዞርኩ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች ”

አበቃ፡፡

 

5 Comments

  1. Minim enkuwa zare fird Biguwadelm…..Eskindir Nega You are Ethiopian Here…..We will always be with You….Death to Weyane Death to Bereket Simon and his slave Agames.

  2. GOD BLESS YOU AND YOUR FAMILY SERKALEM! HISTORY WILL REALLY MAKE HIM FREE; HE IS RIGHT!

  3. Thank you Serkalem, and thank you Wesenseged, thank you all attendees! Ante yene Jegna …! “atimutubin”. Long ago I met Abate Kisho’s Dad and tried him- he replied “he is not like a bar of salt to melt in their prison cell”. Sometime later, an old Sidama women tried Meles: “we’re here to die … Free our Son …”. The current premier was one of the dignitaries attending this same session! If the great Sidama people’s quest for justice bent and made Meles inert, the enormity of the quest for these legendery prisoners of concsience would be at a scale quantum today and a hurricane tonight. Beware, you can’t afford the drama, the details of which have been kept under wraps. We don’t await for Jesus Christ to come. Now we have thousand reasons to say “ashaferegn emmmmmmmbi!” Freeing Eskinder can’t make you “compassionate” as it would never deter us from our long run toward eliminating tyrany and injustice from the land.

  4. I am a grown man. Today, I cried while reading TPLF’s crulity on Eskinder, Andualem, Natnael, and Abebe Kesto.

  5. Last time I read on this website one article,the article was written by the so called “independent journalist Temesgen Desalegn”. He told us the judge will free Eskinder….I wonder what he is going to write this time… may be another fabricated News…denqem gazetegna…kkkkk

Comments are closed.

02
Previous Story

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወግ – ከበእውቀቱ ስዩም

vegas ethiopian and erirtian taxi drivers
Next Story

በቬጋስ ላለፉት ሁለት ወራት በሥራ ማቆም አድማ ላይ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች በድል ወደ ሥራ ተመለሱ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop