የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት የጦርነቱን ገፅታ ሙሉ ለሙሉ መቀዬር ፈልጎ ሁሉን አቀፍ ፀረ-ህዝብ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ሰነባብቷል።
ያልታጠቁ ሲቪሊያንን መጨፍጨፍ፣ የአርሶ አደር ሰብል ማውደም፣ የእምነት ተቋማትን ካምፕ በማድረግ ማራከስ፣ ዜጎችን ወደ ማጎሪያ ካምፖች ማጋዝ እና ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ መውሰድን ጨምሮ በርካታ ፀረ -ህዝብ ተግባራትን በመፈፀም ላይ ነው።
አንዳንድ አካባቢወችም ለመሰረታዊ ፍላጎት የሚውሉ ሸቀጦች እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ ጥሏል፤ ለአብነት ጠላት ከደጋ ዳሞት ከተባረረ ግዜ ጀምሮ ማንኛውም ሸቀጥ ከደምበጫ ወደ ፈረስ ቤት እንዳይገባ እገዳ ጥሏል።
በዚህ ሁሉ የጥፋት በትር አልበገር ያለውን የአማራ ህዝብ በስነ ልቦና ለማዳከም በኢኮኖሚም ለማድቀቅ አስቦ በበርካታ ቦታወች የአርሶ አደር መሳሪያወችን እየነጠቀም ይገኛል።
ይህንኑ የጥፋት ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ከሰሞኑ ደግሞ የአርሶ አደሩን የቀንበር በሬ መዝረፍን አዲስ የጥፋት ስልት አድርጎ ይዟል። ለአብነት ሕዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሰሜን ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ የእናቱን እና የሁለት አርሶ አደር ወንድሞቹን ጨምሮ የመሪያችን የአርበኛ ዘመነ ካሴ ቤተሰቦች ንብረት የሆኑትን 105 የቀንድ ከብቶች ከአራት እረኞች ጋር በመዝረፍ ወደ ባህርዳር መኮድ ወስዷቸዋል።
ጠላት የአርሶ አደሩን በረት ባዶ በማድረግ ከህዝብ ጋር የተጋባውን እልህ ለመወጣት የሚያደርገውን ፀያፍ ተግባር መታገል ታሪካዊ ጥሪያችን መሆኑን ስለምንረዳ በልኩ ተጋድሎ እያደረግን እንገኛለን።
በመሆኑም ወራሪ ሰራዊቱ ከዚህ ተግባሩ የማይታቀብ ከሆነ በጦር ሜዳ ከምናደርገው ተጋድሎ ጎን ለጎን አገዛዙ በህዝባችን ላይ ለሚፈፅመው የዘረፋ ወንጀል ተባባሪ የሆኑ የብልፅግና ካድሬ እና የምሊሻ ንብረት እና የቁም እንስሳትን በማካካሻነት ወስደን ለተጠቂ ወገኖቻችን ለማስረከብ የምናደርገው የአፀፋ እርምጃ መኖሩ ታውቆ ሁሉም ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም
©አስረስ ማረ ዳምጤ