ከቴዎድሮስ ሐይሌ
“አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?
ትንቢተ ኤርሚያስ “13:27
ውሃ ሽቅብ አይሄድም :: በሬ እያለ ወይፈን አያርስም:: ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ባህላችንም ሆነ በሃይማኖታዊ ስርአታችን መንፈሳዊ አባቶችን ማክበር የነበረ ማህበራዊና መንፈሳዊ ሃብታችን ነው። ወንጌሌም ‘’አክብር ገጸ-አረጋዊ እንዲል ታላቆችን ማክበር በተለይም የሃይማኖት አባቶች ሠማያዊ አንባሳደሮች በመሆናቸው የተለየና ከፍ ያለ ክብርና ሞገስ እንደሚገባቸው ከእኛ ከኢትዮጵያውያን የተሠወረ አይደለም::
ነገር ግን የሃይማኖት አባቶች እጅግ ከተከበረው መንበራቸውና ከተቀደሰው ማዕረጋቸው ወርደው ለነሱ ባልተገባና በማይመጥናቸው የዚህ አለም የሃጥያት ማጥ ውስጥ በአደባባይ ሲንቦጫረቁ ስናይ ፤ በጥቅመ ሰናዖርና በዘረኝነት ቆመው ሲገኙ መቃወም ተገቢ ነው:: የተረከቡትን ታላቅ አደራ እንዲያስቡ ማድረግ ሃይለ ቃላትን ተጠቅሞ መገሰጽ መቃወምና እውነታውን ማጋለጥ ነውርም ሃጥያትም ባለመሆኑ ስለ ሕገ ቤተክርስቲያን መከበርና ስለ ምዕመናን ሰላም ዘብ የመቆምና ሀሳውያንን መታገል : ቤተ እምነቶቻችንን ከሽፍቶች የመጠበቅ የአማኞች ተግባር ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው:: ባለፉት 30 የጭለማ አመታት ውስጥ በሃገራችን በኢትዮጵያ እና በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያናችን ላይ የተካሄደው መጠነ ሠፊ የጥፋት ዘመቻ ይህ ነው የሚባል አይደለም።
በተለይም ከሁሉ የሚያሳዝነው መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ የተሾሙት ካህናትና መነኮሳት እንኳን ለመንፈሳዊያን ለአለማዊ አህዛብ እንኳ በማይስማማ የክፉት የተንኮልና የጥላቻ ማጥ ውስጥ የተዘፈቁት አንሶ ከቀደመ ጥፉታቸው በንስሃ ይመለሱ ዘንድ የተስጣቸውን ግዜ ለበለጠ ጥፉት ሲያውሉት መመልከት ፍጹም ልብን የሚስብር ነው::
የትግራይ መነኮሳት ከሕወሃት ፖሊት ቢሮ በመጣ ቀላጤ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገንጥለን የትግራይ ሲኖዶስ አቋቁመናል ብለዋል:: በኢትዮጵያውያን ላብና ደም በክብር ተጠብቀው የኖሩትን ቅዱሳን ገዳማትና አድባራት ሊነጥቁ የተገነቡትን ተቋማት ሊወርሱ መርገምታዊ አዋጅ አውጀዋል:: ትግራይ እግዚዎታ የምህረትና የይይቅርታ ተምሳሌት ሆና በመንፈሳዊነት ትነሳ ዘንድ ሲጠበቅ መነኮሳቷ የመለያየትን የጥላቻና የክፉትን ነጋሪት መጎሰማቸው አስቀድሞ በወንጌል ፈጣሪ እንደተናገረው “ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?” እንደተባለው እኛም ትግራይ ሆይ እስከመቼ የመከራ ምንጭ የጥላቻና የመለያየት ሃዋርያ ትሆኛለሽ ማለታችንን አናቆምም::
ትዕቢት የነፉቸው እብሪት ያሳበጣቸው የታላቂቱ ሃገረ ትግራይ ፈጣሪ እንሆናለን ብለው ጦር የሰበቁት የሕወሃት መሪዎች አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አስጨርሰው እብሪታቸው ተንፍሶ በእርቅ ስም ለገዳያችው በተንበረከኩበት በዚህ ወቅት ካህናቱን ምን ነካቸው:: ወያኔዎች ለሁለት ተከፍለው እንደ ኮረዳ እራሳቸውን ተመራጭ ለማድረግ አብይ አህመድ ፊት በሚኳኳሉበት የሃፍረት ጥግ መነኮሳቱ ምን ታይቷቸው ይሆን::
ሕወሃት የለኮሰችው ጦርነት እስላም ክርስቲያኑ አውግዞታል:: ሕወሃትን ሕዝብ የጠላው አምርሮ የተዋጋው ከበቂ በላይ ምክንያት ስላለው ነው:: ሕወሃት ሌባ ነው! ሕወሃት የጥላቻ ምንጭ የክፉት አባት ነው! ሕወሃት ሰዶምን በመንግስት መዋቅር ውስጥ በእስረኞች ላይ ያስፈጸም መርገምታዊ ድርጅት ነው:: ሕወሃት ሕዝብ በሕዝብ ላይ እንዲነሳ የቀሰቀሰ በዚህም ለሚሊዮኖች እልቂትና መፈናቀል ምክንያት የሆነ ወንጀለኛ ድርጅት ነው:: ሕወሃት ከአልቃይዳ የባሰ ሽብርተኛ ከአይሲስም የከፉ አረመኔ ቡድን ነው:: ሕወሃት ቀንድና ጭራ እዳሪና ፍግ የማይምር የቀን ጅብ ዘራፊ ቀማኛና የማይጠረቃ መጥፉት መወገድ ያለበት መርገማዊ ቡድን ነው::
ሕወሃት ዋልድባን የደፈረ የምንኩስና ሕይወት ውስጥ ካድሬ ያሰረገ ገዳማትን ያቆሽሽ እርኩስ ነው:: በጻጻስ ላይ ጻጻስ የሾመ ቤተ ክህነቱን በዘረኝነት ያጨቀየ ሃይማኖትን ያቀለለ ሰይጣናዊ ቡድን ነው:: እንዴት ይሄ መርገማዊና ሰዶማዊ ድርጅት በቀደደው መስመር ክርስቲያን ነኝ የሚል ግለሰብ ይሁን ማህበረሰብ ይነዳል:: በዚሁ ቡድን በመጣ ጦርነት ሚሊዮኖችን ላጣ ማህበረሰብ ይሄ ይገባዋል?::
የሃገር ድቀት የሞት መንገስ የነውር መስፉፉት:: የጥላቻ ምንጭ የክፉት አባት የሆነው የትግራዩ ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሃት) ከጫካ ትግል እስከ ሃገር ማስተዳደር የሄደባቸው መንገዶች ዛሬ እንደ ሕዝብ ለደረስንበት የመከራ ምኩራብ የመለያየት አፉፍ ዋናውና ግንባር ቀደሙ መንገድ ጠራጊው የትግሬው ነጻ አውጪ ወያኔ ነው:: ለሺ ዘመናት ዜጎቿ በፍቅር እና በአንድነት ተስማምቶ በኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በትግሬ ነጻ አውጪዎች ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ የመጣው የዘር ፖለቲካ ለሚሊዮኖች እልቂት ለማያባራ ጦርነት ለሞራል ድቀትና ለአሰቃቂ ሕይወት ዳርጎናል::
“ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ያለችው ንጹህ ብላቴና የተሰየፈችው ሕወሃት ባራመደው የጥላቻ ትርክት ያደጉ ዜጎች የፈጸሙት ድርጊት ነው:: አብይ አህመድን ከሜዳ አንስቶ ጥላቻ አጉርሶ ተንኮል አሰልጥኖ ;ብርሃኑ ጁላን ከምርኮኝነ ተውሶ ብቀላን አስታጥቆ ጭካኔን እስጨብጦ ለወግ ማዕረግ ያበቃው የትግራይ ነጻ አውጪው ወያኔ ነው::ከሻአብያ በላይ የኤርትራ መገንጠል የመራው; ሻብያን በኢትዮጵያ ሉዐላዊነት ላይ እንደፈለገው እንዲሆን ያደረገው ሕወሃት ነው:: አማራ ላይ ጥላቻ ያወጀው ዛሬም ለደረሰበት መከራ ያሻገረው የትግሬው ነጻ አውጪ ሕወሃት ነው::
ይህ ሁሉ መከራ የተፈጸመበት ሕዝብ ብዙ በደል የደረሰባት ቅድስት ቤተክርስቲያ የብዙዎችን ችግርና ችጋር ያላቀቀች ሃገር ኢትዮጵያን መስደብ ማዋረድ ማፈራረስ በእርግጥ ለትግራይ ይበጃል:: ዛሬ ላይ ትግራይ ላይ ሃይማኖት ያለው አባት ቢኖር እርቅን ይሰብክ አብሮነትን ያስተምር ነበር:: ከጥላቻ የራቀ ሕዝቤ ለሚለው ወገኑ የሚያስብ ፖለቲከኛ ቢኖር ኖር ያለፈውን የውድቀት አካሄድ ገምግሞ አጋርነትን ከጎረቤቶቹ ጋር አጠናክሮ የጋራ የሕልውና ጠላት የሆነውን ሃይል ለመታገል ይዘጋጅ ነበር:: በአንጻሩ መነኩሴውም ካድሬውም በጥላቻ ላይ ጥላቻ በመለያየት ላይ መለያይትን አጠንክሮ ከውድቀት ውጪ አንዳችም ትርፍን ለራሱም ለሕዝቡም አያስገኝም::
ለቤተክርስቲያን መከራ ብርቋ አይደለም:: ከዚህ የባሰ ስቃይ ስደትና ሰቆቃን አሳልፉለች:: ለሺህ አመታት ጸንታ የኖረችው በአምላኳ ጥበቃና ቸርነት በቅዱሳኗ ጸሎትና ትሩፉት ነው::እንኳን ትዕቢታቸው ተንፍሶ ሱሪያቸውን ባወለቁ ተንበርካኪዎችና ከተላላኪነትና ከምርኮኛነት መሪ ለመሆን በበቁት ደንቆሮ ተረኞች የኢትዮጵያ ሕልውና አይናድም:: ይብላኝ ለጎጠኛና ለከፉፉይ በተለይ በመንፈሳዊነት ጭምብል ለምታምታቱና ለመንጋችሁ ::መከራ ይበላችሗል:: ሃይማኖቷም አይረክስም ሕዝቧም አይበተንም:: ሊነጋ ሲል ይጨልማል:: የኢትዮጵያ ትንሳዔ ቅርብ ነው::
«ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች»መዝሙር፤ ፷፯፥፴፩