September 23, 2014
11 mins read

ዋለልኝ መኮንን ማነው? – ከይርጋዓለም ታደሠ

ዋለልኝ መኮንን
ዋለልኝ መኮንን

ወሎ_ደሴ_በኢትዮጵያ_ታሪክ

ወይዘሮ_ስህን_ከታሪክ_ማህደር?

ዋለልኝ መኮንን ከአባቱ ከአቶ መኮንን ካሣ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበች ግዛው መጋቢት 1938 #በአማራ ሳይንት ተወለደ  ዋለልኝ  ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ የተማረው በንጉሥ_ሚካኤል እና በታዋቂው ወይዘሮ_ስሂን ትምህርት ቤት የነበረ ሲሆን እጅግ ብሩህ አእምሮ ነበረው ፣ ከወ/ሮ ስሂን ት/ቤት በዛን ማትሪክ ማለፍ እንደ ቋጥኝ መሸከም ከባድ በሆነበት ዘመን Straight A በማምጣት ዩኒቨርሲቲ የገባ ፣ የአለምን ፖለቲካ ጥንቅቅ አድርጎ የሚያውቅ ፣ እጅግ ጥሩ ፀሃፊና በሳል አንባቢ ነበር ።ዋለልኝ እኮ መለስ ዜናዊን ፣ ኢብሳ ጉተማን ፣ እንድርያስ እሸቴን እና ሌሎቹንም እየኮረኮመ የፖለቲካ ፊደል ያስተማረ በወቅቱ ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በመሰብሰብ ያስተምር የነበረው ልኡል በእደማርያም ትምህርት ቤት በመግባት አዲስ አበባን ለመጀመሪያ ጉዜ ተዋወቃት። በ1958 ዓመተ ምሕረት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቁ የተነሳ ወደቀዳማዊ #ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ሆኖ ትምህርቱን ጀመረ።

የአዲሰ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ሰዓት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በተደረገው የፀሀፊዎች ውድድር “የአዚናራው_እስረኛ” የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ጎበዝ ፀሐፊ መሆኑን አስመሰከረ።

በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ልሣን በነበረው ታገል_ጋዜጣ ላይ በርካታ ፅሁፎችንም በመፃፍ ያለውን የፅሁፍ ተሰጥኦ ከማሳየቱም በላይ በጽሑፍ በርካቶችን ማስተማር የቻለ ድንቅ ፀሐፊም ነበር።

ዋለልኝ ከፃፋቸው ቅኔዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ

«ከለበሱ አይቀር ሱሪ

የጥንቱን ነበር የተፈሪ

ግና አይመችም ለሥራ

አጣብቆ ይዞኝ በቀኝ ግራ»

የመሬት ለአራሹ ጥያቄ በማንሳት ለወገኑ ገበሬ አጋርነቱን በማሳየት የብዙ ሚሊዬኖችን ድምስ አስተጋብቶል፡፡

ዋለልኝ መኮንን የፊውዶ ፋሺሽቱ አገዛዝ ለአፍሪካ አብዮት ጠንቅ ነው የሚል ፅሁፍ ፃፈ ይህ ፅሁፍ አዲስ አበባ ለሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች በመታደሉ ምክንያት ሃይለስላሴ ተማሪዎችን እየለቀሙ ማሳሰር ጀመሩ።

የንጉሡ ተማሪዎችን ማሰርና በሬዲዮ ቀርበው ተማሪውን እንጭጭ ብለው መሳደብ ያናደደው ዋለልኝ ብዙዎቻችን የምናውቀውን ለአዋጁ አዋጅ የተሰኘ ፅሁፍ ፅፎ በተነ

በዚሁ ፅሁፍ የተነሣ ዋለልኝ መኮንን፣ ሄኖክ ክፍሌ፣ ታምራት ከበደ፣ ጌታቸው ሻረውና ሌሎችም ተማሪዎች ከርቸሌ ታሰሩ።

ከእስር ከተለቀቀም በኋላ ትግሉን የቀጠለው ዋለልኝ ጓደኛው ጥላሁን ግዛው አፍንጮ በር አካባቢ መገደሉን በመስማት አስክሬኑን ፍለጋ የካቲት 12 ሆስፒታል በመሄድ ከጓደኞቹ ጋር የጥላሁንን አስክሬን በመያዝ ወደዩኒቨርስቲው ያመራሉ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ወታደር በመላክ የጥላሁንን አስክሬን ለመውሰድ ከተማሪዎቹ ጋር በተደረገው ግብግብ አበበ በርሄ፣ ስብሀቱ ውብነህና ሌሎች ተማሪዎችን ይገድላሉ ዋለልኝና ጓደኞቹም ኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ በመሄድ ታሰሩ።

ከእስር ከተፈታም በኋላም ከዩኒቨርስቲው የተባረረ ሲሆን የትግል ጓዶቹ እነብርሀነ መስቀል ረዳ በርሊን ላይ የኢሕአፓ መሥራት ጉባኤ ማዘጋጀታቸውን ጥሪ ይደርሰዋል። ወደበርሊን ለመጓዝ እድል ያልነበረው ዋለልኝ ብቸኛ አማራጭ ብሎ የያዘው #ህዳር_29 1965 ከአዲስ አበባ ተነስቶ በአስመራ በኩል ሮም፣ አቴንስ ብሎ ፓሪስ የሚደርሰውን #አውሮፕላን ለመጥለፍ ከጓደኞቹ ጋር ተስማሙ ሆኖም አውሮፕላኑን ለመጥለፍ የሞከሩት #ዋለልኝ_መኮንን፣ #ማርታ_መብራቱ፣ #ታደለች_ኪዳነማርያም፣ #ዮሐንስ_ፍቃዱና #ተስፉ_ቢረጋ አውሮፕላኑን ለመጥለፍ በመሞከራቸው ከታደለች በስተቀር ሁሉም እንዲገደሉ ተደረጉ አስገራሚው ነገር ዋለልኝ ሲቀበር እንኳን ፍትሐት እንዳይፈፀም ተደርጐ ነበር።

አሁን ላይ እንዳለው እሳቤ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት (አሁን ላይ አንዱ የበላይ የሆነበት ስርአት ሳይሆን )ቀድሞ በማንሳት የሰወችን እኩልነት በተግባር የጠየቀ ጀግና ነው…

ይህ ነው የዋለልኝ ትክክለኛ ታሪክ

አንድም እንቅስቃሴ ሳያደርጉ የተቻለውን ያህል ሀገሪቱን ለመቀየር ሲንቀሳቀስ የነበረውን ዋለልኝ የሚወቅሱ ማፈሪያዎች አሁንም አሉ።

እኔ በግል ከኢህአፓ አካሄዶች የማልስማማባቸው የተወሰኑ ጉዳዮች ቢኖሩም ለዋለልኝ ጥረት እና ለአህአፓ ትግል ትልቅ ክብር አለኝ ዋለልኝ ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት ማለቱን በመምዘዝ፤ የአማራውና የትግሬው ባህል በሌላው ላይ ተፅእኖ አድርጓል ማለቱን በማውሳት የሚተቹት ብሎም ዋለልኝን ለማዋረድ የሚሯሯጡ ታሪክ አልባ ፀሀፊዎችም አሉ።

ዋለልኝ ከአማራ ክልል የወጡ ገዢዎች በኢትዮጵያዊነት ስም የአማራውን ባህል በሌሎች ጎሳዎች ላይ ለመጫን ሞከሩ አለ እንጂ (ማለትም በስልጣን ላይ ያሉት ሹማምንት በአማራ ህዝብ እየነገዱ ለአማራው ህዝብ ግን የፈየዱለት ከሌላው ኢትዮጰያዊ የተለየ አንዳችም ነገር የለም አብሮ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነበር ህዝቡ ለማለት ነው አሁን ላይ እንደሚታየው በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱ እንደሉ ሁሉ ) የአማራ ህዝብ ሌላው ህዝብ ላይ ባህሉን ጫነ አለማለቱን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል። የማንነት ጥያቄ እንደታቡ በሚታይበት ሀገር ላይ በድፍረት በመናገሩ ሕይወቱን እስከማጣት ደረሰ እንጂ ከተናገረው ውስጥ አንድም ስህተት የለም

ዋለልኝ መኮንን የጎሣ ድርጅቶች የማንነት ጥያቄ እንዲያነሱ መሰረት ሆኗል የሚልም ካለ ስህተት ነው ከዋለልኝም በፊት የባሌ እና የጎጃም ገበሬዎች የማንነት እና በመሬታቸው የመጠቀም መብቶች  ጥያቄዎች ይዘው አመፅ አካሂደው ነበር።

ሌሎች ወገኖች ደግሞ በተለይም የደርግ ባለሥልጣን የነበረውና አሜሪካን ሀገር ፓርቲ አቋቁሞ ኑሮውን እየገፋ ያለው አዛውንት ዋለልኝን የሲአይኤ ሰላይ ነበረ ሲል ያለማፈር በተደጋጋሚ ቃለመጠይቅ ይሰጣል ይህ አስቂኝ ቀልድ ከመሆኑም በላይ ትዝብት ውስጥ የሚጥል ነው

ለመሆኑ ሃገራችን የህዝቡን ጥቅም የሚያስከብር መሪ መቼ አግኝታ ነው ሲአይኤ ሰላይ ከተቃዋሚ መካከል የሚመርጠው? መሪዎቻችን በሙሉ ለሲአይኤ፣ ለኬጂቢ፣ እና ለቻይናው የስለላ ድርጅት አይደለም እንዴ ሲሰሩ የኖሩት ለሰላይነትማ ከተቃዋሚዎች ይልቅ የመንግሥት ሰዎቻችን የተመቹ ናቸው

ዋለልኝ ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ጠንቅቆ የተረዳ ነው ስለፖለቲካችን ጥናት ባይሰራም ያሳደጉት ድሀ ቤተሰቦቹ የሰፊውን የኢትዮጵያን ህዝብ ኑሮ በተግባር አስተምረውታል። የዘመኑን የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ተመልከቷቸው አብዛኞቹ የሀብታም ልጆች ናቸው ሆኖም ሰፊውን ህዝብ እናውቀዋለን ብለው የፓርቲ መሪዎች ሆነው እየታገሉ ነው ዋለልኝ ግን የህዝቡን መከራ በራሱ ህይወት አይቶ በተግባር ታግሎ ሕይወቱን የሰጠ ታላቅ_ጀግና ነው።

ጀግኖች ሲሞቱ ፈሪዎች ይተርፋሉ ፡፡

ከይርጋዓለም_ታደሠ

Go toTop

Don't Miss

ዋለልኝ መኮንን

ዋለልኝ መኮንን ዳግም ሞቷል! – ሙሉዓለም ገ/ መድህን

“ዋለልኝ መኮንን” የሚለው ሥም በኢትዮጵያ (የቅርቡ) የሃምሳ ዐመት ፖለቲካዊ ትርክት
1967-74: Ethiopia's Student Movement

የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ዋዜማ – ፫ በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

(ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. ከ 1950-1975 ‹‹…