ዶ/ር ዮናስ በኦሮሙማዎቹ ሚዲያ ላይ ገጣሚ አጥቶ ብቻውን ግን ምክንያታዊ ሆኖ አቋሙን በሚገባ አስረድቷል። ዶ/ር ዮናስ በዚህ አቀራራቡ ጥሩ ስራ ሰርቷል።
በባዶ ሜዳ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉትና፣ ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ 50% ነው እያሉ በብዙ በሬ-ወለደ ተረቶቻቸውና ብሶታቸው ፈረንጆቹን የሚያሳስቱት “የኦሮሞ ምሁራን” ከክንግዲህ በኋላ እንኳ ተምረው የኢትዮጵያን ህዝብ ባያጋድሉት ጥሩ ነው። ዘርን በማጽዳት፣ የቦታን ስም በመቀየር፣ ህዝብን በማፈናቀል ታሪክን ወደኋላ ለመመለስ የሰራው ማን ነው? የአማራው ህዝብ በዛው ልክ ለደረሰበት በደል ምላሽ ቢሰጥ ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ትደርስ ነበር? በአህመድ ግራኝ ጦርነትና በኦሮሞ መስፋፋት ጊዜ ያለው ታሪክ ቀርቶ ጎሰኞቹ ታሪክን ከምኒሊክ በመጀመር ጥላቻን በመዝራት ለዚህ ጊዜ አብቅተውናል። ጉዳዩ የታሪክ ሂሳብ መታሳሰብ ከሆነ የሁሉም ዘመን የታሪክ መዝገብ ይቅረብ። ዛሬ የሚፈጸመው የነገ ታሪክ መሆኑን መገንዘብስ እንዴት ያቅታል? በዚህ ጉዳይ አዋቂ ነን የሚሉና የጎሳ መብት ተከራካሪ ነን ባዮች በየጎራው ተከፋፍለው ህዝብ የሚያዋጉ በእውነት አዋቂ ከሆኑ በአንድ መድረክ በአደባባይ ቀርበው ይወያዩ/ይከራከሩ። ህዝብም ፍርድ ይስጥ። ሰላምም እናግኝ።
በድሉ