April 25, 2024
17 mins read

ብልግናዎች: ፍላጎታችሁ ምን ይሆን?

ህሩይ እስጢፋኖስ

ገዳይ አብይ አህመድ መመለስ ያለበት ጥያቄ
ገዳይ አብይ አህመድ መመለስ ያለበት ጥያቄ

ይድረስ ለብልጽግና መንግሥትና ፓርቲ ባለሥልጣኖች!

ሕዝብ እናንተን አስተምሮ እሱ ሳይኖር እናንተን አኑሮ በድግሪ በማስተር አስመርቆ ለዚህ ሥልጣን ሲያበቃችሁና ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ የሀገር መምራት ሐላፊነት ሲያስረክባችሁ በእየምነታችሁ በገባችሁት ቃል መሠት መልካም ውለታውን መመለስ ይጠበቅባችሁ ነበር፣ በእውነት የተማረ ሰው ሰብእና ቢኖራችሁ ኖሮ ውለታውን መመለስ ባትችሉ ከድህነት የሚወጣበትን የሥራ ፈጠራ ክህሎትን ባታመቻቹለት እንኳን በድህነቱ እንዲኖር ሰላሙን ልትሰጡት ይገባ ነበር።

ሕዝቡንም ባትበድሉት እና ባትገድሉት ባታጣሉት እና ባታፈናቅሉት ኖሮ ወደ ሥልጣን በመጣችሁበት ጊዜ እንዳሳያችሁ ፍቅሩን ባሳያችሁ ድጋፉንም ባልነፈጋችሁ ነበር።

ሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ያለምንም ልዩነት በዘር በጎሳ ልዩነት ሳይኖረው በአንድ ተጋብቶ እና ተዋልዶ ሲኖር ያሰባችሁት የሙስና እና የሥልጣን ማራዘሚያን ስልት ለመጠቀም ስትሉ አንተ የምሥራቅ አንተ የምዕራብ አንተ የደቡብ አንተ የሰሜን በማለት የማያውቀውን የዘር ጥላቻን በመስበክና በማስተማር የተንኮልና የጥላቻን ዘር ብትዘሩበትም ሕዝቡ ግን አሁንም የእናተን ሴራና ተንኮል ሰምቶ እንዳልሰማ በማለፍ አሁን በፍቅርና በመቻቻል ለመኖር ቢሞክርም እናንተ ግን በሽፍታ ስም ገዳይ ቡድን በማቋቋም እና በማዘጋጀት የዚህን ድሀ ሕዝብ ቤቱን እና ንብረቱን በማቃጠል ከቀየው ከአካባቢው አፈናቀላችሁት።

በገዳም የሚኖሩ መናንያን ባህታውያንን እና መነኰሳትን እንዲሁም ጉባዔ ዘርግተው የሚያስተምሩ መምህራንን እና የሚማሩ ደቀመዛሙርትን በከባድ መሳርያ በመደብደብ ገደላችሁ ገዳማቱንና የጉባዔ ቤቶችንም አቃጠላችሁ ይህ አይነቱ አረመኔያዊ እና ታሪክ ይቅር የማይለው ድርጊት በነ ዮዲት ጉዲትና በእነ ግራኝ አህመድ እንዲሁም በእነ አጼ ሱስንዮድ ዘመንም አልተፈጸምም። የሕዝብ ጥያቄ ተስማምታችሁ ግዙን እንጂ እንግዛ አላልንም።

ይህ የዋህ ሕዝብ ሳይኖር ባኖራችሁ እንዳይኖር አደረጋችሁት ሳይማር ባስተማራችሁ የሚማሩ ልጆቻቸውን በተለይ ማንነትን ተኮር ባደረገ መልኩ የአማራውን ሕብረተሰብ ልጆች ከትምህርት ቤት እያገታችሁ 20 እና 30 ሚሊየን ብር ካልሰጣችሁ ልጆቻችሁ አይለቀቁም በማለት እንኳንስ በምሌን የሚቆጠር በመቶም የሚቆጠር የሌለው ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ የሚኖር ድሀ ሕብረተሰብ በመሆኑና የተጠየቀውን ከፍሎ ልጆቹን ማስለቀቅ ባለመቻሉ የታገቱትን ልጆች በመግደል ወላዶቻቸውን የደም እንባ እያሰለቀሳችሁ በግፍ ቀጥላችኋል።

ይሁንና በተለይ የአማራውን ሕብረተሰብ መግደልና ማግለል ስር ነቀል የዘር ማጥፋት ብሎም ቅርሱን እና ወጉን ባህሉን ማንነቱን ለማጥፋት እየተሰራበት የቆየው ቀደም ያለነ 3 አሰርተ ዓመታትን ያሳለፈ ቢሆንም ነገር ግን በጉልህና በግልፅ የአማራው መጠቃትና በማንነቱ መገደል መፈናቅል እንዲሁም ከቀየውና ከቦታው ከመኖሪያው መባረርና መሳደድ እየባሰ የመጣው በዘመነ ኢሀዲግ ነው

በመቀጠልም ኢሀዲግ ወልዶ ያሳደገው የኢሀዲግ ልጅ የብልጽግና መንግሥትና በእሱ ፈቃድ የተመለመሉ ፓርቲዎች ገዢ ሆነው በወንበር ላይ ከተቀመጡ በኋላ የኢሀዲግን የሴራ ፖለቲካ በእጅጉ ክፋቱንና ተንኮሉን እንዲሁም አንዱን ካንዱ ማገዳደሉን እና ማጣላቱን በ10 እጥፍ በማስበለጥ ከአባታችሁ ኢሀዲግ የተቀበላችሁትን እና የወረሳችሁትን የተንኮል ቃል ኪዳን ለማስፈጸም ስትሉ ይህንን ምኪን እንግዳ ተቀባይ ለወገኑና ለሀገሩ ከራሱ በላይ የሚያስበውን በኢትዮጵያዊነቱና በእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ እንዲሁም የሉዓላዊነቱ መገለጫ በሆነው በሰንደቅ አላማው የማይደራደረውን አማራ ለማጥፋት በጠላትነት ተነስታችሁ ትገድሉትና ታፈናቅሉት ጀመር።

በእውነት ይህ ደጉ የአማራ ሕዝብ ሁሉን አቀፍና የብሔር ብሔረ ሰብ እህት ወንድሞቹን ወዳድና ሁልን አቀፍ እንዲሁም እንኳንስ የሀገሩን ዜጋ ከውጭ ሀገር የመጣውን ዜጋ እንደወንድሙ በመቁጠር እግር አጥቦ ምግብ መግቦ አጠጥቶና በአልጋው አስተኝቶ የሚያስተናግድ ደግ ሕዝብ ሆኖ ሳለ መገደሉ ለምንድ ነው ከተባለ ምክንያቱ ማንነትን ማጥፋት ነው የኢትዮጵያ የማንነቷ መገለጫ የሆኑት መንፈሳዊና ቁሳዊ ቅርሶች በይበልጥ የሚገኙት በዚሁ በአማራው ክልል ስለሆነ እና እንዲሁም ሁለቱ የኦርቶዶኮስና የእስልምናም ሃይማኖቶች በመቻቻል ለሌላው ክፍላተ ዓለማት እንደምሳሌ ሆነው በሰላምና በፍቅር በልዕልናና በክብር ማንነታቸው ጠብቀው የሚኖሩት በዚሁ በአማራው ክልል ስለሆነ ይህንን ማንነት ለማጥፋት ነው።

እንዲሁም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት እዚህ ለመድረሱ እና ወደፊትም በቀጣይነ ሳይደበዝዝና ሳይጠፋ ጎልቶ እንዲኖ ምክንያቱ ይሄው አስተዋዩ የአማራ ሕዝብ ስለሆነ ይህ እንዳይሆንና ኢትዮጵያ የሚለው ስሟና ማንነቷን እንዲሁም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነቷን ለማጥፋት ሳያርፉ ሌት ከቀን የሚሰራ የውጭ ጣልቃ ገብ ጠላቶች እጅ ስላለበት መሆኑ ግልፅ ነው።ከሁለትና ከሦስት ዓመት በፊት ከራሱ ክልል ውጭ እና በሌላው ክልል የሚኖረውን ይህንን ደጉንና ሁሉን አቀፍ የሆነና ከሌላው ብሔር ብሔረ ሰብ ጋር ተዋልዶና ተዛምዶ የሚኖረውን የአማራ ሕዝብ ቀስ በቀስ በማጥፋት ከዚያም ወደራሱ ክልል በመግባት ቀስበቀስ እርስበርሱ በማጣላትና ደም በማቃባት በማገዳደል በቁጥር በሁለተኛ ደረጃ የያዘውን የአማራ ሕዝብ በቁጥር የማሳነስና ብሎም የማጥፋት ፖሊሲ ታቅዶበት እየተሠራ ነበር።

ለዚህም በአንድ ወቅት የሚርጫ ወቅት እየደረሰ ስለነበር አንድ ጋዜጠኛ የኦፌኮ ሊ/ር የሆኑ አንድን ግለሰብ ኢንተርቪ በሚያደርግበት ሰዓት የጠየቃቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር ጋዜጠኛው ይጠይቃል “የተከበሩ ……. አሁን ሰሞኑን ምርጫ እየደረሰ ነው እናንተ መላው የኦሮሞን ሕዝብ ወክላችሁ ነው የምትወዳደሩት ነገር ግን በተለይ በአሩሲና በወለጋ በጅማና በሻሸመኔ ብዙ የአማራ ማኅበረሰብ ነዋሪዎች አሉ ውክልናችሁ ለእነሱ ሁሉ ነው ወይስ ለኦረሞ ብሔረሰቦች ብቻ ነው?” ብሎ ሲጠይቃቸው የመለሱት መልስ በሚገርም ሁኔታ እንዲህ የሚል ነበር።

የተጠያቂው ግለሰብ መልስ “አሁን አንተ በጠቀስካቸው ቦታዎች እና አካባቢዎች ያለን መሬት እንጂ ሰው የለንም” ብለው መለሱ።

በእውነት ይህ መልሳቸው አንድ ተምሬያለሁ ብሎ ዜጋን ይቀርጻል ተብሎ ታምኖበት ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶት በዩንቨርስቲ ከሚያታስተምር ፕ/ር ይህ ሲሰማ ሀገሪቱ በገደል አፋፍ ላይ እንዳለች የሚያሳይ ነው።

እኚህ ግለሰብ በዚያን ጊዜ ይህንን ያሉት ለካ ያቀዱትን እቅድና ፕላን ስለነበር ከዚያ በኋላ በነበሩት ዓመታት መሬት ነው ያለን እንዳሉት ከክቡሩ የሰው ልጅ መሬትን በማስበለጥ የሰው ልጅ ይጠቀምበት ዘንድ ለሰው ልጅ የተፈጠረውን መሬት የኛ ነው ብለው በማሰ ለማስለቀቅ እንዲሁም የተከበረውን የአማራ ሕዝብ እንደሰው ባለመቁጠር በመናቅና በማቃለል መሬት እንጂ ሰው የለንም በሚል ኢሰብአዊ እና ኢምሁራዊ በሆነ መልስ ክቡሩን የአማራ ሕዝብ ከመሬት አሳንሰው መግለጻቸው ሳያንስ፣

እንዳሉትና እንዳቀዱት ያለማቋረጥ በአለፉት ስድስት ዓመታት በእነዚህ በተጠቀሱት በተለይ በአራቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ሌሊት በተኙበት ቀን በተሰማሩበት በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፎ በመግደል ደማቸውን እንደጎርፍ አፈሰሳችሁ። አጥንታቸውንም እንደ ድንጋይ ከሰከሳችሁ፣

የእርጉዞች እናቶችን ማሕፀን ሰንጥቃችሁ የተረገዙትን ብዙ ሕፃናትንና እናቶችን በመግደል እና ዘቅዝቃችሁ በማቃጠል በዓለም ላይ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ የጭካኔያችሁን ጥግ አሳያችሁ።

እንዲሁም ሁሉን ከሚኖርበት ከቀየውና ከአካባቢው በማፈናቀላችሁ ይኸው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በማሳደድ ያለ ምግብ ያለልብስና ያለመጠለያ አስቀራችሁት።

በዚህም ባለመርካታችሁ በእውነት ከሞት አምልጦ ነፍሱን ለማዳን በቤተ ክርስቲያን እና በተለያዩ ተቅዋማት ተጠግቶ እና ተጠልሎ ሲኖር የነበረውን ተፈናቃይ የአማራ ሕዝብ አሁን ሰላም ሆኗል ወደቀያችሁ ተመለሱ ብላችሁ መልሳችሁ ልምን ከሞት ተርፈው አመለጡ በሚመስል መልኩ በድጋሜ አስፈጃችኋቸው።

የመጀመሪያውን ፕላናችሁን በዚህ መልኩ ሸኔ በምትሉት ገዳይና አስገዳይ ቡድናችሁ አስፈጅታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ፣በሁለተኛው ፕላናችሁና እቅዳችሁ መሠረት በመላው የአማራ ክልል እና የአማራ ሕብን ጨርሶ የማጥፋት ጀኖሳይድ ለመፈጸም በመላው የአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ተከፈተበት። ይህም ሕዝብ ከ3 አስርት አመታት ለቅሶና ዋይታ በኋላ ከፈጣሪውና ከነፍጡ በስተቀር የሚታደገው ቢያጣ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ነፍጡን አንስቶ ለመፋለም ከአሁን በኋላ ፋኖ ነኝ ብሎ ጫካ ገብቶ ይታገል ጀመረ።

እንዲሁም ቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገር እና ለወገን ሰላምን እንዲሁም ለሞተው ዕረፍተ ነፍስን በሕይወትም ለሚኖረው ዕድሜና ጤናን ለመግሥትም ማስተዋልን ስጥ እያለች በሌሊትና በቀን የምትጸልይን ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳቶቿን በመከፋፈልና እንደ አርዮስን እንደነ ሰባልዮስ እንደነ ንስጥሮስና መቅዶንዮስ ከሀድያን ጳጳሳት ነን የሚሉ አስመሳዮችን ከውስጥ በማስነሣትና በመከፋፈል ቅዱስ ሱኖዶሱን እና የቅዱስ ሲኖዶሱ ሰብሳቢ የሆኑትን ቅዱስ ፓትርያርኩን በመቃወም በድፍረትና በማን አለብኝነት በመነሳሳት የዘርና የጎሳ ጳጳሳት እንዲሾሙ በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላም በመረበሽ ፈተናዋ እንዲበረታ አደረጋችሁ። ነገር ግን መሥራቿ የሰላም ባለቤት ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ የሲኦል ደጆች አያናውጿትም።

ስለዚህ አሁንም ይህንን የበደላችሁትን በተለይ በማንነቱ ጀኖሳይድ እየፈጸማችሁበት ያለውን የአማራ ሕዝብ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ የሕዝብንም ሥልጣን ለሕዝብ ካላስረከባችሁ ከእግዚአብሔርም ከተገፋውም ሕዝብ ይቅርታ የሌለው ፍርድ የሚጠብቃችሁ መሆኑን ከወዲሁ ልታውቁት ይገባል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop