በትህነግ የጦርነት ክተት አዋጂ  “ወራሪ እና ተስፋፊ ” ማን ነበር ? – ማላጅ

tplfየትግራይ ህዝብ ነፃ አዉጭ ግንባር (ት.ህ.ነ.ግ) ወደ ቀደመ ማንነቱ ተመልሶ እ.ኤ.አ. ህዳር ሁለት ቀን 2022 በወረራ ግዛት ለማስፋፋት አስቀድሞ ከሶስት አሰርተ ዓመታት አስቀድሞ በኃይል ከያዛቸዉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ዉስጥ ከሆኑት ጎንደር እና ወሎ ክ/ግዛቶች በተጨማሪ አስከ ሸዋ በመዝልቅ በታሪክ ወደር የሌለዉ ሠባዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ፈፅሟል፡፡

ይህም አገሪቷ እና ህዝቧ በተለይም የዓማራ ህዝብ ለዳግም ምዝበራ እና ወረራ እንደታሰበዉ ከፍተኛ ዕልቂት እና ሞት አስተናግዷል፡፡

ይህ ሁላ ሆኖ ትህነግ ዓማራ እና ኢትዮጵያን ሲዖል ለመክተት እንዳሰበዉ ሳይሳካለት ሲቀር እና ማጣፊያ ሲያጥረዉ ወደ ሠላም ፍለጋ ፊቱን አዞረ እና እ.ኤ.አ. ህዳር 2, 2022 በደቡብ አፍሪካ በምትገኝ ፕሪቶሪያ በተደረሰዉ የሁለትዮሽ ስምምነት ብረት ሊያወርድ የሚጠላትን ኢትዮጲያ ሳይወድ ሊወድ ከመሞት መሰንበት ብሎ እያቅማማ ተስማምቷል፡፡

ነገር ግን  ጦርነት አምጣ እያለ ምድር አልበቃዉ ብሎ ምድር ሲደበድብ የነበረዉ የጠብ መነሻ

ዓማራ የሚባል ህዝብ እና ኢትዮጵያ ምትባል አገር ከትግራዉያን ዉጭ እንደማይተሰብ ሲዝት ሲዘምት እንደነበር ሲታወቅ በስምምነቱም ሆነ በህገ -ኢህአዴግ መገለሉ የዚህ የሁለትዮሽ የፕሪቶሪያ ስምምነት ያላካተተዉ እንደመሆኑ በአፈፃፀም ረገድ የማይመከተዉ መሆኑን ነዉ ፡፡

የሰሞኑ የትህነግ መግለጫ ሁለቱ ጠላት ያላቸዉን አካላት በስም ጠቅሶ ከክልሉ የግዛት ወሰን እንዲለቁ ማዕከላዊ መንግስት ኃላፊነቱን ይወጣ የሚል ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ አይሉት ማስፈራሪያ ሲነገር ሰምተናል፡፡

ለመሆኑ ትህነግ በህገ -መንግስት/ኢህአዴግ መሰረት የግዛት እና ሉዓላዊነት መብት ይከበር ሲል የሌላዉን ኢትዮጵያ መብት ፣ ሉዓላዊነት እና ተፈጥሯዊ መብት ለመገሰስ ፣ ሠላም ለማደፍረስ ፣ኢትዮጵያን ለማፍረስ አስከ ሲዖል ድረስ…በህገ -ኢህአዴግ ሆነ በደቡብ አፍሪካ ስምምነት የትኛዉ ክፍል ላይ የተሠጠዉ ልዩ መብት ነዉ ፡፡

በጎንደር የሚገኘዉን ወልቃይት በጉልበት የያዘዉ በአስራ ዘጠኝ መቶ ሠባ ዓ.ም በፊት ሆኖ ሳለ፣ በወሎ እና በጎጃም የሚገኙትን ራያ እና መተከል ሲሸነሽን በየትኛዉ ህግ እና ህዝበ ዉሳኔ እንደነበር ለምን አይነግርንም ፡፡

ሌላዉ የጎረቤት አገር ኤርትራ ኃይል ከትግራይ ግዛት እንዲወጣ ማዕከላዊ መንግስት መስራት እንዳለበት ይጠይቃል ፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵ ኤርትራ ጦርነት ለአገር አንድነት እና ለህዝቦች ሉዓላዊነት ህይወቱን የገበረ ህዝብ በተደጋጋሚ በተካደበት ህዝብ አስጨራሽ ጦርነት የከፈለዉ መስዋዕትነት ተረስቶ እና ተክዶ በተለይ ለዓማራ ህዝብ ጦርነት የደረገሰለት ትህነግ የኤርትራ ጦር ሲገባ የት ነበር አስካሁንስ ምን ሲሰራ ነበር ፡፡

የዓማራ ህዝብ ትህነግን  ከደደቢት አስከ አስከ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ጎትቶ ያስገባዉን ዉለታ ደጋግሞ በመካድ ዛሬም በወራሪነት ከመክሰስ ለምን ግዛቱን አያስከብርም ፡፡

የበሬ ግንባር በማትሞላ ባድመ የተከፈለዉ ዋጋ ተረስቶ ዛሬ ላይ ስለ ኤርትራ ወረራ ማዉራት ምን ይባላል ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ በአልሞት ባይ ተጋዳይ ራሱን ለመከላከል የተጠመደለትን የወረራ ፣ ምዝበራ   የሞት ወጥመድ ለማለፍ ባደረገዉ ከፍተኛ ተጋድሎ ወልቃይትን ሆነ ራያን ወደ ነበረ አፎታቸዉ (በታሪክም በህግም) መልሷል፡፡ ይህ ደግሞ ምኑ ላይ ስህተቱ ፡፡ አበዉ “በመማል ከሆነ ላሟ የኔናት ”እንዲሉ በዕዉነት ከሆነ ራያም ወልቃይትም የኢትዮጵያ ዕምብርት አካል የሆኑት ጎንደር እና ወሎ ግዛት አካል ነበሩ ፤ናቸዉ ፡፡ እኮ በህግ አይባል በህግ ሳይሆን በጉልበት ነበር የተወሰዱት  ፤በታሪክ አይባል ታሪክ ይናገራል ፤ይመሰክራል፤በመልካ ምድር አይሉት ተከዜ የት ይሁን ፡፡

ህገ – መንግስት/ ኢህአዴግ የግል የፖለቲካ ትርጉም በመለዋወጥ  በህገ መንግስት መሰረት የሚለዉ የፕሪቶሪያ ስምመነት የተለያዩ ክፍሎች  ትህነግ ያክብረዉ፣ በአንድ አገር ሁለት ጦር የለም የትግራይ መከላከያ ኃይል ይክሰም፣ ድርጂቱ ስሙን ይዞ /ህወሀት ይቀጥል…ይላል እንጂ የትኛዉንም ኃይል ጠቅሶ ከትግራይ ይዉጣ አይልም፡፡

ከዚህ የምንረዳዉ የፕሪቶሪያ ስምምነት በትግራይ እና ማዕከላዊ መንግስጥ ጦርነት ይቁም ፤ ሠላም ይስፈን ፣ ሞት እና ስደት ይገታ…ይላል እንጂ ሌላ ሶስተኛ ወገን በትግራይ ክልል ስለመኖሩ የተነሳ አንዳችም ነገር የለም ፡፡

ለዚህ ነዉ ትህነግ በሰሞኑ መግለጫ ሁለቱ ገዳይ እና ወራሪ ኃይላት የሚላቸዉን በህገ -መንግስት እና በማዕከላዊ መንግስት አማካኝነት ይዉጡ ሲል በስምምነቱ ላይ ያልተገለፁትን  በፕሪቶሪያዉ ስምምነት መሰረት የማይዉ ከሆነ ማለት እንዴት ይቻላል ፡፡

ስምምነቱ ብረትም ሠላምም ይዉረድ ፣ ጥላቻ እና አለመግባባት ይወገድ ብሎ ሁለቱን ተስማሚዎች አስማማ እንጂ በህገ መንግስቱም ሆነ በመንግስት ወራሪዎች እና ተስፋፊዎች የሚል አንድም የለም ፡፡

ወራሪ እናተስፋፊ ቢባል እንኳ በዚህ ምክነያት ጦርነት በዓማራ ህዝብ ላይ የከፈተ ትህነግ ይቅርታ መጠየቅ እና ከሳ ከፍሎ መታረቅ የነበረበት ነዉ ፡፡

እናም ለሁሉም የሚበጀዉ እና ሚያዛልቀዉ ፍቅር እና መተባበር እንጂ ወራሪ እና ገዳይ ማለት “ጂራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ….” ነዉና እየተስተዋለ ቢሆን ለአገር አንድነት እና የህዝቦች ሉዓላዊነት መስራት ይጠቅማል ፡፡ ካሳ እና ጥበቃ ሊጠይቅ የሚገባዉ የተበደለ እና የተገፋ ነበር ዳሩ ኢትዮጵያዉያን ነን ድሮ እንጂ ዘንድሮ የለንም ፡፡

በኢትዮጵያ ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ስምምነት እንዲመጣ የምንፈልግ ሁሉ በትህነግ የግዛት መስፋፋት እና ወረራ ጦርነት ያወጀዉ ፣ ያካሄደዉ እና መጠነ ሠፊ ጥፋት ያደረሰዉ ማን እንደሆነ ሲታወቅ እና የዚህ ባለቤት በስም ሲጠራ እና ተጠያቂ መሆን ሲችል ብቻ ነዉ ፡፡

ለዚህ በጥቂቱ የመጀመሪያ ሮኬት የተላከዉ  አስመራ ፣ ጎንደር እና ባህርዳር መሆኑን ለሚያዉቅ በዳይ እና ተበዳይ ፣ገዳይ እና ሟች ማን እንደሆነ መለየት የሚሳነዉ ቢኖር ለሠዉ ልጆች ደህንነት እና መኖር ግድ የማይሰጠዉ ሠዉ ሆኖ ግዑዝ ለመሆን ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሠዉ መሳይ ፍጡር ብቻ ነዉ ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

ማላጅ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop