November 2, 2023
41 mins read

በኢትዮጵያ ምድር የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን!!! –  ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

corenel Abiyበኢትዮጵያ ምድር የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን  በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋርና በኦሮሚያ ክልሎች ሠላማዊ ዜጎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል!!!

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል በዓየር ኃይልና በድሮውን ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ በትግራይ ክልል፣ በአማራ ክልል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ያደረሰውን የሞትና የማቁሰል አደጋ በመፈጸም  በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ዘንድ ከነማስረጃው በመጋለጥ ላይ ይገኛል፡፡ የኮነሬል አብይ አገዛዝ የኢንተርኔት መረጃ አገልግሎቶችን  በሙሉ በመዝጋት፣ የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክ፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በሙሉ በመዝጋት በአየር የቦንብ ጥቃት፣ በሰው ዓልባ ድሮውን የቦንብ ጥቃት በመፈጸም ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል፡፡  ሰው ዓልባ ድሮውን ከሠማየ ሰማያቱ ላይ የምትበረውን ጢያራ ከምድር ያለ ሰው በርቀት በራዲዬ የሚቆጣጠሩት ቦንብ  ጣይ ድሮውን ስትሆን በቀዶ ጥገና መሣሪያ ኢላማውን ብቻ የሚመታ ያልተፈለጉ ኢላማዎች ማለትም ሰላማዊ ሰዎች፣ አዋቂ ሰዎችና ህጻናትን  ሳይነካ በወታደራዊ ሳይንስ ቀዶ ጥገና በጥበብ የሚፈጸም ሲሆን አላዋቂዎች ግን ሕዝብ ይጨፈጭፉበታል፡፡            ‹‹ Drones are remotely radio-controlled bombs, surgical weapons that could avoid unwanted targets such as civilians, adults and children, but it appears that, as per the PAX report:››……………(1) 

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል ለዘመናት እራሱን የገነባው በሚግ ሃያ ሦስት (Mig-23)፣ ሱክሆይ ሱ ሃያ ሰባት (Sukhoi Su-27) እንዲሁም ሚሳኤልና ቦንብ ጫኝ አጥቂ ሂሊኮፕተሮች ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ድንበር ከጠላት ሲጠብቁ የነበረበት ወርቃማ ዘመን አክትሞል፡፡ ዛሬ የኮነሬል አብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ፣ ዓየር ኃይል በህዝብ ላይ  ጭፍጨፋ የሚፈጽም  ኢላማ ስተው ንፁሃን ዜጎችን በመግደል ላይ ይገኛሉ፡፡ በኮነሬል አብይ ዘመን የገቡ የቱርክ ሰው ዓልባ የጦር ድሮውን ባይራካታር ቲቢ-ቱ (Bayraktar TB-2)፣ የቻይና ዊንግ ሎዎንግ (Wing Loong)፣ የኢራን ሞሃጀር-ስድስት( Mohajer-6) በሃረር ሜዳ፣ በብሸፍቱ፣ በሰመራ፣ በባህርዳር ወታደራዊ ዓየር ማረፍያ፣ በህዝብ ላይ የቦንብ ጥቃት በመፈጸም ግዳጅ ላይ ተሠማርተዋል፡፡

 

በአማራ ክልል፡-የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን የኦክቶበር መጨራሻ 2023እኤአ ሪፖርት መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት የስብዓዊ መብቶች ጥሰት በአማራ ክልል ላይ አድርጎል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአየር በሰው ዓልባ ድሮውን የቦንብ ጥቃትና የመድፍ ጥቃት በሸዋ ምንጃር፣ በጎጃም ደብረማርቆስ፣ በጎንደር ደንበጫ ሥፍራዎች ላይ በመፈጸም ብዙ ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን በሪፖርቱ ገልፆል፡፡ በሰሜን ሸዋ በሰው ዓልባ ድሮውን የቦንብ ጥቃት የተነሳ 3000 (ሦስት ሽህ) ሠላማዊ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡ “The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) on Monday released a statement regarding human rights violations in the Amhara region of Ethiopia. In the statement, it is confirmed that the Ethiopian Defense Force used drone strikes and artillery attacks, resulting in many civilian deaths in the region. Local media outlets in Ethiopia have been reporting on drone strikes and artillery attacks. Among other drone attacks, the EHRC, established by the Ethiopian government, has confirmed that there were drone strikes in North Shoa (Minjar), Gojjam, and Gondar areas of the Amhara region. In one of the drone attacks, many civilians, including a toddler, were killed. Drone attacks in Debre Markos and Dembecha also killed many civilians. In other parts of the region, the Defense Force extensively used artillery against residential homes and civilian infrastructures. Again, all these have been reported by local media outlets, and borkena has covered them. EHRC confirmed the stories by contacting eyewitnesses and residents from affected areas of the region. In areas like North Shoa, as many as 3,000 civilians have been displaced due to shelling and drone strikes.”…………………………..( Ethiopia: EHRC confirms drone strike, artillery attacks killed civilians/October 31, 2023)

{I} በኢትዮጵያ ምድር የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን  በአማራ ክልል ሠላማዊ ዜጎችን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛሉ!!!

 

{1} የተባበሩት መንግሥታትና የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት መሠረት ባለፈው ኦግስት ወር ጀምሮ አማራ ክልል በትንሹ 183 (መቶ ሰማንያ ሶስት) ሰዎች በሰው ዓልባ ድሮዎንና በመድፍ ጥቃት መሞታቸውን አስታውቆል፡፡ ኦክቶበር 10 ቀን 2023 እኤአ በጎጃም አዴት ከተማ 12 የቄስ ተማሪዎች በመንግሥት ኃይል መገደላቸው ተገልጾል፡፡ ከሳምንት በኃላ ደግሞ የአስራ ዘጠኝ ወር ህጻን ልጅ በበረህት ወረዳ በድሮውን ተገድሎል፡፡

“ADDIS ABABA, Oct 30 (Reuters) – Dozens of civilians have been killed this month by drone strikes and house-to-house searches in Ethiopia’s Amhara region, where authorities have touted security gains since conflict erupted in July, a state-appointed human rights commission said on Monday.

At least 183 people were killed in the first month of the conflict, the United Nations said in late August. But with internet connections down across the region, it has been difficult to get a clear picture of the situation.”

“In a new report, the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) documented several incidents in which civilians were killed this month. In one, 12 civilians, including religious students, were killed on Oct. 10 during house-to-house searches by government forces in the town of Adet, the report said.

A week later, a 19-month-old child was among the victims of a drone strike in the town of Berehet Woreda, while another drone strike on Oct. 19 killed eight civilians in Debre Markos, it said.”

 

{2} ጥቅምት 2016ዓ/ም በአማራ ክልል ሦስት ቦታዎች ላይ የድሮውን ጥቃት ተፈፅሞል፡፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካንፓስ፣ በውትር ወንዝና ዩሃንስ አካባቢ በተፈጸመ የድርዎን ቦንብ ድብደባ ብዙ ሠላማዊ ሰዎች ሞተዋል፡፡ የአገዛዙ ሠራዊት ስምንት የአብነት ተማሪዎች በግፍ ረሽኖ ገድሎ መንገድ ላይ እንደጣለ ተረጋግጦል፡፡

{3} በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ በበረህት ወረዳ ሠላሳ አምስት ሰዎች በድሮውን የቦንብ ጥቃት ንጹሃን ሰዎች በግፍ ተገድለዋል፡፡ በአማራ ክልል መራኛና ዓለም ከተማ የድርዎን ቅኝት በተደጋጋሚ ሲከናወን አድሮል፣ አገዛዙ ለሌላ የድሮውን ጥቃት እቅድ ነድፎል፡፡  

{4} ቪኦኤ፤- በአማራ ክልል በኦግስት 14 ቀን 2023 እኤአ 26 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡ ዜናውን ቢቢሲና አልጀዚራ ዘግበውታል፡፡ At Least 26 Killed in Drone Strike in Ethiopia’s Amhara …/VOA/ https://www.voanews.com › at-least-26-killed-in-dro…

Aug 14, 2023 — Health workers say at least 26 civilians were killed in a drone strike in a town in Ethiopia’s Amhara region. Federal government forces and …

  • ቢቢሲ፡- በአማራ ክልል በኦግስት 14 ቀን 2023 እኤአ  በፍኖተሠላም 26 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡Ethiopia Amhara: Air strike kills at least 26 in Finote Selam/BBC/https://www.bbc.com › news › world-africa-6502937/Aug 14, 2023 — A suspected air strike in Ethiopia’s Amhara region has killed at least 26 people, a hospital official said. The strike in Finote Selam on … 
  • አልጀዚራ፡- በአማራ ክልል በኦግስት 14 ቀን 2023 እኤአ  26 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡ Suspected air strike kills two dozen people in Ethiopia’s …/Al Jazeera/https://www.aljazeera.com › news › suspected-air-stri…/Aug 14, 2023 — A suspected air strike in Ethiopia’s Amhara region has killed at … Ethiopia’s government denies the allegations by Fano, an informal …

{5} ዩቲዩብ፡- በአማራ ክልል myYe 18 ቀን 2023 እኤአ ሸዋ ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡ Breaking News Ethiopia: Drone strikes on the Amhara/ …YouTube/https://www.youtube.com › watch/May 18, 2023 — Breaking News EthiopiaDrone strikes on the Amhara Region #Ethiopia #ethiopianews #Amhara #Fano #Shewa #amharanews Subscribe to my other … 

{6} ቦርከና ዜና፡-በአማራ ክልል ጎጃም ሠላማዊ ሰዎች በሴፕቴምበር 19ቀን 2023እኤአ በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡  A drone strike killed at least thirty civilians in Gojjam/Borkena/https://borkena.com › Ethiopian News

Sep 19, 2023 — The drone strikes were in two locations. However, the second drone attack did not cause human casualties as it landed in a forest area, …

{7} ኤጀንዚያ ኖቫ፡-በአማራ ክልል በኦግስት 14 ቀን 2023 እኤአ ሂ ፍኖት በትንሹ 30 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት ተገለዋል፡፡Ethiopia: press sources, at least 30 civilians killed in a …/Agenzia Nova/ https://www.agenzianova.com › news › etiopia-fonti-st…/Aug 14, 2023 — … drone attack in the Amhara region Read all the latest news on Agenzia Nova. … attack in the locality of Hi Finote, in the Ethiopian region of …

{8} ዘ-ኢኮኖሚስት፡- በአማራ ክልል በኦግስት 15 ቀን 2023እኤአ  22 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት እንደ ቆሰሉና ተገደሉ  ተገልፆል፡፡ Ethiopia risks sliding into another civil war/The Economist/https://www.economist.com › 2023/08/15 › ethiopia-…/Aug 15, 2023 — A number of civilians have been injured or killed, some of them in a drone strike on August 13th. “We buried 22 people,” says a resident of …/Aug 15, 2023 — This was the most severe strike since the conflict between the Ethiopian army and a local militia erupted in towns and cities across Amhara.

{9}  ቢቢሲ ኒውስ አፍሪካ፡- በአማራ ክልል በኦግስት 14 ቀን 2023 እኤአ 70 ሠላማዊ ሰዎች በሰው ዓልባ የድሮውን ጥቃት እንደ ቆሰሉና ተገደሉ  ተገልፆል፡፡BBC News Africa/Twitter/ https://twitter.com › BBCAfrica › status/Aug 14, 2023 — An Ethiopian army drone has bombed protesters in Amhara, killing at least 70, local media reports. Air strikes reportedly hit demonstrators, …

 

{10} ጋሮው ኦንላይን/  የኢትዮጵያ መንግስት በሴፕቴንበር 26 ቀን 2022 እኤአ በአማራና አፋር ክልሎች የድሮውን የቦንብ ጥቃት  ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡Drone strike hits UN truck in Tigray, northern Ethiopia/ Garowe Online/https://www.garoweonline.com › world › africa › dro…/ Sep 26, 2022 — … attacks in the Amhara and Afar regions. Ethiopian authorities have not yet commented on today’s air strikes but previously, the government …

የኮነሬል አብይ ፋሽስታዊ ሥርዓት በጫረው  የአማራ ክልል ጦርነት በአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ ከፍተኛ ጥቃት ተፈፅሞበታል፣ ሠራዊቱም ተሸንፎል፡፡ በዚህም የተነሳ በአማራ ክልል ሠላማዊ ህዝብ ላይ አስራ ሦስት የድሮውን ጥቃት ለመፈጸም፣ በሰሜን ሸዋ ሦስት እንዲሁም በጎጃም ስምንት የተመረጡ ቦታዎች ላይ የቦንብ ጥቃት ለማድረግ እቅድ እንዳለ የውስጥ ምንጮች አጋልጠዋል፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት፣ የዓየር ኃይል ሹም ጀነራል ይልማ መርዳሳ በድሮውነ በሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት የቦንብ ጥቃት ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን እየገደለና እያቆሰለ እንዳለ በማወቅ በዓለም ህብረተሰብ ዘንድ ይህ የጦር ወንጀል በመገናኛ ብዙኃን በየእለቱ እየተዘገበ እንዳለ ህዝብ እንዲያውቀውና ወንጀለኞቹ ለዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የማቅረብ እንቅስቃሴን በማስረጃ አስደግፎ ለማቅረብ ኢትዮጵያዊያን እየሰሩ ይገኛል፡፡በአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች የወታደር ካንፕ ሆነዋል፡፡ተማሪዎችና አስተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ የሉም፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት መሠረት ሰባት ሚሊዮን ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ላይ ተለይተዋል፣ ወደ ትምህርት ቤታቸው አልተመለሱም፡፡ በኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት መሠረት ደግሞ በትንሹ 200 ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት በመከላከያ ሠራዊቱ አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል፡፡ የሠላማዊ ሰዎችን ንብረት ማውደም፣ እርሻዎችን ሆን ብሎ ማቃጠል፣ ህዝባዊ መሠረተ-ልማቶችን ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታል፣ ክሊኒክ፣ ጤና ጣቢያ፣ የመብራት፣ ውኃ፣ ስልክ ተቆሞችን ሆን ብለው ማውደም የእለት ተእለት ድርጊታቸው ሆኖል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል ለእራሱ የወደፊት ህልውና ሲል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በማበር አፈሙዙን በኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልጽግና  አገዛዝ ሹማምንቶች ላይ በማድረግ ከህዝብ ጋር መቆም ብቸኛ አማራጩ ነው ብለን እንመክራለን፡፡ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል  የኮነሬል አብይ መንግስት የድሮውን የቦንብ ጥቃት  ዜናውን ከአማራ ክልል ጀምረን የትግራይንና ኦሮሚያ ክልሎች ለናሙና ያህል በተከታታይ እናቀርባለን፡፡ “Schools in many parts of the region are turned into makeshift military camps for the Ethiopian government soldiers. It means that schools are closed, and students are out of school. This month, a report by the UN agency indicated that more than seven million children have not returned to school. Rape in the context of the ongoing war in the region is also confirmed by the EHRC. According to its report, since July this year, at least 200 women were raped by Ethiopian government soldiers. The figures are from hospital sources, indicating the possibility that the number could be much higher, considering that many do not visit health facilities after becoming victims of rape. Another key confirmation from the report is that civilian properties and crops are deliberately destroyed by government forces. Civilian infrastructures are targeted and destroyed.”

{II} በኢትዮጵያ ምድር የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን  በኦሮሚያ ክልል ሠላማዊ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል!!!

{1} በኦሮሚያ ክልል፣ ሸንቡ ዞን፣ አቤደንጎሩ ወረዳ ሃያ ሦስት ንፅሃን ሰዎች በድሮውን የቦንብ ጥቃት ተገድለዎል፡፡

{2} ኦላላአ ደት ኦርግ/ የኢትዮጵያ መንግስት በኦክቶበር 25 2022እኤአ የድሮውን የቦንብ ጥቃት በኦሮሚያ ክልል ህዝብ ላይ ፈፅሞል፡፡ DRONE ATTACKS AND VIOLENCE ACROSS WESTERN …OLLAA -/https://ollaa.org › drone-attacks-and-violence-across-…/Oct 25, 2022 — OLLAA has received reports of drone attacks by the Ethiopian government throughout Oromia in recent days, leading to the death of civilians

{3} አዲስ ስታንደርድ/ የኢትዮጵያ መንግስት በኦክቶበር 13 ቀን 2023እኤአ  በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ 12 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የድሮውን የቦንብ ጥቃት ፈፅሞል፡፡News: Drone attacks coinciding with Irreechaa result in a …/Addis Standard/https://addisstandard.com › Politics/Oct 13, 2023 — Addis Ababa – Over 12 individuals were reportedly killed in two separate drone attacks conducted by government forces in the Horro Guduru …

{4} ኤፒ ኒውስ/ የኢትዮጵያ መንግስት በኦክቶበር 26 ቀን 2022 እኤአ  በኦሮሚያ ክልል ሜታ ወልቃይት ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የድሮውን የቦንብ ጥቃት ፈፅሞል፡፡ Witnesses: Drone strikes in Ethiopia’s Oromia kill civilians/AP News/https://apnews.com › article › africa-kenya-ethiopia-…/Oct 26, 2022 —  “The attack happened around 12 p.m. in the Metta Welkite area. There was an earlier drone strike, and they went out to carry injured people to …

 

{5} ፎሬን ፖሊሲ/ የኢትዮጵያ መንግስት በኖቨንበር  16 ቀን 2022 እኤአ  በኦሮሚያ ክልል ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የድሮውን የቦንብ ጥቃት ፈፅሞል፡፡Ethiopia Faces Growing Crisis in Oromia/Foreign Policy/

https://foreignpolicy.com › 2022/11/16 › ethiopia-war-t…/Nov 16, 2022 — According to the Ethiopia Peace Observatory, drone strikes conducted … 9, Zambian foreign minister Stanley Kakubo said on Monday in a media …

 

{6} Witnesses: Drone Strikes in Ethiopia’s Oromia Kill Civilians/U.S. News & World Report/https://www.usnews.com › News › World News/ Oct 26, 2022 — … Press that drone strikes in Ethiopia’s Oromia region killed several dozen civilians last week. The attacks in strongholds of the rebel Oromo …

{III} የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን በኢትዮጵያ ምድር ላይ የትግራይ ክልል ሠላማዊ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል!!!
{1} ዘአፍሪካ ሪፖርት/ የኢትዮጵያ መንግስት በጀንዋሪ   25 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል በማይ ጠምሪ ከተማ ወፍጮ ቤት አጠገብ 17  ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የድሮውን የቦንብ ጥቃት ፈፅሞል፡፡Ethiopia’s drone wars: Iran, China and Turkey deliver the …/The Africa Report/https://www.theafricareport.com › ethiopias-drone-wars…Jan 25, 2022 — The same day people, a drone strike hit a flour mill near the town of Mai Tsebri in western Tigray, killing at least 17 people. Days earlier a …

{2} የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት/  የኢትዮጵያ መንግስት በአፕሪል 6 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል ሁለት ጊዜ  10  ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የድሮውን የቦንብ ጥቃት ፈፅሞል፡፡2022 Country Reports on Human Rights Practices: Ethiopia/U.S. Department of State (.gov)/https://www.state.gov › reports › ethiopia … media two consecutive drone strikes in a single day killed 10 civilians. According to an April 6 joint report released by HRW and Amnesty International …

{3} ዓለም አቀፍ የስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን / የኢትዮጵያ መንግስት በሴፕቴንበር 22 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት  በሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡International Commission of Human Rights Experts on …/Ohchr/https://www.ohchr.org › 2022/09 › international-co…/Sep 22, 2022 — We have received reports of drone strikes in Tigray in the last four weeks, which have allegedly killed and injured civilians, including …

{4} ዘ-ኒውዬርክ ታይምስ/ የኢትዮጵያ መንግስት በጀንዋሪ 11ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት  በስደተኞች ካንፕ ባሉ  50 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡On Day Biden Calls Ethiopia’s Leader to Urge Peace, a …/The New York  Times/https://www.nytimes.com › World › Africa/Jan 11, 2022 — The attack came days after over 50 people were killed in a strike on a refugee camp, highlighting the growing role of armed drones in a …

{5} ዘጋርዲያን/ የኢትዮጵያ መንግስት በጀንዋሪ 11ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት   19 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡Ethiopia: 19 people killed in latest drone strikes in Tigray/The Guardian/https://www.theguardian.com › world › jan › ethiopi…/Jan 11, 2022 — Nineteen people have been killed in drone strikes in Ethiopia‘s Tigray, in the latest reported attacks in the war-stricken region.

{6}  ሮይተር/ የኢትዮጵያ መንግስት በሴፕቴንበር 13 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት   አንድ ሠላማዊ ሰው   የመቁሰል አደጋ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ደርሶበታል፡፡Drone strikes hit Ethiopia’s Tigray region after ceasefire offer/ Reuters/https://www.reuters.com › world › africa › air-strike-hit…/Sep 13, 2022 — One person was injured in drone strikes on Mekelle University and a TV station in Ethiopia’s Tigray region, the station and a hospital …

 

 

{7} ፈራንስ 24/  የኢትዮጵያ መንግስት በሴፕቴንበር 14 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት   አስር  ሠላማዊ ሰው   ሞተዋል፡፡10 killed in twin air strikes on Ethiopia’s Tigray: hospital/France 24/ https://www.france24.com › France 24 › Live news/Sep 14, 2022 — 10 killed in twin air strikes on Ethiopia’s Tigray: hospital. Nairobi (AFP) … The reported attack followed another drone strike on Tuesday on …

  • Ten dead in second day of air raids in Ethiopia’s Tigray …/Al Jazeera/ https://www.aljazeera.com › news › air-strike-hits-ca…/Sep 13, 2022 — Fasika Amdeslasie, a surgeon at the same hospital, said the first bombing injured two women, followed by a second “dronestrike on the people …

{8} የኢትዮጵያ መንግስት በጀንዋሪ 9 ቀን 2022 እኤአ እስከ ኦክቶበር 18 ቀን 2022እኤአ ድረስ   በትግራይ  ክልል   የድሮውን የቦንብ ጥቃት  146 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 213  ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ Aid workers say Ethiopia air strike in northwest Tigray killed …/CNBC/https://www.cnbc.com › 2022/01/09 › aid-workers-say-…/Jan 9, 2022 — Before the latest strike, at least 146 people have been killed and 213 injured in air strikes in Tigray since Oct. 18, according to a document …


{9} የኢትዮጵያ መንግስት በጀንዋሪ 11ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል በሽሬ ከተማ የድሮውን የቦንብ ጥቃት   በየቀኑ በሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡Ethiopian drone strike kills 17 on day of Biden-Abiy call/CTV News/https://www.ctvnews.ca › world › ethiopian-drone-strik…/
Jan 11, 2022 — Such drone strikes have been reported almost daily in Tigray, a humanitarian worker in the town of Shire told the AP, with an attack over the …

{10} የኢትዮጵያ መንግስት በሴፕቴምበር 14ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል በመቐለ ከተማ  የድሮውን የቦንብ ጥቃት  10 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡10 killed in twin air strikes on Ethiopia’s Tigray: hospital/Arab News/https://www.arabnews.com › node › world/Sep 14, 2022 — 10 killed in twin air strikes on Ethiopia’s Tigray: hospital. 10 killed … The reported attack followed a drone strike on Tuesday on Mekele …


{11} Ethiopia’s economy struggles as war reignites in Tigray

WTOP/https://wtop.com › World News/

On Tuesday morning, a drone strike hit a university campus in Tigray’s capital, Mekele, causing an unknown number of injuries, according to a media worker …

  • How out of place with the news that arrivesthe same day, Monday 10 January , regarding yet another air raid in which 17 civilians were killed by means of killer drones, radio-controlled bombs in Mai Tsebri.
  • On Saturday 8 January, the area of ​​Dedebit, in northwestern Tigray , suffered the same atrocious treatment: target IDP refugee camp where 57 people including children were killed, injuring 126 including 28 critically: the United Nations informed who have suspended humanitarian activities in the area .
  • On Wednesday 5 January, another drone attack bombed a refugee camp with a disastrous conclusion for several Eritrean civilians, including children.
  • On Tuesday 11 January, the e x President of Mekelle University Kindeya Gebrehiwot reported through social media that a drone attack hit the church of Hiwane, in the south-eastern Tigray area, killing 2 civilians.
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ደደቢት የድሮውን የቦንብ ጥቃት   56 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 128 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   አላማጣ  የድሮውን የቦንብ ጥቃት   56 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 48 ሰዎች  150 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   መቐለ ከተማ የድሮውን የቦንብ ጥቃት   33 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 110 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ሚላዛት የድሮውን የቦንብ ጥቃት   30 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 8 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ዳይሮ ሃፋሽ የድሮውን የቦንብ ጥቃት   25 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ማይጸብሪ የድሮውን የቦንብ ጥቃት   20 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 10 ሰዎች በላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ኮረም የድሮውን የቦንብ ጥቃት   15 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 7 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ሽሬና አክሱም የድሮውን የቦንብ ጥቃት   7 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 34 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ማይጨው የድሮውን የቦንብ ጥቃት   3 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 7 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
  • የኢትዮጵያመንግስት በጀንዋሪ 8 ቀን 2022 እኤአ  በትግራይ  ክልል   ጨርጨር የድሮውን የቦንብ ጥቃት   2 ሠላማዊ ሰዎች  ላይ የሞትና 4 ሰዎች  የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
    • ፀረ-ድሮውን መሣሪያ፡-ድሮውን ርቀት በሚተኩስ ጠመንጃ ጥይቶች፣ ሮኬቶች፣ ጄፓርድስ፣ ፓትርዬት፣ ወይም አይሪሽ-ቲ ተመቶ ይወድቃል፡፡ የዩክሬን አስር ሽህ ድሮዎኖቾ በየወሩ በራሽያ ተመተው ይወድቃሉ፡፡ “There are two main ways to down a drone- kinetically and electronically. The first means shooting down a drone with bullets, rockets, or similar. Ukraine has been using Gepards, Patriots, or Iris-T to fight against attacks from the air. The second means jamming or interrupting the signal between the drone and its operator(s).” https://ecfr.eu>article>drones-in-…

 

መደምደሚያ

ስብዓዊ መብቶችና የህግ የበላይነት Human rights and rule of law በኮነሬል አብይ አምስት አመት አገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶችና የህግ የበላይነት ውልቅልቁ ወጥቶል፣ ህዝቡ በህይወት የመኖር የህልውና መብቶቹን ለማስከበር በዱር በገደሉ ሥርዓቱን በመፋለም ላይ ይገኛል፡፡ የጦር ወንጀለኞቹን፣ የዘር ፍጅት ወንጀለኞቹን እንዲሁም የጦር ወንጀለኞቹን ለፍርድ ለማቅረብ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡

  • የኮነሬል አብይ ኦሮሙማ መንግሥት ሊወድቁ አንድ ሃሙስ የቀረው መንግሥትነው ስንል ከዋና መለኪያ መሥፈርቶች ውስጥ ማንኛውም ሰው በግል የሚፅፋቸውና የሚጻጻፋቸው በፖስታ፣ የሚልኮቸውን ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም ቴሌፎን በቴሌኮሙኒኬሽንና በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች የሚያደርጎቸውን ተፈጥሮዊ መብቶችና ግንኙነቶች በማፈን፣ በመሰለልና ጆሮ በመጥባት ጋዜጠኞችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ምሁራኖችን  አፍኖ በማሰር፣ ሰዎችን በመሰወር ፣ ባለጸጎችን አግቶ ገንዘብ በመጠየቅ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በጉራጌ፣ በወላይታ፣ ወዘተ ዜጎች ላይ በፈፀሙት ወንጀል ህግ ፊት የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ የሃገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዝጋት አፋኝ ሥርዓት መሆኑ በዓለም ተጋልጦል፡፡
  • የኮነሬል አብይ ኦሮሙማ መንግሥት ሊወድቁ አንድ ሃሙስ የቀረው መንግሥትነው ስንል ከዋና መለኪያ መሥፈርቶች ውስጥ በስብዕና ላይ በፈጸሞቸው ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑት ወንጀሎች፣ በሠላማዊ ሰዎች ላይ በሰው ዓልባ ድሮውኖች ህዝብ መጨፍጨፍ፣ ሴቶች አስገድዶ መድፈር፣ የስው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውስድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ፣ ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡ በህግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግስት አካል ውሳኔዎች በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡ የኮነሬል አብይ መንግስት ሥልጣኑን በተቆጣጠረ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዬታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የወንጀል ተጠያቂዎች የትግራይ ህወኃት፣ የአማራው ብአዴን፣ የኦሮሞው ኦህዴድ፣ የደቡብ ደኢህዴን ዋና ወንጀለኞች በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡  በአስቸኳይ ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ የኮነሬል አብይ የብልጽግና ፓርቲ አስራሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን አባላትና ካድሬዎች በተለይ ዋናዎቹ ቀንደኛ ወንጀለኞች በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም፡፡  በአስቸኳይ ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በሰው አልባ ድሮውን በትግራይ፣ አማራ፣ አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ሠላማዊ ሰዎች የሞትና የመቁሰል አደጋ ላደረሱና በአምስት አመቱ የግፍ አገዛዝ ለተለኮሱ ጦርነቶች  የጦር ወንጀለኞችን  ለፍርድ ለማቅረብ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ መተባበር ያስፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

1ኛ/ ህወሓት ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት ግንባር ሆነው የገዙ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴድ በዋነኝነት አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሎቹ  ም/ሊቀመንበሮች  እና ካቢኔያቸው ውስጥ በፊትና አሁን የሠሩ ሁሉ፤ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡  የትግራይ ህዝብ የወያኔ ህወሓት አንባገነን ገዥዎችን ማስወገድ ግድ ይለዋል፡፡ የአማራ ህዝብ ብአዴን አንባገነን ገዥዎችን ማስወገድ ግድ ይለዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የኦህዴድ አንባገነን ገዥዎችን ማስወገድ ግድ ይለዋል፡፡ የደቡብ ህዝብ የደኢህዴድ አንባገነን ገዥዎችን ማስወገድ ግድ ይለዋል፡፡

2ኛ/ ህወሓት፣  በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ እስከአሁን ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና ቁስዊ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡

3ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጀምሮ እስከ ተጠናቋል በተደጋጋሚ ጊዜ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የተደረገው የሰላም ስምምነት ድረስ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው የህዝብ እልቂት፣ ሞት፣ መደፈርና ስደትና  ሰቆቃ፣ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡

4ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው፡፡

 

በኢትዮጵያ ህዝባዊ እንቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ለማቀጣጠል የአማራ ፋኖን ጥሪ እንጠብቃለን!!!

የኢትዮጵያ ህዝብ የሰው ዓልባ ድሮውን የቦንብ ጥቃትን በመቃወም በአማራ ህዝባዊ ግንባር ፋኖ፣ በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት በአገርአቀፍ ደረጃ በሚጠራ አገር አቀፍ ህዝባዊ ጥሪ በመጠበቅና በመዘጋጀት የኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥትን ግብአተመሬት ለመፈጸም የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘጋጅቶ የፋኖን ጥሪ ይጠብቃል፡፡ የፋኖን አገር አቀፍ ጥሪ ውስጥ፡-

  • በመላ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ውስጥ የሚካሄድ፣ የሦስት ቀናት ቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ፣
  • በመላ ኢትዮጵያ የሥራ ማቆም አድማ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር፣ የመምህራን ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር፣ የተማሪዎች ማህበራት፣ የወጣቶች ማህበር፣የሴቶች ማህበር፣ የባንኮች ማህበር ወዘተ የሥራ ማቆም አድማ
  • በመላ ኢትዮጵያ የታክሲዎችና የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ መኪኖች ማህበራት የሥራ ማቆም አድማ
  • በመላ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ሠራተኞች ማህበራት የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልጽግና ፋሽስታዊ መንግሥት ሥርዓትን መገርሰስ የሁሉም ክልሎች ህዝባዊ ኃላፊነታችን ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል አፈሙዝህን ወደ ኦህዴድ ብልጽግና አዙር!!!

የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!

ፍትህ ርትህ የሚሠጥ መንግስት ይመጣል!!!

ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

መከላከያ ሠራዊት ድንበር ይጠብቅ!!!

 

ምንጭ

(1) Ethiopia, drone air strikes with hundreds of civilian deaths in Tigray/January 13, 2022/ Davide Tommasin

(2)  source: SIPRI

(3) Ethiopia government to increase military budget by 500%{ByAddis Insight/May 28, 2022

ተጨማሪ ምንጮች  Sources:

Report by Wim Zwijnenburg – PAX: https://paxforpeace.nl/news/blogs/turkish-drones-join-ethiopias-war-satellite-imagery-confirms

Oryx Report: https://www.oryxspioenkop.com/2022/01/confirmed-arms-transfers-to-ethiopian.html

UNOCHA Infographic: https://gho.unocha.org/

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop