July 7, 2023
2 mins read

የዐማራ ኅልውና ቃል-ኪዳን

Amhara

ግንቦት ፪ ሽህ ፲፭ ዓ/ም

“የዐማራ ኅልዉና ቃል-ኪዳን” ባለፉት ሁለት ትውልዶች የዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠሙትን የኅልውና ተግዳሮቶች በሚገባ አስገንዝቦ አብረው የመጡ ዕድሎችን ለመጠቀም፣ አደጋዎችንም ለመቋቋም የሚያስችሉ ስልቶችን የሚጠቁም አቅጣጫ ሰጭ ሰነድ ነው። በዘመን ተሻጋሪ የወል እይታ የዐማራ ሕዝብ ማንነትን፣ ዕጣ- ፈንታውንና ሰቆቃ የወለደውን ንቃተ-ኅሊና በተጨባጭነት ይተርካል። በተለይም የዚህን ትልቅና ታላቅ ሕዝብ ታሪካዊነት፣ አኩሪ ስልጣኔ፣አብነታዊ እሴቶች፣ የፖለቲካ ማንነትና መሠረታዊ ጥቅሞችን ጨምቆ ያቀርባል።

ስለዚህም ዐማራዊ ድርጅቶችም ሆኑ ንቅናቄዎች የሕዝቡን ርቀተ-ሰፊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅሞችን አገናዝበው፤ “ዐማራነት መነሻችን፣ ኢትዮጵያዊነት መዳረሻችን” በሚል ብሒል እንዲታገሉ የሚረዳ የወል ራዕይን ይነድፋል። በተለይም በቅርቡ በፌደራል መንግስት የታዎጀበትን ጦርነት በዘላቂነት ለማሸነፍ ጠንካራ ድርጅትንና መሪዎች ማፍራት፣ ፍሬያማ ስልቶችንና ከመስዋዕትነት በኋላ ለሚገነባው ነጻና የበለጸገ ህብረተሰብ ፍኖተ-ካርታ እንዲነደፍም አቅጣቻዎችና አስቸኳይ ጥሪ ያቀርባል።The Amara Freedom Charter_May 2023

——

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop