May 13, 2023
82 mins read

በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያስቀር የአስቸኳይ ጊዜ ማኒፌስቶ – ዮናስ ብሩ (ዶ/ር)

ይህ የመወያያ ጽሁፍ የተዘጋጀው በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የብዙ ታዋቂ ኢትዮጽያውያን ግለሰቦች ና ቡድኖች ግብዐት ታክሎበት ነው ። 556 አካላት በተካፈሉበት የ ቅድመ ዳሰሳ ጥናት 67.6% የሚሆኑቱ በጽሁፉ የታሰበውን አለማቀፍ ንቅናቄ ደግፈዋል።  ጽሁፉ ለህዝብ የተሰራጨው በሀገር ውስጥ ና በውጭ የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጥልቀት እንዲወያዩበት ለማበረታታት ነው። አላማው አዲስ ድርጅት መፍጠር አይደለም ይልቁንም አሁን ያሉት ሕብረት እንዲፈጥሩና በሚገባ የተቀናጀ ንቅናቄ እንዲፈጥሩ ለማነሳሳት ነው ። ተስፋ ሰጪ ምልክቶች አሉ ።የፀሃፊው አድራሻ:   [email protected]

በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያስቀር የአስቸኳይ ጊዜ ማኒፌስቶ - ዮናስ ብሩ (ዶ/ር) 1

“የአማሮ ህዝብ በሶስት በኩል በኦሮሞ የተከበበ በመሆኑ ከሌሎች አጎራባች ብሄሮች ጋር እንዳይገናኝ መንገድ ተዘግቶበታል:: ለመግለጽ በሚያዳግት እና ይህ ነው በማይባል አፈና እና በመከራ ውስጥ ይገኛል:: ከመወረርና ከመጨፍጨፉም አልፎ እንደ አንድ ብሄር ህልውናው አደጋ ላይ ነው:: …”  (ሃሰን ሼካ  የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 11 ኛ መደበኛ ስብሰባ መጋቢት  2015)

“አንዳንድ የኦሮሞ ጅሎች የሸገር ከተማ ፊንፊኔን ከቦ የሚገነባው ምን ታስቦ እንደሆነ አይረዱም ጠላቶቻችን ሃሳባችን ገብቷቸዋል ‘” (ሺመልስ አብዲሳ ፣ የኦሮሞ ክልል ፕሬዝዳንት ለኦሮሞ ወጣቶች ያደረጉት ንግግር 2015)

‘’ የፌደራል መንግስቱን ለመገልበጥ የሚያሴሩ ፀረመንግስት ፅንፈኞች በአንድ ምሽት በመቶ ሺዎች  ሲገደሉ  ያያሉ’’ (ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በቴሌቪዥን የተላለፈ ንግግር 2015)

‘’ የፌዴራል መንግስቱን በሃይል ለማስወገድ ዐመፅ የሚያነሳሱ ፅንፈኞች በ 1970 ከነበረው ቀይሽብር የከፋ ደም የሚያፋሰስ  መዘዝ  እንደሚያስከትል ማወቅ አለባቸው.” (ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በቴሌቪዥን የተላለፈ ንግግር 2015)

“የዛሬይቱ ኢትዮጽያ ሩዋንዳ በዘር ፍጅት ዋዜማ በነበርችበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች” (አዲሱ አረጋ ፣ የብልጽግና ፓርቲ አለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ፣ ፌስ ቡክ 2015)

አበይት ጭብጦች 

‘’የኦሮሞ ብልፅግና ፍላጎት ምንድን ነው ?’’ ጥያቄው ቁልፍ ነው ምክንያቱም የጥያቄው መልስ ወደ ቀውሱ ምንጭ ስለሚወስደን ነው። ታዋቂው የኦሮሞ ማህበረስብ አንቂ ጃዋር መሃመድ ባወጣው ባለ 76 ገጽ ጽሁፍ ችግሩ የመጣው የኦሮሞ ብልጽግና የኦሮሞን ማንነትና ባህል በሌሎች አካባቢዎች ለመጫን ባለው ፍላጎት ነው ብሏል ። የኦሮሞ ብልጽግና ከምስረታው ጀምሮ በአከራሪዎችና ለዘብተኛ ቡድኖች መካከል ውስጥ ውስጡን የተካረረ ትግል ሲያደረግ ቆይቷል ።  ከአንድ አመት ተኩል ወዲህ ፅንፈኛው ቡድን በኦሮሙማ ዶግማ እየተመራ የስልጣን መዘውሩን ከእለት ወደ እለት ይበልጥ በመቆጣጠር ላይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀስ በቀስ ይህንን አካል ተቀላቅለዋል። ኦሮሙማ እኩል በእኩል በከፊል የአምልኮ ስርዐት ሲሆን በከፊል የፖለቲካ ዶግማ ነው። አስተሳሰቡን የተቀበሉ ሰዎች ከቤተሰብም ከሃይማኖትም በላይ አድርገው ያዩታል  መሪዎቹ  ኦሮሞ ማንነታቸው ከሃይማኖታቸው እንደሚበልጥ በአደባባይ ተናግረዋል።

የኦሮሙማ አላም በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የኦሮሞ የበላይነት የስፈነበት ስርዐት ከመፍጠር isባለፈ የባህል የበላይነት ለማስፈንም ያለመ ነው ። የማስፈፀሚያ መሳሪያው ሞጋሳ ነው ። ይህ የኦሮሞ በጉልበት የማስገበር ባህል ነው።

የኦሮም ክልል ፕሬዚዳንት ሺመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ብልፅግና ለወደፊቷ ኢትዮጽያ ያቀደው ስርዐት ገዳ መሆኑን ሲገልጹ ምንም አላመነቱም ። ገዳ የ16ኛው መቶ ክፍለዘመን ባህላዊ የኦሮሞ አገዛዝ ስርዐት ነው። ሺመልስ የብልጽግና ፓርቲ የተፈጠረው የኦሮሞን ጥቅሞች ለማስከበር ነው ስለሆነም መንግስታቸው የኦሮሙማን ምልክቶች በአዲስ አበባ ለማኖር በቢሊዮኖች እያወጣ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል። አዲስ አበባ 19% ብቻ ኦሮሞ የሚገኝባት ከተማ ነች ።

የኦሮሙማን የበላይነት ለማስፈን ባለው ጭፍን ፍላጎት መንግስቱ ምንም አይነት ፖለቲካዊ ይሁን ሌላ ተቃውሞ አይታገሰም ። በፌብርወሪ 15 የፀጥታ አካላት በጉራጌ ዞን የጠና የውሃ እጥረትን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ስድስት ሰዎችን ገድለው ከ 15 በላይ የሆኑትን አቁስለዋል

የጉራጌን ክልልነት የሚደግፉ የጉራጌ ብልፅግና  ና ሰላማዊ የጉራጌ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች የጥቃት ኢላም ሆነዋል።

የተከበሩ ሃሰን ሼካ በመጋቢት 2015 በተደረገው መደበኛ የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ያቀረቡት ቅሬታ ኦሮሞ ያልሆኑ ሌሎች ትንሽ ይሁን ትልቅ ብሔሮችን ስሜት የሚያንፀባርቅ ነው። ጭንቀት የታከለበት ጥያቄው ብሔሩ ኣማሮ የህልውና አደጋ ስጋት እንደተጋረጠበት የሚያመላክት ነው።

“የአማሮ ህዝብ በሶስት በኩል በኦሮሞ የተከበበ በመሆኑ ከሌሎች አጎራባች ብሄሮች ጋር እንዳይገናኝ መንገድ ተዘግቶበታል:: ለመግለጽ በሚያዳግት እና ይህ ነው በማይባል አፈና እና መከራ ውስጥ ይገኛል:: ከመወረርና ከመጨፍጨፉም አልፎ እንደ አንድ ብሄር ህልውናው አደጋ ላይ ነው:: …”

ምንም እንኳን ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች የተባባስ ቢሆንም ቀውሱ በመላ ሀገሪቱ የተስፋፋ ነው ። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ና የኦሮሞ ብልፅግና  አደገኛ ትርክቶችን በግዴለሽነት በመፈብረክ ና አማራውን በማጥቃት የፖለቲካ ማደናገርያ እያደረጉት ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንት ሺመልስ ‘’የኛ ጠላቶች” ሲሉ አማራን ማለታቸው እንደሆነ ሀገር ያወቀው ሚስጥር ነው። በቅርቡ ፕሪዚዳንት ሺመልስ ና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቻቸው ለ ትህነግ መሪዎች ያደርጉት ግብዣ ና የሞቀ አቀባበል ሃላፊነት የጎደለው የአማራ ና ትግራይ የድንበር ግጭትን እንደ መደለያ ና ማስፈራሪያ ለመጠቀም ያለም አደገኛ የኦሮሞ ብልፅግና የፖለቲካ ቁማር ማሳይ ነው። ይህ ያለጠቅላይ ሚኒስትሩ እውቅና ና ፈቃድ የተደረገ ነው ብሎ ለማሰብ ይከበዳል።

በአዲሱ የኦሮሞ ና ትግራይ የጫጉላ ሽርሽር ፣ ትህነግ አሁን ያለውን ቀውስ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የይገባኛል ጥያቄ የሚነሱባቸውን መሬቶች ለመያዝ እየተዘጋጀ ነው። የኦሮሞ ብልፅግና ና የትህነግ የወረት መተቃቀፍ ወደ አማራ ና ኤርትራ ሕብረት ያመራል። ይህ አደገኛ ውጤት ይፈጥራል። የአሜሪካ ድምፅ ‘’ በሀገሪቱ  የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እየተስፋፋ ነው ‘’ ሲል የዘገበው ልክ ነበር።

ከመንግስት መሩ የዘርማጥፋት ወንጀል በፊት የሩዋንዳ ሕዝብ ብዛት ከ 8 ሚሊዮን ያነስ እንደነበር ማስተዋል ያሻል ። የኢትዮጽያ ሕዝብ ብዛት በቅርቡ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተፈፀመባቸው ኣራት ሀገራት (ሩዋንዳ ፣ ቦስንያ ፣ ሱዳን ና ማይናማር) ድምር ይበልጣል።

ቀውሱ ሀገሪቱንና የአፍሪካ ቀንድን ወደ የመጨረሻው የጥፋት ዘመን ሊቀይራቸው አንድ ሓሙስ ቀርቶታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ልዩ ሃይል ና የሚሊሻ አባላት ትጥቅ እንዲፈቱ በማዘዝ ቀውሱን በማባባስ ላይ ናቸው። ምንም እንኳን መመሪያው ለሁሉም ክልሎች መሆን ቢገባውም ትኩረት የተደረገው በአማራውና በሁለተኛ ደረጃ በሶማሌ ክልል ነው።

በ ኖቨምበር 3 2022 ፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ትህነግ ትጥቅ መፍታት ነበረበት ። ከአራት ወራት በላይ አልፎ ስምምነቱን አላከበርም የፌደራሉ መንግስትም ምንም እርምጃ አልወሰደም ። በንፅፅር የአማራ ሃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ ከታዘዘ በሳምንቱ የፌዴራል ሃይሎች የአማራ ሃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት የጦር ሰፈሮቻቸውን እየከበቡ ነው። በፍጥጫው ሁለት የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ተገድለዋል። ትጥቅ የማስፈታት ውሳኔው ለዘላቂ ሰላም አስፈላጊ ነው  ነገር ግን በግልፅነት መተማመን በሚያጎለብት መንገድ ና የአፈጻጸም ማረጋገጫ እንዲኖረው ታቅዶ መተግበር አለበት ።

አማራ የትጥቅ ማስፈታት አላማውን ና ለማስፈጸም የተመረጠውን ጊዜ የመጠየቅ ሕጋዊ ምክንያቶች አሉት ። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግጭት በነበረበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ሽማግሌዎችን በቢሮው ጠርቶ ይህን ግጭት ያነሳሱት መንግስታቸውን ለመጣል የሚፍልጉ የአማራ ፅንፈኛ ሃይሎች ናቸው ብለው ነበር። መንግስቴን ከተገዳደሩ በአንድ ጀንበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እጨርሳለሁ ያሉት እኝሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ። አማራዎች የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አዘውትረው ጠላት እያሉ የሚጠሯቸው ሕዝቦች ናቸው። አማራ የትጥቅ ፍቱ ጥያቄውን ስጋቶቹ እስኪቀረፉ ና መተማመን የሚያስፍኑ እርምጃዎች እስኪወሰዱ ድረስ መቃወም አለበት ። ሁሉም አማራ ወጣት ና አዛውንት ሳይል የልዩ ሃይሉን ካምፖች ተራ ገብቶ በመቀመጥ በሰላማዊ መንገድ  መጠበቅ አለበት ። ኦሮሞ መራሹ ብልፅግና ጦርነት ካወጀ አማራው እራሱን መከላከል አለበት ። መሳሪያ ታጥቆ ራስን መከላከል ትጥቅን አውርዶ ጦርነት ከመግጠም ይሻላል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ ገብቶ በአስቸኳይ መፍትሄ ማምጣት አለበት ። በሰዎች ላይ ከተደቀነው የመጨረሻው ዘመን ፍጅት በተጨማሪ ለአለም አቀፍ ንግድ ና ፀጥታ ጥበቃ እየመጣ ያለውን አደጋ በቸልታ ሊያልፈው አይችልም። ከ አስር በመቶ የሚልቀው የአለም ንግድ ና 40 ከመቶ የሚሆነው የአውሮፓ እስያ ንግድ የሚተላለፈው በቀይ ባህር ነው ። ኢትዮጽያ ለቀጠናው መረጋጋት ወሳኝ ሀገር እንደመሆኗ በኢትዮጽያ የሚፈጠረው ሁሉ ለቀንዱ አካባቢ ይተርፋል።

ብሔራዊና አለምአቀፋዊ ንቅናቄው ሶስት አቅጣጫዎችን የተከተለ ይሆናል ። አንዱና ዋናው ተግባር እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቀልበስ የሚያስችል ሰፊ ቅንጅት መፍጠር ነው ። በምሳሌያዊ አገላለጽ በሚናወጽ አየር ውስጥ የሚበርን ሞተሩ የተበላሸ አውሮፕላን በሰላም የማሳረፍ ተግባር ነው ። እኛ እንደምናምነው ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር አውሮፕላኑን በሰማይ ላይ ከመሰባበር ማዳንና ከጥቅም ውጭ የሆነውን አውሮፕላን በሰላም ማሳረፍ ነው።

ሁለተኛው ተግባር በሕገመንግስቱ ማእቀፍ ለለውጥ ና ተጠያቂነት መስፈን መታገል ነው ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብልፅግና ውስጥ እያደገ የመጣ ቅራኔ እየታዘብን ነው  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የብልፅግና አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቅርብ ጊዚያት ገለፃዎች አይታደሙም ። ምክር ቤቱ የትህነግን የአሸባሪነት ፍረጃ ለማንሳት በተሰበሰበበት ወቅት ምልዐተ ጉባኤው የተሟላው ለጥቂት ሲሆን ከ60 የሚበልጡቱ ውሳኔውን ተቃውመዋል ። የጉራጌን ክልል መሆን የደገፉ አብዛኛዎቹ ጉራጌ የብልፅግና አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ና የኦሮሞ ብልፅግና  ደስተኛ ደጋፊዎች አይደሉም። የአማሮ ዞን ተወካይ ለምክር ቤቱ የገልፁት የኦሮም ብልፅግና የጋረጠው ስጋት ሁሉም አክባቢዎች የሚጋሩት  ነው።

ንቅናቄው የብልፅግና አባላት የኦሮሞ ብልፅግናን እንዲታገሉ ማንሳሳትና ማገዝ ላይ ማተኮር አለበት ። ሁሉንም የክልል ብልፅግና አባላት በኦሮሞ ብልፅግና ዐይን ማየት ትክክል አይደለም ። ለምሳሌ ብዙ አማራዎች ፀረ አማራ ብልፅግና አቋም አላቸው እንዲሁም እንዲጠፋ ይፈልጋሉ ይህ ግን ራስን መውጋት ና በጣም አደገኛ ነው። ሌላ አማራጭ የአማራ ድርጅት በሌለበት ደካማ ድርጅት ከምንም ይሻላል  በየደረጃው ካሉ  የአማራ ብልጽግና አባላት ጋር በመስራት ና አመራሩ ላይ ተፀእኖ በማድረግ ለሕዝባቸው እንዲቆሙ ማድረግ ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ የአማራ ሕዝብ የአማራ ብልፅግና አመራሮችን በማንሳት የአማራን ሕዝብ ጥቅም በንቃት በሚያስከብሩ ተወካዮች የመተካት ዘመቻ መጀመር አለበት ። በተመሳሳይ በሕገወጥ ስራ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ብልፅግና አባላትን የማንሳት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።   በብልፅግና ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ና የኦሮሞን ብልፅግናን የሚገዳደር ወሳኝ ሃይል ለመፍጠር አመቺ ሁኔታ አለ ።

የኢትዮጽያን የመገነጣጠል አደጋ በማስቀረት በአጭር ጊዜ ውጤት ለማምጣት የሚያስችለው የተሻለ መንገድ ይሄ ነው።

ሶስተኛው ዘላቂ ጥቅምን ያገናዘቡ ሶስት ተጨባጭ ተግባራዊ ጉዳዮችን ያካተተ አለማቀፍ ንቅናቄ ማድረግ ነው ።

  • የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፀረ ሕዝብ በሆኑ ወንጀሎች እንዲሳተፉ የሚጠይቅ ትእዛዝ እንዳያከብሩ በኢትዮጽያ ጦር ሰራዊት ና ፖሊስ አመራሮች ላይ አለም አቀፍ ጫና እንዲፈጠር ማስተባበር።
  • የተባበሩት መንግስታት መርማሪ ቡድንን ሃላፊነት በኦሮሚያ ና አዲሳበባ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንዲያካትት በማድረግ አለም አቀፍ ምርመራ ማስጀመር።
  • አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉትን እንደ ኣግዋ ያሉትን ና ሰብአዊ ድጋፎችን ያላካተተ አለም አቀፍ ማእቀብ ማስጣል።

ከአለም አቀፉ ማእቀብ ጎን ለጎን ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት በህጋዊ መንገድ እንዳይልኩና አስቸኳይ ለሆኑ የቤተሰብ ጉዳዮች ካልሆነ በቀር ወደ ሀገርቤት እንዳይሄዱ ንቅናቄው ያስተባብራል። መንግስት ከአለም አቀፉ ማህበረስብ የአለም ባንክ ና የአለም የገንዘብ ድርጅት ጭምር ከሚያገኘው ገንዘብ ትውልደ ኢትዮጽያውያን ወደ ሀገርቤት የሚልኩት ይበልጣል ። ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ በመንግስት ፖሊሲ ላይ ጫና የማስደሪያ መንገድ አላቸው ። በቁርጠኝነት እርምጃ መውሰድ አለባቸው።

ትህነግ በ2018 ስልጣን በሰላም እንዲለቅ ያስገደደው አንዱ ምክንያት የውጭ ሃይሎች ጫና እንደሆነ ማስታወስ ያሻል። ትህነግ ሀገሩን ማረጋጋት ሲሳነው አለም አቀፉ ማህበረስብ ፊት ነሳው። አሁን ላይ አለም አቀፉ ማህበረስብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀውስ አባባሽ መሪ እንደሆኑ እየተረዳ ነው ።  ይህ ንቅናቄ ይህንን አጋጣሚ ይጠቀምበታል።

ለማጠቃለል ንቅናቄያችን ሰላማዊ ና ሁሉን አሳታፊ ነው። አላማውም ሀገሪቱን በመገነጣጠል ላይ  ያለውን ተቀጣጣይ ቀውስ መቀልበስ ነው። ሁሉንም አሸናፊ ለማድረግ የምንጠቀመው ዘዴ የሚያተኩረው መንግስት ከጀመረው የጥፋት መንገድ እንዲመለስ ጫና ማድረግ ላይ ይሆናል ከዚህ አንፃር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየደረጃው ወሳኝ እርምጃዎች እንዲወስዱ እንጠይቃለን ። ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ባይሆኑ ትግሉ  ሕገመንግስታዊ ስርዐቱን ተከትሎ ከስልጣን ወደ የሚያወርዳቸው ደረጃ ይሸጋገራል።

  1. እየተባባሰ የመጣው የፖለቲካ ና ኢኮኖሚ ቀውስ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ና ፓርቲያቸው የኦሮሞ ብልፅግና በ2018 ወደ ስልጣን የመጡት የፖለቲካ ና ኢኮኖሚ ቀውስ የፈጠረውን ብሔራዊ አመጽ ተንተርሶ ነው።  ኢትዮጽያ በ2023 ተመሳሳይ ሁኔታዎችን በድጋሚ ተጋፍጣለች ። ቀውሱ በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊቀሰቅስ ወደሚችል ከፍተኛ ብሔራዊ አመፅ ሊያመራ ይችላል ።  ጃዋር ሞሃመድ በባለ 76 ገፅ መግለጫው ‘’ኦሮሞ ሁሉ በኦሮሞ ብልፅግና አመራር ማፈር አለበት ‘’ ለምን አለ ብለን መጠይቅ አለብን ። ጃዋር ‘’ ሰዎች ኦሮሞ ሀገሪቷን ማስተዳደር ይችል እንደሆነ እየጠየቁ ነው ‘’ ብሎ ለመቆዘም ያበቃው ምንድን ነው? ይህንን ለማለት ያበቃው የሀገሪቱ የፀጥታ፣ ኢኮኖሚ ና ፖለቲካዊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣት ነው። መረጃዎች የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው።

በ2018 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች ነበሩ። በ 2021 ኢትዮጽያ በአንድ አመት 5.1 ሚሊዮን በማፈናቀል የአለምን  ክብረወሰን ጨብጣለች ። በ2023  4.6 ሚሊዮን የተፈናቀሉ ኢትዮጽያውያን አሉ ። በ2018 30,000 የፖለቲካ እስረኞች ነበሩ። ዛሬ ቁጥሩ ከዚህ በጣም ይልቃል። እንደውም የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ኢትዮጽያ የጋዜጠኞች እስር ከሚከፋባቸው ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች አንዷ ሆናለች። ጋዜጠኞች ና የማህበረስብ አንቂዎች በተደጋጋሚ በጠራራ ፀሃይ ታፍነው ፣ አይናቸው ተሸፍኖ ፣ ወደ ኦሮሞ ክልል ተወስደው በግለሰብ እስርቤቶች ይደበደባሉ። አልፎአልፎም ጋዜጠኞች ና ታዋቂ የማህበረሰብ አንቂዎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ። ከዚህም በላይ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ የሚታዘዙ አመታዊ ስብሰባዎችን እንዳያደርጉ ይከለከላሉ።

ስርዐት አልበኛ ኦሮሞ ባለስልጣናት ባለሆቴሎች የስብሰባ አዳራሽ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዳያከራዩ በተደጋጋሚ ያስፈራራሉ። በ ማርች 15, 2013 የኢትዮጽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ‘’ህገወጥ አፈናዎች፣ ማስፈራራት ና ትንኮሳ በ ፓርቲ አባላት ና አመራሮች ’’ እንደሚደርስ ገልጿል። በተጨማሪም ቦርዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ መከልከላቸው አሳስቦኛል ብሏል።

ሁኒታው በኢኮኖሚው መስክ እንዲሁ የከፋ ነው።  በ2018 , የኢትዮጽያ የዋጋ ግሽበት 13.8 በመቶ ነበር በወቅቱ ከሰሃራ በታች ያሉ  ሀገሮች አማካይ የዋጋ ግሽበት 4.1 በመቶ ነበር  ። በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ዘመን በ2021 በኢትዮጽያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ 26.4 በመቶ አሻቅቧል። በጃንዋሪ 2022፣ ኢትዮጽያ የከፋ ዋጋ ግሽበት ካስመዘገቡ 10 የአለም ሀገራት አንዷ ነበረች ።  እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የ 2023 የኢትዮጽያ የዋጋ ግሽበት 28.6 በመቶ ይደርሳል። በአንጻሩ ለአፍሪካ ሀገሮች ትንበያው ከ 3 አስከ 6 በመቶ ብቻ ነው። ድርጀቱ የኢትዮጽያ ከፍተኛ ግሽበት ምክንያቱ መንግስቱ ከአቅሙ በላይ እየተበደረ ና እያጠፋ መሆኑ ነው ብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ መንግስት ከብሔራዊ ባንክ 100 ቢሊዮን ብር ተበድሯል።  በተጨማሪም ጦርነቱ ፣ የመንግስት የምንዛሬ ዋጋ የመቀነስ ፖሊሲ ና የኦሮሞ ብልጽግና የጣለው ሀገር አቋራጭ የሰዎች ፣ የሸቀጦች ና የአገልግሎት እንቅስቃሴ ገደብ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ና የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲያቸው ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከውጭ የገቡ የኢትዮጽያ የጥራጥሬ ና የሌሎች ምግቦች በ 2018/19 ከነበረው 1.16 ቢሊዮን  በ2021/22 ወደ 3.61 ቢሊዮን ዶላር  312 በመቶ አድጓል። በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ለኢትዮጽያ የተደረገው አለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ከ142.5 ሚሊዮን ወደ 1.17 ቢሊዮን 821 በመቶ አሻቅቧል።

በ2018 በኢትዮጽያ አለም አቀፍ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 7.88 ሚሊዮን ዜጎች ነበሩ ። በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ዘመን 20.4 ሚሊዮን ዜጎች አለም አቀፍ የምግብ እርዳታ አስፍልጓቸዋል። በ 2023 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስንዴን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መወሰናቸው የሀገሪቱን የምግብ ቀውስ አባብሶታል የዚህ ውጤቱ ከፍተኛ የሆነ 33.6 በመቶ የምግብ ዋጋ ግሽበት ነው ይህም ከጠቅላላው የዋጋ ግሽበት 17 በመቶ ይበልጣል።

የቅርብ ጊዜው የኢኮኖሚ ዜና (አፕሪል 8 , 2023 )” ከ 2022 ወዲህ 394 የኢትዮጽያ ቡና የውጭ ገበያ አቅራቢዎች ስምምነቶች ተቋርጠዋል ‘’  ዘጋቢው እንዳለው “ አቅራቢዎቹ አለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከሀገር ውስጥ የመሽጫ ዋጋው እጅግ ስለወረደ የጠበቁትን ትርፍ ስለማያገኙ  ስምምነቱን ከማቋረጥ በስተቀር ምንም አማራጭ አልነበራቸውም ‘’ ።  የከፍተኝ ዋጋ ግሽበት አንዱ መዘዝ በውጭ ንግድ ተፎካካሪ መሆን አለመቻል ነው። ሌላ መጥፎ እርስተ ዜና እንዲሁ አንዳስነበበው “ የኢትዮጽያ ስጋ አምራቾች ና የውጭ ገበያ አቅራቢዎች ከ06 አፕሪል 2023 ጀምሮ ስጋን  ለውጭ ገበያ ማቅረብ አቁመዋል’’። ማህበሩ ችግሩ የመጣው ከውጭ ምንዛሬ ምዝበራ ነው ብሏል። ፍቃድ ያገኙ አምራቾች ና አቅራቢዎች ወደ ጎን ተገፍተው ህገወጥ የኦሮሞ የጨረቃ እርድ ቤቶች የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ ተመቻችቶላቸዋል ።

ኢኮኖሚው በሁሉም መስክ ፈተና ውስጥ ገብቷል። እንደ ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን ‘’ በ 2023 የኢትዮጽያ የኢኮኖሚ ነጻነት ነጥብ 48.3 ነው ይህም ከአለም 155 ኛ ያደርጋታል ። ይህ ውጤት ከባለፈው አመት 1.3 ነጥቦች ያነሰ ነው ‘’። በተመሳሳይ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ፊች ሬቲንግ የኢትዮጽያን የፋይናንስ ግዲታዎቿን የመወጣት ደረጃ ያለማቋረጥ ዝቅተኛ ነጥብ ሰጥቶታል ። የኢትዮጽያ የደረጃ ታሪክ በ ኖቨምበር 2018 (B+)፤ ኦክቶበር 2019 (B) ፣ ጁን 2020 (CCC)፣ ፌብርወሪ 2021 (CCC) ፤ ና ዴሴምበር 2022 (CCC _) ነበር።

እንደ ኢንተርናሽናል ትራንስፓረንሲ (የ አለም የመጨረሻው የሙስና ደረጃ መዳቢ)፣ በ 2022 የኢትዮጽያ የሙስና ደረጃ ከባለፈው አመት የከፋ ነበር። በ ሪፖርቱ እንደተመላከተው ሀገሪቱ ከአመት አመት መሻሻል እያሳየች ነበር ። በሌላ አገላለፅ ኦሮሞ ብልፅግና መራሹ መንግስት ሙስናን በተመለከተ ከትህነግም የከፋ ነው። ከዚህም የከፋው በ2022 የነበረው ሙስና ከ 2021 የበለጠ ነበር ። የ 2023 ደረጃ ገና አልወጣም ነገር ግን ሁሉም ምልክቶች የሚያሳዩት ከ2022 የባሰ እንድሚሆን ነው። ሁሉም ነገር ቁልቁል እየተጓዘ ነው ።

2የጠቅላይ ሚኒስትሩ ና ኦሮሞ ብልጽግና ኢትዮጽያን ማስተዳደር አለመቻል

27 ዓመት ከቆየው ትግራይ መራሹ መንግስት ሲነጻጸር ኦሮሞ መራሹ መንግስት ገና በአምስት አመቱ መቶ በመቶ ለመውደቁ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያው ምክንያት በጀዋር መሃመድ የቅርብ ጊዜ  መግለጫም እንደተጠቀሰው አብዛኞቹ የካቢኔ አባላት ና የመንግስት ሃላፊዎች የሚመደቡት በብቃት ማለትም እውቀት ፤ችሎታ፤ልምድ ና ስነ ምግባር አይደለም በአጠቃላይ ሀገሪቱ የምትመራው ዋነኛ የብቃት ማረጋገጫቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍጹም ታማኝነት ና ታዛዥነት በሆነ የፖለቲካ ካድሬዎች ነው።

ሁለተኛው ምክንያት  ከምንም ነገር በላይ የኦሮሞ ዶግማ ለሆነው ኦሮሙማ ፍጹም ታማኝነት የሚጠይቀው ጽንፈኛ ጠባብ የኦሮሞ ብሔርተኝነት ነው። ጀዋር መሃመድ ፤ ሺመልስ አብዲሳ ና ሌሎች ብዙ የኦሮሞ መሪዎች ክርስቲያን ወይም ሙስሊም ከመሆናቸው በፊት ኦሮሞ መሆናቸውን ሲገልጹ ሰምተናል። መጀመሪያ ኦሮሞ ና ኢትዮጽያ ፍላጎታቸውን ካሟላች ብቻ ሁለተኛ ኢትዮጽያ መሆናቸውን በኩራት ሲገልጹ አይተናቸዋል። ከታዋቂ የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች አንዱ በቀለ ገረባ ኦሮምኛ ከማይናገር ከማንም ጋር እንዳይገበያዩ ሲምክር ታዝበናል። እንዲሁም ብሔር ተሻጋሪ ጋብቻዎች ለኦሮሞ ቋንቋ መዳከም መንስኤ እንደሆኑ ሲናገር ተሰምቷል።

የኦሮሞ ማህበረሰብ አንቂዎች ኦሮሞዎችን ከአማራ ሚስቶቻቸው ና ባሎቻቸው ነፃ ለማውጣት ፍቺዎች በብዛት እንዲደረጉ ጥሪ ሲያደርጉ ሰምተናል። አክራሪው የኦሮሞ የፖለቲካ ማህበረስብ በአመራር ላይ ያሉትን ጨምሮ ሰው እንኳን ከመሆናቸው በፊት ኦሮሞ እንደሆኑ ይሰማቸዋል ከሃይማኖት የእምነት አስተምሮ እስከ የቤተሰባዊ ዝምድና አስፈላጊነት ሁሉንም ነገር የሚያዩት በጎሳ መነጽር ነው ፣። የፖለቲካ ቀውስ ና ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ የሃይማኖት መሪዎችን በድንጋይ ወግሮ መግደል ፤ አንድን ምስኪን ሰው እስከ ህይወቱ ዘቅዝቆ መስቀል ና ንፁሃን ህጻናትን ና አዛውንትን በገጀራ መግደል ሁሉ የኦሮሙማ ክስተት ውጤት ናቸው።

3. የኦሮሙማ ወረራ ና የሕግና ደንብ መጣስ

ጎሰኝነት ከስብዐዊነት በሚቀድምበት ማህበራዊ ስረዐት ጭካኔ ወግ ይሆናል በአሁኒቱ ኢትዮጽያ የምናየው ይህንን ነው። ።በኦሮሞ መንግስት ቤት ማፍረስ ና ማፈናቀል ነፍሰጡር ና የሚያጠቡ ሴቶች ከልጆቻቸው ፤ ከአረጋውያን ና ታማሚ ወላጆቻቸው ጋር ከቤታቸው ተባረዋል   የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በከፊል እንዲህ ይነበባል ‘’ የኢትዮጽያ ስብአዊ መብቶች ኮሚሽን የመንግስት ሃይሎች ፤ ፖሊስ ፣ ልዩ ሃይሎች ፤ ና ሚሊሻ ቤቶችን ሲያፈርሱ ና በጉልበት ሰዎችን ሲያባርሩ ታዝቧል በስፍራው ዱላ የያዙ ሲቪል ሰዎችም ነበሩ።

የብልጽግና ማእከላዊ ኮሚቴ ሀገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሪፖርቱን በቅንነት ያየዋል ብለን ጠብቀን ነበር። የሚያሳዝነው የትህነግን የ2017 ድራማ ሲደገም ነው የተገኘው የብልጽግ ና ስራ አስፈጻሚ ያወጣው ባለ 5 ነጥብ መግለጫ  ሃላፊነት መውሰድ ቀርቶ የቀውሱን እውነተኛ መልክ ማሳየት አልቻለም እንደውም ስራ አስፈጻሚው ተፎካካሪዎችን ና መገናኛ ብዙሃንን ወደ መውቀስ ነው የዞረው።

ይሄ ተፎካካሪዎችን ና መገናኛ ብዙሃንን ለመወንጀል እንደ ምክንያት የተጠቀሙበት ነው ከመግለጫው በኋላ ግልፅ እንደሆነው መገናኛ ብዙሃኑ ና ታዋቂ ተቃዋሚ ሰዎች ኢላማ ተደርገዋል ።

ኦሮሙማን በእውር ድንብር መከተል የሀገሪቱ ቀውስ ማእከል ነው ይህ በተለይ አምስት ማሳያዎች አሉት 1)  የኦሮሞ ፅንፈኞች የማያባራ አድንቋሪ ጩሀት 2) የሀገሪቱን ታሪክ መስረቅ ና የኦሮሞ ማድረግ 3) የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለሁለት የመክፈል ሴራ 4) ሰብእዊና የዜግነት መብትን መግፈፍ 5) የሐብትና ኢኮኖሚ መብት ገፈፋ

  1. የኦሮሞ ጽንፈኞች የማያባራ አደንቋሪ ጩሀት

ኦሮሞን የአማራ በሃይል ማስገበር ዋነኛው ተጎጂ አድርጎ የሚያቀብረው የማያባራ የብሶት ፖለቲካ የኦሮሞ ጽንፈኞች የፖለቲካ ትርክት ማጠንጠኛ ነው ። ነገርግን አማራን ጨምሮ ሌሎችን በጉልበት ስለጨፈለቀው ኦሮሞ ምንም አይሉም። በታሪክ እንደሚታወቀው ኦሮሞ በሌሎች ከደረሰበት አስገድዶ መጨፍለቅ ይልቅ በሞጋሳ ስርዐት የጨፈለቃቸው ይበልጣሉ። ይሄ በስፋት በሚጠቀሰው በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በታተመው የኦሮሞ የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን መጽሐፍ ተፅፏል ።በመጽሐፉ በስፋት እንደተገለፅው ኦሮሞ  ብዙ  የኩሽ ና ሴሜቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦችን በጉልበት በማስገበር ወደ ራሱ ጎሳ ቀላቅሏል ። በጉልበት የገቡት ሕዝቦች ስማቸውን ፤ ቋንቋቸውን፤ና ባህላቸውን እንዲተው ይገደዱ ነበር። እንዲሁም የመሃመድ መፅሃፍ ለጎሳዎቹ የሐሰት የኦሮሞ የዘር ግንድ ይፈጠርላቸውና ዘራቸውን ወደኋላ ብዙ ትውልድ እንዲቆጥሩ እንደሚደረጉ ይገልጻል።

ኦሮሞ ጽንፈኞች አዳማ ና ቢሾፍቱን የመሳሰሉ የኦሮሞ ከተሞች ናዝሬት ና ደብረዘይት የሚል አማራ ስም ተሰጣቸው እያሉ ያማራሉ   ነገር ግን  በመቶ የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ትንንሽ ና ትልልቅ ከተሞች ስሞች ኦሮሞ በሚስፋፋበት ወቅት በኦሮሞ ስሞች እንደተቀየሩ አያወሩም ዛሬ  በወሎ የሚገኘው ከምሴ የሚባለው ና አካባቢው ገኝ ይባል ነበር ። ምእራብ ወሎ ወረሂመኑ ፤ ወረኢሉ ና ቦረና ቤተ አማራ ይባሉ ነበር ።

የኢትዮጽያ ህልውና ዋነኛው አደጋ የማይመለሱ ጥያቄዎችን የሚያነሳው የኦሮሞ ጽንፈኝነት ነው  ምክንያቱም ጥያቄያቸው የሀገሪቱ መላው የመንግስት መዋቅር ለማያባራ አደንቋሪ ጩሀታቸው እስካልተንበረከከ ድረስ ስለማያቆም ነው ክፋቱ የኦሮሞ ጽንፈኞች የሚፈጥሩት ችግር በመጮህ የሚቆም አይደለም ። ኢትዮጽያን በሞጋሳ ኦሮሞ የማድረግ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ጥረት ያደርጋሉ።

  1.  የሀገሪቱን ታሪክ መስረቅ ና የኦሮሞ ማድረግ

ኢትዮጽያውያን አንድ በጋራ የሚታወቁበት ነገር በጋራ ታሪካቸው መኩራታቸው ነው አድዋ የኢትዮጽያውያን የክብር አክሊል ና የአንድነታቸው ምልክት ናት  አድዋን የኢትዮጽያውያን ሁሉ ኩራት ለማድረግ ደሙን ና ህይወቱን ያልገበረ ጎሳ የለም ነገር ግን የኦሮሞ ብልፅግና ብሔራዊውን የአድዋ ድል ክብረ በዐል ጎሳዊ  ና የኦሮሞ ብቻ ገድል ማሳያ አድርጎ አቅርቦታል ። በ 2023 የዛሬዎቹ ኦሮሞ ፖለቲከኞች የ 15 ኛው ና 16 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቀደምት አያቶቻቸው በሞጋሳ ጊዜ ያደረጉትን እያደረጉ ነው። ኣድዋን ኦሮማዊ የማድረግ የመጀመሪያው ወሳኝ ተግባር የንጉስ ሚኒሊክን ገድል መፋቅ ነበር ። የአድዋ ድል በዐል ለዘመናት የተከበረው በሚኒሊክ አደባባይ ነበር የኦሮሞ ብልጽግና ክብረ በዐሉን ከንጉሱ ለመነጠል ወደ መስቀል አደባባይ አዙሮታል ።  በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የመስቀል አደባባዩ አከባበር ላይ የታደሙት የተጋበዙ ብቻ ነበሩ  እራሳቸውን ጋብዘው ወደ ሕዝባዊና ብሔራዊ በዐሉ የሚኒሊክ ፎቶ የታተመበት ካኒቴራ ለብሰው የተገኙት በሃይል ተበትነዋል፣ ተደብድበዋል ፤ ታስረዋል። እንዲሁም በዐሉን በሚኒልክ አደባባይ በስላም የማክበር መብታቸውን ተነፍገዋል። የሚኒልክን

ካኒቴራ ና ባነር ይዘው በሚኒልክ አደባባይ የተገኙ ከአንድ ጎሳ የወጡ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም የኢትዮጽያ ጎሳዎች የተውጣጡ ሰዎች አሰቃቂ ድብደባ ና እስራት ገጥሟቸዋል።

ሁለተኛው አድዋን ኦሮሞ የማድረግ ተግባር ደግሞ በሁሉም መንግስታዊ የአድዋ በአል ባነሮች ና በራሪ ወረቀቶች ላይ ኦሮሞዎችን የአድዋ መገለጫ አድርጎ ማቅረብ ነው።

ሁሉም በጠባብ ኦሮሞ ባለስልጣናት የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶች ና አርማዎች ኦሮሞዎችን የአድዋ መገለጫ አድርገው አሳይተዋል አንድ አንድ ሰዎች አላማው የአድዋን ድል ከሰሜን (ትግራይ ና አማራ) ወደ ደቡብ መውሰድ ነው ይላሉ  ይህ እውነት አይደለም ቢሆን ኖሩ ምርጥ ከጉራጌ ሃድያ ወላይታ ሶማሌ የተገኙ ኦሮሞ ያልሆኑ የአድዋ ጀግኖች ይታወሱ ነበር።

  1.   የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለሁለት የመክፈል ሴራ

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ና የኢትዮጽያ እስልምና ማህበረስብ ከአድዋ ሌላ ሀገሪቱን ያስተሳሰሩ ሃይሎች ተደርገው ይታያሉ ሁለቱ ሃይማኖቶች ለዘመናት በሰላም ና በጋራ አብረው ከመኖራቸውም በላይ ተከታዮቻቸውን አንዱ የሌላውን ሃይማኖት እንዳያቃልል ና ተገቢውን ክብር እንዲሰጥ ያስተምራሉ ። ጽንፈኛ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን የሰሜነኞች (አማራ ና ትግራይ) አድርገው ይመለከታሉ በዚህም ሊገነጣጥሏት ይፈልጋሉ ። በ ፌብርወሪ 2023 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ና የኦሮሞ ብልጽግና የቤተክርስትያንን ዶግማ ና ቀኖና በመጣስ የኦሮሞ ሲኖድ ለማቋቋም የሞከሩ ተገንጣይ የኦርቶዶክስ ጻጻሳትን በመደገፍ ብሔራዊ ቀውስ ፈጥረዋል ። የኦሮሞ ብልጽግና ለተገንጣዩ ቡድን ፖለቲካዊ ድጋፍ ከመስጠት ባሻገር ጻጻሳትን  ፣ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪዎችን ና አማኞችን ለማፈን ልዩ ሃይሉን ልኳል ። ይህ የህልውና ቀውስ የተቀለበሰው ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ቀውሱን ላለማባብስ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረጓ ነበር።

  1.  ሰብእዊና የዜግነት መብትን መግፈፍ

ከአማራ ክልል የሚጓዙ ኢትዮጽያውያን በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ተከልክለዋል ይህ የሚደረገው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ና በአዲስ አበባ ከንቲባ ቢሮ መናበብ ነው ከዚህም በላይ የከተማው መስተዳድር ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎችን ቤታቸውን ና ሱቃቸውን በ ዶዘር እያፈረስ ያባርራል  ይህ በተለይ የሚደረገው በከተማው ዳርቻዎች ነው

  1.  የሐብትና ኢኮኖሚ መብት ገፈፋ

የኦሮሞ ብልጽግና ሹመኞች የማያቋርጥ ሙስና ና የኦሮሞ መንግስታዊ  ዘራፊ ቡድኖች የፋብሪካ፣ የምግብ ምርቶችን የጅምላ ና ችርቻሮ ንግድን ከላይ እስከታች ተቆጣጥረውታል። ከከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት የሚጠቀም ብቸኛው ሃይል በኦሮሞ ብልጽግና ጥበቃ የሚደረግለት መንግስታዊ ቡድን ነው ። የመንግስት ሸሪኮቻቸውን በመጠቀም የምግብ ምርት ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ይከለክላሉ በዚህ የተነሳ በሚፈጠረው ትልቅ የዋጋ ንረት ከፍተኛ ትርፍ ያጋብሳሉ። አብዛኞቹ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች የያዟቸው ስራዎች ድንገት ለቀናት ያለ ህግ  እንዲስተጓጎሉ ይደረጋል በአዲስ አበባ በባጃጅ ታክሲዎች የሆነው ይህ ነው በህጋዊ መንገድ በመንግሰት በተሰጠ ፈቃድ የሚሰሩ  10,000 የሚደርሱ የባጃጅ ባለቤቶች  መንግስት የባጃጅ አስፈላጊነት እስኪገባው ያለስራ ና ገቢ ተቀምጠው ነበር  የባጃጅ እገዳ በመጨረሻ የተነሳው የሕዝብ እሮሮ ከተስማና አላማው አብዛኛውን የባጃጅ ስራ የተቆጣጠሩትን  አማሮችን ና የደቡብ ሕዝቦችን መጉዳት መሆኑ ከተጋለጠ በኋላ ነው

በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ሸቀጦች ና አገልግሎቶች ወደ አዲሳ አበባ እንዳይገቡ የተጣለው እገዳ ነው ። ምንም እንኳን ፖሊሲው አላማው አማራውን መጉዳት ቢሆንም ሌሎች ሕዝቦች የጎንዮሽ ጉዳት ሰለባ ሆነዋል ምክንያቱም አዲስ አበባ ብዙ ክልሎችን ስለምታገናኝ ነው ለምሳሌ አንድ ከደቡብ የመጣ ወደ አማራ ክልል ለንግድ የሚሄድ ነጋዴ ወደ ቤቱ በአዲስ አበባ በኩል ለመመለስ እክል ይገጥመዋል  በተመሣሣይ አማራ ነጋዴዎች ምርት ና አግልግሎታቸውን ወደ አዲስ አበባ ለማድረስ ከቀን ወደ ቀን የከፋ ችግር እየገጠማቸው ነው ይህ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ጉዳት ተነግሮ የማያልቅ ነው።

ከላይ እንደተጠቀሰው የምግብ ዋጋ ንረቱ የተከሰተው አንድም ህገወጥ የምርት ና አገልግሎት እገዳ ስለተጣለ ነው  ክፋቱ የፖሊሲው አርቃቂዎች ይህ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣውን መጠነ ሰፊ ጫና አይረዱም።

4. ህሊና ያላቸው የብልጽግና አባላት ሕገመንግስታዊ ሃላፊነት

ሃላፊነት የሚሰማቸው የብልጽግና አባላት በኦሮሞ ብልጽግና ውስጥ ያሉ አክራሪ ሃይሎች ዋነኛ መለያ እየሆነ የመጣውን ህገወጥነት የማስቆም  ህገመንግስታዊ ና የሞራል ግዲታ አለባቸው። በውጭም በውስጥም ያሉ  የተለያዩ ኢትዮጽያውያን የህብረተሰብ ክፍሎች በቅርቡ የአማራ ብልጽግና በወሰደው የተቃውሞ እርምጃ ተበረታትተዋል። የበለጠ ተስፋ ሰጪው ነገር ደግሞ ተቃውሞው የተለኮሰው በተራ የፓርቲው አባላት መሆኑ ነው በተጨማሪም በኦሮሞ ሃይሎች የተደረጉ መሬት የመውረር ጥረቶችን የተቃወሙ እንቅስቃሴዎች በአዋሳኝ ሶማሌ ጋምቤላ ና ሲዳማ ክልሎች አይተናል ።

በሃገር ውስጥ ና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጽያውያን እነዚህን ሁነቶች ዝምብለው እየታዘቡ አይደለም  ተቃውሞውን ለመቀላቀል ና ሰላም ወዳድ ለሆነው ዲሞክራሲን ለተጠማው የኢትዮጽያ ሕዝብ ድጋፍ ለማድረግ ተዘጋጅተው ጨርሰዋል  የኢትዮጽያ ሕዝቦች እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቀልበስ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ና ተጠያቂነት ሰፍኖ ማየት ይፈልጋሉ  ይህ ከታች ተለይተው በተዘረዘሩት መጀመር አለበት

  • የግል ወህኒ ቤቶች ያሏቸውን ና የአዲስ አበባን ህዝብ የሚያሸብሩትን መያዝ ና ለፍርድ ማቅረብ
  • ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጨምሮ ከፈተኛ የ ሙስና ተግባራትን መመርመር

(1) 200 የቻይ ና አውቶብሶች ግዥ; (2) በአዲስ አበባዋ ከንቲባ የግል ሂሳብ የተቀመጠው 40 ሚሊዮን ብር; (3). የወርቅ የውጭ ንግድ በ 59  በመቶ መውረድ; (4)  የቅርብ ጊዚያት ህገወጥ የመሬት ዝውውሮች

  • ሙሉ ህገወጥ የመሬት ማከፋፈል ምርመራ እስኪደረግ ና ለወደፊቱ የቁጥጥር ስርዐት እስኪዘረጋ በአዲስ አበባ ና በዋና ዋና ከተሞች የመሬት ሊዝ ሽያጭን ማስቆም እንደምሳሌ የሚጠቀሰው በቅርቡ የተደረገው የወረዳ 17 ና 23 የማህበረሰብ ማእከላትን መቀማት ነው የፈረሱት ማእከላት ዳግም ተገንብተው ወደ ማህበረሰቡ መመለስ አለባቸው
  • ቤት ማፍረስ ና ማፈናቀልን ማስቆም ገለልተኛ ቡድን አቋቋሙ የማፍረስና ማፈናቀል ሂደቱን መገምገም ና የአላግባብ የተፈናቀሉትን ተጎጂዎች ማቋቋም
  • በፌደራል መንግስቱ ና ክልል መንግስታት መካከል መተማመን እስኪፈጠር የክልል ልዩ ሃይሎችን ና ሚሊሻዎችን ትጥቅ ማስፈታት  ማዘግየት በሂደት ግልጽ ና ተአማኒነት ያለው ትጥቅ የማስፈታት እቅድ የሚነድፍ ና ተፈጻሚነቱ ን የሚከታተል የሁሉም ክልሎች ልዩ ሃይሎች ና ሚሊሺያ መሪዎች የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ መቋቋም አለበት ።
  • የጠቅላይ ሚኒስትሩን ና የቀዳማዊት እመቤት የታይታ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ምንጭ ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ ና ለወደፊቱ ሙሉ በሙሉ ግልጽ መሆናቸውን ና የሃገሪቱን ህግ ማክበራቸውን ማረጋገጥ
  • የጠቅላይ ሚኒስትሩን አምባገነናዊ አገዛዝ በመግራት ውሳኔዎቻቸው የሃገሪቱን ጥቅም ያማከሉ መሆኑን ማረጋገጥ

እነዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተባባሰ የመጣው ቀውስ ወደ ማይቀለበሰበት ደረጃ ሳይደርስ እንዲመለስ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት መውሰድ የሚገባቸው መተማመን የሚያደርጁ እርምጃዎች ናቸው  የጀመረውን የጥፋት መንገድ ለመቀጠል ከፈለገ በሀገር ውስጥ ና ውጭ የሚገኙ ኢትዮጽያውያን  ከስልጣኑ ለማውረድ ህገመንገስታዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ንቅናቄ ከመፈጠር በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም።

5. ሰላማዊ ና ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ

ንቅናቄያችን ሰላማዊ ፤ ሁሉን አቀፍ ና ሁሉን አሸናፊ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው ። የኦሮም ሕዝብ ንቁ ተሳትፎ ያላደረገበት ምንም ሰላም በኢትዮጽያ እንደማይመጣ በሙሉ ልባችን እናምናለን  የኦሮሞ ህዝቦች የኦሮሞ ጽንፈኝነት ተጠቂ ናቸው ። በወህኒ ቤት የሚገኙ ኦሮሞዎች ና አባ ገዳዎችን ጨምሮ በኦሮሞ ብልጽግና ና ሸኔ የተገደሉ ብዛት ያላቸው ኦሮሞዎች ተገቢውን ትኩረት አላገኙም  ጃዋር በማኒፊስቶው በኦሮሞ ብልጽግ ና ዘመን የተገደሉት ኦሮሞዎች በሃይለስላሴ ፣ በደርግ ና በትህነግ በጠቅላላው ከተገደሉት ይበልጣሉ ያለው ትንሽ ግነት ቢኖረውም ከእውነቱ ብዙም የራቀ አይደለም።

በቅርቡ ይፋ በተደርገው ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የኦሮሞ ተማሪዎች ከአማራም ከደቡብ ክልል ተማሪዎችም እጅግ ያሽቆለቆለ ውጤት ማምጣታቸው ለኦሮሞ ህዝቦች የወደፊት እጣ ፈንታ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።  እንዲሁም የኦሮሞ ገበሬዎች ምርታቸውን ከገበያው እጅግ በወረደ ዋጋ እንዲሸጡ ያስገደዳቸው የኦሮሞ ብልጽግና ፖለሲ ዋነኛው ተጎጂ ናቸው። ማንኛችንም ከኦሮሞ ብልጽግና ና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የከሽፈ አመራር ጉዳት የራቅን አይደለንም።

6. ጽንፈኛ ሃይሎችን ጠራርጎ ማስወጣት

ሃገራችን የምትገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ። ህዝቡ መቃወም ያለባቸው ቢሆንም ቀውሱን ከማባባስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል   ሁሉም የፖለቲካ ና ሃይማኖት አቋም ያላቸው ኢትዮጽያውያን ከእርባና አልባ የፉክክር ሃሳብ መራቅና ሁሉንም ጽንፈኛ ሃይሎች ማስወጣት አለባቸው ። የአንድነት ሃይሉ ጽንፈኞች ከኦሮሞ ጽንፈኞች ምን ያህል ትኩረት እንደሚያገኙ ከኦሮሞ ማህበራዊ ሚድያ ማየት ይቻላል። ይህንን የሚያደርጉት የጽንፈኝነቱን እሳት ለማቀጣጠል እንደ ነዳጅ ስለሚያገለግል ነው።

7. የአናሳ ጎሳዎች ሚና

ህገ መንግስቱ ብሄር ብሄረሰቦችን ያከብራል ና ይጠብቃል የሚባለው ልብወለድ ነው። የብሄር መብት የዜጎች  ፍላጎትን በሌሎች ላይ ለመጫን እንደ ሽፋን በሚያገለግልበት ሃገር ፣ ከፈተኛ ቁጥር ያላቸው ጎሳዎች በሕገመንግስቱ ጭራሹኑ አልተጠቀሱም።

በሕገመንግስቱ የተጠቀሱት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢወከሉም በተወካዮች ምክርቤት አልተወከሉም ።የፌዴሬሽን ምክርቤት ህግ የማጽደቅ ወይም የማገድ ምንም መብት የለውም። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊያተኩሩበት የሚገባ አንድ ጉዳይ ሁሉንም ከ ትግራይ እስከ አማሮ ያሉ የተገለሉ ጎሳዎችን በአንድነት ማስነሳት ነው።

8. የሞያ ማህበራት ና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

በሃገሪቱ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ዘመን እያደገና እየተባባሰ ከመጣው ቀውስ የሚተርፍ አንድም የኢትዮጽያ ህብረተሰብ ክፍል የለም ። መምህራን ፣ ሀኪሞች ፤ ነጋዴዎች፤ገበሬዎች፤የመንግስት ሰራተኞች ፤የሰራዊት አባላት፤ ፖሊስ ፤የጎዳና ንግድ ተዳዳሪዎ ች፣ የታክሲ ሾፌሮች ና ሌሎች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ የዋጋ ንረት እየተሰቃዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስት ሰራተኞችን (መምህራን ና ሀኪሞችን) ሰብስበው የደሞዝ ጭማሪ መጠየቅ እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል። ዘወር ብለው ለማይረቡ ፕሮጀክቶቻቸው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለአዲሱ ታላቅ ቤተመንግስት ግንባታ ጭምር ያትማሉ ። ይህ የዋጋ ንረቱን ያባብሳል እንዲሁም የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አንስተኛ ገቢ ያላቸውን የመግዛት አቅም ያዳክማል ። እርባና ቢስ የሆኑ ፕሮጀክቶቹን ለማስቀጠል ገንዘብ በማተም ለመቀጠል እንዳቀደ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።

ኢኮኖሚስቶች እንደሚሉት ‘’ ገንዘብ ማተም ከድሆች እንደመስረቅ ነው ‘’ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የስንዴ የውጭ ንግድ ተረት እውነት ለማድረግ ስንዴቸውን በርካሽ እንዲሸጡ በተገደዱት የኦሮሞ ገበሬዎች ዘንድ ይወሳል። የንቅናቄው አንዱ ትኩረት የሞያ ማህበራትን ና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማንቀሳቀስ ይሆናል።

9. ወታደራዊ መሪዎች ና መኮነኖች

ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል የበለጠ ጉዳት የደረሰበት ወታደሩ ነው ። በጠንካራ ምሽግ በተከበበ ተራራ የተደበቁ የትህነግ መሪዎችን ለመያዝ በትግራይ በተደረገ ዘመቻ አንድ የልዩ ሃይል ቡድን ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል። ከ10,000 በላይ የመከላከያ አባላት ከነታንክ ና ከባድ መሣሪያዎቻቸው ተይዘዋል  ሰራዊቱ በአካል ና በህይወቱ ከባድ ዋጋ ከፍሏል ቤተሰቡ በተዳከመው ኢኮኖሚና በከፍተኛ ዋጋ ንረት እየተሰቃየ ነው በጦርነቱ የቆሰሉት በጎዳናዎች እየለመኑ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ለጉራ ና ቅንጦት በሚሰራቸው እርባናቢስ ፕሮጀክቶቹ ተጠምዶ ብዙ ዘመን ያገለገሉ የሰራዊቱን አባላትን ቤተሰቦቻቸውን መንከባከብ አልቻለም።

የሰራዊቱ አዛዦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብ ላይ በሚያውጁት ጦርነት መሳተፍ የለባቸውም ሀገሪቱን ለመጠበቅ መሃላ ገብተዋል  ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆነ የኦሮሞ ብልጽግና የሃገሪቱ ሉአላዊነት ሆነ የግዛት አንድነት አደጋ በሚሆኑበት ጊዜ ሊያስቋሟቸው ይገባል።

ማንኛውም ዘመቻ ዘላቂ ሰላም ሊይስገኝ ከሆነ ሰራዊቱን በማንቃት ና ማስገንዘብ ላይ ያተኮረ የህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ማተኮር አለበት.

10. ቀውሱን መቀልበስ የሚያስችሉ ሰባት ብሔራዊ ና ዓለም አቀፍ ጫና ማሳደሪያ ነጥቦች

ባለፉት አምስት አመታት ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለት ባህርያት ተረድተናል ። በመጀመሪያ ምንም ወጥ አቋም የለውም።  ከሃዲ የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ኤጺስ ቆጾሳትን ሲደግፍ ቆይቶ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥመው ገሸሽ አደረጋቸው። በኢትዮጽያዊ ና ኦሮሞ ብሄርተኝነት መካከል በዓይን ጥቅሻ ፍጥነት ሲዋልል አይተነዋል። ሁለተኛው በትህነግ ና ሸኔ ጦርነት ተዳክሟል ራቁቱን የቀረውን የተረትና ምሳሌ ንጉስ ይመስላል። ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ና ደጋፊዎቿን አይተውት በማያቁት የዐመፅ መሳሪያ እንደሚገጥማቸው ሲያስፈራራ ቆይቶ ቢያደርገው ራሱን እንደሚያጋልጠው ሲሞግቱት አፈገፈገ ። ለአለም አቀፍ ጫና ና ማእቀብ ከማጎበድድ አንገቴን እሰጣለሁ ሲል ቆይቶ ለእያንዳንዱ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ቅጽበታዊ ፍላጎት ሲያጎበድድ ይገኛል።

ለውጥ ሊመጣ የሚችለው ሃላፊነት የሚሰማቸው የብልጽግና አባላትና የኢትዮጽያ ህዝቦች በጋራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ና በኦሮሞ ብልጽግና ላይ ጫና ማሳደር ሲችሉ ብቻ እንደሆነ እናምናለን። ከዚህ አንፃር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ስሌቱን ና እየተባባሰ ያለውን ቀውስ ለመቀልበስ የሚያስገድደው ሰባት ጫና ማሳደሪይ ነጥቦች እንዳሉ እናምናለን ። ይህ በድንብ የተቀናጀ ብሔራዊ ና አለም አቀፍ ንቅናቄ ይጠይቃል። አለም አቀፉ ንቅናቄ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን አስፈላጊ የመጨረሻ አማራጭ ነው።

  1. አራት የተቀናጁ የሀገር ውስጥ ንቅናቄዎች

የመጀመሪያው ና ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣው ድምፅ የማያሰማውን ብዙሃን ማንቀሳቀስ ነው። የዚህን ድምፅ አልባ ሃይል በኦርቶዶክስ ልምድ አይተነዋል  ድምፅ የማያሰማውን አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ለማንቀሳቀስ ቁልፉ ተግባር ጽንፈኝነትን በማስወገድ ና ሰላማዊ መንገድን በመከተል  ሁሉም አሽናፊ የሚሆንበትን ዘዴ መቀየስ ነው።

ሁለተኛው የሀገር ውስጥ ንቅናቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተጠያቂ ማድረግ ነው ። ይሄ የተከፉ የብልጽግና የምክርቤት አባላትን የማሳተፍ ስራ ይጠይቃል ። ሕገመንግስቱ በብዙ ቦታዎች ላይ የሕዝብ ተወካዮች የሕዝቦችን ሕገመንግስታዊ መብት የማክበር ና የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ይገልፃል። በአንቀጽ 12’’ የመንግስት ተግባር ና ሃላፊነት’’ ‘’ ማንኛውም የመንግስት ሃላፊ ወይም የሕዝብ ተወካይ የተሰጠውን ሃላፊነት በሚገባ ካልተወጣ ተጠያቂ ይሆናል ‘’ ይላል ። ይህ ህገመንግስታዊ ስርዐቱን መጠበቅ ና የሚጥሱትን ተጠያቂ ማድረግን ይጨምራል ።

አንቀጽ 35 ለሕዝብ ተወካዮች ‘’ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ና ሚንስትሮችን የመጥራት ና የመጠየቅ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቱን የመመርመር ‘’ ስልጣን ይሰጣል።  በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ‘’ አንድ ሶስተኛው የምክር ቤት አባል ሲጠይቅ በስራ አስፈፃሚው ስልጣን ስር ያለ ማንኛውንም ጉዳይ መመርመር እንደሚችል ‘’ ያብራራል ። ይህ ሰውየውን ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ና  ከብልፅግ ና ሊቀመንበርነት ማንሳትን ይጨምራል።

ሶስተኛው የሃገር ውስጥ ንቅናቄ የገቡትን መሃላ ያፈረሱ የምክርቤት አባላትን ውክልና ማንሳት ላይ ማተኮር አለበት። በሕገመንግስቱ መሰረት ብሔራዊ ንቅናቄው ውክልናን የማስነሳት ና ማሃላቸውን በሚያከብሩ ና ሕገመንግስታዊ ግዴታቸውን በሚወጡ ሰዎች የመተካት እንቅስቃሴ ያደርጋል። ይሄ በተመሳሳይ ሃላፊነት ና ተጠያቂነት ለሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላትም በእኩል ሃይል ይተገበራል።

አራተኛው የሃገር ውስጥ ንቅናቄ ሁሉንም አሸናፊ ለሚያደርግ ሰላማዊ ትግል የቆረጡ የክልል ብልፅግና ና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያሳተፈ የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንቅስቃሴ መደገፍ ነው።  የዚህ ንቅናቄ አላማ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ ፣ጥያቄዎቻቸውን ፤ ስጋታቸው ና  ፍርሃታቸውን ለአለም አቀፍ ማህበረስብ ማድረስን ጨምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ለታችኛው ህብረተሰብ ክፍል ለማድረስ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው።

  1. አለም አቀፍ ምርመራ ና ወደ ሀገር ቤት የሚላክ የውጭ ምንዛሬ ማስቀረትን ጨምሮ ማእቀብ መጣል 

የመጀመሪያው ወሳኝ ንቅናቄ በሰብአዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ላይ በትግራይ ፤ አፋር ና አማራ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያ ና አዲስ አበባ ክልሎች ጭምር አለም አቀፍ ምርመራ ማድረግ ነው ። ኢትዮጽያውያን ለአለም አቀፍ ምርመራ የሀገር ሉአላዊነት ይጥሳል በሚል ያላችውን ስጋት እንረዳለን ። አለም አቀፍ ምርመራ ወደን የምናደርገው ነገር አይደለም ይልቁንም አስፈላጊነቱን ተርድተን የምናደርገው ነው።

ክፋቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ና የኦሮሞ ብልፅግ ና ሀገሪቱን ወደ ጨርሶ መፈራረስ እየገፏት ነው ኢትዮጽያ ከሌለች ሉአላዊነት አይኖርም ። የኛ  ተግባር  ከምንም በላይ ኢትዮጽያን እንዲህ ካለ ሃላፊነት ከጎደለው መንግስት መታደግ ነው። ኢትዮጽያውያን አለም አቀፍ ምርመራን መደገፍ የሚያስገድዱን ምክንያቶች አሉ። በማርች 2023 የአሜሪካ መንግስት አንዳረጋገጠው ‘’ ህጉን ና መረጃዎችን በጥንቃቄ በመመርምር ‘’ ‘’የኢትዮጽያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ፤ የኤርትራ መከላከያ አባላት ፣የትህነግ ሃይሎች ና የአማራ ሃይሎች በሰሜን ኢትዮጽያው ግጭት የጦር ወንጀል ፈፅመዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያቋቋመውን አለም አቀፍ ምርመራ እንዲቀበል አሜሪካኖች አስገድደውታል፣ በዚህም ኢትዮጽያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መርማሪ የማገድ ጥያቄዎችን አቋርጣለች ነገር ግን የስራ ዘመኑ እንዳይራዘም መንግስት ጠይቋል። ይሄ ኦሮሞ ብልፅግና ን ከምርመራ ና ተጠያቂነት ለማዳን ነው። ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ የአለም አቀፍ ምርመራ ቡድኑን የስራ ዘመን ለማራዘም ና ምርመራው በሰብአዊነት ላይ የተፈፅመ ወንጀልን ፤ በኦሮሞ ክልል የተፈጸመውን የዘር ማጽዳት ና በአዲስ አበባ የሰብአዊ መብት ጥሰትን እንዲያካትት ለማድረግ ጥረት ማድረግ አለባቸው።  ብዛት ያላቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሰለ ትግራይ የቅድሚያ ሪፖርት አውጥተዋል።  ተጨማሪ አለም አቀፍ ምርመራዎችን ማስቆም የኦሮሞ ብልፅግና ና የኦሮሞ ሸኔ ተጎጂዎችን ፍትህ እንዳያገኙ መከልከል ነው።

ሁለተኛው የዓለም አቀፍ ንቅናቄያችን አካል አለም አቀፍ ማእቀብ ነው። ይህ ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል ። የመጀመሪያው የኢትዮጽያ ሰራዊት ና ፖሊስ ማንኛውንም ወንጀል እንዳይፈጽሙ አለም አቀፍ ጫና ማሳደር ነው። በአብዛኛው በአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች የዘር ማጥፋት ክስ የሚመስረትባቸው  ወታደራዊ ባልስልጣናት እንደሆኑ ለወታደርና ፖሊስ ባለስልጣናት ማስገንዘብ ያስፈልጋል።

ብቅርቡ በ ጓቲማላ፤ ማይናማር ፤ ና ሰርብያ የተደረጉት ማስጠንቀቂያ ቀይ መብራት ናቸው።

ሌላው አለም አቀፍ ማእቀብ የኢኮኖሚ ማእቀብ ነው ለወዲያው በድሃው የሕብረተሰብ ክፍል ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እንደሚያስከትል እናውቃለን ነገር ግን የተመረጠ ማእቀብ በሦስት ምክንያቶች ተገቢ ነው

  • የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ መፍቀድ የማእቀብን ሃይል ያሳያል
  • የኦሮሞ ብልፅግና በነፃ የሕዝቦች፤ ሸቀጥ ና አግልግሎት እንቅስቃሴ ላይ የጣለው ገደብ ና ተወዳዳሪ የሌለው የኦሮሞ ብልጽግና መሪዎች ና መንግስታዊ  ቡድኖች  ዝርፊያ በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከማንኛውም የኢኮኖሚ ማእቀብ የከፋ ነው
  • ማንኛውም አለም አቀፍ ማእቀብ የሚፈጥረውን ጉዳት በተመረጡ ና ዘዴ የታከለበት ማእቀብ መቋቋም ይቻላል ። የተመረጡ ማእቀቦች ሰብአዊ ርዳታ ና ድሃዎችን የሚረዱ እንደ አጎዋ ያሉ ፕሮግራሞችን አይጨምሩም ። የማእቀቡ አላማ የኦሮሞ ብልፅግናን  አውሬ የኦሮሞ አገዛዝን ለማስፈን የሚጠቀምበትን የውጭ ምንዛሬ ማስጣት ነው ።

ሶስተኛው አለም አቀፍ ንቅናቄ የትውልደ ኢትዮጽያውያን የገንዘብ አስተዋጽኦ ነው። የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ የአንበሳ ድርሻ የሚይዘው ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ ወደ ሀገርቤት የሚልኩት ገንዘብ ነው። ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ በባንክ ገንዘብ መላክ ማቆም አለባቸው። ወደ ሀገርቤት የሚላከውን ገንዘብ ቤተሰብን ለመርዳት ብቻ መገደብ ና መደበኛ ባልሆነ መንገድ መላክ። አስቸኳይ የቤተሰብ ጉዳይ ካልገጠመ በስተቀር ወደ ኢትዮጽያ አለመጓዝ ።

የኢትዮጽያና አሜሪካን ግንኙነት ለማሻሻል ታስቦ የተደረገው የአሜሪካ የውጭጉዳይ መስሪያቤት ሃላፊ አንቶኒ ብሊንክን የኢትዮጽያ ጉዞ ያልተሳካው የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል ና ፍትህን ለማስፈን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት በማጣቱ የተነሳ ነው። ፍትህን  ና ተጠያቂነትን ለማስፈን ብሔራዊ ና አለም አቀፍ ጫና ማሳደሪያው ጊዜ አሁን ነው።

 

https://zehabesha.com/averting-civil-war-in-ethiopia-an-emergency-manifesto/

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop