March 20, 2023
10 mins read

አማርኛን የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ የማድረግ ግዴታነትና ተገቢነት (በራህማቱ ኪየታ)

በራህማቱ ኪየታ
ትርጉም  በአብርሃም ቀጄላ
።።//።።።።።///።።

gettyimages 1199576225 612x612 1

አፍሪካዊ ቋንቋና ፊደል እያለን በባዕድ የቅኝ ገዥዎች ቋንቋ መገልገል የለብንም።

ፕሬዚዳንት ሴኩቱሬ
የጊኒ ፕሬዚዳንት ሴኩቱሬብ 1955 a.ም እ.ኤ.አ ( በ1963 አፍሪካ አንድነት ድርጅት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ላይ የምስረታ ጉባዔ አድርጎ ሲቋቋም የጉባዔው መሪና ሰብሳቢ የሆኑት ፕሬዚዳንት ሴኩቱሬ በቅኝ ገዥዎቻችንና በባሪያ አሳዳሪዎች በተጫነብን ቋንቋና ፊደል የአፍሪካን አንድነት ቻርተር መፃፍና መመዝገብ ተገቢ አይሆንም ይልቅ የኛ አፍሪካዊ የሆነ የራሳችን ኢትዮጵያ በቀል አፍሪካዊ ቋንቋችን አማርኛ ቋንቋና ፊደል ስላለን በዚሁ በራሳችን አፍሪካዊ ቋንቋ ለአሁንም ለወደፊት ለዘለቄታም የራሳችንን የኛነቱን አክብረን መጠቀምን መገልገል አለብን በማለት ለጉባዔው በግሳፄ በማቅረባቸው ይሄው ፍሬ ሀሳብ በጉባዔው በሙሉ ድምጽ ፀድቆ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር በአፍሪካዊ ቋንቋና ፊደል በአማርኛ ቋንቋ ተከትቧል።
የአማርኛ ቋንቋ ግስግሴ አሁናዊ ከፍታና ምጥቀት ደረጃ

381 681x1024 1

1/ አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋ ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ “እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!” የሚል ጽሁፍ ማየት የተለመደ ሲሆን አሁን ደግሞ በአሌክሳንዴሪያ ሁለትኛ ደረጃ ት/ቤቶችና እንዲሁም በሜሪይ ላንድ ሞንቶጎሞረ አማርኛ እንደ ትምህርት ይሰጣል።

2/ ለአፍሪካ ህብረትም ለስራ ቋንቋነት ቀርቧል። ቀድሞም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.ኤ.አ በ1963 ሲመሰረት ቻርተሩ አፍሪካ በቀል በሆነው አፍሪካዊ ቋንቋ አፍሪካን በብቻው በመወከል በአማርኛ ተጽፎ ፀድቋል።
.
3/ ለአፍሪካ የሳይንስ ቋንቋ መተርጎሚያነት ተመርጧል።
4/ በእስራኤልም ለስራ ቋንቋነት ታጭቷል።
5/ በጃማይካም ለመንግስት ዘርፍ ቀርቧል
6/ በቲሪንዳድና ቶቤጎ ከ75 በላይ እድባራት እየተገለገሉበት ነው
7/ Dstv’ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።
8/ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች 90% ይማሩታል።
9/ በሆሊውድ የፊልም እንዱስትሪ ውስጥ ገብቶ በካሚንግ አሜሪካ 2 ፊልም ላይ ፊደላችን፣ አልባሳታችንና መስቀላችን ሳይቀር በፊልሙ ውስጥ ተከስቷል፣
10/ በሙዚቃውም በኩል ቢሆን እድሜ ለአቤል ተስፋዬ (aka the weeknd) አማርኛችንን ሆሊውድ መንደር እንዲደመጥ አድርጎታል!
11/ ራመቱ ኬይታ የተባለች ኒጄር /አፍሪካዊ ኮከብ አለም አቀፍ ፊልም መግለጫ ሆኖ አለም ላይ ይታይል። I
 12/ በአላም ላይ ከ15 ታላላቅ  ዩኒቨርስቲዎች በላይ አንደ አንድ ትምህርት ይሰጣል። ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት በላይ ሆኖታል።
.
13/ በአሜሪካ የሚገኙ ሳይንቲስቶች አብዛኛዎቹ 90% ይማሩታል።
14/  በ2007 ዓ.ም. የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል።
15/ በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል።
16/ በኢትዮጵያ በስነ-ጽሑፍ ቅርስነት በዮኔስኮ ከተመዘገቡት መካከል፦ – ታሪከ ነገስት ዘዳግማዊ ምኒልክ፣ -ዐፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዝ ንግስት ቪክቶሪያ የፃፉት ደብዳቤ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ለመስኮብ ቄሳር ዳግማዊ ኒኮላስ የፃፉት ደብዳቤና ሌሎችም በአማርኛ የተጻፋ ናቸው።
17/  አማርኛ ቋንቋ በአፍሪካ ምድር በስነ ጽሑፍ ሀብት የበለጸገ ብቸኛው  ዘመን ዘለቅ ነባር ቋንቋ ሲሆን አማርኛ ቋንቋ በአንድ ድምፅ የኮምፒውተር መተግበሪያ ተሰርቶለት እንግሊዝኛ ቋንቋ በቀላሉ መጻፍም ተችሏል።
 በጉንደት፣በጉራዕ፣በአድዋ እና በማይጨው በተደረጉ ጦርነቶች ወታደሩን ከየብሄሩ ያሰባሰበ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ነው። መይሳው ካሳ (ዐፄ ቴዎድሮስ) ለእንግሊዝ ማስጠንቀቂያ የሰጠው በአማርኛ ነው። ዐፄ ዮሐንስ አዋጅ ያስነገረው በአማርኛ ነው። ዐፄ ምኒልክ አለምን ያስደነቀ አመራር የሰጠው በአማርኛ ነው። ዐፄ ኃይለሥላሴ ጀኔቫ ላይ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንግግር ያደረጉት በአማርኛ ነው። መንግስቱ ኃይለማሪያም 17 አመታት ሀገሪቱን አንቀጥቅጦ የገዛው በአማርኛ ነው። መለስ ዜናዊ እድሜ ልኩንም አገር የመራው በአማርኛ ነው አማርኛ በኤርትራ በጅቡቲ በሱዳን በደቡብ ሱዳን በግብጽ በሱማሊያ በደቡብ አፍሪካ ይነገራል። በጥቅሉ ከ150 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪ አለው።
18/  እንደ ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1888 ዓ.ም ለቅኝ ግዛት ወረራ የመጣውን የኢጣሊያ የሰለጠነ የነጭ አውሮፓን ጦር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በማሸነፍ ለአፍሪካና ለሙላው ጥቁር ህዝብ የነፃነትን ብርሀን ያሳየች በመሆኗና በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ እብሪተኛውን ነጭ የቅኝ ገዥ በአፍሪካዊ ጥቁር ህዝብ ተሸንፎ አድዋ ላይ የተዋረደበትን አብዛኛው 99% ፓንአፍሪካኒስቶችና የጥቁር ህዝብ ጀግንነት የቅኝ ገዥን ነጭን አሸንፎ መላሽነት ብሎም የነፃነት ተምሳሌትና ሰንደቅ አርአያነት ምልክት አድርጎ የኢትዮጵያ ባንዲራን የኣፍሪቃና የጥቁር ዘር ሁሉ ነፃነት፣ ኩራትና ክብር ነው በማለት መልኩን ከተከተሉት አብላጫ 95% ግድም የአፍሪካ አገሮች 10 አገራት አረንጓዴ ብጫ ቀይ ፍጹም አንድ አይነት ከኢትዮፕያ ሰንደቅአላማ ጋር ሲከተሉ ሌሎች 37 አገራት አንድ ወይም ሁለት መልክ የተደባለቀ ጠቅላላ ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገሮች 47ቱ የሚከተሉት አረንጓዴ ብጫ ቀይ ሰንደቅ አላማን ነው ።
19/ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በከባድ ጥረትና  ልፋት እንዲፈጠር ከማድረጓም በላይ  ለደቡብ አፍሪካው የነፃነት ታጋይ ኒልሰን ማንዴላ እና ለዚምባቡዌ ነፃነት ታጋይ ሮበርት ሙጋቤ  እና ለብዙ ሌሎችም ነፃነት ታጋዮች መጠለያ ስልጠናና እገዛ ከፍተኛ እስትዋፅኦ በማድረግ ከአድዋ 1888 ቅኝ ገዥን ማሸንፍ እርማነት ጊዜ  ጀምራ እስከ  የመጨረሻዋ  የአፍሪካ ቅኝ ተገዥ አገር ደቡብ አፍሪካ  ነፃ እስከወጣችበት ጊዜ ለአንድ ምእተ አመት
(100 አመት)  ለአፍሪካዊያን ነፃነት ታግላለች።
እነዚህ ከላይ በተጠቀሱትና ሌሎችም ባልተጠቀሱ  በርካታ ሀቆችና እውነታዎች ምክንያቶች አማርኛ ከነፊደሉ አፍሪካዊና የሁሉም እፍሪካዊ የተፈትሮ ሀብትና ቅርስ በመሆኑ ለአፍሪካ ህብረት የስራ. ቋንቋ አድርጎ መንከባከብና መጠበቅ የሁሉም እፍሪካዊ ግዴታ ነው።
——–\

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop