December 18, 2022
6 mins read

ሰንደቅ አላማ “ጨርቅ” መሆኑን የማያውቅ የዓለም ሕዝብ ባንዲራውን ለብሶ እያበደ ነው!

Flag

በላይነህ አባተ ([email protected])

 

በእየ አራት ዓመቱ በሚደረገው የዓለም የእግር ኳስ ውድድር ከሁሉም የሚደንቀው ሕዝብ ለአገሩ ሰንደቅ አላማ ያለው ከልብ የመነጨና የሚያስለቅስ ፍቅር ነው፡፡ የአሸነፈ ሕዝብ ከልጅ እስከ አዋቂ በደስታ የተሸነፈውም በሐዘን ሰንደቅ አላማውን በእንባ ሲያጥብ ማየት የተለመደ ነው፡፡ በእውነቱ ይህ የሰንደቅ አላማ ፍቅር ተአካላዊና መንፈሳዊ ሰውነት ጋር ያለው  ቁርኝት ልዩ ሳይንሳዊ ጥናት የሚያስፈልገው ነው፡፡

በልጅነታችን ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ መዝሙር ሲዘመርና ሰንደቅ አላማዋ ኩል ወደ መሰለው የኢትዮጵያ ሰማይ ቀስተ ደመና መስላ ስትወጣ ብዙዎቻችን እንባችን በጉንጫችን  ያለማቋረጥ ይወርድ ነበር፡፡ ሰንደቅ አላማዋን ለመስቀል አስተማሪዎቻችን ሲመርጡን እግዜር የመረጠን ያህል በደስታ መንፈስ እንሞላ ነበር፡፡ አባቶቻችን ሰንደቅ አላማዋን ሲያዩ  በክብር ቀጥ ብለው ቆመው እንደ ታቦት ተሳልመዋት ያልፉ ነበር፡፡ የኔ አባት እንዲያውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንደ ዳዊት ተኪሱ አትጠፋም ነበር፡፡ ድንገት ረስቷት ተወጣ ወደ ቤት ተመልሶ መጥቶ ይወስዳት ነበር፡፡ እንኳን ሰንደቅ አላማዋን ቀስተ ደመና ሲያዩ ከብቶቻቸው ሳይቀር ቆመው እንዲያከብሯት የሚያደርጉ ዜጎችም እመለከት ነበር፡፡

እንደ አለመታድል በ1991 ዓ.ም. ባንዶች ሰንደቅ አላማዋን ክፉኛ የሚጠሉ ኃይሎችን ትክሻ ተፈናጠው ወደ ወንበር ሲወጡ ይህችን ስንት ትውልድ ደምና እምባ ሲገብራት የኖረችውን ሰንደቅ አላማ እያወረዱ መቀዳድ ጀመሩ፡፡ ሰንደቅ አላማዋን አናስነካም ወይም አታወርዱም በሚል ብዙዎች እንደ ቅድመ አያቶቻቸው  ለብሰዋት ተሰው፡፡ በሰንደቅ አላማዋ ምክንያት ሕዝቡ ሲቆጣ የባንዳዎች አምበል ስለሰንደቅ አላማ ሕዝብን ሲያስተምር “ለመሆኑ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን ያውቃል?” ሲል ተሳለቀ፡፡ መቼም በዚህ ዘመን ኢትዮጵጵያ ወንበር እውቀትን እንጅ እውቀት ወንበርን ስለማይወልድ ብዙው ባንዳና ወለወልዳም የዚህን ከንቱ “ጨርቅ ድስኩር” እንደ እውቀት ቆጥሮ እያደነቀ ገለፈጠ፡፡ የሕዝብ ልብ ግን እስካሁን እንደ አዘነና እንዳረረ አለ፡፡

የብራዚል ሰዎች የእግር ኳስ ታላሸነፉና ሰንደቅ አላማቸው ከፍ ከፍ ታላለች ራሳቸውን እስከማጥፋት እንደሚደርሱ የታወቀ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የዓለም የእግር ኳስ ውድድርም የሚፍለቀለቅ የሰንደንቅ አላማን ፍቅር እንደ ጉድ እየታየ ነው፡፡ የአርጀንቲናና የፓሪስ ሕዝብ ፊቱን፣ ክንዱን፣ እግሩን፣ ምግቡንና ምድሩን ሁሉ ሰንደቅ አላማ እየነቀሰው ነው፡፡ የዓለም ሕዝብ ሰንደቅ አላማውን ለብሶ የሚያብደው እንደ ኢትዮጵያውያን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን የሚያስተምር “መሪ” ነኝ ባይ ገና “ስላልታደለ” ወይስ የሰንደቅ አላማ ትምህርት የማይገባቸው ደነዝ ስለሆነ ነው?

ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን የሚያስተምር ሌላ “መሪ”  ነኝ ባይ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ አልነበረም፤ መተንበይ ታስፈለገም ወደፊትም ሌላ አገር አይኖርም፡፡ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ምናልባትም እስክታልፍ ድረስ ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን በሚያምን ከንቱና ከንቱው ይኸንን እያስተማረ ባሳደጋቸው እርጉም የእንጀራ ልጆቹ የተገዛች አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናትና ይህ እርግማን እንደ ጉም በኖ እንዲጠፋ አስራ ሁለት ጊዜ “እግዚኦ መሐርነ” በሉ! ያላችሁን እግዚያብሔር ይባርካችሁ ያላላችሁትንም  ምህረት ያውርድላችሁ፡፡

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ. .

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop