ኦነጋዊ ጴንጤነት – መስፍን አረጋ     

“The Europeans give us bibles only so that, when we close our eyes to pray, they can take our land.”

“አውሮጳውያን መዱስ የሚሰጡን፣ ለመጸለይ ዓይናችንን ስንጨፍን መሬታችንን ለመንጠቅ ነው፡፡”

ጆሞ ኬንያታ (Jomo Kenyata)

ታላቁ አፍሪቃዊ አርበኛ ጆሞ ኬንያታ አብክረው ሊያስገነዝቡን እንደሞከሩት፣ ሚሲዮኖች የክርስትና ሐዋርያወች ሳይሆኑ፣ የቅኝ ገዥወች ፊታውራሪወች ነበሩ፡፡  የአውሮጳ ጅቦች አፍሪቃ የገቡት ሚሲዮን ውሾቻቸው በቀደዱላቸው በር ነበር፡፡  ያገራችን ጴንጤወችስ?

ያገራችን ጴንጤወች በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚጫወቱት ሚና፣ ሚሲዮኖች ባፍሪቃዊነት ላይ ከተጫወቱ ሚና ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ የሚሲዮን ሚና በሐይማኖት ሽፋን አፍሪቃዊነት ማጥፋት እንደሆነ ሁሉ፣ የጴንጤም ሚና በሐይማኖት ሽፋን ጦቢያዊነትን ማጥፋት ነው፡፡  ሚሲዮንነት ያፍሪቃ ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ እንደነበረ ሁሉ፣ ጴንጤነትም የጦቢያ ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ (Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus) በሚል ስያሜ ጴንጤነትን በጦቢያ ላይ በ1950ወቹ የዘሩት ጉዲና ቱምሳን የመሳሰሉ ቀንደኛ ኦነጋውያን ነበሩ፡፡ ለጴንጤነት ምሥረታ ከፍተኛውን እገዛ ያደረጉት ደግሞ የሉተራን (Lutheran) እና ፕሬስቢቴርያን (Presbyterian) ሚሲዮኖች ነበሩ፡፡  ነጮቹ ሚሲዮኖች ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት፣ የቅኝ ገዥወች ዋና እንቅፋት በመሆኗ ሲሆን፣ ኦነጋውያን ጴንጤወች ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት ደግሞ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አጼጌ (empire) ለመገንባት ነው፡፡  ስለዚህም ነጮች ሚሲዮኖችና ኦነጋዊ ጴንጤወች ግባቸው (goal) እየቅል ቢሆንም፣ ትልማቸው (strategy) ግን አምሳል ነው፡፡   ሁለቱም ግቦቻቸውን ሊመቱ የሚችሉት ጦቢያን በማፈራረስ ብቻና ብቻ ነው፡፡

ጦቢያን ማፈራረስ የሚቻለው ደግሞ ጦቢያ የተገመደችባቸውን ገመዶች በመጣጠስ ነው፡፡  ከነዚህ ጦቢያን ካስተሳሰሩ ገመዶች ውስጥ ደግሞ አንዷና ዋናዋ የጦቢያ ርቱምነት (ርቱዕ ዕምነት፣ orthodox) ተዋሕዶ ናት፡፡  የሐይማኖትን ገመድ መበጣጠስ የሚቻለው ደግሞ በሐይማኖት ነው፣ እሾህን በሾህ እንዲሉ፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ጴንጤነትን የመሠረቱት ለክርስትና አስተምህሮ ግድ ኑሯቸው ሳይሆን፣ ጦቢያን ለማፈራረስ የሚያስችላቸው ፍቱን መሣርያ ሆኖ ስላገኙት ብቻና ብቻ ነው፡፡  በሌላ አባባል ለኦነጋዊ ጴንጤወች፣ ጴንጤነት የግብ መምቻ እንጅ ግብ አይደለም፡፡

እስቲ መንግስተ ሰማያት መግባቱ ይቆየንና ቤታችን እንኳ በሰላም እንግባ!

ለኦነጋዊ ጴንጤወች ጴንጤነት የግብ መምቻ ሳይሆን በራሱ ግብ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስትያናዊቷን ተዋሕዶን ከማጥቃታቸው በፊት በዋቄፈታ ላይ በዘመቱ ነበር፡፡  ዋቄፈታን እያንቆለጳጰሱ ተዋሕዶን ባላንኳሰሱ ነበር፡፡  መስቀል መሳለምን እያወገዙ፣ ኦዳን በቅቤ ባላወዙ ነበር፡፡  ኢሬቻን እያደነቁ፣ በመስቀል በዓል ባልተሳለቁ ነበር፡፡  ካቶሊክን ሳይነቅፉ፣ ተዋሕዶን ባልዘለፉ ነበር፡፡  እስልምናን እየፈሩ፣ ተዋሕዶን ባልደፈሩ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች - ግርማ ካሳ

ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ ጴንጤነትን ላጀንዳቸው ማስፈጸሚያነት የሚጠቀሙ የክርስትና ቁማርተኞች እንጅ፣ ክርስቲያኖች አይደሉም፡፡  ዓላማቸው ተሳክቶላቸው በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ቢመሠርቱ ደግሞ፣ በመጀመርያ የሚያደርጉት የቀሩትን ሁሉንም ሐይማኖቶች (ክርስትና፣ እስልምና፣ ባሃይፍና ወዘተ.) በሕግ ከልክለው፣ ዋቄፈታን ነጥለው ብቸኛ መንግሥታዊ ሐይማኖት ማድረግ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡

እንቆቅልሹ ደግሞ አብዛኞቹ ጴንጤወች፣ የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ባለመረዳት ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ ተመልክተው የጰነጠጡ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  በሌላ አባባል አብዛኞቹ ጴንጤወች በኦነጋዊ ጴንጤወች የተደለሉ (convince) ወይም የተታለሉ (confuse) አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው፡፡  እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች በሐይማኖት ሽፋን ዓይናቸው ስለተሸፈነ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች እየሱስ፣ በየሱስ የሚሉት ጦቢያዊነት እስኪደመሰስ ድረስ እንደሆነ አልተገለጠላቸውም፡፡

እጅጉን የሚያሳዝነው ደግሞ በስብከትና በዝማሬ ክሂሎታቸው ጴንጤነትን እንደ ሰደድ እሳት በማስፋፋት፣ የሚወዷትን አገራቸውን የኢትዮጵያን ሞት የሚያፋጥኑት እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን፣ ኢትዮጵያዊነት የተገመደበት ሌላኛው ገመድ ለሆነው ለአማርኛ ቋንቋ ካላቸው የመረረ ጥላቻ የተነሳ ቋንቋውን በቅጡ የማይችሉ፣ ቢችሉም የማይችሉ ለመምሰል የሚጣጣሩ ከንቱወች ስለሆኑ፣ በስበከትም ሆነ በመዝሙር የማጰንጠጥ ችሎታቸው ከመ አልቦ ነው፡፡

ስለዚህም ተዋሕዶን በመግድል ጦቢያን መግደል ዓላማው ያደርግው ኦነጋዊ ጴንጤነት የተመሠረተው በኦነጋዊ ጴንጤወች ቢሆንም፣ የቆመው ግን በኦነጋዊ ጴንጤወች በተደለሉ ወይም በተታለሉ አገር ወዳድ ጴንጤወች ነው ማለት ነው፡፡  በሌላ አባባል ጦቢያን የማፈራረሻ ስልት ለሆነው ለጴንጤነት መስፋፋት ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት፣ ጦቢያ ከልባቸው የሚወዱ አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው፡፡

ስለዚህም አገር ወዳድ ጴንጤወች የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ተረድተው የዓላማው አስፈጻሚ ላለመሆን ከወሰኑ፣ ተዋሕዶን በመግደል ጦቢያን ለመግደል የተፈጠረው ኦነጋዊ ጴንጤነት ባጭር ጊዜ ውስጥ ያከትማል፡፡  ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ የሚመለከቱት አገር ወዳድ ጴንጤወች፣ ወደ ሐይማኖታቸው ሲያንጋጥጡ፣ ሐይማኖታቸው የቆመበትን አገራቸውን እንዳያጡ አበክረው ሊያስቡበት ይገባል፡፡  በተለይም ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ በሽልማት መልክ ከፍተኛ በጀት መድቦለት ተዋሕዶን በየለቱ የሚዘልፈውን ዮናታን አክሊሉን እና መሰሎቹን ባለጌ ጴንጤወች አንቅረው ሊተፏቸው ይገባል፡፡

ሐይማኖታዊ ነጻነትን (religious freedom) ጨምሮ ሁሉም ነጻነቶች፣ የሀገር የነጻነት ዛፍ የሚያፈራቸው ፍሬወች ናቸው፡፡  ለምሳሌ ያህል ቢሊ ግራሃምን (Billy Graham) የመሳሰሉ ምዕራባውያን ጴንጤወች፣ ሰበካቸውን በጨረሱ ቁጥር be with our soldiers in harms way እያሉ አምላካቸውን ከወታደሮቻቸው ጎን እንዲቆም የሚማጸኑት፣ የሐይማኖት ነጻነት የሚቆመው ባገር ነጻነት ላይ መሆኑን  ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊነት  ከአፋር እና ዓማራ ዉጭ አይታሰብም!  

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን አገር የግዜር ነው እያሉ ለጦቢያዊነት ዘብ መቆምን ኀጢያት ያደርጉታል፡፡  ይህን የሚያደርጉት ደግሞ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ለመገንባት ያቀዱትን ፀረጦቢያ እቅድ የሚያከሽፍ፣ ለጦቢያ ቀናዒ የሆነ አፍቃሪ ጦቢያ ትውልድ እንዳይፈጠር ነው፡፡  አገር የግዜር ነው በሚሉበት አፋቸው ደግሞ ኦሮሚያ ኬኛ ይሉበታል፡፡  እልፍ አእላፍ የተዋሕዶ አርበኞች በደም ባጥንታቸው ባቆሟት አገር ላይ፣  የተዋሕዶ መዕምኖችን ባዕድ ለማለት ይዳዳቸዋል፣ በማን ላይ ቁመሽ ማንም ታሚያለሽ እንዲሉ፡፡

ባጭሩ ለመናገር፣ ኦነጋዊ ጴንጤነት ማለት ሰሙ ክርስትና ወርቁ ኦሮሙማ የሆነ የኦነጋዊ ቁማርተኞች ቅኔ ነው፡፡  አገር ወዳድ ጴንጤወች ግን፣ በኦነጋዊ ጴንጤወች በመደለል (convince) እና በመታለል (confuse) እንዲያዩ የተደረጉት የጴንጤነትን ኦሮሙማዊ ገጽታ ሳይሆን፣ የጴንጤነትን ክርስቲያናዊ ገጽታ ብቻ ነው፡፡  የጴንጤነት ቅኔ፣ ሰሙ እንጅ ወርቁ አልተገለጠላቸውም፡፡  ስላልተገለጠላቸው ደግሞ በጴንጤነትና በተዋሕዶ መካከል ያለው መሠረታዊ ችግር ያሰተምህሮ (doctrine) ልዩነት ይመስላቸዋል፡፡

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን ለዋቄፈታ እንጅ ለክርስትና ዴንታ ስለሌቸው፣ ፀባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንጅ ከተዋሕዶ አስተምህሮ ጋር አይደለም፡፡  ተዋሕዶነት ከጦቢያዊነት ጋር ባይቆራኝ ኖሮ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች የካቶሊክን አስተምህሮ የሚያከብሩትን ያህል፣ ተመሳሳዩን የተዋሕዶን አስተምህሮ ባከበሩ ነበር፡፡  ችግሩ ግን ካቶሊክ የጣልያን፣ ተዋሕዶ የጦቢያ መሆኑ ነው፡፡

ጦቢያን የምትወዱ አገር ወዳድ ጴንጤወች፣ እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡  ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩን፣ ብኻዩን… ወደ ጎን ትተው፣ ተዋሕዶውን ብቻ እግረ በግር እየተከታተሉ “እየሱስን ተቀብለሃል?” እያሉ መነዝነዝን ምን ይሉታል?  ተዋሕዶወች ብቻ እንዲጰነጥጡ የተፈለገበት ምክኒያት ምንድን ነው?  የተዋሕዶ ዐብያተ ክርስቲያኖች በቄሮ መንጋ ሲጋዩ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች ደስታቸውን መደበቅ እስከሚያቅታቸው ድረስ ፊታቸው እንደ ፈንድሻ የሚፈካው ለምንድን ነው?  በመንግሥታዊ ቢሮስፍና (bureaucracy) ውስጥ የተሰገሰጉ ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ የሌሎች ሐይማኖታዊ በዓሎችን አከባበር እያመቻቹ፣ የተዋሕዶ ባዕሎች ግን እንዳይከበሩ አያሌ ቢሮስፍናዊ (bureaucratic) መሰናክሎችን የሚቸክሉት ለምንድን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባለቄራው ፓስተር - አሁንገና ዓለማየሁ

አገር ወዳድ ጴንጤወች ሆይ፣ ዓይናችሁን ክፈቱ እንጅ፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች በየሱስ ስም የከነቧችሁን ክናብ (ዓይነ ርግብ፣ veil) ገልጣችሁ፣ ግማሹን ውነት (half truth) ሳይሆን ሙሉውን ውነት የምታዩት፣ የጴንጤነት ቅኔ ሰሙ ብቻ ሳይሆን ውርቁም የሚገለጥላችሁ መቸ ነው?  ጦቢያ ከሞተች በኋላ?  በዳግም ምጽኣት?

ድኅረ ኪታብ (Post-script)

ጴንጤወች ጴንጤ መባልን ስለሚቃወሙ፣ ራሳቸውን የሚጠሩት ፕሮቴስታንት (protestant) ብለው ነው፡፡  ጴንጤወች ፕሮቴስታንትፓስተርቸርችባይብል የመሳሰሉትን ባዕድ ቃሎች መጠቀም መብታቸው ነው፡፡  ነገር ግን አንድን ያማረኛ ተናጋሪ ራሱ እስካልፈቀደ ድረስ ያማረኛ ባልሆነ ቃል ጥራኝ ብለው ማስገደድ አይችሉም፡፡

ተዋሕዶወች ራሳቸውን ኦርቶዶክስ የሚሉት ምርጫቸው ስለሆነ ነው (ምንም እንኳን ኦርቶዶክስ ከሚለው ባዕዳዊ ቃል ይልቅ ርቱምነት የሚለው አገራዊ ቃል የሚሻል ቢሆንም፡፡  ማናቸውም ሐይማኖት ያማረኛ ስም እስከሌለው ድረስ፣ ያማረኛ ተናጋሪወች ያማረኛ ስም ሊያወጡለት ሙሉ መብት አላቸው (ስሙ አንቋሻሽ ወይም አራካሽ እስካልሆነ ድረስ)፡፡  ለምሳሌ ያህል የነብዩ ሙሐመድ እምነት ተከታዮች፣ አማረኛ ተናጋሪወችን እንደ አረበኛው ሙስሊም እንጅ፣ እንደ አማረኛው እስላም አትበሉን ብለው ማስገደድ አይችሉም (እስላም የሚለው ቃል ያሉበትን ችግሮች ዘርዝረው እስካላብራሩ ድረስ)፡፡

የፕሮቴስታንት ያማረኛ ትርጉም ዓማፂ ስለሆነ፣ የእምነቱን ተከታዮች ዓማፂያን ብሎ መጥራት ያማረኛ ተናገሪወች ሙሉ መብት ነው፡፡  ፕሮቴስታንቶች ባማረኛ ሲጠሩ ዓማፂያን ወይም ጴንጤ እንዳይባሉ ከፈለጉ ደግሞ ራሳቸውን በራሳቸው ባማረኛ ይሰይሙ፡፡  ይህን እንዲያደርጉ ግን ኦነጋዊ ጴንጤወች እንደማይፈቅዱላቸው እሙን ነው፣ ሐይማኖቱ ጦቢያዊነትን ተላብሶ ጦቢያዊነትን እንዳያራምድ ይፈራሉና፡፡

በመጨረሻም ለተዋሕዶ ማሳሰቢያ፡፡  ጠላት የሚገባው በደካማ ጎን ስለሆነ፣ የሽንፈት መንስዔው የራስ ድክመት እንጅ የጠላት ጥንካሬ አይደለም፡፡  ጴንጤነት ደግሞ መንፈሳዊ ስካር ስለሆነ፣ ጥንካሬው የብቅል ነው፡፡  ስለዚህም ምንም እንኳን የኦነጋዊ ጴንጤነት ዓላማ ተዋሕዶን መግደል ቢሆንም፣  ተዋሕዶ ልትሞት የምትችለው ግን ኦነጋዊ ጴንጤነት ጥንካሬ ሳይሆን በራሷ ድክመት ነው፡፡  በመሆኑም ተዋሕዶ ሐይማኖት እሷ ራሷ ሙታ ጦቢያን ይዛ እንዳትሞት፣ ራሷን አብጠርጥራ መርምራ፣ በሽታወቿን በደንብ አውቃ፣ ፍቱን መድሐኒቶችን አጥብቃ መሻትና መራራ ቢሆኑም እንኳን ባፋጣኝ መውሰድ አለባት፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

 

3 Comments

  1. መስፍን አረጋ ጊዜህን ሰውተህ እውቀት ላይ እውቀት ንቃት ላይ ንቃት ስለሰጠኸን እናመሰግናለን። አንተ ስትጽፍ ጸረ ኢትዮጵያው ሀይል ይርዳል ብስጭቱን መቆጣጠር አቅቶት ያቀረሻል አንተ ግን ግንዛቤ ከማስጨበጥ ወደ ኋላ አትበል። እናመሰግናለን

  2. መስፍን አረጋ የተባልክ ሰው ነገሮችን ባልተጣራ ትንታኔ የኢትዮጲያ ማህበረሰብ ከመቶ 20 የሚሆኑትን በጭፍን ስታዋርድ ስትሳደብ ዝም ማለት አይቻልም:: ጴንጤ የሚለው መጠሪያ በንጉሱ ዘመን መገባደጃ ላይ ለወሎ ድርቅ ርዳታ ማሰባሰቢያ ሃገር ፍቅር የወንጌላዊያን መዘምራን ሲዘምሩ የባለስልጣኖቹ ሚስቶች ተነክተው ሲያለቅሱ ጳጳሱ ቴዎፍሎስ ምን እንጠብቃለን ብለው በሲሶ መንግስት ስልጣናቸው የጸጥታ ሹሙን ኮ/ል ከድርን በማሳሰብ የተሰሩት የጴንጤቆስጤ እምነት ተከታዮች ታሪክ መነሻ ሆኖ መንፈሳዊ መረዳት ያላቸው የኦርቶዶስክ ተዋህዶ ሃቀኛ ጳጳስ አቡነ መርሃክርስቶስ ጀምሮ በቅጽል የሚጠሩበት ሆኗል:: የሚሲዮናዊያን በጎም ክፉም ጎን መኖሩን ለኢትዮጲያ አንድነት ሲፋለም ለመይሳው ካሳ የተሰዋ ዮሃንስ ቤል ከዚያም በጣልያን ወረራ ከህዝባችን ሳይለዩ የቆሞ ዶክተር ላምቤን መጥቀስ ይቻላል:: የማይካደው ክፉ ሚሲዮናዊያን ከክፉ ፖለቲካ ጋር ማበራቸው በሃገራችንም ክፉ ጳጳሳት ቀሳውስት የነገስታቱን ግፍ ሳይገስጹ በደሉ የከፋ ለመሆኑን የፍቅር እስከመቃብሩን አባ ሞገሴን ባህርያት በብዙዎቹ ምንደኞች ጳጳሳት ቀሳውስት ላይ ማየት ይቻላል:: ዶክተር ሃዲስ የኢዮጲያ ገባር ህዝቦችን ታሪክ በፍቅር መሰል ታሪክ ያቀረቡት የቀድሞዋ ሲዊዲን ሚሲዮን ቆይቶ የመካነኢየሱስ የመጀመሪያ ቄስ ፓስተር ባድማ ያለው ተማሪ መሆናቸው መጽሃፍቶቻቸውን አርታኢ እንደነበሩ ብታውቅ ምላስህን ባላረዘምክ ነበር:: መካነኢይሱስ መሬት ላራሹ የሚለውን ትክክለኛ ጥያቄ በወቅቱ ለነበረው የንጉሱ ፓርላማ ያቀረበች በደርግ የዩኔስኮ ተሸላሚ የሆንበትን የመሰረተትምህርት ዘመቻ በብቃት የተወጣች መሆኑን ታሪክ ከሚያውቁ ጠይቅ:: ወያኔ ስልጣን በያዘበት ሰሞን ሃገራዊ እርቅና ሰላም በግዮን ሆቴል ሲካሄድ መካነኢየሱስ ዋና ተባባሪ መሆኗ ያንተ መሰሎቹ ተራ ክስ በጎ ታሪኳ አይቀይርም:: ይህን ብዬ ግን የጠቀስካቸው ቄስ ጉዲና በተገቢ መልኩ የኦሮሞና ሌሎች ገባር ህዝቦች መብት ይከበር ዘንድ ከንጉሳ በተሰብና ባላባቶች ሳይቀር የተወለዱት ይዚያ ትውልድ ታጋዮች ያቀረቡትን መርህ ወደሳተ የዘረኘነት መስመር ማስገባታቸው መናሀሪያቸው በነበረው ሚኒሶታ የወጣቱ ትውልድ መፈክርን “አማራ ይውደም “ያስተማሩትን የመጽሃፍ ቅዱሱን በለአም በሚመስል “ኦሮሞ ይውደም” ብሎ የተራገመው ልጅ ውጤቶች ሁሉም ወንጌል አማኙ ማህበረሰብን የሚወክል በማድረግ ማቅረብ ነውርም ሃጢያትም ነውና ክርሲያን ከሆንክ ንስሃ ግናባ ቀና ምልከታ ይኑርህ ::ወንጌላዊያን ወይም ጴንጤዎችም ከሰሜን አሜሪካ እስከ ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጲያ ጉዳይ የሚገዳቸው ለተዋህዶ ኦርቶዶክስም ክብር ያላቸው መኖራቸውን ቢመርህም ሃቁን ተቀበል::

  3. ደጎኔው ሞረቴው ትንሽ ሲቆነጠጡ ከመንፈሳዊ እሳቤ ወደ ቆንጨራ ተሸጋገሩ በቦታው ላይ ቢገኙ ቄሮ ካደረገው ያነሰ አይሰሩም ነበር። Ethiopia under Italian occupation የምትል አንድ አነስ ያለች መጽሀፍና ጀርመኖች ወደ ወለጋ ምን እንደሰሩ ከኛ በላይ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ መድገም አያስፈልግም። የናንተው ልጅ ዮናታን አክሊሉና አብይ አህመድን ጨምሮ ትላንት በአውሮፓ ሰላዮች ሰብሳቢነት ይህ መጽሀፍ መመሪያችን ነው ከዚህ ውጭ አታንብቡ ተብሎ የተሰጣችሁን የ king James version ትላንትና 300 አመት ያልሞላውን እምነትና መጽሀፍ ከሙሴ የተቀበላችሁት ያህል ትመጻደቁበታላችሁ። በመሰረቱ ሀይማኖቱን እናንተ ላይ ጭነው አፍሪካን ያበጣብጡበታል እንጅ እነሱ መጀመሪያም ለወረራ አሁንም ለወረራ ነው የተጠቀሙት። ዛሬ እምነቱን የላኩላችሁ የምእራብ አገሮች ቤተእምነቶቻቸውን ዘግተው መጨፈሪያ አድርገውታል ቀሪውንም ሽጠውታል። 90%ያህሉ እምነት የለውም ሌላም ሌላም። መስፍን ደንቆሮ ወይም ያላገናዘበ ሳይሆን የሀገር መፍረስ እረፍት የነሳው ዜጋ ነው። እስከዛሬ ካላገናዘቡት እነዚህ ሰዎች እነሱ የማያምኑበትን ለምን እኛ እንድናምንላቸው ፈለጉ ብለው እራስዎን ይጠይቁ። ሙጋቤ እንዳለው ቻይና በአመት 50ሚሊዮን ኢንጅነር ስታሰለጥን የናንተ ወዳጆች 50 ሚልዮን ስራ ፈት ፓስተር፣ነብይ እያሉ ለአፍሪካ ያሰለጥኑልናል። ጌታዬ እስራኤል ዳንሳ፣ ነብዩ ጩፋ፣ ዮናታን አክሊሉ የሚባሉ ወሮበሎች ወጣቱን እንደዛ ሲጫወቱበት ህግ ቢኖር ፍርዳቸውን ያገኙ ነበር። እነዚህ ፓስተሮች ነብዮች በጫት ፣በሀሽሽ፣ በመጠጥ እየነበዙ የሰሩትን ስራ ሳይመለከቱ አይቀሩም በVOAም የተላለፈውን ሳይሰሙም አልቀሩም እንደዚህ ናቸው የኛ ጴንጤዎች ኦርቶዶክስ መጥፋት አለበት የሚሉን። ባጠቃላይ ለፈረንጅ ያልጠቀመ ለእኛ የተላከውን ፓኬጅ ለምን ብሎ መመርመር ግድ ይላል መስፍንም ያደረገው ይህንኑ ነው እርሶ የጻፉት ትክክል ሁኖ መስፍን የጻፈው ስህተት የሚሆንበት አመንክዮ አይታየንም። ፈረንጅ የላከውን ሳይቀነስ እንተገብረዋለን ካሉም ለሚቀጥለው ይዘጋጁ ቤተ መቅደስ ውስጥ አበበን ከመገርሳ ጫሉትን ከነፊሳ ጋብቻችሁን ይባርክ ሲጠበቅባችሁ ነው። መልካም ገና በየቦታው የሚቀነጠሱት እረፍት ያጡ እናቶች ህጻናት ደካሞች ጉዳይ ወደ ነብሳችሁ ይድረስ አመሰግናለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share