በመሥከረም 28/ 2015 ዓ/ም በሶሻል ሣይንሥ ተማሪዎች ፈተና ይጀመራል ። ይህ በፈተና አሰጣጡ ልዩ የሆነው አገር አቀፍ ፈተና ፣ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ጥንካሬ እና ደካማ ጎን በግልፅ እና በተጨባጭ የሚያመላክት ፣ በትምህርት ጥራት ላይ በትጋት እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ። ተብሎ ይጠበቃል ። እንደሚታወቀው ገንዘብ ተኮር የትምህርት አሠጣጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መኖሩን ( በግል ትምህርት ቤቶች በክፍያ በመንግሥት ተምህርት ቤቶች ኮራብት በሆኑ መምህራን የተነሣ … ) በይፋ የሚያሳውቀን ይኽ በየዩኒቨርስቲ የሚሠጠው ፈተና በመሆኑ ፣ የትምህርት ሚኒሰትር እና መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጡት ይታወቃል ።
ይህ ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ፣ በፊደራል ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ነው የሚካሄደው ። ፈተናው ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል ። ፈታኝ መምህራንም በዕጣ ነው ፣ ለየዩኒቨርሥቲዎቹ የሚመደቡት ። እያንዳንዱ አሥፈታኝ ትምህርት ቤት ፤ ተማሪዎች እና ዩኒቨርስቲዎችን የሚመለከት ግዴታ ና መብትም በግልፅ ወጥቷል ። ይህንን በተመለከተ ያገኘሁትን መረጃ አሣጥሬ ለተማሪዎች እና ለወላጆች አሣውቃለሁ ።
የአሥፈታኝ ተምህርት ቤቶች ግዴታ
- የተፈታኝተማሪዎችንሥም ዝርዝር አሥቀድሞ ለሚመለከተው ክፍል ፕሮቶኮሉን በጠበቀ መልኩ ያሳውቃል ።
2 . በበቂ ሁኔታ ተፈታኙን ሥለ ዩኒቨርስቲው እና ሥለ ፈተናው ህግ ያሣውቃል ።
3 . በሳይኮሎጂ የተጎዱትን ተማሪዎች ( በኮቪድ እና በሶሻል ሚዲያ ውዠንብር ) ሞራል መገንባትና ከኩረጃ ይልቅ በራሳቸው አእምሮ መሥራት አማራጫቸው መሆኑንን በወጉ ያሥረዳል ። አቅማቸውን ሣይጠቀሙ ቀርተው ጠባቂ በመሆን እንዳይወድቁ አሥቀድሞ ያነቃል ።
4 . የትምህርት ቤት እና የአድሚሽን ካርዳቸውን እንዳይረሱ ያሳስባል ።
5 . እያንዳንዱ አሥፈተኛ ት/ቤት ፤ የማህበራዊ ሣይንሥ ተፈታኞችን በመሥከረም 28/01/2015 የተፈጥሮ ሣይንሥ ተማሪዎችን ደግሞ በጥቅምት 6/ 2015 ዓ ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች ቀጥሮ የማሥረከብ እና ፈተናቸውን ሲጨርሱ ቆጥሮ የመረከብ ግዴታ አለበት ።
የተፈታኝ ተማሪውች ግዴታ
- አንሶላ፣ብርድልብስ እና የሌሊት ልብሶች ( ቱታ እና ፒጃማ ) ይዘው መምጣት አለባቸው ።
- ማንኛውንም ብልጭልጭ ቁሣቁሥ ፣ የመዘነጫ መነፅር ፣ የጆሮ ጌጥ ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ሌላ የጌጥ ቀለበት ማድረግ የለባቸውም ።
- ማንኛውም ሞባይል ሥልክ ፣ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት ፣ ይዞ ወደ ዩነኒቨርስቲ መግባት ክልክል ነው ።
- እርሳስ ፣ ላቢስ፣ መቅረጫ ፣ ማሥመሪያ መያዝ አለባቸው ።
- የትምህርት ቤታቸውን እና የመፈተኛ መታወቂያቸውን የመያዝ ግዴታ አለባቸው ።
- ዩኒቨርሲቲከገቡበኋላ በሚገለፅላቸው በዩኒቨርሲቲው ህግ የመተዳደርና ህጉን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።
- እርጉዝተማሪዎችመፈተን አይቹሉም ። ከወለዱ በኋላ የሚፈተኑበትን ሁኔታ መንግሥት ያመቻቻል ።
የዩኒቨርስቲዎች ግዴታ
- አሥቀድሞ በተጠቀሰው ተማሪዎችን የመቀበል ቀን ፣ ከሚመለከተው አካል አሥቀድሞ በተረከቡት ሰነድ ፣ አንድ በአንድ ተማሪዎችን ማንነታቸውን በማረጋገጥ እና ከላይ የተጠቀሰውን ግዴታ ተማሪው ማሟላቱን በማረጋገጥ ፣ ህጋዊ ፍተሻ አድርገው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው የማሥገባት ግዴታ አለባቸው ።
- ለተፈታኝ ተማሪዎች ፣ የሚያድሩበት ክፍል ፣ አልጋ እና ፍራሽ አሥቀድሞ አዘጋጅተው የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።
- ለተማሪዎቹቁርስ፣ ምሣና እራት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ። ( በምግብ የሚነሳን ቅሬታ ከወዲሁ ለማሶገድ ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል ።)
- የተማሪዎቹ ፀጥታ እንዳይናጋ ፣ ማንኛውንም የፀጥታ ሥጋት እንዳይኖር ከፍተኛ ጥበቃና ምሥጢራዊ ክትትል ያደርጋል ።
- ፈተናውንበተመለከተለተማሪዎቹ መብራሪያ እንዲሰጥ አደራሾችን ያመቻቻል ።