September 8, 2022
7 mins read

የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ – ሰማነህ ታምራት ጀመረ፤ ኦታዋ፤ ካናዳ

ጵጉሜን 3 ቀን 2014 ዓ.ም.

መቸመ እንደ አማርኛ ነገርን በቅኔ ሃሳብን በዘዴ እያዋዛና እያሳቀ የሚገልፅና የልብን የሚአደርስ ቋንቋ ብዙ አይገኝም።  ከኢትዮጵያዊያ አባባሎች ውስጥ ‘የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ’ ምትለዋ የውያኔን ዓይን ያወጣ ጩኸትና ኡአኡታ የሚገልፅ ሌላ አባባል ካለ ወዲህ በሉኝ። ለአባባሉ መነሻ ሊሆን የቻለው የሰሞኑ የደብረፅዮንና የቧግዴው ጌታቸው እረዳ  ’ተከበናል፤ አስጥሉን፤ ማሩን፤ እንደራደር ወዘተ  እያሉ ለምዕራቡ ዓልምና ለደጋፊዎቻቸው የሚአሰሙት ጩኸትና ስሞታ ነው። ለዚህም ይህችን መልዕክት አጠር አርገን ልናስተላልፋ ወደድን። ብዙ ነገር  ባአሕያ አይጫንም እንዲሉ ያለዝባዝንኬ እንዲህ እንበላቸው።

አሸባሪው ሕወሃት ተከበብሁ እያለ ያናፋል አሉ። እስይ እንኳአንም ተከበባችሁ።  ስለተከበባችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ የዓለም አቅፍ ማሕበረሰብ የሚአነባው እንባ፤ የሚአሰማው ሐዘን፤ የሚአወርደው  ሙሾና የሚአቀርበው ተራድዖ አይኖርም። አቤቱታውና እየየው ለመታዘል ከሆነ እንስሳቱንም እንደሰው እረሽናችሁ ስለጨረሳችሁ አንቀልባ የለም። ኢትዮጵያ እና ህዝቧ 48 ዓመታት አዝሏችሁ የደም እንባ ሲአነባ ኖሯል። እርኩስ መንፈስን ጭናችሁ ስታስለቅሱት ለአስርት ዓመታት ትከሻው ጎብጧል። የመሸከም አቅሙ ስለደከመ የደም እንባ ማንባት በቃን ብሏል-ይሰማል። እርግጥ ነው ዛሬ እናንተ በጫራችሁት ሰደድ እሳት ተከባችሗል። ይህ በደደቢት ዋሻና በመቀሌ ምድር ላይ ያለሐቅ ስለሆነ የምንሸሽገው ሳይሆን የምንኮራበትና አፋችን ሞልተን አዎ ተከባችሗል እያልን በድፍረት የምንናገረው ይሆናል። መከራ ቻዩና ትዕግስተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እሰየው ስለተከበባችሁ ደስብሎናል ይላችሗል።

አዎ እወቁት ዛሬ ተከባችሗል ነገ ደግሞ ወደ መቃብር ስትወርዱ ለማየት የዋሁ ሕዝብ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል። የትግራይ ሕዝብ ነፃ ሊወጣ አፋፍ ላይ ይገኛል። ያኔ የኢትዮጵያ ሸክም ይቀላል። በናንተ የጎበጠው ትከሻ ይቃናል። እፎይታና ሰላም በኢትዮጵያ ይሰፍናል።  አዎ-ያኔ በኢትዮጵያ የደም እንባ ታበሰ ይባላል። ተከበናል  ስላላችሁ የዓለም ማሕበረሰብ እርዳታ የሚአቀርብ ከመሰላችሁ እውነትም በቁማችሁ ሞታችሗል።

ዓለም የላከላችሁን  የእርዳታ እህል ከተራበውና ከታረዘው ትግራዊ ሕዝብ ነጥቃችሁ ወታደራችሁን  መግባችሁበታል።  የእርዳት እህል የሚአጓጉዙ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የተባበሩት  መንግስታት  ድርጅት ሃብት የሆኑ ካሚዎኖችን ነጥቃችሁ የወታደር ማጓጓዥ አድርጋችሗል። ሆስፒታልና ጤና ጣቢያን ለመርዳት የተላከ ነዳጅ (570,00 ሊትር)  ዘርፋችሁ ለዋሻችሁ ጀነሬተር  አውላችሗል።

በምን መልኩ ነው የዓለም ማሕበረሰብ እንደገና እርዳት የሚልከው። ምናችሁን አምኖ ይርዳችሁ። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት እርዳታውን ከዓለም እየተቀበለ በቀጥታ ለተጨነቀው፤ ለተራበውና ለተጠማው ደጉ የትግራይ ሕዝብ በመንግስት መዋቅር አማካይነት እርዳታው እንዲደርስ ያደረጋል። ሕጋዊው መንገድም ይህ ብቻ ይሆናል-ይሰማል!!!። አሸባሪው ሕወሃትን “የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የሚለው የሃገራችን አባባል በሚገባ የሚገልፀው ነውና እኛ ስራችን እንስራ። ከዚህ በሗላ ሌባው፤ ወስላታውና አሸባሪው ሕወሃት ዳግም እናዳይነሳ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንቅበረው። የናቶች፤ የአባቶች፣ የሴቶች፣ የወጣቶች፤ የአዛውንቶች፤ የገበሬዎች ወዘተ እንባና ሰቆቃ ይቁም። ለኢትዮጵያ ሕዝብ እፎይታ እንስጠው። በምድረ ኢትዮጵያም ፍስሐን እናንግስ።

በመጨረሻም ሕወሃት ሆይ ብንረሳ ብንረሳ የሽብሬን ሞት(97)፤ በእስራት ድብደባ ሁለት እግሩን የቆረጣችሁትን ወጣት፤ በሽህ የሚቆጠሩ የዓማራ፤ አፋር፤ ሶማሊያ፤ ደቡብ ሕዝቦች እና የኦርሞ እንቦቀቅላ ልጃገረዶችን እየደፈራችሁ ለዓረብ ሃገራት የሸጣችሗቸውን እህቶች ግፍ፤ ያፈናቀላችሁትንና በጅምላ የጨፈጨፋችሁትን የዓማራ ሕዝብ አንረሳውም። ቢረሳ ቢረስ 424 አኝዋኮችን በአንድ ጀምበር የጨፈጨፋጩሁትን፤ አርባ ጉጉ ላይ ከነነፍሳቸው የጨረሳችሗቸውን ዓማሮችና ሕፃነት እንዴት እንርሳው። አሁን ጨዋታው አልቋል (Game Over)  በሰላም  እጃችሁን  ስጡና  ከበባው  ይነሳላችሁ። እኛም ተጨማሪ ደም ሳይፈስ እንገላገላችሁ ወይ ተገላገሉን።  ከሕወሃት ነፃ የሆነ 2015ን በደመቀና በእልልታ እንቀበለው።  ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴና ምኞቴ ነው። 

እንቁጣጣሽ!!!

 

ሰማነህ ታምራት ጀመረ፤

ኦታዋ፤ ካናዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop