September 5, 2022
7 mins read

ጥቁር – ጠበንጃ  ወይስ ጥቁር -ሙጃ

Amhara 7አበዉ “ዉኃን ምን ያጮኸዋል ቢሉ ድንጋይ ”ይሏል  ፡፡ በኢትዮጵያ ሰዶ ማሳደድ አይነተኛ የፖለቲካ ስልጣን ምርኳዝ ማዳበሪያ መሆኖ የሀገረ ታሪካችን የዘመናት ትዉፊት መሆኑ ማይካድ ገሀድ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያን ከዉጭ ወራሪ ጋር የወጋ ያስወጋ ፤ በዓለም ታሪክ የራሷን ግዛት እና የባህር በር አሳልፎ የሰጠ ፣የነበረዉን ህዝባዊ ጦር ኃይል በትኖ በብሄር እና  በፖለቲካ ቅኝት ያደራጀ ፣ ነባሩን  ብዙኃን ህዝብ ያገለለ፣ በማንነት ላይ ጥላቻ ዘመቻ ያካሄደ እና ጥቃት የፈፀመ  በብኄራዊ ክህደት እና ጥፋት ያልተጠበቀባት አገር ኢትዮጵያ መሆኗን ማናችንም አንረሳም ፡፡

ይህም ብቻ አይደለም አናቷን አፈርሶ ፤ የባህር በሯን አሳልፎ መሰረቷን በማናጋት ኢትዮጵያን ታሪክ አድርጎ ለማክሰም ባልተማከለ የአገር አስተዳደር (ክልል) ስም እምብርቷን በመዉጋት ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን ከሁለት አሰርተ ዓመታት በላይ በተግባር ያሳየ ያለማንም ከልካይ ተጠያቂ ባልሆነባት አገር በድጋሚ የሆድ አቃዋን ለመዘርገፍ ጦር አምጣ እያለ መሬት ደብዳቢ በወረሳት አገር ጥቁር  ጠበንጃ መፈለግ ለኢትዮጵያ ህመም ጠላትን ማስታመም ነዉ ፡፡

ትህነግ የአገሪቷን አንጡራ ሀብት ከአገሪቷ ካላት ትጥቅ እና ስንቅ በላይ ከነግብረ ቸበር አገር አፍራሾች ጋር አስከ አፍንጫዉ ከምድር አስከ አስከ ሰማይ ፤ ከየብስ አስከ ዉኃ  ስንቅ እና ትጥቅ ይዞ እያለ ህይወት እና አካል ገብረዉ ለራሳቸዉ ፣ለህዝባቸዉ እና ለአገራቸዉ ባዶ እጂ ከጠላት ጋር በመተናነቅ ከጠላት የጠገኘን መሳሪያ መታጠቅ ሊያስመሰግን እና ሊያስሾም ሲገባ ጥቁር ጠበንጃ ፍለጋ በሚል ጥቁር የታሪክ ሙጃ መትከል  አህያዉን ቢፈሩ ዳዉላዉን ነዉ ፡፡

በአስራ ዘጠኝ መቶ ሠላሳዎች  ድህረ ኢጣሊያ ወራራ ማግስት ለህይወት እና ለድሎት ሳይሳሱ በአምስት ዓመት ተጋድሎ  ቅጠል በመልበስ ድንጋይ በመንተራስ ኢትዮጵያን የታደጉት በከዱት እና በሸሹት  ተሳድዋል ፡፡

ያም ጥቁር የታሪክ ሙጃ አየተስፋፋ ነቃይ እና ተዉ ባይ አጥቶ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ያ ዘመን ከአሁኑ የሚለየዉ የዚያን ዘመን ማሳደድ በዉጭ ጠላት ገፊነት በዉስጥ አድር ባይነት ሴራ ደመድ ኢትዮጵያን መጥለፍ ሲሆን ያሁኑ በዉስጥ ራስ ወዳድነት በችግር ጊዜ ኢትዮጵያን ከአጥፊዎች ወረራራ እና ምዝበራ አገሪቷን፣ ህዝቧን እንዲሁም ያለዉን ስርዓት የታደጉትን አንድያ ነፍሳቸዉን ለዓላማ አሥይዘዉ ባገኙት የጠላት መሳሪያ  ኢትዮጵያ ቁስሏ ሳይሽር  የክፉ ቀን ፈጥኖ ደራሽ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆችን በመሳሪያ ( ጥቁር-ጠበንጃ) መለወጥ ጥቁር የታሪክ ሙጃ መትከል ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ጀግኖች ሲታጠቁ ፣ሲነቁ እና ሲበቁ የሚሰጋዉ ፀረ-ኢትዮጵያዊ ብቻ ነዉ ፡፡  ኢትዮጵያ ከዉጭ እና ከዉስጥ ፤ ከሩቅ እና ቅርብ በጠላት ጥርስ እየደማች እና እየቆሰለች  ድቅድቅ ጭለማዉን ጊዜ አሳልፈዉ ለብርኃን ያበቁትን  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ሊኮሩ እና ሊከበሩ ይገባል እንጂ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ስም የሚያሰጥ ጥቁር የታሪክ ሙጃ መነቀል አለበት ፡፡

ለዉጭ ጠላት አንገቱን ያልደፋ ፤ለኩርማን መሬት ያልተገፋ ህዝብ ዛሬ በዉስጥ እና በከዳተኛ ኩሉም የአግረቷ ክፍል አቅጣጫ እንደ ወተት የሚናጥ እና የሚገፋ በዉስጥ አንድነት እና ህብረት ማጣት ድክመት እንጂ በዉጭ ጠላት አይደለም ብርታት አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ፡፡

ኢትዮጵያን ከዳር አልፎ መኃል የሚያፈርስ ኃይል የጥፋት መሳሪያ እንዲታጠቅ የሆነዉ እና ህዝብን ቁም ስቅል በመንሳት ሠላም የሚነሳ፤ የሚያፈናቅል ፣ የሚገድል እና የሚበድል በኢትዮጵያ ህዝብ ኪስ እና መቀነት በተገዛ መሳሪያ ነዉ ፡፡ ለምን ጥቁር መሳሪያ ከሚባል የኢትዮጵያን ሀብት እና ንብረት በኢትዮጵያ ምድር በመዝረፍ እና በማዘረፍ በህዝብ ላይ ዕሳት የሚያቀጣጥሉትን ከእነዕሳታቸዉ ማጥፋት ለምን አልተፈለገም ፤አልተቻለም የሚለዉንም ሳንዘነጋ ፤ አሁንም ሱዳን 60 እና 70 ከ.ሜ. የኢትዮጵያን ግዛት አሳፍታ ይዛ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ “ጥቁር ጠበንጃ ” ከምንል  አገር እና ህዝብን ከባርነት እና ድህነት ቀንበር ከጫንቃዉ ላይ ለማዉረድ  ጥቁር የታሪክ ሙጃ ምንጭ እና መሰረት መድረቅ እና መናድ ይኖርበታል ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ

NEILOSS –Amber!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop