ኦርማኒያ እስከ ኦሮሚያ፣
ደረጀ ተፈራ (የግል ምልከታ)
- መግቢያ፣
እንደሚታወቀው አውሮፓውያን በተለያዩዘመናት በእምነት ስም፣ በአሳሽነት (Exploration)፣ በጎብኚነት፣ በዲፕሎማትማዕረግ እና በመሳሰሉት ሽፋን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሃገራችንን በመሰለል ለቅኝ ገዥ መንግስቶቻቸው መረጃ ያስተላልፉ የነበረ ሲሆን ከስለላው በተጨማሪ የእምነትና የታሪክ ቅርሶችን ይዘርፉ፣ ባህላችንን እና የቆየ ሃገራዊ እሴቶቻችንን በመበረዝ የነጭን የበላይነት ስነ ልቦናን ያስፋፉ፣ ህዝቡንም ይከፋፍሉ ነበር። ለምሳሌ በ 17 መ/ክ/ዘመን ጀምስ ብሩስ የተባለ እንግሊዛዊ (የስኮትላንድ ተወላጅ) የአባይን ምንጭ ፉለጋ በሚል ሰበብ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ታቦተ ፅዮንን ለማግኘት ብዙ ጥሮ ባይሳካለትም በመጨረሻ ግን በተሟላ ሁኔታ የሚገኙ ሁለት የመፅሀፈ ሄኖክ የግዕዝ ኮፒዎችን እና ሌሎች የብራና መፅሀፍትን ሰርቆ ሊወጣ ችሏል። ከእሱም በመቀጠል ሌሎችም ወደ ሃገራችን የመጡ ፈረንጆች በብራና የተጻፉ መጽሃፍትን፣ ታቦትን ጨምሮ በርካታ ነዋየ ቅዱሳትን እና የተለያዩ የታሪክ ቅርሶቻችን በመዝረፍ ወደ ሃገራቸው አግዘዋል። እስረኛ ለማስለቀቅ በሚል ሰበብ የእንግሊዝ መንግስት በፈጸመቸው ወረራ አጼ ቴዎድሮስ ባቋቋሙት ቤተ መዛግብት ይረኙ የነበሩ በርካታ የሃገራችን ቅርሶችና መጻህፍት ተዘርፈዋል፣ “የሰው ጌጥ አያደምቅ” እንደሚባለው ፋሽስት ጣሊያን የእነሱ ታሪክ ያልሆነውን የአክሱምን የድንጋይ ሃውልት ሳይቀር ወደ ሃገሩ ጭኖ በመውሰድ በኢትዮጵያ ቅርስ ሊያጌጥ በሮም ከተማ ማቆሙ ይታወሳል። እነዚህ ወደ ሃገራችን የሚመጡ አውሮፓውያን የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነቱን በማላላት ሃገራችንን ለመቆጣጠር በህዝቡ መሃል እየተሽለኮለኩ መርዛቸውን ይረጩ ነበር። ለምሳሌ የክርስቲያኑን መንግስት ለማገዝ ወደ ኢትዮጵያ መተው የነበሩ ፖርቹጋሎች የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስን በሮማ ካቶሊክ ለመቀየር በመሞከራቸው በእነሱ ጦስ በርካታ ህዝብ በርስ በርስ ጦርነት እንዳለቀ በታሪክ ይታወቃል። ቅባትና ጸጋ የሚባል አስተምህሮ እርሾው ከነሱ የመጣ ነበር። የአውሮፓ የግል የመርከብ ካምፓኒዎች ቀይ ባህርን አቋርጠን ስንሄድ ተላላፊ መርከቦቻችን ሲበላሹብን አቁመን መጠገኛ የሚሆነን ለጋራዥ ስራ የምንጠቀምበት አነስተኛ መሬት ተባበሩን በማለት በአሰብ እና በሌሎች በቀይ ባህር ጠረፍ መሬቶችን ከአካባቢውን የጎሳ መሪዎች አባብለው ከገዙ በኋላ ለመንግስቶቻቸው አሳልፈው በመስጠት ቅኝ ግዛት ለማስፋፉት በመነሻነት ተጠቅመውበታል።
~
በዲፕሎማት ስም አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው ሃገራችችንን በመሰለል ወደ መንግስታቸው መረጃ ይልኩ ከነበሩ በርካታ የአውሮፓ ተወላጆች ውስጥ ሮማን ፕሮችዝካ (Roman Prochazka) የተባለ ኦስትሪያዊ ይገኛል። የነጭ የበላይነትን አቀንቃኝ የሆነው ሮማን ፕሮችዝካ ኢትዮጵያ ይኖር በነበረበት ጊዜ በሰላይነት ሲንቀሳቀስ ተይዞ በቀ/ኃ/ስላሴ መንግስት በ1927 ዓ/ም የተባረረ ነው። እንደተባረረም ሃገሩ ሄዶ “ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል” (Abyssinia the Powder Barrel) በሚል ርዕስ መፅሐፍ ጽፎ በአውሮፓ ሃገራት አሰራጨ። የመፅሐፉ ዋና ይዘት ኢትዮጵያውያን የነጭ የበላይነትን የማይቀበሉ ኩሩ ህዝቦች በመሆናቸው ሃገራቸው በአውሮፓ ቅኝ ግዛት ስር ካልወደቀች ለሌሎች በቅኝ ግዛቶቻችን ውስጥ ለሚገኙ ጥቁር አፍሪካውያን መጥፎ ምሳሌ ይሆናሉ የሚል ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በመጽሃፉ ውስጥ ኢትዮጵያ በርካታ በቋንቋ፣ በባህልና በእምነት የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚኖሩባት ሃገር ስለሆነች ይህንኑ ልዩነት በመጠቀሞ የህዝቡን ህብረት በማላላት በቀላሉ ሃገሪቷን በጦርነት አሸንፎ በቅኝ መግዛት ይቻላል ይላል። የሮማን ፕሮችዝካ ሃሳብ አድዋ ላይ ባባቶቻችን ተሽንፎ የተባረረው የጣሊያን መንግስት ኢትዮጵያን ለመበቀል ከ40 ዓመት በኋላ ዳግም ለወረራ ሲዘጋጅ በነበረበት ጊዜ የታተመ በመሆኑ ለቤኒቶ ሙሶሊኒ (Benito Mussolini) ግብዓት እንደሆነው ይታመናል።
~
ከዚህ በላይ ከተገለጹት የፋሽስት ጣሊያን ወረራዎች እጅግ ቀደም ብሎ ህዝቡን የእጅ ሞያ ጥበብ (ተግባረ ዕድ) ለማስተማር ከአውሮፓ ወደ ሸዋ የመጣ ዮሐን ክራፕፍ (Johann Ludwig Krapf) የተባለ የጀርመን ሚሲዮናዊ ነበር። ዮሐን ክራፕፍ እ.አ.አ ከ1837 እስከ 1842 ኢትዮጵያ (ሸዋ) ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት ከመጣበት ዓላማ ውጭ በሸዋና አካባቢው በየገጠሩ በመዟዟር፣ እንዲሁም ከሸዋ ርቀው በሚገኙ እንደ እናርያ ከፋ፣ ጎንደር እና በመሳሰሉት የሃገራችን ክፍሎች በንግድ እና በኑሮ ወደ ሸዋ የሚመጡ ሰዎችን በማናገር መረጃ ያሰባስብ ነበር። አንዱን ህዝብ በሌላው ላይ በማነሳሳት ግጭት ለመፍጠር ይቀሰቅስ ነበር። ለምሳሌ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን የአፍሪካ ጀርመኖች ናችሁ (“The Germans of Africa”) ሌላ ጊዜ ደግሞ ሃገራችሁ “ዖርማኒያ (ORMANIA)” ናት፣ የአውሮፓን ባህልና ሃይማኖት ብትከተሉ መልካም በሆነ ነበር እያለ መርዙን ይረጭ ነበር። (ከዚህ ጽሁፍ በስተመጨረሻ ላይ በተገለጸው ምንጭ #1፡ ገጽ 52 /pdf ገጽ 2 እና ምንጭ #2፡ ገጽ 63 /pdf ገጽ 104 ላይ ይመልከቱ)።
~
2. ሚሲዮናውያን እና የቅኝ ገዢ መንግስታት፣
ታሪክን ወደ ኋላ ሄደን ስንመረምር በመካከለኛው ዘመን በተለይም በአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮት ተከትሎ በአውሮፓ ሃገራት የታየው እድገትና መሻሻል የሰሙ የኢትዮጵያ ነገስታት ከወቅቱ የስልጣኔ ትሩፋት በመቋደስ ሃገራችንን ለማሳደግ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ ለአውሮፓ መንግስታት ህዝባችንን የእጅ ሞያ ጥበብ አስተምሩልን የሚል ጥያቄ ያቀርቡ ነበር። ይሁንና አውሮፓውያን የኢትዮጵያ ንጉሶች ሃገራቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ቅን ፍላጎት ታከው በወንጌል አስተማሪነት ስም የሚነግዱ ሰላይ የፕሮቴስታንት ሚሲዮናዊውንን እና የካቶሊክ እየሱሳውያንን በመላክ የሃገራችንን መግቢያና መውጫ፣ የህዝቡን አኗኗር፣ ስብጥር፣ የመንግስቱን ጠንካራና ደካማ ጎን በማስጠናት መረጃ ይሰበስቡ ነበር። በሚያገኙትም መረጃ መሰረት የእምነት፣ የባህልና የመሳሰሉ ልዩነቶችን በማስፋት፣ በንጉሳዊው መንግስት ላይ የሸፈቱ መሳፍንትን በማስታጠቅ፣ በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸው ህዝቡን ለያይተው አንድነቱን በማላላት ከቻሉ አጠቃላይ ሃገራችንን ካልቻሉ የተወሰነውን የኢትዮጵያ ክፍል ከሌላው በመገንጠል የራሳቸውን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ይሸርቡ ነበር። ለምሳሌ ጀርመናዊው ሚሲዮናዊ ዮሐን ክራፕፍ በሃይማኖት ሽፋን ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ምሥራቅ አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት አቅዶ ለነበረው ለሃገሩ ለጀርመን ኢምፔሪያል መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ በመሰለል መረጃ ያስተላልፍ ነበር።
~
ዮሐን ክራፕፍ ምሥራቅ አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት አቅዶ ለነበረው ለሃገሩ ለጀርመን መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ በመሰለል ካስተላለፈው መረጃ ውስጥ የሚከተለው ይገኛል፦ ጀርመን የምሥራቅ አፍሪካን ከኢትዮጵያ በመነሳት ቅኝ ግዛቷ ማድረግ እንደምትችል፤ በተለይም የጋ*ን ጎሳዎችን መቆጣጠር ከተቻለ የእስልምና ሃይማኖት በአፍሪካ የሚያደርገውን መስፋፋት መግታት እንደሚቻል እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ ነዋሪዎችን በፕሮቴስታንት ክርስትና ሃይማኖት በማጥመቅ የጀርመን ወዳጅ አድርጎ በአካባቢው የጀርመንን የበላይነት (ቀኝ ግዛት) ማረጋገጥ ይቻላል፤ በተለይም በተለያየ የጎሳ መጠሪያ ስም በየአካባቢው እዚህም እዛም የሠፈሩ የጋ*ን ጎሳዎችን በአንድ ካርታ (ግዛት) ውስጥ ከልሎና አንድ የጋራ መጠሪያ ስም በመስጠት እስከ ሩዋንዳና ብሩንዲ ድረስ የምስራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ሃይቅ ሃገራትን አንድ ላይ በማድረግ ትልቅ የጀርመን ቅኝ ግዛትን መፍጠር ይቻላል የሚል ምክረ ሃሳብ ለሃገሩ ለጀርመን መንግስት በጽሁፍ አቀረበ።
~
ዮሐን ክራፕፍ በምሥራቅ አፍሪካ የፕሮቴስታንት ክርስትና ሃይማኖትን በማስፋፋት በጀርመን ባህል እና እምነት ህዝቡን ሸብቦ በማሰር የጀርመን ቀኝ ግዛትን ማስፋፋት ይቻላል የሚለውን ሃሳቡን እውን ለማድረግ መረቡን ለመጣል የሞከረው በሸዋና በዙሪያው የሚገኙ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦች ብቻ ሳይሆን የንጉሱን እናት ወ/ሮ ስናማ ወርቅን በማግባባት ልጃቸው ንጉስ ሳህለ ስላሴን በእናታቸው በኩል ለማጥመድ ሙከራ አድርጎም ነበር። ታሪኩ እንዲህ ነው። ዮሐን ክራፕፍ በሃገር ስለላ ተይዞ ሲባረር ከሃገር የወጣው ሸዋን እና ወሎን በግሼ በኩል አቋርጦ በመተማ ጎንደር ከዛም በሱዳን በኩል ወደ ግብጽ ካይሮ ነበር። በዛወቅት እንዳሁኑ ስልጣኔ ባለመስፋፋቱ በየቦታው ሆቴል ስላልነበረ የንጉሱ መልዕክተኞች እና ተጓዦች እያረፉ የሚጓዙት በየ መኮንንቱና የሃገረ ገዢው ቤት ነበር። እናም ንጉሱ ዮሐን ክራፕፍን ከአጃቢ ወታደሮች ጋር አድርገው መንዝ ሰላ ድንጋይ እናታቸው ቤት አርፈው እንዲሄዱ አዘዙ። በዚሁ መሰረት ዮሐን ክራፕፍ ከተመደቡለት ከአጃቢዎቹ ጋር በመሆን March 12/ 1842 ከሸዋ አንኮበር ከተማ ተነስቶ በሚቀጥለው ቀን March 13/ 1842 ከሰዓት በኋላ መንዝ ሰላ ድንጋይ የንጉሱ እናት ወ/ሮ ስናማ ወርቅ መኖሪያ ቤት ደረሱ። እዛም እንደደረሱ የንጉሱ እናት አሽከሮች እንግዶቻቸውን ተቀብለው በማስተናገድ አሳደሯቸው። በንጋታው ዮሐን ክራፕፍ ወደ ንጉሱ እናት እንግዳ መቀበያ እልፍኝ አዳራሽ (Reception Room) ከአጃቢዎቹ ጋር በመሄድ እጅ ከነሳ (ሰላምታ ካቀረበ) በኋላ ከሻንጣው ውስጥ ጸጉር ማበጠሪያ፣ ፊት ማያ መስታዎት፣ መቀስ እና መጽሐፍ ቅዱስ አውጥቶ ስጦታ አበረከተላቸው። ወ/ሮ ስናማ ወርቅ ስጦታውን ተቀብለው ካመሰገኑ በኋላ፣ “የሃገሬ ወንዶች ጥበበኛ በመሆን እነዚህን አስደናቂ (የሚያምሩ) ነገሮችን እንዴት እዚሁ ሃገራችን ውስጥ መስራት (ማምረት) ይችላሉ?” የሚል ጥያቄ ለዮሐን ክራፕፍ አቀረቡለት። እሱም ሲመልስ:- “እንግሊዝ፣ ጀርመኖች እና ባጠቃላይ መላው አውሮፓውያን በአንድ ወቅት እንደ ጋ*ች “rude and ignorant” ነበሩ፣ ነገር ግን ወንጌልን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በሳይንስ እውቀትና በኪነጥበብ ባረካቸው። እናም የእርሶ ልጅ ንጉስ ሳህላ ሥላሴ እሺ ብለው እንደ አውሮፓ ወንጌልን (ጌታን) ቢቀበሉና ህዝቡም መልካም ስነምግባር ቢላበስ አሁን እርሶ ያስገረሞትን ድንቅ ነገሮችን መስራት በቻሉ ነበር” በማለት መልስ ሰጣቸው። ሚሲዮናዊው ዮሐን ክራፕፍ ይህንን ማለቱ ንጉሱ እሺ ብለው ቢስማሙ ወደ አንኮበር በመመለስ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ በጀርመን የሉተራል ፕሮቴስታንት እምነት በእናታቸው በኩል በማግባባት ለመቀየር ነበር። ይሁን እንጂ በክራቸውና በሃገራቸው የማይደራደሩት የንጉሱ እናት ወዲያው አሽከሮቻቸውን በማስጠራት ወደሚቀጥለው የግሼን ሃገረ ገዥ በመላክ ከሃገር እንዲወጣ አደረጉት (ከዚህ ጽሁፍ በስተመጨረሻ ላይ በተገለጸው ምንጭ #2፡ ገጽ 74 /pdf 115 ይመልከቱ።
~
ይሁን እንጂ ከኢትዮጵያ ላይ ዓይኑን አልነቅልም ያለው ዩሃን ክራፕፍ ወደ ሃገሩ ከሄደ በኋላ አራት ፈረንጆችን አስከትሎ ወደ ሸዋ ተመልሶ መጣ። ለምን ተመልሶ እንደመጣ ሲጠየቅ፡ ቀድሞ የተባረረው ህዝቡን የእጅ ሞያ ባለማስተማሩ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ያመጣቸው ሰዎች የእጅ ሞያ ጥበብ ማስተማር የሚችሉ ናቸው በማለት መልስ ሰጠ። ንጉሱም እውነቱን ከሆነ ጊዜ ሰጥተነው እንየው በማለት ለሁለተኛ ጊዜ እድል ሰጡት። ይሁን እንጂ የንጉሱን እናት ጨምሮ ህዝቡን ወደእሱ እምነት ለመቀየር ሞክሮ ስላልተሳካለት “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል” እንደሚባለው የኦርቶዶክስ ክርስትና በመላዕክት የምታምን ናት፣ ወዘተ ወዘተ እያለ ያለግብሯ ስሟን ያጠፋ ነበር። ኦርቶዶክሶች እሺ የማይሉ ግትሮች ናቸው፣ እነሱን ከመቀየር እምነት የሌላቸውን “ጋ*ችን ክርስትናን ማስተማር ይሻላል በማለት ትኩረቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ባህላዊ አምልኮት በሚከተሉ የሃገራችን ማህበረሰቦች ላይ በተለይም ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ ላይ አዞረ። ከአውሮፓ ያመጣቸው ፈረንጆች ሰባኪ ሚሲዮናውያን እንጂ የእጅ ሞያ ማስተማር የማይችሉ መሆናቸው በመረጋገጡ፣ እሱም ቢሆን የእጅ ጥበብ ሞያ ከማስተማር ይልቅ በህዝቡ ውስጥ እየተሽለኮለከ በሃገር ሰላይነት እና ህዝቡን ለመከፋፈል በመሞከሩ የተነሳ ዳግም ከሃገር ሊባረር ቻለ። ነገር ግን ከሃገር ሲባረር ወደ ግብጽ ካይሮ፣ ከዛም በመርከብ ወደ የመን የኤደን ወደብ በኩል ወደ ኬንያ (ሞምባሳ) እና ታንዛኒያ (ዛንዚባር) ተጓዘ። በመጨረሻም ተመልሶ ኬንያ ሞምባሳ ለረጅም ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ በ1875 ወደ ሃገሩ ጀርመን በመመለስ በ1881 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
~
ዮሃን ክራፕፍ 500 ገጽ ብዛት ባለው አሰልቺ የጉዞ ማስታወሻው ውስጥ እራሱ በኢትዮጵያም ሆነ በኬንያ የሚገኙትን ሁሉንም ጋ* እያለ ነበር በተደጋጋሚ የሚጠራቸው። ካላመነበት እራሱም ቢሆን ቃሉን መጠቀም አልነበረበትም ይሁን እንጂ በከፋፍለህ ግዛ የአውሮፓ የፖለቲካ ቁማር የኢትዮጵያን ህዝብ በዘርና በጎሳ ከፋፍሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ነገር ሲሸርብ “ጋ*” የሚለው ቃል ሕዝቡን ለመሳደብ በሐበሾችና አረቦች የተሰጠ ነው በማለት ይቀሰውስ ነበር። ይሁን እንጂ “ጋ*” የሚለው ቃል መሰረቱ የኩሽ ቃል እንጂ ሴማዊ ከሆኑት ከግዕዝም ሆነ ከአማርኛ ቋንቋዎች ጋር ግንኙነት እንደሌለው የቋንቋ ምሁራን ያስረዳሉ። በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ “ጋ*” የሚለው ቃል የተጠቀሙት ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር በሶማሌ ውስጥ በጉርብትና ይኖሩ የነበሩ ሙስሊም የሶማሌ ከብት አርቢ ጎሳዎች ናቸው። እንደሚታወቀው በኦሮሞ እና በሶማሌ አርብቶ አደር ጎሳዎች መሃል ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በግጦሽ መሬትና በውሃ ምክንያት ግጭት ይከሰት ነበር። ለምሳሌ በቅርቡ በ2009 ዓ/ም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተን ግጭት ጥሩ ማሳያ ምሳሌ ነው። ይሁንና በተለይ የሱማሌ ጎሳዎች እስልምና ከተቀበሉ በኋላ የባህል አምልኮት ከሚከተሉት ከጎረቤቶቻቸው የኦሮሞ ጎሳዎች ጋር በእምነት ልዩነት ምክንያት ግጭታቸው ይበልጥ እየተካረረና አድማሱን እያሰፋ ሄደ። በዚህም የተነሳ በርካታ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ጦርነትን በመሸሽ ከአካባቢው በመፈናቀል ተሰደዱ። ጥንታዊ የኦሮሞ ጎሳዎች ከሶማሌ ምድር ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በእምነት ልዩነት ግጭት መከሰቱን ከሚጠቁሙ ቃላቶች ውስጥ ለምሳሌ በሶማልኛ ቋንቋ Gaal, Gaalo, Gaalnimo, Gaalada, Gaalabah የሚባሉ ቃላቶች ይገኛሉ። እነዚህ ቃላቶች ትርጉማቸው በአላህ የማያምን ወይም Infidel(s), Disbeliever ማለት ነው። ቃላቶቹም በሶማልኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ውስጥ የሚገኙ ስለሆኑ ማወቅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በግሉ ማረጋገጥ ይችላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሱማሌና የኦሮሞ ጎሳዎች የተዋጉበት “Gaal Madow Wars” ወይም “Galkayo” የሚባል የጦርነት ታሪክም አለ። እንደ ሶማልኛ በኩሽ ቋንቋ ቤተሰብ ስር የሚመደበውና ከሶማለኛ ቋንቋ ጋር ዝምድና ባለው በራሱ በኦሮምኛም ቋንቋ ውስጥም ቢሆን “ጋ*” ከሚለው ቃል ጋር ተዛማጅነት ያላቸው በርካታ ቃላቶች አሉ። ለምሳሌ Gala (ግመል)፣ gala-na (ወንዝ)፣ ma-gaalaa (ከተማ)፣ gal-gala (ምሽት)፣ Gallee (ገሊ – ወደ ውስጥ ገባን)፣ gaaʼelaa (ጥንድ ወይም ባልና ሚስት) ወዘተ። ይሆንና እዚህ ላይ ማስታወስ የሚገባን ነገር ቢኖር አንድ ሰው ወይም ማህበረሰብ በዚህ ስም መጠራት አልፈልግም ካለ ሊከበርለት ይገባል። በሌላ በኩል ደግሞ በወቅቱ ካለመሰልጠን ጋር ተያይዞ በሃገራችን እና አጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ የነበረ ኋላ ቀር ባህል፣ ልማድ፣ ንግግር፣ ስራን መናቅና የመሳሰሉት ነበር። ከስድብም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎችም ሰውን ለመስዋዕትነት እስከማቅረብ የሚደርሱ አምልኮቶች፣ ጌቶቻቸው በሞቱ ጊዜ አሽከሮቻቸውን በህይወት አብሮ የሚቀብር መጥፎ ባህል ነበር። በመሆኑም መንግስት ካለመዘመኑ በተጨማሪ በራሱ በህዝቡ ውስጥም የነበሩ ኋላ ቀር ባህሎች፣ ልማዶችና አምልኮቶች እንደነበሩ ማስታወስ ይገባል። ለምሳሌ “ጎጃሜ ቡዳ ነው ብለሽ ያወራሽው ሰው ሰውን ሲበላ የታባሽ አየሽው” ብሎ በስነ ቃል የጎጃም አዝማሪ ለደንቆሮ ባለጌዎች በጨዋ ደንብ መልስና ግሳጼን ሰጠ እንጂ ተሰደብኩ በማለት በመንግስት እና በህዝብ ላይ ለበቀል ጫካ አልወረደም፣ ኢትዮጵያዊነቱንም አልካደም። ተናጋሪው የየትኛው ብሔረስብ አባል እንደሆነ እንኳን በማይታወቅበት ሁኔታ በየመንገዱ ስለተነገረ አማራ ነው ይህንን ያለን ማለት ነውር ነው። በአማርኛ የተሳደበ ሁሉ አማራ አይደለም። ለምሳሌ ትግሬው መለስ ዜናዊ፣ ኦሮሞው አብይ አህመድ እና የመሳሰሉት ቱባ ባለስልጣናት በአማርኛ ቋንቋ (በቀጥታም ሆነ በአግቦ) የአማራን ህዝብ በፓርላማ ውስጥ ሳይቀር ሲሰድቡ፣ ስሙን በማጠልሸት በሃሰት ሲወነጅሉት፣ ንጹሃን አማራዎች ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ማፈናቀል ከማውገዝ ይልቅ ሲያድበሰብሱና በቀለኛነታቸውን በሚያሳብቅ መልኩ በንጹሃን ሞት ሲያላግጡ ሰምተናል። ~ - በሬውን በማስደንበር የፓለቲካዓላማን የማስፈፀምስልት፣
ባጠቃላይ “ጋ*” የሚለው ቃል ትርጉምና የአጀማመር ታሪኩ ከሶማልኛ ቋንቋ ጋር የተገኘና የኩሽ ቃል መሆኑን አይተናል፣ ይሁን እንጂ የኦነግ መስራቾች እና የኦሮሞ ብሔርተኛ ልሂቃን ዮሃን ክራፕፍ በማስታወሻው ላይ የጻፈውን ሳይመረምሩ እንደወረደ ተቀብለው አማራ ይህንን ስም እንደሰጣቸው በመናገር ህዝቡን በሃሰት ሲቀሰቅሱ፣ ጥላቻ ሲዘሩ፣ በአማራ ህዝብ ላይ ጦር ሲያዘምቱ ኖረዋል። ድሮ ልጅ እያለሁ ለአመት በዓል የሰፈራችን አባቶች ለቅርጫ የሚሆን በሬ ለመግዛት ወደ ቄራ ሲሄዱ ዱርዬ የሚባሉ የቄራ ልጆች በሬዎቹን ከኋላ ሳይታዩ በመርፌ እየወጉ ወይም በፉጨትና በመኪና ጥሩንባ በማስደንበር (ፊጋ በማድረግ) በሬውን እንድንይዝላችሁ ገንዘብ ክፈሉን ይላሉ ሲባል እሰማ ነበር። በሬውም ብዙ ጥፋት ካደረሰ፣ ከተማውን ካተራመሰ በኋላ በመጨረሻ ባስደነበሩት የቄራ ዱርዬዎች ይያዝ ነበር። ኦነግም እንደ ቄራ ዱርዬዎች ህዝቡን የሚያስቆጣ ነገር እየፈለገ ይህንን ተባልክ፣ ያንን አደረጉህ እያለ ሃሰተኛ ትርክት እየፈጠረ በተለይም ወጣቱን በማነሳሳት የፖለቲካ አላማውን ለማስፈጸም ሃገር እንደሚያተራምስ ይታወቃል። ሃላፊነት የማይሰማው ኦነግ በሚያሰራጨው የሃሰት ትርክት (ፕሮፓጋንዳ) ምክንያት በርካታ ንጹሃን አማራዎች በግፍ ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል። ለምሳሌ የኦነግ መስራች እና የድርጅቱ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር የነበረው ዲማ ነገዎ የተባለ ሰው በ1983 ዓ/ም በወያኔና ኦነግ ባቋቋሙት የሽግግሩ መንግስት የማስታወቂያ ሚ/ር የነበረ ሲሆን (አሁን ደግሞ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የጠ/ሚ አብይ አህመድ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪ ነው) በለውጡ አካባቢ ከኢትዮጵያ ውጭ እያለ ከአሜሪካ ቪኦኤ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ጋር (ካልተሳሳትኩ ከአዳነች ፍስሃዬ ጋር) ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ “ጋ*” የሚለው መጠሪያ አማራ ነው የሰጠን እያለ ያለምንም መረጃና ማስረጃ ህዝብን በጅምላ ሲወነጅል በመስማቴ በቁጭት የቃሉን እውነተኛ ምንጭ ለማወቅ ባደርኩት ጥረት በግሌ የተረዳሁት ነገር ቢኖር “ጋ*” የሚለው ቃል መገኛ ግንዱ (ምንጩ) የኦነጋውያን እንደሚናገሩት የአማርኛ ቋንቋ ሳይሆን የኩሽ ቋንቋ ከሆነው ከሶማልኛ ቋንቋ እንደሆነ ነው። እስልምናን ያልተቀበሉ (አላህን የማያመልኩ) ጎረቤቶቻቸውን የሶማሌ ጎሳዎች ለመጥራት ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን፣ ቀስ በቀስ በሌላውም አካባቢ እየተለመደና እየተስፋፋ የመጣ ነው። በመሆኑም “ጋ*” የሚለው ቃል ሲጀመር የትኛውንም ቋንቋ ይናገሩ በአላህ ለማያምን ሁሉ መጥሪያነት ያገለግል የነበረ እንጂ ለአንድ ጎሳና ቋንቋ ተናጋሪ ብቻ የተሰጠ እልነበረም። የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ ደግሞ ቁጥሩ ብዛት ያለው በመሆኑ ለእነሱ ብቻ ተለይቶ የተሰጠ እየመሰለ መጣ። “ጋ*” የሚለው ኩሻዊ መሰረት ያለው ቃል ካልተሳሳትኩ ተዛማጅ የማርኛ ትርጉሙ “አረማዊ ወይም ኢአማኒ” ነው። ስለዚህ “ጋ*” መሰረቱ የኩሽ ቃል እንጂ ሴማዊ ከሆኑት ከግዕዝም ሆነ ከአማርኛ ቋንቋዎች እንዳልሆኑ ከተግባባን ኦሮሞና ኦሮሚያ የሚለውን ቃል አመጣጥን በተመለከተ በትንሹ ለማየት እንሞክር።
~
4. ከዮሃን ክራፕፍ ኦርማኒያ እስከ ኦነግ ኦሮሚያ፣
በ9ኛው ክ/ዘመን የክርስትና እምነት በአውሮፓ ከመስፋፋቱ በፊት የሮማ ወታደሮች ጎል (Gaul) ከተባለው ግዛታቸው በመነሳት የራይንን ወንዝ በመሻገር የጀርመን ነገዶችን (Germanic tribes) ለማስገበር በዘመቱ ጊዜ ቱተበርግ በተባለ ጫካ (Teutoburg Forest) ውስጥ ተሸሽጎ በመጠበቅ የጎሳውን አባላት በማስተባበር በደፈጣ ውጊያ የሮማን የሰለጠኑ ወታደሮችን ያሸነፋቸው አርመኒየስ (Arminius) የተባለ የጀርመን የጦር መሪ በታሪክ ይታወቃል። አርመኒየስ ጀርመኖች የሚኮሩበት ታሪካዊ ጀግናቸው ስለሆነ በተለያዩ የጀርመን ከተሞችና ሙዚየሞች ሃውልቱ ቆሞ ይታያል። የጀርመን ሚሲዮናዊው ዮሐን ክራፍ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሰብስቦ “ጋ*” ስድብ ስለሆነ በዚህ ቃል መጠራት የለባችሁም፣ እናንተ የአፍሪካ ጀርመኖች ናችሁ፣ እንደ “አርመኒየስ” ጎበዝ (ጀግና) በመሆናችሁ የሃገራችሁ መጠሪያ “ኦርማኒያ” (ORMANIA) ነው በማለት ቀድሞ የማይታወቅ አዲስ የአካባቢ መጠሪያ ስም ሰጣቸው። የደርግ ውድቀትን ተከትሎ ወያኔና ኦነግ በ1983 ዓ/ም የመንግስት ስልጣን ሲይዙ ሃገሪቱን ቋንቋን መሰረት ባደረገ በ14 ክልል የተከፋፈለ የጎሳ ፌዴራሎዝም ፈጠሩ፣ ከነዚህም ውስጥ አንዱ “ኦሮሚያ” የሚባል ክልል ነው። ከዚህ በተረፈ “ኦሮሙማ” የሚለው ቃል ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኛ ልሂቃን የፈጠሩት ተረት ተረት ነው። ናዚዎች እኛ ጀርመኖች ምርጥ የሰው ዘር ከሆነው “ከአርያን ዘር” የተገኘን በመሆናችን መላው አውሮፓ በእኛ ስር መገዛት አለበት ይሉ እንደነበረው የኛዎቹ ጽንፈኞች ደግሞ እራሳቸውን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ከፍ በማድረግ ምርጥ ከሆነው ከኦሮሙማ ዘር የተገኘን ነን በማለት የሃገሩ ልዩ ባለቤት በማድረግ ሌላውን ለመጨፍለቅ የሚጠቀሙበት ነው። ከላይ እንደተገለጸው “ኦርማኒያ” (ORMANIA) የሚባለውን መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዕምሮው አፍልቆ መጠቀም የጀመረው የጀርመን ሚሲዮናዊው ዮሃን ክራፕፍ ሲሆን በጉዞ ማስታወሻው ላይ እንደሚከተለው ይገልጸዋል፡ “What a noble land would ORMANIA be if it were under the influence of Christianity and European (German) culture !” (ምንጭ #2፡ ገጽ 3 /pdf 104)። ነገሩን ጠቅለል ስናደርገው ዮሐን ክራፕፍ መጀመሪያ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን የአፍሪካ ጀርመኖች (“The Germans of Africa”) እያለ ይጠራቸው ነበር፣ ነገር ግን በኋላ ላይ አውጥቶና አውርዶ “ኦርማኒያ” የሚል የዳቦ ስም ሰጣቸው፣ በሂደት ኦርማኒያ ወደ ኦሮሚያ ተቀየረ። “ጋ*” በሶማሌ ነገዶች፣ ኦርማኒያ ደግሞ በጀርመን የፕሮቴስታንት ሚሲዮናዊው በዮሐን ክራፕፍ የተሰጡ ስሞች ናቸው። ሃቁ ይህ ከሆነ የህዝቡ እውነተኛ መጠሪያ ማን ነበር? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። መልሱን እራሱ ዮሐን ክራፕፍ ለማህበረሰቡ አዲስ ስም ማውጣት የፈለገበትን ምክንያት ሲዘረዝር በግልጽ ይነግረናል። “በተለያየ የጎሳ መጠሪያ ስም ተራርቀው የሠፈሩ የጋ*ን ጎሳዎችን አንድ ላይ አሰባስቦ የጋራ ካርታና መጠሪያ ስም በመስጠት፣ ከቀሪው ኢትዮጵያ በመለየት እስከ ሩዋንዳና ብሩንዲ ድረስ የጀርመን ቅኝ ግዛት ለመፍጠር” እንደነበር በማስታወሻው ላይ ተጽፎ ይገኛል። ስለዚህ ቀድሞ አንድ የጋራ ስም አልነበራቸውም፣ ነገር ግን ይጠሩ የነበረው በተናጠል በጎሳቸው ስም ቦረና፣ ባሬንቱ፣ መጫ፣ ቱለማ፣ ከረዮ፣ ኢቱ፣ አርሲ፣ ሆሮ፣ ጉድሩ፣ ሊበን፣ ገላን፣ በቾ፣ ጉጂ ወዘተ ተብለው በተናጠል ነበር። አጠቃላይ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ መጠሪያ ስሙ በአዋጅ ኦሮሞ ተብሎ እንዲጠራ የተደነገገው በደርግ መንግስት የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን ሲሆን ኦሮሚያ የሚባል ክልል የተፈጠረው ደግሞ ደርግ ወድቆ ወያኔና ኦነግ በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግስት ባቋቋሙ ጊዜ ነው።
የክልሉን ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር ቀለማት ያለው ባንዲራ ወይም አንዳንዶች የአባ ገዳ ባንዲራ ታሪካዊ አመጣጡ ምን ይመስላል? የሚለውን ስንመለከት ደግሞ በቅድሚያ ግልጽ መሆን ያለበት በጥንታዊው የገዳ ስርዓትም ሆነ በመሃበረሰቡ ዘንድ ባንዲራ አይታወቅም፣ ባህልም አልነበረም ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የፕሮቲስታንት ሚሲዮናውያን የጀርመን ባንዲራን ይዘው ይንቀሳቀሱ ነበር። በ19ኛው ክ/ዘመን የጀርመን ኢምፓየር መንግስት ባንዲራ ጥቁር፣ ነጭና ቀይ የነበረ ሲሆን በአንደኛው የዓለም ጦርነት በመሸነፉ ጦርነቱ እንዳበቃ። የጀርመን ህዝብ በሽንፈቱ ሃፍረትና ውርደት ተሰማው፣ በመንግስቱም ላይ ቁጣውን አሰማ፣ በአመጽ ንጉሳዊ መንግስቱን ከስልጣን በማስወገድ በሪፕብሊክ መንግስት በማቋቋም ነጩን በቢጫ (ወርቃማ) ቀለም በመለወጥ የሃገሪቷ ባንዲራ ጥቁር፣ ቢጫና ቀይ አደረጉት። እናም ወደተነሣንበት ጉዳይ ስንመለስ አሁን የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ ወይም “የአባ ገዳ ባንዲራ” እየተባለ የሚጠራው መሃሉ ካለው ከዋርካው ዛፍ (ኦዳ ዛፍ) በቀር ቀለማቶቹ ከጀርመን ኢምፓየር መንግስት ባንዲራ (German Empire Flag) ጋር ተመሳሳይነት አለው። የጀርመን ሚሲዮናዊ ዮሐን ክራፕፍ ለሃገሩ መንግሥት ቅኝ ግዛት ለመፍጠር በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሃገራችን ቀብሮት የሄደው መርዝ፣ የእሱንም ቃል ፈጻሚ ደቀመዘምራን የሆኑት ነጭ አምላኪ ኦነጋውያን በሃፈራችን እና በህዝባችን ላይ ብዙ መከራ አስከትለዋል። እናም አሁን በአዲስ አበባ በኦሮምኛ ት/ት ቤቶች የሚያውለበልቡት የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና የሚዘምሩት መዝሙር የዚህ ሁሉ የተዛባ ማንነት ድምር ውጤት ነው።
~
5. የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሔርተኞች እና የአውሮፓ ሚሲዮናውያን፣
የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሔርተኞች አንዱ መነሻቸው የቅኝ ገዢዋ ጀርመን ሰላይ የነበረው የዮሐን ክራፕፍ ስሁት አስተምህሮ ሲሆን ሌላው ደግሞ የኮሚኒስቶች የጨቋኝ ተጨቋኝ ፕሮፓጋንዳና የስታሊን የብር ፖለቲካ ነው። በተለይም መቀመጫቸውን ወለጋ ላይ አድርገው የነበሩ የአውሮፓ ሚሲዮናውያን ቤተክርስቲያን ከመመስረት ጎን ለጎን ህዝቡን በመያዝ እምነታቸውን በአካባቢው ለማስፋፋት ት/ት ቤቶችን፣ የህክምና ክሊንኮችን፣ የእርዳታ ተቋማትን በማቋቋም ለረጅም ጊዜ በአካባቢው በመቆየታቸው በትውልዱ ላይ ከእምነት እስከ ፖለቲካ አስተሳሰብ (ርዕዮት) ቀረጻ ድረስ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመቶ አለቃ ማሞ መዘምር እና በጄነራል ታደሰ ብሩ ይደገፍ ስለነበረው መጫና ቱለማ ማህበር በተመለከተ አንድ ነጥብ አንስቼ ልለፍ።
እንደሚታወቀው የመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት እና የልማት ስራዎችን ለማከናወን በሚል በ1956 ዓ/ም የተመሰረተ ነው። ነገር ግን የማህበሩ አመራሮች እንደ ልማት ማህበር ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ድርጅት የሚንቀሳቀሱና በየስብሰባዎች ላይ የሚያደርጉት ንግግርም ከልማት ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ነበሩ። በመሆኑም ማህበሩ ከተቋቋመለት የልማት ስራዎች ውጭ የአመጽ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ያደርግ ስለነበረ በወቅቱ መንግስት ሊታገድ ችሏል። በመሆኑም የመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር የኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲካ ተቦክቶ የሚጋገርበት፣ የፖለቲካ መድረክ ነበር ማለት ይቻላል። በመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር የብሄርተኛ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተነቃቁ የያ ትውልድ አባላት፣ የሚሲዮናውያኑ ተማሪዎች የነበሩት እነ ሃይሌ ፊዳ፣ ዲማ ነግዎ፣ ሌንጮ ለታ፣ ገለሳ ዲልቦ፣ ኢብሳ ጉተማ፣ ባሮ ቱምሳ፣ ነጋሶ ጊዳዳ እና የመሳሰሉት በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶች ሲቋቋሙ አብዛኛዎቹ በመኢሶን እና በኦነግ ስር ተደራጁ። መኢሶን የሚባለው ድርጅት በአብዛኛው ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ መኮንኖች ከሚበዙበት ከደርግ ወታደራዊ መንግስት ጋር ለጊዜውም ቢሆን መሞዳሞድ ቢችልም እንኳን ደርግ ኢህአፓ የሚባል ትልቁን ጠላቱን ካጠፋና የእውቀት ድርቀቱን በመኢሶን ከተወጣ በኋላ በሁለት እግሩ መቆሙን ሲያረጋግጥ መጨረሻ ፊቱን ወደ መኢሶን አዞረ። በዚህ ጊዜ በርካታ የመኢሶን አናላት ህይወታቸን ለማትረፍ ለደርግ በወዶ ገብነት እጃቸውን ሲሰጡ፣ ከፊሎቹ ደግሞ የጀርመንና የሌሎች የአውሮፓ የፕሮቴስታንት የእምነት ድርጅቶች ጋር በነበራቸው ግንኙነት የሃይማኖት ሽፋን እየተሰጣቸው በመለኮታዊ ትምህርት (Theology Study) በሚል ስም ወደ አውሮፓ እየሾለኩ ወጡ። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ በደርግ መንግስት ውስጥ ከነበሩ የኦሮሞ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ኔትዎርክ በወቅቱ ሶሻሊስት ሃገሮች የሚሰጡትን የነጻ ት/ት (free scholarship) በመጠቀም በትምህርት ስም ወደ ውጭ ሃገር ተላኩ። ለምሳሌ ከብዙ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የመካነየሱስ ቄስ የሆኑት የቄስ ጊዳዳ ልጅ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በእምነት ስም ወደ ጀርመን ለትምህርት ከወጡት ውስጥ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመን በትምህርት ሳሉ በኦነግ ስር ወጣቱን በማደራጀት የፖለቲካ ተሳትፎ ነበራቸው፣ አሰፋ ጃለታ የተባለ ሰው ደግሞ ለደርግ መንግስት ያገለግል የነበረና ለአብዮቱ ላበረከተው ውለታ ደርግ ወደ ሶሻሊስት ቡልጋሪያ “Karl Marx Higher Institute of Economics” በነጻ ለትምህርት የላከው ሲሆን “ከአርያን ዘር” የተገኘን ምርጥ የሰው ዘር ነን በማለት አውሮፓን ብሎም መላው ዓለምን በጦርነት እንዳተራመሰውና የዘር ጭፍጨፋ እንደፈጸመው የጀርመኑ ናዚ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የኦሮሞ ህዝብ “ኦሮሙማ” ከሚባል ምርጥ የሰው ዘር የተገኘ ነው የሚል ናዚያዊ አስተሳሰብ የሚያራምድ ግለሰብ ነው። ይህ ሰው Journal of Oromo Studies በሚል ስም በርካታ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጭ የኖረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ኗሪነቱን ያደረገ የአንድ ዩኒቨርስቲ የሶሾሎጂ መምህር (ፕሮፌሰር) ነው፣ በንቲ ቴሶ ጀርመን ውስጥ የፕሮቴስታንት መለኮታዊ ትምህርት የተማረና በጀርመን ሉተራል ካህናት የተቀባ የኦነግ ፓስተር ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የኢትዮጵያ ስም በኩሽ መቀየር አለበት የሚል ዘመቻ ከፍቶ እንደነበር ይታወሳል። ባጠቃላይ በትምሀርት፣ በእምነት፣ በስራ እና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ውጭ ሃገር ወጥተው በአሜሪካና በአውሮፓ ተቀጥረው በመስራት ላይ የሚገኙ ለሞያቸውና ለእውነት ታማኝ ያልሆኑ በርካታ ኦነጋውያን የሚገኙ ሲሆኑ ያለ በቂ መረጃና ምሁራዊ ፍተሻ በጥናት (research) ስም ለርካሽ የፖለቲካ ዓላማቸው የሚያመች ሃሰተኛ ትርክት እየፈጥውሩ ህዝቡን ለማነሳሳት ሲያሰራጩ ኖረዋል፣ መጸሃፍትና ምሁራን ለማለት ከተፈለጉት (context) ውጭ ሆን ብለው ቃላትን እና ታሪክን አጣመው በመተርጎም ብዙዎችን አሳስተዋል። በደርግ ዘመን የኦነግ አባላት የነጻ ስኮላር ሺፕ ትምህርት ይከታተሉ በነበረበት ሶሻሊስት ሃገራት የተማሩትን ወይም የሰሙትን የተለያዩ ብሔረሰቦች የግጭት ታሪክ ለፕሮፓጋንዳ በሚያመቻቸው መልኩ የቦታና የስም ለውጥ በማድረግ በሃገራችን የተፈጸመ አስመስለው በማቅረብ የፖለቲካ መቀስቀሻ ጽሁፍ ያዘጋጁ ነበር። ለምሳሌ የስሎቫክ ቋንቋ ተናጋሪ በሆኑት የሰርቢያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቦስኒያ እና የመሳሰሉ ማህበረሰቦች በሚኖሩበት በምስራቅ አውሮፓ የሚገኘው የባልካን አካባቢ ለረጅም ጊዜ ያልተረጋጋና የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ የነበረበት ነው። በዚሁ አካባቢ የኦስትሪያ_ሃንጋሪ ልኡል ፍራንዝ ፈርዲናንድ በጉብኝት ላይ እያሉ በአንድ የሰርቢያ ብሔርተኛ መገደልን ተከትሎ የአንደኛው የአለም ጦርነት እንደተጀመረ ይታወቃል። ባጠቃላይ አንዱ ምሁር ነኝ ባይ ኦነጋዊ አይኑን በጨው አጥቦ የጻፈውን የሃሰት ትርክት ወይም የሰጠውን ኢንተርቪ ሌላው ተቀብሎ ኦቦ (ዶ/ር) እገሌ ይህንን ብለዋል እያሉ በመጥቀሰ የተመረጡትን እንደሚያስቱ ሀሰተኛ ነቢያት የኢትዮጵያ ህዝብ የተማረ ሰው አይዋሽም፣ ለህሊናው ያደረ ነው ብሎ ስለሚያምን የሚሉትን እውነት ነው ብሎ በመቀበሉ የእነሱ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነ።
- የመሬትቅርምት እና ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፖሊሲ፣
እንደሚታወሰው በ1983 ዓ/ም ደርግ ወድቆ ወያኔና ኦነግ የሽግግር መንግስት ሲያቋቁሙ በወቅቱ ኦነግ እና ወያኔ ቅድሚያ (Priority) ሰጥተው ከተንቀሳቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ዋናዎቹ፦ እታች ወረዳና ቀበሌ ድረስ ጎጠኛ አመለካከትን በማህበረሰቡ ውስጥ ማሰራጨት፣ ለሺ ዓመታት ሲተላለፍ የመጣን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሃብት የሆነን መሬት በተለያዩ ክልሎች ከፋፍሎ መቀራመት፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ እሴቶች ማፈራረስ፣ ደማቸውን አፍሰው በነጻነት ያቆዩዋትን ጀግኖች አባቶቻችንን ስም ማጠልሸት፣ የሃገራችንን ታሪክ ማራከስ፣ የአማራ ጥላቻን በማስፋፋት በመላው ሃገሪቷ ተሰራጭቶ የሚገኘውን የአማራ ደሃ ገበሬ ላይ ቂማቸውን መወጣት ነበር። በ1885 (እኤአ) «Scramble for Africa» ተብሎ በሚታወቀው የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ጀርመን በርሊን ላይ ስብሰባ አድርገው የአፍሪካ ካርታን ጠረጴዛ ላይ ዘርግተው እንደ ቅርጫ ስጋ አፍሪካን እንደተቀራመቷት በተመሳሳይ ሁኔታ በ1983 ዓ.ም ደርግ ወድቆ ወያኔና ኦነግ የሽግግር መንግስት በጋራ ሲመሰርቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ውክልና (Mandate) ሳይኖራቸው፣ የህዝብ ብዛት፣ የህዝቡን ፍላጎትና ስብጥር፣ አሰፋፈር፣ የተፈጥሮ ወይም ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ስነልቦና፣ ቋንቋ፣ ታሪክ እና የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ከጠመንጃቸው በተገኘ ማናህሎኝነት በፖለቲካ ውሳኔ ኢትዮጵያን ለ14 ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ሽንሸኗት። ወያኔና ኦነግ የመሬት ነጠቃና ቅርምቱን እንደጨረሱ በመቀጠል አዲስ የትምህርት ፓሊሲ በማወጅ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ መመሪያ አወጡ። ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸው መልካም ሆኖ ሳለ በጣፋጭ ማር እንደተለወሰ መርዝ የት/ት አዋጁ ብዙ ችግሮች ነበሩት። በነገራችን ላይ የአፍ መፍቻ እና የክልሉ የስራ ቋንቋ ሊለያይ ይችላል። ወያኔና ኦነግ በዘፈቀደ በከለሉት ክልል ውስጥ ከአንድ በላይ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ሊኖሩ ይችላሉ። በመሆኑም ልጆች በአፍ መፍቻ ወይም በእናታቸው ቋንቋ ይማሩ የሚለው የተባበሩት መንግስታት ህግ እና በክልሉ የስራ ቋንቋ ማስተማር ፈጽሞ የተለያየ ነገር ነው። ለማንኛውም በየአካባቢው የክልሉ የስራ ቋንቋ ይህ ነው ተብሎ በፓለቲከኞቹ በተወሰነው መሰረት የተማሪዎች መማሪያ መፃህፍት በክልሉ የስራ ቋንቋ መዘጋጀት ተጀመረ። በሽግግሩ መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የነበረው የኦነጉ አመራር የነበረው ኢብሳ ጉተማ ነበር። ኢብሳ ጉተማ በ60 ዎቹ በተማሪው እንቅስቃሴ ወቅት የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ “ማነው ኢትዮጵያዊ” የሚል መርዘኛ ግጥም ያቀረበ ነው። ለማንኛውም ኦነግ በሽግግሩ ጊዜ አማራ የጋራ ጠላታችን ነው በማለት ከወያኔ ጋር በፈጠረው ወዳጅነት የኦነግን የፓለቲካ አስተሳሰብ (ርዕዮት) ወደ ህዝቡ ለማውረድና የኦሮሞን ወጣቶች በዘረኝነት፣ በአማራና በኦርቶዶክስ ጥላቻ ለመበከል ተጠቅሞበታል።
በኦነጉ ኢብሳ ጉተማ ይመራ የነበረው የትምህርት ሚኒስቴር የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የተማሪዎችን መማሪያ መፃህፍትና የመምህራንን መመሪያ (Students Text Book and Teachers Guide) እንዲያዘጋጁ ውክልና ለክልሎች ሰጣቸው። በዚሁ መሰረት የክልል የትምህርት ቢሮዎች ካድሬ መምህራንን በመመልመልና ስልጠና በመስጠት በየክልላቸው ለሚማሩ ተማሪዎች የሚያገለግል የሙከራ (Trail Edition) መማሪያ መፃህፍት በክልሉ የስራ ቋንቋ ማዘጋጀት ጀመሩ። ባዘጋጁትም የታሪክ፣ የቋንቋና የጂኦግራፊ (የህብረተሰብ) መፃህፍት ውስጥ በፊት በደርግ መንግስት ታትሞ በነበረው መጻህፍት ውስጥ እንደ አብዲሳ አጋ፣ ዘርዓይ ደረስ፣ አበበ ቢቂላ እና የመሳሰሉ የኢትዮጵያ አርበኞችና እውቅ ሰዎች የተጋድሎ ታሪኮች፣ ስለ አድዋ ጦርነት እና ስለ አቡነ ጴጥሮስ ተገጋድሎ፣ ስለ አጼ ቴዎድሮስ፣ ስለ አጼ ምኒልክ እና ስለመሳሰሉት የሃገር ባለውለታ ጀግኖች ታሪክ፣ ለሃገራቸው ስልጣኔ ስላበረከቱ ታዋቂ ሰዎች፣ ስለ ህዝቡ ወንድማማችነት ወይም ኢትዮጵያዊነትን የሚያስተምሩ ጽሁፎች ከታሪክ፣ ከቋንቋና ከጂኦግራፊ (ከህብረተሰብ) ማስተማሪያ መጻህፍት ውስጥ ለቅመው በማውጣት ነፍጠኛ ይህንን ያንን አደረገ በሚሉ በካድሬዎች በተፈጠሩ አሉባልታ ትርኪ ምርኪ ወሬዎች እና የሃሰት ትርክቶች ሞሏቸው። በርካታ የአካባቢ እና የከተማ ስያሜዎችንም ቀየሩ። የተማሪውን አዕምሮ በእውቀት፣ በፍቅርና በወንድማማችነት የሚያንጽ ሳይሆን ጥላቻን እና ቂምን የሚያስፋፋ ጽሁፎችን በተማሪው መጽሐፍት ውስጥ አካተቱ። በተለይ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በመሳሰሉት ክልሎች በተዘጋጁ የመማሪያ መጻህፍት አማራውን ጠላትና በዳይ አድርገው በመኮነን፣ ጠላታቸው እንደሆነ፣ ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ሃይማኖት መሆኑን፣ የምኒልክ ይህንን ያንን አድርጓል፣ እገሌ የሚባል የአማራ ራስ ወይም የጦር አለቃ እዚህ አካባቢ ጦርነት ከፍቶ ይህንን ጉዳት አድርሷል ወዘተ የሚሉ የፈጠራና የውሸት ትርክቶች ያለ አንዳች መረጃ በተማሪው መፃህፍት ውስጥ አካተቱ። በተቃራኒው ደግሞ እገሌ የሚባል የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የሲዳማ ተዋጊ ወይም አባ ገዳ ነፍጠኛን ተዋግቶ እዚህ ቦታ አሸንፎታል በማለት እራስን የማጀገንና ታሪክን የማዛባት፣ ጥላቻን የሚያስፋፋ ፁሁፎች በተማሪው መፅሐፍት ውስጥ አካተቱ። ባጠቃላይ በወጣቱ ላይ ጥላቻንና በቀልን በመዝራት ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን አስተምረዋል። ኢትዮጵያም ከሰው ልጅ መፈጠር ጀምሮ በሂደት እዚህ የደረሰች የሰው ልጅ መገኛ ሳትሆን ከመቶ አመት እንኳን የማይበልጥ እድሜና ታሪክ የላት፣ ህዝቦቿም ዝምድና፣ የጋራ ታሪክ እና እሴት የሌላቸው ጥርቅም ህዝቦች እንደሆኑ፣ ባንዲራዋም ጨርቅ እንደሆነ ሰበኩ።
ኦነግ በወያኔ ስልጣኑን ተቀምቶ ከሽግግር መንግስቱ ከተባረረ በኋላ በኦነጉ ኢብሳ ጉተማ ተይዞ የነበረውን የት/ት ሚኒስቴርን የተካችው የህወሃት ታማኝ አገልጋይ የምትባለው የብአዴኗ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ነበረች። ገነት ዘውዴ ኦነግ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች በሙከራ (Trail Edition) ስም ጀምሮት የነበረውን ትውልድ አምካኝና ሃገር አፍራሽ የሆነውን የትምህርት ስርዓት (ካሪኩለም) እስከ ዩኒቨርስቲርስቲ ድረስ በመቀጠል አጠናቃ አፀደቀችው። ባጠቃላይ ላለፋት 31 ዓመታት ፍቅርንና አንድነትን ሳይሆን ጥላቻንና በቀልን ተሰብኮ ያደገው ወጣት ትውልድ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ጥቂት የማይባሉት በክልል እና በፌዴራል መንግስት ውስጥ በመንግስት ሃላፊነት ላይ በመስራት ላይ ይገኛሉ። በኢብሳ ጉተማና በገነት ዘውዴ የትምህርት ፓሊሲ የተማረና በዚህ ዘረኛ አፓርታይድ ህገ መንግስት ያደገ ትውልድ እድለኛ ሆኖ ቤተሰቡ ወይም ታላላቆች ካላስተማሩት በስተቀር ከክልሉና ከጎጡ የዘለለ እውቀት የሌለው፣ ነገሮችን አስፍቶ ማየት የማይችል፣ ነፍጠኛ ይህንን ባንዲራ ይዞ ነው የወጋህ፣ የገደለህ እየተባለ በቂም ያደገና፣ አድጎ ለመበቀል፣ መኖሪያ ቤቱ የሆነች ሃገሩን ለማፍረስ ሲዝት የኖረ ብኩን፣ መጻጉ ትውልድ ነው።
ከዚህ በተረፈ “ኢትዮጵያ የብሄረሰብ እስር ቤት ናት”፣ “ማነው ኢትዮጵያዊ” ወዘተ በማለት በጥራዝ ነጠቅ እውቀት ሃገራቸውን ለማፈራረስ የተነሱት ያ- ትውልድ የሚባሉት 60ዎቹ ተማሪዎች የብሔር ጭቆና የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ሃገራችን ያስገቡት ከውጭ እንደ ወረርሽኝ በዓለማችን ሲዛመት ከነበረው ኮሚኒስታዊ የጨቋኝ ተጨቋኝ ርዕዮተ ዓለም እንጂ በተጨባጭ ሃገራችን ውስጥ በወቅቱ የብሔር ጭቆና ስለነበር አይደለም። በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ድንቁርና፣ ያልሰለጠነ የመንግስት አስተዳደር፣ ከትምህርት አለመስፋፋት፣ ካለመማር፣ ካለማወቅ ወይም ካለመሰልጠን የሚመጣ ኋላቀር ባህልና አኗኗር፣ በአንዳንድ የሃገራችን አካባቢዎች ሰውን ለአምልኮት እስከ መስዋት እና አሽከሮች ጌቶቻቸው በሞቱ ጊዜ በህይወት አብሮ የሚቀብር አሰቃቂ ባህሎች የነበሩበት እንጂ ህዝብን ጠላቴ ነው በማለት የዘመተ፣ ዓለምን እንደ ቂጣ ጠፍጥፎ የፈጠራት እስኪመስል ድረስ ሰማዩም ምድሩም የኔ የብቻዬ ነው በሚል የስግብግብ የኬኛ ፓለቲካ እሱና መሰሎቹ ብቻ የሃገሩ ባለቤት ሆነው ሌላውን ህዝብ ግን መጤ፣ ሰፋሪ እያሉ በማሸማቀቅ ደቁሰውና ገድለው መኖር የሚፈልጉ ጠባብ ብሔርተኞች የነበሩበት አልነበረም። ወጣቱ ስለ ራሱ ሃገር የነበረው እውቀትና ግንዛቤ እጅግ ያነሰ እና የተንሻፈፈ በመሆኑ ከውጪ በቃረመው ፀረ ኢትዮጵያ በሆነ አስተሳሰብ ተሞልቶ ሃገሩን ኢትዮጵያን የብሔሮች እስር ቤት፣ ወንድሙን የአማራ ህዝብ ጭቋኝ በማለት እራስን በራስ የማጥፋትና የማዋረድ ዘመቻ ከፈተ። የብሔር ጭቆና ያለው ድሮ ሳይሆን ዛሬ ህዝብን ጠላታችን ነው በማለት ማኒፌድቶ ፅፈው፣ በሃሰት ሃውልት አቁመው ጠላታችን የሚሉትን የአማራ ህዝብን ነፍጠኛ የሚል የኮድ ስም ሰትተው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሚፈጽሙበት በዚህ ወቅት ነው። የብሔር ጭቆና ያለው ቀድሞ በወያኔ/ ኢሃዴግ አሁን ደግሞ በተርኛው ኦህዴድ/ ኦነግ ብልጽግና አገዛዝ ዘመን ህዝብን ጠላት ያደረጉ ጽንፈኛ የፓለቲካ ድርጅቶች የመንግስትን ስልጣን ይዘው ሃገር በሚያምሱበት በዚህ በቋንቋ ላይ በተመሰረተ አፓርታይድ የጎሳ ፌዴራል ስርዓት ነው።
በመሆኑም ዛሬ ባለንበት ጊዜ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሚናገሩት ቋንቋ፣ በብሔር ማንነታቸው አማራ ነህ፣ ጌዶ ወይም ጋሞ ወይም ሌላ እየተባሉ በሚፈናቀሉበት፣ ዜጎች በሃገራቸው ላይ መጤ፣ ሰፋሪ እየተባሉ በሚሸማቀቁበት፣ ክልላችሁ ስላልሆነ በሚል የመምረጥና የመመረጥ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተነፍጓቸው በሃገራቸው ላይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በሚቆጠሩበት፣ ቋንቋችንን አትናገርም፣ የኛ ብሔር አይደለህም በሚል ምክንያት ሰውን ያለ ጥፋቱ ተዘቅዝቆ በሚሰቀልበት፣ በሚፈናቀልበት እና የዘር ጭፍጨፋ በሚፈጸምበት በዚህ የጎሳ ፌዴራል ስርዓት ነው የብሔር ጭቆና ስጋ ለብሶ ቆሞ ሲሄድ የሚታየው። በራስ ሃገር ላይ፣ አባቶችህ የህይወት ዋጋ ከፍለው በነጻነት ባቆዩዋት ሃገርህ ላይ ያንተ ክልል አይደለም ወደ ክልል ሂድ እየተባልክ ስደተኛ ከመሆንና ከመገለል በላይ የከፋ የብሔር ጭቆና የለም። ዓለም ሰለጠነ በምንልበት በዚህ ዘመን አልተማሩም የሚባሉት፣ የኮሌጅንና የዩኒቨርስቲ ደጅ ያልረገጡ ኋላቀር ፊውዳል ተብለው ሲሰደቡና ሲገደሉ የነበሩት ያላደረጉትን ዛሬ ግን ተምረናል የሚሉን የኦነግ እና የህወሃት ዶክተሮች ማኔፌስቶ ጽፈው፣ ወጣቱን አደራጅተውና አስታጥቀው ከብሔር ጭቆናም በላይ በንጹሃን ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ እያየን ነው።
ለኦሮምኛ ቋንቋ መጻፊያነት የላቲንን ፊደል (A, B, C . . ) እንዲሆን በኦነግ የተወሰነው በዚሁ የሽግግር መንግስት ወቅት ነበር። አማርኛ ቋንቋ የግዕዙን ፊደል ለራሱ በሚስማማው መንገድ አስተካክሎ እንደተጠቀመበት ሁሉ ለኦሮምኛም በተመሳሳይ መንገድ አስተካክሎ መጠቀም ይቻል እንደነበር የቋንቋ ምሁራን ያስረዳሉ። ነገር ግን ኦነጋውያን የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሃብት (ቅርስ) የሆነውን የግዕዝ ፊደል የአንድ የአማራ ብሔር ብቻ በማድረግ ጥላቻ በወለደው በፖለቲካ ውሳኔ ባህር ማዶ ተሻግረው የላቲንን ፊደል ከፈረንጆች በመዋስ ለኦሮምኛ ቋንቋ መፃፊያነት ተጠቀሙበት። ለዚህም የሰጡት ምክንያት የላቲን ፊደል ተጠቃሚ ከሆኑት ከሶማሌና ከኬንያ ጎረቤቶቻችን ጋር ያቀራርበናል፣ የአውሮፓን ቴክኖሎጂ ያስገኝልናል የሚል ነበር። ይህን ማለታቸው በሌላ በኩል ለዘመናት አብረውት ከኖሩትና በደም ከተሳሰሩት ከቀሪው የኢትዮጵያ ወገናቸው ለመነጠል መፈለጋቸውን ከመጠቆሙም በላይ በተለይም ኦሮምኛ ተናጋሪውን ወጣቱን ትውልድ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በመነጠል የእነሱን ፓለቲካና የሃሰት ትርክት እየጠቀጠቁ ለማሳደግ አመቺ ስለሆነላቸው መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ሁኔታ የዓዕምሮ እጥበት እያደረጉ በጥላቻ ያሳደጓቸው ወጣቶች በቄሮና በኦነግ ሸኔ ስም በንፁሃን አማራዎች ላይ ያደረሱት የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ፣ ማፈናቀል እና የንብረት ውድመት ማድረሳቸው፣ የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ በመንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በተፈናቃዩ መሬት ላይም ገዳይ ቄሮዎችን ማስፈራቸው፣ ከወንጀለኞች ጎን በመቆም የተከበረውን የሰው ልጅ ህይወት ከችግኝ በታች በማድረግ በንፁሃን ሞትና እንግልት ማላገጣቸው ምን ያህል ጥላቻው እና ስርዓት አልበኝነቱ በኦሮሚያ ክልል እንደተስፋፋ የሚያሳይ ነው። (የላቲንን ፊደል ለኦሮምኛ ቋንቋ ከመጠቀም ጋር በተለይም ከስነ ልሳን ጋር በተገናኘ የግል ግንዛቤን ለማስፋት “ውይይት Dialogue” በሚል ርዕስ የአ/አ/ዩ መምህራን ማህበር 3ኛ ሴሪ፣ ቅፅ 1፣ ቁ1 በመጋቢት 1984 እትም “ስርዓተ – ፅህፈት” በሚል በበባዬ ይማም የቀረበ ፅሁፍ ማንበብ ይቻላል።)~
7. ማጠቃለያ፣
ሲጀመር የኦነግ ፖለቲካ በአሉባልታ፣ በጥላቻና በክህደት ላይ የተመሰረተ ነው። የኦነግ እና የህወሃት የጥላቻና የበቀል ፖለቲካ ህገ መንግስት ተቀርጾለት ሃገር እየተመራበት ይገኛል። ይህን የዘር ፖለቲካ (tribalism) ወደትውልዱ ለማጋባት ተብሎ በወያኔና በኦነግ አዲስ የትምህርት ስርዓት (ፖሊሲ) ተቀርጾ በተማሪው መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ የጥላቻ ሃውልት ተስሎ፣ የአባቶችህ ሃገር የኦሮሚያ ካርታና ወሰን ይህ ነው፣ እገሌ ጠላትህ ነው ተብሎ የተነገረው ትውልድ አድጌ፣ ነፍጠኛን ተበቅዬ፣ ኢትዮጵያን አፈራርሼ፣ ባንዲራዋን ረግጬ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ሰፋሪ በማለት አፈናቅዬ፣ ወዘተ ወዘተ ቢል ለዚሁ የተፈጠረ ማመዛዘኛ ህሊና የሌለው ሮቦት ስለሆነ ሊያስገርም አይገባም። በመሆኑም ኦሮምያ በሚባለው አፓርታይድ ክልል ውስጥ ህግና ሞራል የማይዳኘው፣ ፈራሂ እግዚአብሔር የሌለው ስርዓት አልበኛ መንጋ ትውልድ ፈጥረዋል። በመሆኑም በኦነግ አስተምህሮ የተጠመቁ የኦሮሞ ብሔርተንኝነትን የሚያቀነቅኑ ልሂቃን ክፋትን፣ ጥላቻን ውሸትን፣ ክህደትን፣ ቂም በቀልና፣ ጭካኔን የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይል ለማስፈጸም ይጠቀሙበታል። ሃገር በመምራት ላይ የሚገኙ የኦህዴድ/ ብልጽግና ባለስልጣናት ከላይ እስከ ታች ድረስ የፖለቲካ እውቀታቸው የተቀረጸው አንደኛ ከዚሁ ከኦነግ የበቀል እና የጥላቻ ስሁት አስተምሮ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ወያኔ ስልጣን ላይ እያለ ከምልመላ ጀምሮ በስልጠና እና በግምገማ የአማራንና የኦርቶዶክስ ጥላቻን እየጋተ ያሳደጋቸው፣ በየመድረኩ አማራን በመሳደባቸው፣ በማፈናቀላቸውና በመግደላቸው ሹመትና ስልጣን የተስውጣቸው ናቸው። ሃገር በጥላቻና በቂም አይመራም። መጀመሪያ ህዝብ ለማስተዳደር ከክፋትና ከአድልዎ የጸዳ ቅን ልብ ያስፈልጋል። የደሃ ሞትና እንግልት ግድ የማይሰጠው ቂመኛና አላጋጭ፣ ለውጥ መጣ ሲባል አደባባይ ወጥቶ የደገፈውን ህዝብ ቀን አይቶ የሚከዳ፣ በጨነቀው ጊዜ ከወያኔ ያስጣለውን ፋኖን የካደ ውለታ ቢስ፣ ቁማርተኛ መንግስት ህዝብን የመምራት ሞራል የለውም። እንደ እውነቱ ከሆነ ወያኔና ኦህዴድ የተጋጩት በርዕዮተ ዓለም ልዩነት ወይም ኦህዴድ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ህወሃት የሚፈጽመው እስርና ግድያ ተቆርቁሮ ሳይሆን በጥቅም በተለይም በአንድ ጊዜ ቢሊየነር ሃብታም በሚያደርገው በአዲስ አበባ እና በዙሪያው በሚደረግ በመሬት ሽያጭ (እነሱ እንደሚሉት በኪራይ ሰብሳቢነት) እንደሆነ የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ።
“በራስህ ሊደረግብህ የማትፈልገውን በሌላ ሰው ላይ አታድርግ”መጽሃፉ እንዲል፣ መብትን ለማስከበር የሌላውን መብት መግፈፍ፣ ከዛም አልፎ የንፁሃንን ደም በግፍ ማፍሰስ ወንጀልም፣ ሃጢያትም ነው። እራስን በራስ ማስተዳደር ሌሎች ማህበረሰቦችን እኔን ካልመሰላችሁ በማለት በመግደልና በማፈናቀል መሬታቸውን መቀማት ማለት አይደለም። የመንግስት ስልጣን በአሉባልታ ፖለቲካ፣ በትርክት፣ በበቀልና በጥላቻ የሚመሩ የኦህዴድ/ ኦነግ የብልጽግና ባለስልጣናት ህዝብን ማገልገልም ሆነ ማሻገር አይችሉም። መጀመሪያ ህዝብ ለማስተዳደር ከእልህና ከበቀል የጸዳ ቅንና የተረጋጋ ስብእና ያስፈልጋል። ይሁም እንጂ ኦነጋውያን የውሸት ታሪክ ፅፈው የኦሮሞን ወጣት አነሳስተውና ህዝቡን አሳስተው በጨበጣ ሃገራችንን ቀምተው ስር እንደሌለው እንጉዳይ ነቅለው አውላላ ሜዳ ላይ ሊጥሉን ተነስተዋል። በቡራዮ፣ ለገጣፎና በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ወታደራዊ ካምፖችን በመገንባት ያሰፈሩትን የኦሮሚያ ፖሊስ እና ልዩ ሃይል አዲስ አበባ ዘልቆ በማስገባት በተለያየ ጊዜ ህዝቡን በማሸበር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ሳይቀር እየገቡ የንፁሃንን ደም በጥይት እሩምታ ማፍሰስና ያለፍርድ ቤት ማዘዣ ነዋሪውን እያፈኑ በመሰወር ስርዓት አልበኝነትን በሃገሪቷ እያስፋፉ ይገኛሉ። ብልጽግና ኦህዴድ በሴራና በበቀል የተሞላ፣ የአማራ ጥላቻ ከውስጡ አልወጣም ብሎት የሚሰቃይ የወያኔና የኦነግ የበኩር ልጅ ነው። በለውጥ ስም አስመራ ድረስ ሄደው አምጥተው ባደራጁት ኦነግ ሸኔ በሚባለው አሸባሪ የኢንተር ሃሞይ ቡድናቸው በአማራ ህዝብ ላይ ናዚዎች በይሁዶች ላይ ከፈጸሙት ጭካኔና ግፍ የማይተናነስ የዘር ማጥፋት ፈጽመዋል፣ አስፈጽመዋል። በመሆኑም ከተዛባ የኦነግ የታሪክ ትርክትና የነቀዘ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተቀረጸው ኦነጋዊው የኦህዴድ/ ብልጽግና መንግስት በስልጣን ዘመኑ ለፈጸመው ወንጀል በህግ መጠየቅ የሚገባው ነው። ሃገራችን እንድትቀጥል በኢትዮጵያ ምድር ስቃይና መከራ ያመጣ ለሰላማችንና አብሮነታችን ጠንቅ የሆነ ይህ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የጎሳ ፌዴራል ስርዓትና ህገ መንግስት እስከ ግሳንግሱ አስወግዶ በአዲስ ዘመኑን በዋጀ ስልጡን ስርዓት መተካት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሃገራችንን እንወዳለን የምንፈል ሁሉ ፋሽስት ህወሃት እና ናዚ ኦነግ ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያና የመን ሳይበታትኗት፣ እኛንም ስር እንደሌለው እንደ እንጉዳይ ነቅለው ሳይጥሉን ወገባችንን ታጥቀን ዋጋ እንደከፈሉልን አባቶቻችን እኛም በተራችን ፋሽስት እና የናዚ ተላላኪዎችን ብልሃትን በተላበሰ አርበኝነት ነጻነታችንን በትግላችን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ምንጭ፣
1. J.L Krapf A Personal Portrait in Memory of His Entry to East Africa in 1844 (Africa Journal of Evangelical Theology) pdf
2. “Travels, Researches and Missionary Labours During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa” pdf
3. የህይወት ተሞክሮ፣ የግል ግንዛቤና ምልከታ፣
http://amharic-zehabesha.com/archives/174751