“ለአቶ ግርማ የሽጥላ የፊልድ ማርሻል ማዕርግ ቢሰጠው አያንሰውም” – አብይ አህመድ
አቶ ግርማ ሠሞኑን ብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሠባ ላይ የአማራ ፋኖን ህግ በማስከበሩ ሂደት ውስጥ የክልሉ ብልፅግና የተጠቀመበትን የአመራር ጥበብና የተገኘውን ውጤት የማእከላዊ መንግስት የድጋፍ አቅጣጫ፣ የክልሉ አመራር ቅንጅትና መናበብ፣ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የአመረራ ቅብብሎሽና ፍሠት የህዝቡ ድጋፍና አጋርነት፣ የመረጃ ስረአቱ ፍሠትና ተአማኒነት የሁሉም መስተጋብር አማራ ክልል የማንም ጋጠ ወጥና አጉራ ዘለል አሸባሪ ቡድን መፈንጫ እንዳይሆን ማድረግ አስችሏል ብሏል።
በዚህም “ክልሉን አስተማማኝ ሠላም የሠፈነበት ክልል ማድረግ ተችሏል” የሚል ሪፖርት በማቅረቡ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝቷል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል። አብይ አህመድ “አያችሁ አሁን አማራ ክልል እንደ እነ ግርማ አይነት ጀግናና ደፋር መሪዎች እናገኛለን ብላችሁ አስባችሁ ታውቁ ነበር ወይ?” ብሎ በመጠየቅ ነባርና አሮጌ አመራር ጠራርገን በማባረራችን የተገኘ ውጤት ነው በማለት አድናቆት አክሎለታል።
እንደ አቶ ግርማ የሽጥላ ያሉ ጀግና መሪዎችን መሸለም እና እውቅና መስጠት አለብን። የብልፅግና አንዱ ልዩነት ጀግኖቹን መሸለም መቻሉ ነው። የዛሬን የብልፅግና ጀግና ሣትሸልም የነገ አድስ የብልፅግና ጀግናን ማባዛትና መፍጠር አትችልም የሚል ድንፋታና ፉከራ የበዛበት ምስጋና ከቀረበለት በኋላ የአማራ ክልልን የሠላም ማስከበር ተሞክሮ ተቀምሮ ሁሉም ክልል እንድንጠቀምበት ትዛዝ ተላልፏል።
ከዚህ ምስጋና በኋላ የሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ብልፅግና ገዳይ ነው፣ አማራነት አይገደል፣ አብይና ብልፅግና ይልቀቁ የሚል ሠልፍ በማካሄዳቸው 8 (ስምንት ) ሠላማዊ ሠዎችን ግርማ የሽጥላ ትዕዛዝ ሠጥቶ አስገድሏል።
ግረማ ተወክሎ የሄደው ከዚሁ ሰሜን ሸዋ አካባቢ ነው። በማንኛውም መስፈርት አማራን ከገደልክ እና ካስገደል ብልፅግና ከፍ ያለ ሽልማት ይሠጥሃል። አማራ ለምን ይሞታል ብለህ ከጠየቅክ፣ ካለቀስክ አልቃሻ ተብለህ ወደ ከርቸሌ ትወርዳለህ። እውነታው የኸው ነው።
ፈለገ ግዮን
shewa-robit-killing-and-injuring-many/