April 5, 2013
23 mins read

የአርሰናል ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? – የአረብ ከበርቴዎች አነጣጥረውበታል

(ልዩ ዘገባ)
ለመግዛት የቀረቡት ከበርቴዎች እነማን እንደሆኑ አይታወቅም፡፡ ኩባንያዎቻቸው እነማን እንደሆኑ ለመናገር ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ነገር ግን የዓረብ ባለሀብቶች መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎችን ያቀፈ ህብረት (consortium) መሆኑም ምስጢር አልሆነም፡፡ በሪከርድ ዋጋ አርሰናልን ለመግዛት ፍላጎት መኖሩ የተረጋገጠው እነዚሁ አካላት የአሁኖቹ የክለቡ ባለቤቶች በእምቢታ ሊተዉት የማይችሉትን ሂሳብ ለመክፈል እንዳሰቡ ካሳወቁ በኋላ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜናውን ይፋ ያደረገው ሰንደይ ቴሌግራፍ የተባለው ጋዜጣ ነው፡፡ የወሬውን መሰማት ተከትሎ ሌሎቹ ሚዲያዎችም እንዲሁ የየራሳቸውን ዘገባዎችን በማከል የመድፈኞቹ ክለብ እንደማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ በአረብ ከበርቴዎች እጅ ሊወድቅ እንደሚችል አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ክለባቸው በታላላቅ ተጨዋቾች እንዲጠናከር የሚፈልጉ ደጋፊዎችን ቀልብ የሚስብ ጉዳይ ነው፡፡
በ1910 የአርሰናል እግርኳስ ክለብ በከባድ ኪሳራ በመመታቱ ለመፍረስ ተቃርቦ ነበርር፡ ቀውጠውን ጊዜ ያሳለፉት ሄንሪ ኖሪስ የተባሉት ባለሀብት ሲሆኑ የክለቡን መቀመጫ ወደ ሃይበሪ በማምጣት ነፍስ ዘርተውበታል፡፡ ለ19 ዓመታት በሊቀመንበርነት ካገለገሉ በኋላ ኖሪስ ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ፡፡ ሳሙኤል ሄልውድ እና ሰር ብሬስዌል ስዊዝ የተባሉ ባለሀብቶች ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላይ የአርሰናልን ባለቤትነት ይዘው ዕድሜያቸው ሲገፋም ለቤተሰቦቻቸው አውርሰውታል፡፡ በ1983 የአርሰናልን 16 በመቶ ድርሻ የገዘት ዴቪድ ዴይን በ1990ዎቹ ድርሻቸውን ወደ 42 በመቶ አሳደጉ፡፡ ዴይን ከለቀቁ በኋላም ስታን ክሮኤንክ የተባሉት አሜሪካዊ ቱጃር ቀስ በቀስ የባለቤትነት ድርሻቸውን ወደ 64.44 በመቶ ከፍ አደረጉ፡፡ ሬድ ኤንድ ኋይት ሆልዲንግ በሚል የሚጠራው የኡዝቤክስታዊው ከበርቴ ኩባንያ ደግሞ 29.11 በመቶ ያህሉን በባለቤትነት መያዝ ቻለ፡፡ የተቀሩት አነስተኛ ድርሻዎች ተፅዕኖ ሊፈጥሩ በማይችሉ ሰዎች እጅ ላይ ይገኛል፡፡
አርሰናልን ለመግዛት የሚፈልግ ባለሀብት ሁሉ መደራደር ያለበት ከሁለቱ ከፍተኛ ባለድርሻዎች በተለይም ደግ አመዛኙ ባለቤትነት በእጃቸው ላይ ከሚገኘው ክሮኤንክ ጋር ነው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ይፋ በሆነው ዘገባ መሰረት ስማቸው ያለተጠቀሰው አረቦች ከእኚሁ አሜረካዊ ነጋዴ ጋር ኮስታራ ድርድር ለማድረግ አቅደዋል፡፡
ድርድሩ ከመደረጉ አስቀድሞ አረቦቹ ለታላላቆቹ የሚዲያ ውጤቶች በሰጡት መረጃ መሰረት የሚያቀርቡት ሂሳብ የማልኮልም ግሌዘር ቤተሰቦች ማንቸስተር ዩናይትድን ከገዙበት ዋጋ በእጥፍ ይበልጣል፡፡ አረቦቹ አርሰናልን ለመግዛት የሚፈልጉት በከፊል ድርሻ አይደለም፡፡ 100 ፐርሰንት እንጂ፡፡ በማንቸስተር ሲቲ እና በፓራሰን ዠርመ የአቡዳቢ እና ካታር ባለሀብቶች የሰሯቸውንና እያገኙ ያሉትን የህዝብ ግንኙነት ጥቅሞች እነዚህ አረቦች ተረድተውታል፡፡ ስለዚህ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ስም ያለውንና በመላው ዓለም ከፍተኛ ደጋፊዎችን ያፈራውን የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቢገዙ አላማቸውን ለማሳካት እንደሚጠቀሙ ተማምነዋል፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት የአርሰናል እግርኳስ ክለብ ዋጋ ከተመገበት ዋጋ በእጥፍ ሊያቀርቡ ፍቃደኛ መሆናቸውን የተገለፀው ከበርቴዎች ግዢውን ከፈፀሙ የክለቡን የ250 ሚሊዮን ፓውንድ ገደማ ዕዳ በአንድ ጀምበር ከፍለው ያጠናቅቃሉ ተብሏል፡፡ ከዚያም ለታላላቅ ከዋክብት ተጨዋቾች ግዢ ከፍተኛ በጀት በመፍቀድ አርሰናልን በፕሪሚየር ሊጉም ሆነ በቻምፒየንስ ሊግ ላይ የማይጋፉት ሃል ለማድረግ ወሳኙን እርምጃ ይጀምራሉ፡፡ በዓለም እግርኳስ መድረክ ላይ ሃያል እንዲሆን በማስቻል ብቻ ሳይገቱ ደጋፊውም በርካሽ ዋጋ ጨዋታዎችን ይታደም ዘንድ በኢምሬትስ ስታዲየም የመግቢያ ቲኬት ዋጋ በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡ አሁን በስራ ላይ ባለው ዋጋ የአርሰናልን ቲኬት በዓለም ውድ ተብለው ከሚጠቀሱ የስታዲየም መግቢያ ዋጋዎች ተርታ ይገኛል፡፡
የአርሰናልን ሁለት ሶስተኛ ባለቤትነት የያዙት ክሮኤንክ ከሌለው አብላጫ ባለድርሻ ኦሊቨር ኡስማኖቭ ጋር ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል መግባባት የላቸውም፡፡ የሁለቱ ሰዎች አለመግባባት በአርሰናል የቡድን አስተዳደር ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ደጋፊው ያውቃል፡፡ የክለቡ ሙሉ በሙሉ ባለቤት ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ የተዘጋጁት አረቦችም የባለሀብቶቹ አለመስማማት በክለቡ ላይ የፈጠረውን ጥፋት በሚገባ ተረድተውታል፡፡ ስለዚህ ባለቤትነቱን አንድ ማድረግ የከበርቴዎቹ ተቀዳሚ ተግባር ይሆናል፡፡ ይህም በአጠቃላይ የክለቡን አክሲዮኖች በሙሉ ጠቅልሎ የአንድ አካል ንብረት ማድረግ ማለት ነው፡፡
የአርሰናል ባለቤትነት በ62217 አክሲዮን ድርሻዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ክሮኤንክ በባለቤትነት የያዙት 41581 ያህሉን ሲሆን ከሁለት ዓመታት በፊት በወጣለት ዋጋ መሰረት የእያንዳንዱ አክሲዮኖች ዋጋ 17 ሺ ፓውንድ ገደማ ነበር፡፡ የአሁኖቹ አረቦች እንደሚያቀርቡ የተገነረው ዋጋ ለእያንዳንዱ አክሲዮን 20 ሺህ ፓውንድ ገደማ ነው፡፡ በቀላል አገላለፅ ክሮኤንክ የያዙትን 66.83 በመቶ ድርሻ እንዲሸፍኑ የሚቀርብላቸው የመግዣ ዋጋ 830 ሚሊዮን ፓውንድ ይሆናል፡፡ አሜሪካዊው ባለሀብት ተስማምተው ሲሸጡት በድምሩ 830 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፈላቸዋል፡፡ የተጠቀሰውን የባለቤትነት ድርሻ ሲገዙ ያወጡት 430 ሚሊዮን ፓውንድ ገደማ ነበር፡፡ ስለዚህ ከሽያጩ የተታራ 430 ሚሊዮን ፓውንድ ትርደፍ ያገናሉ ማለት ነው፡፡ የኡስማኖቭ ድርሻም በተመሳሳይ ለባለቤቱ ከፍተኛ ትርፍ በሚያሳፍስ መልኩ የመሸጥ እድል ያገኛል፡፡ ጥቃቅን ድርሻዎችን የያዙት ሌሎችም ባለአክሲዮን በይዞታቸው መጠን እያተረፉ አርሰናልን ለአዲሶቹ ባለቤቶች ያስረክባሉ፡፡ በአፕሪል 2011 ዳኒ ፊዝማንና ሌዲኒና ብራስዌል ስሜዝ ድርሻቸውን ለክሮኤንክ ሲሸጡ የአርሰናል ድምር ዋጋ 731 ሚሊዮን ፓውንድ ተገምቶ ነበር፡፡ ሰሞኑን ድምፃቸው የተሰማው ዓረቦች ደግሞ ሊገዙት ያቀዱት በ1.5 ቢሊዮን ፓውንድ ነው፡፡ እውን ጥያቄው በይፋ ይቅረብ እንጂ ክሮኤንክ፣ ኡስማኖቭም ሆኑ መላው የአክሲዮን ባለቤቶች አንፈልግም ሊሉት የማይችሉትን ትርፍ ወደ የኪሳቸው ያስገባላቸዋል፡፡
እንደ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘገባ አረቦቹ ከወዲሁ ከክሮኤንክ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ለመደራደር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የአርሰናልን መቶ በመቶ ባለቤትነት መጠቅለል የዘወትር ህልማቸው የሆነው ኡስማኖቭ ድርሻቸውን ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆኑባች ጊዜያት መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ክሮኤንከ ደግሞ በአረቦቹ ፊት ለዋጋ ድርድር ቃል ሊተነፍሱ የሚያስችል ሁኔታ የሚኖር አይመስልም፡፡ ምክንያቱም የቀረበው ገንዘብ ድርሻቸው ከሚገባው ዋጋ በላይ በመሆኑ ነው፡፡ አስማኖቭ የ29 በመቶ ድርሻ ይኑራቸው እንጂ በአርሰናል ቦርድ ውስጥ አስካሁን ድረስ መቀመጫ አላገኙም፡፡ አረቦቹ ኡስማኖቭ የክሮኤንክ ነገር እንደማይምጠማቸው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ከኡዝቤኪስታኑ ቢሊየነር ጋር ተግባብቶ ለመስራት ይቻላል የሚል እምነት አላቸው፡፡ በአርሰናል ጉዳዮች ላይ የበለጠ የመወሰን መብት እንዲያገኙ የሚፈልጉትና ይህንንም ያላገኙት ኡስማኖቭ ሁኔታም ለአረቦቹ አስቸጋሪ ይሆናል ተብሎ አይገመትም፡፡
የአርሰናል በአረብ ባለሀብቶች መገዛት በቀጥታ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ቢገመትም ከበርቴዎቹ ግን ክለቡን በፈረንሳዊው አሰልጣኝ ስር ለማስኬ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው፡፡ የቬንገርን የእግርኳስ አመለካከት ማጣት ስለማፈልጉ ከክለቡ ጋር እንዲቀጥሉ የአረቦቹ ምኞት ነው፡፡ ሆኖም አርሰናል አሁን የያዘው ጉዞ ለእነዚሁ የመካከለኛው ምስራቅ ሰዎች አርኪ አይደለም፡፡ እያደር የውጤታማነቱ ደረጃ እያሽቆለቆለ መሄዱ ምስጢር አይደለም፡፡ አዲሶቹ ባለሀብቶችም የሚገዙት ክለብ በተለይ በቻምፒየንስ ሊግ ደረጃው ዝቅ ማለት እንደሌለበት ያምናሉ፡፡ እንደዘገባዎቹ ዘንድሮ አርሰናል በሊጉ እስከ አራተኛ ድረስ ካላጠናቀቀ እነርሱም የግዢ እቅድ አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ በቬንገር ስር ላለፉት 16 ዓመታት ከአውሮፓ ትልቁ የክለቦች ውድድር ላይ ያልጠፋው አርሰናል በመጪው የውድድር ዘመንም እዚያው መድረክ ላይ ሊገኝ ይገባል ባዮች ናቸው፡፡ የለንደኑ ክለብ ባለፉት ዓመታት በሊቨርፑል ላይ የደረሰው የደረጃ ማሽቆልቆልን እንዳይደግም የዓረቦቹ አብይ ስጋት ነው፡፡ ‹‹ይህን መሰል ማሽቆልቆል ካሳየ ግን ለግዢው አንጫረትም›› ብሏል- የአረቦቹ ምንጭ ለቴሌግራፍ ጋዜጣ፡፡
‹‹አሁን እያንዳንዱ የአክሲዮን ባለድርሻ ከሚገባው በላይ ትርፍ የሚያገኝበትን ሂሳብ ልንከፍለው ተዘጋጅተናል፡፡ ግዢው ከተፈፀመ በኋላ አርሰናልን በእንግሊዝ፣ በአውሮፓ እና በዓለም ደረጃ ከባድ ተፎካካሪ ለማድረግ የሚያስፈልግ ወጪ ስለሚኖር ለክለቡ ግዢ ከዚህ በላይ ዋጋ መጨመር የማይቻል ነው›› ብሏል ምንጩ፡፡ ክለቡ ከዋንጫ ጋር የመራራቁ ነገር ደጋፊዎችን ክፉኛ ቅር ማሰኘቱ የአደባባይ ምስርጢር ነው፡፡ የአረቦቹ ጥያቄ ደግሞ ከዋክብት ተጨዋቾቹን በመሸጥ ውጤታማነቱን በማጣቱ የተከፉትን ደጋፊዎች ድጋፍ እንደሚያገኝ ይታመናል፡፡ ‹‹የትኛውም ትልቅ ክለብ ስምንት ዓመታት ሙሉ ያለዋንጫ መጓዝ አይችልም፡፡ ለስምንት ዓመታት ዋንጫ ያላመጣ አሰልጣኝ፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንም ቢሆኑ በኃላፊነት ላይ እንዲቆዩ የሚፈቅድ ትል ክለብ የለም›› በማለት ምንጩ አስተያየቱን አክሏል፡፡ ሀሳቡ የተሳሳተ አይመስልም፡፡
ቬንገር ከአዳዲሶቹ ባለቤቶች ጋር አብረው ይስሩ አይስሩ በኋላ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ግዢው ከተፈፀመ አንዳንድ ክለቦች በሀብታም ባለቤቶች ቁጥጥር ስር እየገቡ ‹‹የፋይናንስ ብልግናን›› ፈፅመዋል በማለት በይፋ ለተቹት ቬንገር በካታር ባለሀብቶች ባለቤትነት ስር ከሚገኘው ፓራሰን ዠርመ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው መነገሩ ግራ ያጋባል፡፡
የቬንገር የአሁኑ ኮንትራት በጁን 2014 (በሚቀጥለው ዓመት ክረምት) ይጠናቀቃል፡፡ ቡድኑ እያደር በመዳከሙ ምክንያት ስራቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ጫና ቢያይልባቸው ቬንገር ከአርሰናል የሚለዩ አይመስሉም፡፡ ይህን ያሉት ቬንገር በካታር ባለሀብቶች ባለቤትነት ስር ከሚገኘው ፓሪስን ዠርም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው መነገሩ ግራ ያጋባል፡፡
የቬንገር የአሁኑ ኮንትራት በጁን 2014 (በሚቀጥለው ዓመት ክረምት) ይጠናቀቃል፡፡ ቡድኑ እያደር በመዳከሙ ምክንያት ስራቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ጫና ቢያይልባቸው ቬንገር ከአርሰናል የሚለዩ አይመስሉም፡፡ አርሰናል እስከ አራተኛ ድረስ ባያጠናቅቅ እንኳን በቦታቸው ላይ ይቀጥላሉ የሚለው ግምት ሚዛን ይደፋል፡፡
አረቦቹ ከበርቴዎች ደግሞ አርሰናል እስካሁን በቬንገር ስር በተራመደበት የፋይናንስ አስተሳሰብ እንዲቀጥል አይፈልጉም፡፡ ክለቡ ገንዘብን እንዲሰራ ሳይሆን ኢንቨስት እንዲያደርግ እንደሚፈልጉ ከወዲሁ ግልፅ አድርገዋል፡፡ እንደ ባለሀብቶቹ እምነት አርሰናል የተፎካካሪነት ጥንካሬውን ያጣው በክሮኤንክ እና በወንድ ልጃቸው ጆሽ ባለቤትነት ስር በመቆየቴ ነው፡፡ አሜሪካዊያኑ ስለ እግርኳስ ያላቸው ግንዛቤ ደካማ መሆኑን ለአርሰናል የሜዳ ላይ ስኬት ደንቃራ ሆኗል በውል ያምናሉ፡፡ የአረበቹ ምንጭ አክሎም ‹‹የአርሰናል ትልቁ ችግር ግልፅ የሆነ እና ችግርን የሚገልፁለት ባለቤት አለመኖሩ ነው፡፡ በክለቡ ማኔጅመንት ላይ የሚገኙ ሁሉ የሚቆጣጠራቸው አካል የለም›› ይላል፡፡ ክሮኤንክም ሆኑ ልጃቸው ከክለቡ ገንዘብ እንጂ ውጤታማነት ላይ ደንታ ስለሌላቸው መሆኑን አረቦቹ ይጠቁማሉ፡፡ የኤምሬትስ ስታዲየም ታማኞች ክሬኤንከ ለአርሰናል የሚገባውን ትኩረት አለመስጠታቸውን በተቃውሞ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው፡፡ በደጋፊ ማህበራት ልሳን ሚዲያዎችም ክሮኤንክ ተወዳጅ አይደሉም፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለውና በክሮኤንክ ተፅዕኖ ስር ያለው ቦርድ ጥንካሬና የአስተዳደራዊ ብቃት እንደሚያንሰው ደጋፊዎችም ያምናሉ፡፡
ቺፍ ኤግዜኪዩቲቭ ኢቫን ጋዚዲስ ለቬንገር ያላቸው ክብር ከመጠን ያለፈ ነው በሚል ይታማሉ፡፡ ቬንገር ደግሞ በክለቡ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ደጋፊዎች ክሬኤንክ ራሳቸውን የሚደብቁ ሰው ናቸው ይሏቸዋል፡፡ አለመታየታቸውና ከፍተኛውን የአክሲዮን ድርሻ ከያዙ በኋላ ከአነርሱ (ደጋፊዎች) ጋር አለመገናኘታቸው በደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡ በቅርቡ ከባየርን ሙኒክና ከአስቶን ቪለ ጋር በኢምሬትስ ባደረጓቸው ግጥሚያዎች ላይ ታይተዋል፡፡ ከክለቡ ይህን ያህል ርቀው መኖራቸው በደጋፊዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የሰሉ ትችቶች እንዲሰዘርባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡
አርሰናል በገቢ ራስን የመቻል ሞዴልን እንደሚከተል ምስጢር አይደለም፡፡ ክለቡ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲን የማሳሰሉት ክለቦች በባለቤቶቻቸው ድጎማ የሚንቀሳቀሱበትን ሞዴል አይቀበልም፡፡ በተለይ በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፋይናንስ ስፖርታዊ ጨዋነት ደንብን ተከትሎ ክለቡ አሁን የተያያዘው መንገድ አዋጪ መሆኑን ያምናል፡፡ ደጋፊዎች ግን ይህንኑ ሞዴል ይዞ ከቀጠለ ክለቡ የተፎካካሪነቱ ደረጃ እያደር እያሽቆለቆለ በመሄድ ከዚህም በታች ይወርዳል ብለው ይሰጋሉ፡፡
የአረቦቹ የግዢ ሙከራ በስኬት ከተጠናቀቀ አርሰናል ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ እንደሚል አያጠራጥርም፡፡ አርሰናል በአውሮፓ እግርኳስ ላይ ታላቅ ኃይል የማድረጉ የአረቦቹ ህልም ክለቡን በፕሪሚየር ሊጉ ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማንችስተር ሲቲ ጋር እንዲሁም በቻምፒየንስ ሊጉ ከባርሴሎና፣ ባየርን ሙኒክ፣ ሪያል ማድሪድና ፓሪሰን ዠርመ ጋር በብቃት መፎካከር የሚችል ቡድን ከፍተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ይፈልጋል፡፡ እንዲህም ሆኖ የፋይናንስ ስፖርታዊ ጨዋነት ደንቡን ማክበር ይቻላል ብለው ያምናሉ፡፡ አረቦቹ በክለቡ ውስጥ ለዓመታት የሰፈነውን የፋይናንስ መረጋጋት ለማስቀተል ቢፈልጉም በንፉግነት እንዳልሆነ ግን ግልፅ ነው፡፡ S

ምንጭ፡ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 49

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop