January 31, 2022
19 mins read

በፋኖ ደም ሊነግድ የገባው የለንደኑ ወራዳ ፣ ልክስክስ፣ ይሉታቢስና ውታፍ ነቃይ ዲያስፖራ – ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ

መቸም እኔ ዲያስፓራ/Diaspora/ ከሚለው የእንግሊዝኛ የቁም ትክክለኛ ተነፃፃሪ ትርጉም አንፃር የኢትዮጵያው ዲያስፖራ ለየት ያለ ትርጉም ሊሰጠው ይገባል እላለሁ። እንደ እኔና መሰሎቹ በተለይ የእንግሊዙ ዲያስፓራ ልመስገን ፣ ልታይ ልታይ ባይ፣ አሸርጋጅ ፣ጥቅም ፈላጊና ባዶቂጥ ቢባል ደስ ይለኛል።

በሃገሬ አነጋገር “ባዶ ቂጥ” ይቅርታ “ለቋንቋው ገላጭ ቃል” ማለት በአገረ ኢትዮጵያ በምንም ኢንቨስትመንት የማይሳተፍና ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ የማያደርግ ያውም በሚኖርበት እንግሊዝ ሃገር ሰርቶ ደሞዝ ተከፋይ ከመሆን ይልቅ የመንግስት ተጠማኝ ሆኖ የሚኖር ማለት ነው። ወደ ዋናው ነጥቤ ስመጣ ሰሞኑን በጎንደር ከተማ የፋኖ ትውልድ ሃገር በሆነችው የእምነትና የስልጣኔ ፈር ቀዳች ብለን ብምናቆለጳጵሳት ምድር የለንደን ውታፍ ነቃዮችና ዘራፊዎች የሰሩት ስራ በጣም የወረደ ፣ ይሉታ ያጣ፣ ልክስክስና የለማኝነት ባህሪ የተጠናወተው ነበር።

እኛ ስናድግ ስለፋኖ የተዜመልን “ ፋኖ ደስ ይለኛል ሲታጠቅ ማለዳ የሚያበላ መስሎ የሚሸኝ እንግዳ”፣ “ኧረ የፋኖ እናት ታጠቂ በገመድ ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ” በደርግ ስርአት ከመንግስት ጋር በነበረው ፍልሚያ “ ፍኖ ተሰማራ እንደ ኦቺሚኒ እንደ ቸጉቤራ” እየተባለ እየተነቃቃና እየተዜመለት እልፍ አዕላፍ ጀግኖች ወንድሞቻችን ለሃገረ ኢትዮጵያ የወደቁበት፣ የደሙበትና እምቢ ለሃገሬ ብለው የተሰውበት የኢትዮጵያ የጦር ጀግኖች የወል መጠሪያ ስያሜ ነው።

“ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ “ እንዲሉ የለንደኖቹ ልክስክስ ተጠማኝ ዲያስፖራዎች “የድሃ ሙርጥ ከሃብታም ፊት ያብጣል” እንዲሉ ይቅርታ እንደገና ለአገላለፄ ከባለፀጋው አቶ ወርቁ አይተነው ፊት ቀርበው ያደረጉት ፀያፍ ስራ ያቅልሸልሻል።

ነገሩ እንዲህ ነው የማህበረሰብ አንቂውና የበይነ መረብ ተከራካሪው አቶ ሰለሞን ቦጋለ፣ ለሃገሩ ክብር፣ አሸባሪውንና ተስፋፊውን የሕወሃት ትግራይ ቡድን ሊፋለም “ጨርቄን ማቄን” ሳይል ለትግል ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛል። በክብርና በአይዞህ ባይነት ሸኘነው።

ታጋይ ሰለሞን ቦጋለ የኢትዮጵያ መንግስት ለፋኖ ጦር ይህ ነው የሚባል ድጋፍ ሳላላደረገለት ከትግል ሜዳው አፈፍ ብሎ ለአጭር ጊዜ ወደ ሎንዶን ጎራ በማለት የገቢ ማሰባሰቢያ ለማዘጋጀት ወደ ሚኖርባት ታላቅዋ ብሪታንያ ብቅ ይላል።

ይህን ሰናይ ተግባር አማክሮን እኛም “አበጀህ” ብለን “ተፍ ተፍ” አልን ። ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ ይህን ዝግጅት ቀን ተሌት ከአጋር ጓደኞቹ ጋር በመሆን አዘጋጅቶ ለፍሬ ያበቃዋል።

በዝግጅቱ ዕለት የፋኖ አማራ ተከታዮችና ደጋፊዎች ተገኝተው የአቅማቸውን አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፣ የተገፋው ፋኖ ወገናችን ነውና!! ።

እነ ውታፍ ነቃይና የኢምባሲ እሽከሮች እንደዚህ ሞቅ ያለ ገንዘብ ከማይዘረፍበት ዝግጅት መገኘት ለነሱ ኪሳራ ስለሆነ በዝግጅቱ ዕለት አምባሳደሩን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጥሪ ቢደረግም ብቅ አላሉም።

በዕለቱ የምግብ ፣ የመጠጥ ፣ የተገፋውን አማራ ጉዳይ የሚያትት መፅሃፍ ሽያጭ ፣ የሙዚቃ ዝግጅትና የጨረታም ዝግጅት ነበር።

ብዕለቱ ትንሽ ግራ የሚያጋባ በጨረታው ፕሮግራም የተፈጠረው ግብ ግብና ቅጥ ያጣ የተወሰኑ ተጫራቶች መቅበዝበዝ፣ የይታይልኝና ለሚ መለከተው ለአቶ ወርቁ አይተነው የይሰማልኝ ቧረቅታ

ማሰማታቸው ነው። ከጎንደር የሽልማት ስነስርዓት በኋላ ነው ይህ ድብቅ ዓላማቸው የተገለፀልን። አንድ እህታችን አላማውን በማናውቀው አካሄድ በታጋይ ንግስት ይርጋና በባለፀጋው አቶ ወርቁ አይተነው ስም ጨረታውን ታጣጡፈዋለች።

እኛም በጎንደር ለአቶ ወርቁ አይተነው የተበረከተውን የትግላቸውን ጥረት የሚያሳይ ሰራዊቱን ያማከለ ስህል ለማስቀረት “ተፍ ተፍ” እልን ግን “ እነ አጂሬዎች ይህን የጨረታ ሂደት የህልውና የንግድ ጦርነት ጉዳይ አርገውት” እኛም በዝረራ ተሸነፍን።

ከዚያም ጨረታ ያሸነፉት ግለሰብ ከሕዝብ ጋር ተወዳድረው ስለነበር እኛ ፊት ለፊት ስንከፍል ፣ ያሸነፉበትም ገንዘብ ደጎስ በማለቱ “ በሉ ይክፈሉ ያሸነፋችሁትን ገንዘብ?” ብለን ስንጠይቃቸው። “ ወገቤን ፣ በኋላ እንከፍላለን“ አሉ። እኛም “የሃገር ልጅ የማር እጅ” ብለን ያሸነፉትን ስህል “ጀባ አልናቸው”።

ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ ገቢ የሆነውን ገንዘብ አወራርደው ወደ ትግል ግዳጃቸው ይሄዱ ዘንድ የገቢ ማሰባሰቢያው ዝግጅት ካለቀ በኋላ ስንጠይቃቸው። “ዝባዝንኬ ወሬና ምክንያት” አቀረቡ። እስከአሁንም ለፋኖ ድጋፍ ተብሎ ቃል የገቡትን ገንዘብ አልተከፈለም።

በለማተብና አማኝ በሆነው ጎንደር ከተማ እነ አጂሬ ስግብግብ ዲያስፓራዎች ያውም ከንቲባውና ባለፀጋው አቶ ወርቁ አይተነው በታደሙበት ያደረጉት ድፍረት የተሞላበት ሤራ ና የተከናወነው ድራማ “አጃይብ የሃገሬ ሰው የሚያሰኝ ነው” ።

ከዚህ ላይ የኛን ድንጋጤ የጫረው “ወይ ዘድሮ ፣ ጀሮ የማይሰማው ፣ ዐይን የማያየው የለም”ና “ ለወደፊቱ ምን ታሳየን ይሆን” ያሰኘን ታላቁ ምክንያታችን እንደሚከተለው እናሸራሽረዋለን።

ባለፀጋው አቶ ወርቁ አይተነው በፋኖ ስም በጨረታ የለንደን ማህበረሰብ በተገኘበት በአሸናፊነት ተወስዶ የተሸለሙት ወይም የተበረከተላቸው የጀግናው ሰራዊታችንና የእሳቸውን አስተዋፅኦ የሚያመለክተው ስእል እዳው ያልተወራረደ በመሆኑ አንዱ ያስገረመን ትዝብትና ያፈርንበት ነው።

ክቡር አቶ ወርቁ አይተነው የእንዲዚህ አይነቶቹ የስግብግቦች ብሽቅ ስራ የሚያሳፍርና ማንአለብኝነት የተሞላበት መሆኑን አውቀው፣ ለመልካም ስምዎ ሲባል ይህን ቆሻሻ ድርጊት እንዲያወግዙና የሚመለከተው አካል እንዲያውቀው ቢደረግና ግለሰቦቹ መቀጣጫ ቢሆኑ እንላለን።

እንዲህ አይነቱ የብልጣብልጥ ስራ ሊወገዝ ይገባልና።

ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ እውን እንዲሆን የወጡት የወረዱት ሃገረ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ወደ ሃገር ቤት ጎራ ብለዋል።

የሚገርም የክንዋኔው እድምታ ነው፣ ዋናው አዘጋጅ የጎንደር ተወላጅ ጎንደር ከግዳጅ መልስ በከተማው እያለ ፣ እንዲሁም መሰል የፋኖ ደጋፊዎች በአካባቢው የሚገኙ መሆኑ እየታወቀ ዘራፊው፣ አለሁ ባዮ ፣ ድፍረት ቢሱና አይን ያውጣው የለንደን ፍርፋሪ ለቃሚ ዲያስፓራ ሲሸልምና ሲሸላለም ላየ ያሳፍራል።

ለንደን ዮናይትድ ኪንግደም የተዘጋጀው ዝግጅት በለንደን ፋኖ አባላትና ደጋፊዎች መሆኑ እየታወቀ ግለሰቦች እራሳቸው እንዳዘጋጁት አድረገው መሸለማቸውና ጉራ መንዛታቸው በመድረኩ የፋኖ ስም አለመጠቀሱ እውነትም “ፋኖ አመድ አፋሽ ነው። ያሰኛል፣ እውነትም ያማል።

ከሁሉ የሚከነክነው የፋኖ ደጋፊዎችና አባላት እያሉ የለንዶኖቹ የኦዲድ ፣ የቄሮና የአዜማ አባላት በፋኖ ደም መነገዳቸው የምንፋረዳቸው ይሆናል። እውነትም በየዘርፉ ፋኖ ስሙ የማይነሳ መሆኑ በጋራ ጠላቶቻችን የተስማሙበት ጉዳይ መሆኑ ልብ ይሏል ወገን ። እሱን ጊዜ ያሳየናል።

ክቡር አቶ ወርቁ አይተነው ሽልማቱን ሲቀበሉ” ይህ ሽልማት ለጀግናው ፋኖና ለጥምር ሰራዊቱ ለኔ አይገባኝም” ማለትዎ የሚያስመሰግንዎና የእርስዎን ታላቅ ንግግር የምንጋራ በመሆኑ ለጀግናው ፋኖ ለንደን በሚገኙት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስም እንዲበረከት ሁኔታውን ቢያመቻቹ። ካልሆነ ሌላ መድረክ ተመቻችቶ በተገቢው መንገድ የሚመለከተው አካል ቢሸልመዎ የሚል ሃገራዊ የመቆጨትና የእልህ ጥያቄአችን እናቀርብልወታለን።

“እንኳን እቺንና የምን ጠንጋራ እናውቃለን” እንዲሉ እነዚህ አፍረት ቢሶች በጨረታ ሊያስገቡ የሚገባውን ገንዘብ ከእርስዎ ተቀብለው ሊያስገቡ አስበው ከሆነ እኛ እውነተኛ የአማራ ልጆችና የፋኖ ዓላማን ያነገብን ምንም ባለፀጋ ቢሆኑ ከማይመለከተው ገንዘብ አንፈልግም፣ እርማችን ነው።

ክቡር አቶ ወርቁ አይተነው ለእነዚህ የእንግዲህ ልጆችና ለማኞች እንደልማዳቸው ቢደጉሟቸውና ቢቸሯቸው አይከፋንም።

በዚህ አጋጣሚ በተለይ አቶ ወርቁ አይተነውና አቶ በላይነህ ክንዴን የማሳስበው ጉዳይ አለ። እንደምታውቁት በአማራ ክልል በሕውሃት አቀነባባሪነት በጎንደር አማሮችና ቅማንቶች ግጭት ተፈጥሮ መፈናቀል እዳጋጠመ ይታወቃል።

ይህን የተፈናቀለ ወገን መልሶ ለማቋቋም ታላቅ ዝግጅት ተከናውኖ ነበር። የዚህን ዝግጅት ቁመና ያማረና ጠቀም ያለ ገንዘብ ይገኝ ዘንድ እናንተን ባለፀጎች ለሃገራችሁ የአደረጋችሁት ታላቅ እስተዋፅኦ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የበጎ ሰው ተሸላሚ ትሆኑ ዘንድ ጋበዝናችሁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ እውነታና ትውስታ ነው ።

ከብዙ ውጣ ውረድና ፍልሚያ በኋላ ሁሉ ነገር ተሳክቶ ወደ ለንደን ዝግጅቱን ለመታደም ዘለቃችሁ። ለዝግጅት የወጣው ወጭ የናንተን ቸርነትና ድጋፍ በመተማመን የትየለሌ ነበር። እናንተም አላሳፈራችሁንም አቶ ወርቁ አይተነው ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም አቶ በላይነህ ክንዴ የተወሰነ ሚሊዮኖችና በጎንደር ትልቅ ትምህርት ቤት እንደሚያሰሩ ቃል ገቡ። ይህ ቃል የገባችሁት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ በቩዲዮ ተቀርፆ በእጃችን ይገኛል። ከነገ ዛሬ “ቃል ከሚጠፋ ምን ያሉት ይጥፋ” እንዲሉ ምላሽ ብንጠብቅም ከዝግጅቱ አዘጋጅ ከነበረችው ስሟን አልጠቅስም የተሰጠን ምላሽ ባይዋጥልንም የለንደን ማህበረሰብ በየጊዜው እየጠየቀን በመሆኑ የተለመደውን ቀና ምላሻችሁን በጉጉት እስከአሁኗ ደቂቃ ድረስ እየጠበቅን ነው። ለሚመለከተው ለአማራ ክልል የአደጋና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ቃል የገባችሁትን አስገብታችሁ ከሆነ ያስገባችሁበትን የደረሰኝ ወይም የቼክ ኮፒ ብታሳውቁን ወይም ብትልኩልን። ከዚህ ሌላ ለግለሰብ የአዘጋጅ ኮሚቴዎ አባል ቃል የገባችሁትን በእምነት ሰጣችሁ ከሆነ ብታሳውቁን መልካም ነው እንላለን። ከዚህ ሌላ ይህን ቃል የገባችሁትን የገንዘብ ሆነ የአይነት ድጋፍ ላለመስጠት የሚያበቃ በቂ ምክንያት ካለ በሕዝብ ስም እድታሳውቁና እራሳችንን ነፃ እንወጣ ዘንድ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

እኔ አቶ ተዘራ አሰጉ የዚህ ዝግጅት እንዲሳካ ታላቁን ሙያዊ ሚና የተወጣሁት እኔ ነበርኩ ብል ማጋነን እይሆንም። በተለያየ ጊዜ ለኮሚቴ ሊቀመንበሯና ለእነዚህ ባለፀጋዎች ቅርብ ለሆኑ ሰወች አቤት ብልም አመርቂ የሆነ ምላሽ አላገኘሁም።

በዚህ አጋጣሚ የእኔን ስም በዚህ ጉዳይ እያነሳችሁ ለምትከሱ ወገኖቼ “ከደሙ ንፁህ ነኝ” እያልኩ በጋራ ሁነን ይህን ጉዳይ የሚመለከተውን አካል እንድንጠይቅ ከአደራ ጋር አሳስባችኋለሁ።

በመጨረሻ የሰው ልጅ በብዙ ዘርፎች በአምላክ ዕርዳታና ፍቃድ ባለፀጋ ይሆናል ፣ የጥበብ ባለፀጋ ፣ የዕውቀት ባለፀጋ፣ የዕምነት ባለፀጋ ፣የሃብት ባለፀጋ ወ.ዘ.ተ ባለፀጋ ይሆናል።

ኢትዮጵያዊያን የሃብት ባለፀጎችን የማሳስበው የማትፈፅሙትን በስሜት ወይም በይሉኝታ ተነሳስታችሁ ቃል አትግቡ። መርዳት ከፈለጋችሁ ለእይታ ሳይሆን ከአምላክ ጋር ተነጋግራችሁ ከላይ

ከጠቀስኳቸው አምላክ ባለፀጋ ካደረጋቸው ማህበረሰቦች ጋር ተወያይታችሁ ማድረጉ መልካም ሲሆን ከዘራፊ፣ ከልታይ ልታይ ባይና በማህበረሰቡ ጥያቄ ውስጥ ከገቡ ከእየኢምባሲው ከሚግተለተሉ እርሙቻወችና መሰሎች ጋር መዋዋል ትርፉ ቁጭትና እራስን አምላክ ከስጣችሁ ፀጋና ስፍራ ማውረድ ነው እንላለን።

 

ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop