November 22, 2021
10 mins read

ለብሄራዊ ህልዉና አለኝታነት እና ቀጣይነት የዓማራ መደራጀት እና አንድነት “አማራጭ አልባ አማራጭ !!”

የኢትዮጵያ አንድነት እና ህልዎት ዕዉነተኛ መቀጠል ለሚፈልግ ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያዉያን መደራጀት ፣ህብረት እና አንድነት ፈስኃ ነዉ ፡፡

ይሁንና ከዚህ በተቃራኒ ፀረ ኢትዮጵያዉያን የጥፋት እና የሞት ዛር መንፈስ ለሚንጣቸዉ የኢትዮጵያዉያን አንድነት እና ህብረት ማየት ቀርቶ ማሰብ የሚያሰጎራቸዉ ዕዉነተኛ ታሪካዊ እና ቀንደኛ ጠላቶች መሆናቸዉን ነዉ ፡፡

ያለፉት ወደር የለሽ የዜጎች ጀምላ መገለል፣ መፈናቀል እና መገደል ለቡድን እና ግል ጥቅም ስልጣን እና ጥቅም አይቶ ባላየ ሲመለከቱ የነበሩ ዛሬ ላይ ይህን የመሰለ መሪር ግፍ በአገር እና ህዝብ ለዚያዉም በኢትዮጵያ ዕምብርት አካባቢዎች ሲፈፀም እያዩ አገር እና ህዝብ ከጥፋት መዳን የሚችሉት በህዝባዊ የጋራ ፍላጎት እና ህብረት መሆኑን እያወቁ ለመቀበል የሚቸገሩ መኖራቸዉ ለሚረዳ ከህወኃት /ኢህአዴግ የጥገኝነት ቆፈን አለመላቀቅ የዜጎች ሞት እና ስደት የማያሳስባቸዉ በቁጥር የበዙ ዛሬም እንዳለፉት የጨለማ ጊዚያት በጥቅም የቦዘዙ መሆናቸዉን ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያን ህብረት እና አንድነት መኖር እና መጠናከር የሚያተኩሰዉ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ቢምል ቢገዘት ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ድፍን ዓለም የአዞ ዕንባ እንዲለዉ ካልሆነ በቀር እየሞተ ያለ ህዝብ የሞት ዕለት በቀጠሮ ለመያዝ አለሁ ለሚል ከጠላትነት ዉጭ ምንም ሊባል አይችልም ፡፡

በየትኛዉም የሠዉ ልጂ ታሪክ ከመለኮት ቀጥሎ ሠዉ / ዜጎች አገር መስርተዉ ፤ ህግ አዉጥተዉ መንግስት መሰረቱ እንጅ መንግስት ሆነ ፖለቲከኛ ህዝብም ሆነ አገር አልመሰረቱም ፡፡

በተለያየ የጊዜ እና ታሪክ አጋጣሚ የዉጭ እና ዉስጥ ጠላት የገጠማቸዉ ህዝቦችም በህብረት እና በአንድነት በዓለማ ፅናት እና ቁርጠኝነት ጠላቶቻቸዉን ድል አድርገዉ ፣ አንድነታቸዉ አፅንተዉ ፣ አገር መስርተዉ መንግስት አቆሙ እንጅ መንግስት /ፓርቲ አገርም ሆነ ህዝብ አልሰሩም ፡፡

ለዚህም የእኛን አገር የ፭ ዓመት የነጻነት ትግል ወራሪዉን የኢጣሊ እና ጥገኛ ከዳተኞችን ታግሎ ህዝብን ከባርነት ፤አገርን ከቅኝ ግዛት የታደጉት ህዝብ እና ዕዉነተኛ የነጻነት መሪዎች የተቀናጀ ህብረት እና አነድነት እንጅ የነበረዉ መንግስት (ዘዉዳዊ ስርዓት) እንዳልነበር ……ለታሪክ እና ለዓለም ህዝብ ይደር፡፡

እንዲያዉም ከጥቂት ጀግኖች በቀር የዘመኑ የስርዓቱ አቀንቃኞች እና አገልጋይ ባለጊዜዎች የሽሽት እና ዕግሬ አዉጭኝ ጊዜ ነበር ፡፡

የዓረብ ፤እስራኤል፣ የአሜሪካ ፤ኩየባ፤ የአሜሪካ ፤ቬትናም…..ሁኔታ እና የነበረዉን ዕዉነታ ታረክን የኋላ ማየት እና መማር ለኢትዮጵያዉን የሚያዳግት አይሆንም፡፡

በእኛ ዘመንም ከዚህ የተለየ ነገር ለማየት ብንጓጓም አለመታደል ሆኖ አንኳንስ ከህዝብ እና አገር በፊት እኔ የሚል መሪ እና መካሪ ማግኘት ቀርቶ የአገር እና ህዝብ ህልዉና መከበር ወይም መደፈር ከራሱ የግል ጥቀም እና ከብር ጋር ስላለዉ መስተጋብር የሚረዳ ስለመኖሩ ሲታሰብ በተጨባጭ የምናየዉ ነገር የሚያሳዝን እየሆነ መጥቷል፡፡

ኢትዮጵያን አገሬን ለሚሉ መደራጀት እና ህብረት ጠላቶች በአገር እና ህዝብ ላይ ካደረሱት እና እያደረሱ ካሉት መጠነ ሠፊ ስቃይ እና መከራ በላይ የሚያሳስባቸዉ መሆኑን በገሀድ ይስተዋላል፡፡

በተለይም የዓማራ ህዝብ በየትኛዉም የአገራችን የታሪክ አዉድ ከዉጭ እና ከዉስጥ ለሚነሱ ጠላቶች ያለመሪ እና አስተባባሪ ራሱ በፈጠረዉ እና በሚፈጥረዉ አደረጃጀት አገርና ህዝብ መታደጉን ዛሬም መካድ ለሁሉም የመጀመሪያ የዉድቀት እና ጥፋት ምዕራፍ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያዉያን በተለይም የዓማራ አለመደራጀት በመላ አገሪቷ ለደረሱት እና እየደረሱ ላሉት ሠባዊ፣ ቁሳዊ እና ብሄራዊ ምስቅልቅል መንስዔ መሆኑን ለመረዳት የሚከብደን ዛረም ቁጥራችን ብዙ ነገር ግን ሠባዊነታን ያነሰ የትየለሌ ነን፡፡

የዓማራ መደረጃት እና በበሳል አመራር መካተት ለኢትዮጵያ ህልዉና ዋስታና ከመሆኑም በላይ መሰረቱ በአለት ላይ እንደቆመ ቤት የህዝቦች አብሮነት እና አንድነት አብቦ እና ተዉቦ ለዘላለም የሚኖር እንጂ በከንቱ ሽንገላ እንደ አፈር ካብ እየቆየ የሚናድ አይሆንም ፡፡

ነጻ ህዝብ በሌለበት ነጻ አስተሳሰብ ፤ ነጻ አስተሳሰብ በማይኖርበት ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ዕድገት ማሰብም ማለምም በአንድ እጅ እንደ ማጨብጨብ ይሆናል ፡፡”

እናም የኢትዮጵያን እና ህዝቦች በተለይም ዓማራን እና ሁለንተናዊ ማንነት ማጥፋት የጠላት ዕቅድ እና መንገድ ሆኖ ለሩብ ዓመታት የነበረዉን ጥቃት፣ ሞት ፣ዉርደት እና ስደት ዛሬም መቀጠል ኢትዮጵያን ለማጥፋት “ሀ” ዕቅድ ኢትዮጵያዊነትን ( ዓማራነት ) ማክሰም ከሆነ የዓማራ መደራጀት እና ህብረት ለጠላት የሚያም ከሆነ ይህ ኢትዮጵያዊነት የሚያነበንብ ሁሉ ለምን የዓማራ ህብረት እና አንድነት ህልዎት የሚያማቸዉ የቀደመዉ የጥገኝነት እና አድርባይነት አባዜ አልለቀቃቸዉም እንዳማለት ፡፡

የዓማራ ህዝብ ህብረት እና አንድነት ለኢትዮጵያ ህልዉና መረጋገጥ እና መቀጠል አማራጭ አልባ ዕዉነተኛ ወርቃማ አማራጭ መሆኑን ሳይታለም የተፈታ ዕዉነት ነዉ ፡፡

ዘላለማዊ ክብር እና ምስጋና ለዕዉነተኛ የኢትዮጵያ ቁርጥ ልጆች ፡፡”

በሠላም እና መከባበር ለመኖር የመጨረሻዉ አማራጭ ኃይል ነዉ ”

በአንድነት በፅናት ለአንድ ዓላማ ለሚባበር እና ለሚኖር ህዝብ እና አገር የሠላም እና ድል በር ምንጊዜም ክፍት ነዉ ፡፡

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዲሉ ፤ “ኢትዮጵያዊዉ ቢተባበር ጠላት በተገኘበት ይቀበር ፡፡”

የዓማራ ህዝባዊ ሠራዊት (ፋኖ/FANO- Fighter Amhara Nations Organization) መመስረት፣ ህብረት፣አንድነት እና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መንስዔ እና ትንሳዔ መሆኑን መገንዘብ ሳንዘገይ ልንቃትት ይገባል፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳን ጠላትን የማዳን ርካሽ አድር ባይነት በአስተሳሰብም ሆነ ድርጊት በዕዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ሊወገዝ ይገባል፡፡

ብቸኛዉ እና ወቅታዊ ኢትዮጵያን ከፍርሰት ህዝቧን ከሞት እና ስደት መታደግ የሚቻለዉ በዓማራ ህዝባዊ አንድነት እና ህብረት ብቻ ነዉ ፡፡ ለዚህ ነዉ የዓማራ መደራጀት ዓማራጭ አልባ ምርጫ በሌላ አነጋገር ብቸኛዉ እና ሁነኛዉ ኢትዮጵያን ወደ ገናና ማንነት እንዲሁም ህዝቧን ከጥፋት ለመታደግ የዓማራ ክንድ ህብረት እንደ ብረት መጠንከር ፤እንደ ድር መተሳሰር ዕንቀልፍ ለሚነሳቸዉ የዉስጥም ሆነ የዉጭ ጠላቶች ለይኩን የዓማራ ህብረት እና አንድነት ነዉ ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ ”

ማላጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop