ከሃቅ ጋር ፣ እሥከ ቀራኒዮ ወደፊት !! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ከአይሁድ ና ከክርስትና እምነት በፊት አባቶቻችን እንደፈረኦኖች ሥርዓተ ፀሐይን ያመልኩ ነበር ።አክሱም የፀሐይ ምኩራብ ( sun temple ) አንክበርም የህይወት በር ነበሩ ። ( እውነተኛው የአንኮበር ሥም አንክ በር ነው ። አንክ ማለት ህይወት ነው ። አንክ በር ማለት የህይወት በር ማለት ነው ። ) የአንክ ፊደል ምልክት ከላይ ፀሐይ ከታች መሥቀል ቶ ነበር ። አይሁዳውያኑ እና ሮማውያኑ በፀሐይ ሥፍራ ክርሥቶሥን አሥገብተው ቸነከሩት እንጂ ፤ የመሥቀሉን ምልክትነት አልሰረዙትም ። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ከአይሁዳውያን እና ከሮማዊያን ጀምሮ ፣ ከግሪኮችና ከፈርኦኖች በፊት ጀምሮ ከልቡ ሃቅ ያከብራል ። ከልቡ ክህደት ይጠላል ። የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን ያውቃል ። ከኩሽና ከሴም የተቀየጥን እንጂ ፣ ከሰማይ እንዳልወረድን የውቃል ። አሥተዳደጋችን ግን በመቻቻል ላይ ሳይሆን በመበላለጥ ና በመሸናነፍ ላይ ሥለተመሠረተ ፣ በኃይማኖቶችና በቋንቋዎች አጥር ታግዶ ፣ በባላባቶች ዝርፍያ ሥለከረረ ፣ የዛሬዎቹ እንደበቀደሞቹ የመተማመን ጎዶሎዎች ነን ። ፈተናችን የሚመነጨው ከዚህ ከመንፈሥ ጎዶሎነት ነው ። ሰሜነኛው ሆነ ደቡበኛው ፣ የሱማሌው ቤት ሆነ የጋዳ ቤት ፣ ክርስቴያኑ ሆነ እሥላሙ ፣ምሁሩ ሆነ መሀይሙ ፣ ፍም የመሠለው ቀይ ሰው ሆነ ኑግ የመሠለው ሻንቂላ ፣ በተለይ ትንሽ ሥልጣን በቀመሠ ማግሥት ፣ ቶሎ የመካድ ና በትምክህት የመወጠር አዚም ፣ ይጠናበታል እንጂ ፣ በዘር ግንድ አመጣጡ ሁሉም የአንድ እናት ልጅ ነው ። ሠልሥቱ ታላላቅ ሼኮች የምላቸው ታላቁ ሣይንቲሥትና አንትሮፖሎጂስት ሼክ አንታ ዲዮፕ ፣ ታላቁ ባለቅኔ ሼክስፒር ታላቁ ንግርተኛ ( oraculath ) ሼክ ሁሴን ጂብሪል ፣ በጥልቀት ቢያሥተምሩንም ፣ እኛ ከትምክህትና ከከህደት አዚም መገላገል አልቻልንም እንጂ ። ኢትዮጵያዊያን እና ሱማሊያውያን ፣ ኪስዋሂሊያንና ኤርትራውያን ፣ የአንድ እናት ልጆች ነን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ተከበረው ለኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት!!!

( የዓለም ሎሬት ባለቅኔ ፣ የትያትር ደረሲ እና የኢትዮጵያ ቋንቋ ና ባህል ተመራማሪ ፣ ውዱ ኢትዮጵያዊ ፣ ክቡር ፀጋዬ ገ/መድህን ፤ በጦቢያ መፅሔት በቅፅ 13 ቁጥር 1 ፤ ነሐሴ ወር 1997 ። የተወሰደ ፡፡ )

የባለቅኒያችን የዓለም ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ህልፈት ፣ ምናልባትም ለሞቱ አንዱ ምክንያት ፣ የምሁራኑ ና የፖለቲካ ሊሂቃኑ የመተማመን ጎዶለነት ዘመን ተሻጋሪ ሆኖ ፣ ምንም የማያውቀውን ህዝብ ለሞት ሲዳርግ በማየቱ ፣ ይኽንን እኩይ ድርጊት ለማቆም በብዕሩ አብዝቶ ቢታገልም ፣ የኢትዮጵያውያኑ ሰቆቃ ያለማባራቱ ልቡን ክፉኛ ሥለሰበረው ይመሥለኛል ።

ዛሬ በህይወት ቢኖር ኖሮ እጅግ በበዛ ሐዘን ውሥጥ ተዘፍቆ ይህንን አይን ያወጣ የወያኔን እና የልደቱ አያሌውን የመንፈሥ ጎዶሎነት ና ከህደት በቅኔው በረገመ ነበር ። በሐሰት ትርክት ኢትዮጵያን ያህል ትልቅ አገር ለማፍረስ ሲጥሩ ከማየት ፣ የበለጠ ህመም የለምና ጀግናችንን ህመሙ እጅግ ያሰቃየው ነበር ።

ዛሬ ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እናቃለን የሚሉ ግን አንዳችም የማያውቁ ። ከሆድ የዘለለ ህልም የሌላቸው ። በቁሥና ጥለውት በሚሄዱት ንብረት ሠቀቀን የተያዙ ።ለዛም ሲሉ የራሳቸውን ህይወት ብቻ ሣይሆን የሚሊዮን ድሆች ህይወት እንዲገበር የሚያደርጉ ። የህይወት ትርጉሙ ሌሎችን አደኽይቶ መበልፀግ እንደሆነ የሚያሥቡ ። ሥርቆትን ባህል አድርገው ከልጅነት እሥከሽምግልና ሲኖሩ ፈፅሞ የማያፍሩ ። የአገርን ሀብት ወደውጪ በማሸሽ እነሱ እየወፈሩ አገር እየቀጨጨች ሥትሄድ የሚደሰቱ ። በመጨረሻም ያለአንዳች ሥም ተራ ሟች ሆነው የሚቀበሩ መሆናቸውን ፈፅሞ የማያውቁ ። ሲፈጠሩ ሞኝ የነበሩ ሲሞቱም ሞኝ እንደሆኑ የሚሞቱ እንደ አሸን ፈልተው ሲመለከት ፤ “ ምናለ ፈጣሪ ይኽንን የህሊና ቢሱን ና የሞኝን ወያኔንን ድርጊት ሣታሣየኝ ብትገድለኝ ኖሮ ! “ በማለት ፈጣሪን ያማርር ነበር ። ?

ወያኔዎች ፣ “ በተደጋገመ ውሸት ፣የህዝብን ህሊና መቀየርና መንጋ አድርጎ መንዳት ይቻላል ። “ በማለት

ተጨማሪ ያንብቡ:  ክተቱን ክተትበት!  በውጭ አገር የምትኖረው ኢትዮጵያዊ ሆይ እቤትህ ድረስ የመጣውን ዕድል ተጠቀምበት!

፣ ዛሬም በህዝብ ንቀታቸው ገፍተውበታል ። በወኪሎቻቸውም አማካኝነት በከፋፋይ ና ዘረኛ ቅሥቀሣቸው ገፍተውበታል ።

ይኸው ዛሬ በትልቁ አገራቸውና የወያኔ ሰላይ እንደነበሩ ሲወራላቸው በነበሩት ና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በመላሣቸው ሢቆሉት ለሁለት አሥርት ዓመታትት በከረሙት ፣ አቶ ልደቱ አያሌው አማካኝነት በየፋ

ኢትዮጵያ ፈርሳለች አሥብለዋል ። ኢትዮጵያ በልጅነታቸው የደረደሩት ኮርኪ ወይም የጭቃ ቤት መሰለቻቸው እንዴ በዋዛ ና በፈዛዛ የምትፈርስው ? በእርግጥ ይህ ቅዠት የወያኔዎች ብቻ አይደለም ። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በሙሉ እንጂ ።

ይህንን የምንረዳው ፣ በድብቅ መሣሪያ እየሰጡ ፣ የትግራይ ደሃ ገበሬን እና ደሃ የከተማ ነዋሪን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፣ በሆዱ በመግዛት ወደ ጦርነት ሲያሰማሩት ነው ። ነገ የተሻለ ዳቦ ተገኛለህ ። እኛ ሥልጣን ሥንይዝ ወይም ትግራይን ነፃ ሥናወጣ እቤትህ ድረሥ በርገር እናቀርብልሃለን ። እያሉ በመሥከብ ፈፅሞ በማይሆን ተሥፋ ተገፋፍቶ እንዲሰዋ ያደርጉታል ። በርገር ቀርቶ የጠላ ቂጣ እንኳን ሊያቀርቡለት አይችሉም ። የትግራይ ህዝብ ያለ ኢትዮጵያ ህዝብ የሞተ ነው ። ይህ የታወቀ ነው ። የዛሬው ጦርነትም በአበዱ እና ህሊናቸው ማሰብ ባቆመ ግብዝ ጥቂት ባንዳዎች በትህነግ ሥም የሚደረግ በውጪ በዝባዥ ኃይሎች ና በጠላቶቻችን ደጋፍ የሚካሄድ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ጦርነት ነው ።

ጦርነቱ ፀረ ህዝብ ነው ። ጦርነቱን የጀመሩት ፍፁም ማሰብዬ ህሊና የሌላቸው እብዶች ናቸው ። እደግመዋለሁ ጦርነቱን የጀመሩት በትምክህት ያበዱ ጥቂት ህሊና ቢሥ ፀረ ህዝብ ና ፀረ ኢትዮጵያ የሆኑ ኃይሎች ናቸው ።

አቶ ልደቱም ሆነ ወያኔዎች ፣ የአዞ እንባ የሚያነቡ እልም ያሉ ነፍሰ በላዎች ናቸው ። የላሊበላ የወያኔ ሚሽን የልደቱ ሚሽን ነው ። ላሊበላን ጥቂት ወያኔዎች ቢያጠፉት የትግራይ ህዝብ ምህረት የለሽ ቅጣቱን በሥሙ በሚነግደው ትህነግ ላይ ይፈፅማል ። የትግራይ ህዝብ ነፃ ህዝብ ነው ። ምን ያደርጋል ዛሬም ከጠመንጃ አፈሙዝ ፍራቻ ነፃ አልወጣም ። ዛሬ ህዝቡ የወያኔ ባርያ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቋንቋችንን ማጎልመስ ውጤቱ በሁሉም ዘርፍ የላቀ ነው - ባንትይሁን ትዕዛዙ

ይኽ እውነትን የምናስተውለው የአንድ አገር ህዝብ ፤ ያውም የተዛመደ ፣ ደም ፣ አጥንት ና ሥጋው የተዋሃደ ህዝብ ፣ ለእነሱ ሥልጣን ሲል በማያምንበት ጦርነት ተገዶ ተሠልፎ እንደቅጠል ሲረግፍ ቅንጣት ያህል ሐዘኔታ እንደሌላቸው ሥንገነዘብ ነው።

ቅንጣት ያህል ሀዘኔታ እንዳይኖራቸው ያደረጋቸውም ፣ በንዋይ ፍቅር የተደፈነው ልባቸው ነው ። በንዋይ ፍቅር የጨለመው አእምሯቸው ነው ። እነዚህ ሰዎች የሚያሥቡት ነገ ሥልጣን ሲይዙ ሥለሚበቀሉት ሰውና ሥለሚዘርፉት የአገር ሀብት እንጂ ወንድም ወንድሙን በመግደሉ ከቶም አይፀፀቱም ። ያ እንደ ቅጠል የሚረግፈው የትግራይ ህዝብ ፣ አስከሬኑ ተሰብስቦ በሰማዕታት ሀውልት ውሥጥ ለጎብኚ የሚቀመጥ ህዝብ ነው

  • በጉብኝቱም ወቀት ወድማችን የሆነውን የአማራን ህዝብ ወረን ህይወቱን አጥፍተን ንብረቱን እየዘረፍን ሣለ ፣የኢትዮጵያ ዜጎች ተባብረው ባደረጉት የመከላከል ውጊያ የተሰው ታጋዮች ናቸው ። ለማለትም ከወዲሁ የተዘጋጁ አሳዛኝ አእምሮ ያላቸው ግብዞች ናቸው ። ወያኔዎች ፡፡

እነዚህ ግብዞች ከነግብረ አበሮቻቸው መጥፋታቸው አይቀርም ። በኢትዮጵያ የተከሉትም የዘር ና የቋንቋ ፖለቲካ ከሥሩ እንደሚነቀል አምናለሁ ። ኢትዮጵያ በቋንቋ ሥም እየተጠራሩ ጥሬ ሀብቷን ለብቻቸው የሚቦጠቡጦት ፣ ዜጎቿ የበይ ተመልካች የሚሆኑባት ሥርዓት ከመሥከረም 24/2014 /ም በኋላ እንደማይኖር አምናለሁ ። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በእኩልነት የምታገለግል እንደምትሆን ፤የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ እና የልደቱ አያሌው አይነት የብልጣ ብልጥ ፖለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፋይሉ እንደሚዘጋ ፤ ተሥፋ አደርጋለሁ ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሃቅ ሟች ነውና እውነትን ይዞ ከሚመራው መሪ ጋር እሥከ ቀራኒዮ ይጎዛል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share