ከአይሁድ ና ከክርስትና እምነት በፊት አባቶቻችን እንደፈረኦኖች ሥርዓተ ፀሐይን ያመልኩ ነበር ።አክሱም የፀሐይ ምኩራብ ( sun temple ) አንክበርም የህይወት በር ነበሩ ። ( እውነተኛው የአንኮበር ሥም አንክ በር ነው ። አንክ ማለት ህይወት ነው ። አንክ በር ማለት የህይወት በር ማለት ነው ። ) የአንክ ፊደል ምልክት ከላይ ፀሐይ ከታች መሥቀል ቶ ነበር ። አይሁዳውያኑ እና ሮማውያኑ በፀሐይ ሥፍራ ክርሥቶሥን አሥገብተው ቸነከሩት እንጂ ፤ የመሥቀሉን ምልክትነት አልሰረዙትም ። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ከአይሁዳውያን እና ከሮማዊያን ጀምሮ ፣ ከግሪኮችና ከፈርኦኖች በፊት ጀምሮ ከልቡ ሃቅ ያከብራል ። ከልቡ ክህደት ይጠላል ። “የአንድ እናት ልጆች ” መሆናችንን ያውቃል ። ከኩሽና ከሴም የተቀየጥን እንጂ ፣ ከሰማይ እንዳልወረድን የውቃል ። አሥተዳደጋችን ግን በመቻቻል ላይ ሳይሆን በመበላለጥ ና በመሸናነፍ ላይ ሥለተመሠረተ ፣ በኃይማኖቶችና በቋንቋዎች አጥር ታግዶ ፣ በባላባቶች ዝርፍያ ሥለከረረ ፣ የዛሬዎቹ እንደበቀደሞቹ የመተማመን ጎዶሎዎች ነን ። ፈተናችን የሚመነጨው ከዚህ ከመንፈሥ ጎዶሎነት ነው ። ሰሜነኛው ሆነ ደቡበኛው ፣ የሱማሌው ቤት ሆነ የጋዳ ቤት ፣ ክርስቴያኑ ሆነ እሥላሙ ፣ምሁሩ ሆነ መሀይሙ ፣ ፍም የመሠለው ቀይ ሰው ሆነ ኑግ የመሠለው ሻንቂላ ፣ በተለይ ትንሽ ሥልጣን በቀመሠ ማግሥት ፣ ቶሎ የመካድ ና በትምክህት የመወጠር አዚም ፣ ይጠናበታል እንጂ ፣ በዘር ግንድ አመጣጡ ሁሉም የአንድ እናት ልጅ ነው ። “ሠልሥቱ ታላላቅ ሼኮች ” የምላቸው ታላቁ ሣይንቲሥትና አንትሮፖሎጂስት ሼክ አንታ ዲዮፕ ፣ ታላቁ ባለቅኔ ሼክስፒር ታላቁ ንግርተኛ ( oraculath ) ሼክ ሁሴን ጂብሪል ፣ በጥልቀት ቢያሥተምሩንም ፣ እኛ ከትምክህትና ከከህደት አዚም መገላገል አልቻልንም እንጂ ። ኢትዮጵያዊያን እና ሱማሊያውያን ፣ ኪስዋሂሊያንና ኤርትራውያን ፣ የአንድ እናት ልጆች ነን ።
( የዓለም ሎሬት ባለቅኔ ፣ የትያትር ደረሲ እና የኢትዮጵያ ቋንቋ ና ባህል ተመራማሪ ፣ ውዱ ኢትዮጵያዊ ፣ ክቡር ፀጋዬ ገ/መድህን ፤ በጦቢያ መፅሔት በቅፅ 13 ቁጥር 1 ፤ ነሐሴ ወር 1997 ። የተወሰደ ፡፡ )
የባለቅኒያችን የዓለም ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ህልፈት ፣ ምናልባትም ለሞቱ አንዱ ምክንያት ፣ የምሁራኑ ና የፖለቲካ ሊሂቃኑ የመተማመን ጎዶለነት ዘመን ተሻጋሪ ሆኖ ፣ ምንም የማያውቀውን ህዝብ ለሞት ሲዳርግ በማየቱ ፣ ይኽንን እኩይ ድርጊት ለማቆም በብዕሩ አብዝቶ ቢታገልም ፣ የኢትዮጵያውያኑ ሰቆቃ ያለማባራቱ ልቡን ክፉኛ ሥለሰበረው ይመሥለኛል ።
ዛሬ በህይወት ቢኖር ኖሮ እጅግ በበዛ ሐዘን ውሥጥ ተዘፍቆ ” ይህንን አይን ያወጣ የወያኔን እና የልደቱ አያሌውን የመንፈሥ ጎዶሎነት ና ከህደት በቅኔው በረገመ ነበር ። በሐሰት ትርክት ኢትዮጵያን ያህል ትልቅ አገር ለማፍረስ ሲጥሩ ከማየት ፣ የበለጠ ህመም የለምና ጀግናችንን ህመሙ እጅግ ያሰቃየው ነበር ።
ዛሬ ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እናቃለን የሚሉ ግን አንዳችም የማያውቁ ። ከሆድ የዘለለ ህልም የሌላቸው ። በቁሥና ጥለውት በሚሄዱት ንብረት ሠቀቀን የተያዙ ።ለዛም ሲሉ የራሳቸውን ህይወት ብቻ ሣይሆን የሚሊዮን ድሆች ህይወት እንዲገበር የሚያደርጉ ። የህይወት ትርጉሙ ሌሎችን አደኽይቶ መበልፀግ እንደሆነ የሚያሥቡ ። ሥርቆትን ባህል አድርገው ከልጅነት እሥከሽምግልና ሲኖሩ ፈፅሞ የማያፍሩ ። የአገርን ሀብት ወደውጪ በማሸሽ እነሱ እየወፈሩ አገር እየቀጨጨች ሥትሄድ የሚደሰቱ ። በመጨረሻም ያለአንዳች ሥም ተራ ሟች ሆነው የሚቀበሩ መሆናቸውን ፈፅሞ የማያውቁ ። ሲፈጠሩ ሞኝ የነበሩ ሲሞቱም ሞኝ እንደሆኑ የሚሞቱ እንደ አሸን ፈልተው ሲመለከት ፤ “ ምናለ ፈጣሪ ይኽንን የህሊና ቢሱን ና የሞኝን ወያኔንን ድርጊት ሣታሣየኝ ብትገድለኝ ኖሮ ! “ በማለት ፈጣሪን ያማርር ነበር ። ?
ወያኔዎች ፣ “ በተደጋገመ ውሸት ፣የህዝብን ህሊና መቀየርና መንጋ አድርጎ መንዳት ይቻላል ። “ በማለት
፣ ዛሬም በህዝብ ንቀታቸው ገፍተውበታል ። በወኪሎቻቸውም አማካኝነት በከፋፋይ ና ዘረኛ ቅሥቀሣቸው ገፍተውበታል ።
ይኸው ዛሬ በትልቁ አገራቸውና የወያኔ ሰላይ እንደነበሩ ሲወራላቸው በነበሩት ና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በመላሣቸው ሢቆሉት ለሁለት አሥርት ዓመታትት በከረሙት ፣ አቶ ልደቱ አያሌው አማካኝነት በየፋ “
ኢትዮጵያ ፈርሳለች ” አሥብለዋል ። ኢትዮጵያ በልጅነታቸው የደረደሩት ኮርኪ ወይም የጭቃ ቤት መሰለቻቸው እንዴ በዋዛ ና በፈዛዛ የምትፈርስው ? በእርግጥ ይህ ቅዠት የወያኔዎች ብቻ አይደለም ። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በሙሉ እንጂ ።
ይህንን የምንረዳው ፣ በድብቅ መሣሪያ እየሰጡ ፣ የትግራይ ደሃ ገበሬን እና ደሃ የከተማ ነዋሪን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፣ በሆዱ በመግዛት ወደ ጦርነት ሲያሰማሩት ነው ። ነገ የተሻለ ዳቦ ተገኛለህ ። እኛ ሥልጣን ሥንይዝ ወይም ትግራይን ነፃ ሥናወጣ እቤትህ ድረሥ በርገር እናቀርብልሃለን ። እያሉ በመሥከብ ፈፅሞ በማይሆን ተሥፋ ተገፋፍቶ እንዲሰዋ ያደርጉታል ። በርገር ቀርቶ የጠላ ቂጣ እንኳን ሊያቀርቡለት አይችሉም ። የትግራይ ህዝብ ያለ ኢትዮጵያ ህዝብ የሞተ ነው ። ይህ የታወቀ ነው ። የዛሬው ጦርነትም በአበዱ እና ህሊናቸው ማሰብ ባቆመ ግብዝ ጥቂት ባንዳዎች በትህነግ ሥም የሚደረግ በውጪ በዝባዥ ኃይሎች ና በጠላቶቻችን ደጋፍ የሚካሄድ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ጦርነት ነው ።
ጦርነቱ ፀረ ህዝብ ነው ። ጦርነቱን የጀመሩት ፍፁም ማሰብዬ ህሊና የሌላቸው እብዶች ናቸው ። እደግመዋለሁ ጦርነቱን የጀመሩት በትምክህት ያበዱ ጥቂት ህሊና ቢሥ ፀረ ህዝብ ና ፀረ ኢትዮጵያ የሆኑ ኃይሎች ናቸው ።
አቶ ልደቱም ሆነ ወያኔዎች ፣ የአዞ እንባ የሚያነቡ እልም ያሉ ነፍሰ በላዎች ናቸው ። የላሊበላ የወያኔ ሚሽን የልደቱ ሚሽን ነው ። ላሊበላን ጥቂት ወያኔዎች ቢያጠፉት የትግራይ ህዝብ ምህረት የለሽ ቅጣቱን በሥሙ በሚነግደው ትህነግ ላይ ይፈፅማል ። የትግራይ ህዝብ ነፃ ህዝብ ነው ። ምን ያደርጋል ዛሬም ከጠመንጃ አፈሙዝ ፍራቻ ነፃ አልወጣም ። ዛሬ ህዝቡ የወያኔ ባርያ ነው ።
ይኽ እውነትን የምናስተውለው የአንድ አገር ህዝብ ፤ ያውም የተዛመደ ፣ ደም ፣ አጥንት ና ሥጋው የተዋሃደ ህዝብ ፣ ለእነሱ ሥልጣን ሲል በማያምንበት ጦርነት ተገዶ ተሠልፎ እንደቅጠል ሲረግፍ ቅንጣት ያህል ሐዘኔታ እንደሌላቸው ሥንገነዘብ ነው።
ቅንጣት ያህል ሀዘኔታ እንዳይኖራቸው ያደረጋቸውም ፣ በንዋይ ፍቅር የተደፈነው ልባቸው ነው ። በንዋይ ፍቅር የጨለመው አእምሯቸው ነው ። እነዚህ ሰዎች የሚያሥቡት ነገ ሥልጣን ሲይዙ ሥለሚበቀሉት ሰውና ሥለሚዘርፉት የአገር ሀብት እንጂ ወንድም ወንድሙን በመግደሉ ከቶም አይፀፀቱም ። ያ እንደ ቅጠል የሚረግፈው የትግራይ ህዝብ ፣ አስከሬኑ ተሰብስቦ በሰማዕታት ሀውልት ውሥጥ ለጎብኚ የሚቀመጥ ህዝብ ነው
- በጉብኝቱም ወቀት ” ወድማችን የሆነውን የአማራን ህዝብ ወረን ህይወቱን አጥፍተን ንብረቱን እየዘረፍን ሣለ ፣የኢትዮጵያ ዜጎች ተባብረው ባደረጉት የመከላከል ውጊያ የተሰው ታጋዮች ናቸው ። ” ለማለትም ከወዲሁ የተዘጋጁ አሳዛኝ አእምሮ ያላቸው ግብዞች ናቸው ። ወያኔዎች ፡፡
እነዚህ ግብዞች ከነግብረ አበሮቻቸው መጥፋታቸው አይቀርም ። በኢትዮጵያ የተከሉትም የዘር ና የቋንቋ ፖለቲካ ከሥሩ እንደሚነቀል አምናለሁ ። ኢትዮጵያ በቋንቋ ሥም እየተጠራሩ ጥሬ ሀብቷን ለብቻቸው የሚቦጠቡጦት ፣ ዜጎቿ የበይ ተመልካች የሚሆኑባት ሥርዓት ከመሥከረም 24/2014 ዓ/ም በኋላ እንደማይኖር አምናለሁ ። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በእኩልነት የምታገለግል እንደምትሆን ፤… የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ እና የልደቱ አያሌው አይነት የብልጣ ብልጥ ፖለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፋይሉ እንደሚዘጋ ፤ ተሥፋ አደርጋለሁ ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሃቅ ሟች ነውና እውነትን ይዞ ከሚመራው መሪ ጋር እሥከ ቀራኒዮ ይጎዛል ።