መስከረም 20 ቀን 2014
ውይይቱ በግንባሩ ያሉ ሴቶች በተልዕኮ አፈፃፀም ውስጥ ላሳዩአቸው ጥንካሬዎች እውቅናና ክብር መስጠትን አላማው ያደረገ ነው ።
በመድረኩ የሴቶች እኩልነትና የእንችላለን ስሜት ከቃል ባለፈ በተግባር የህይወት መስዋዕትነትን በሚጠይቀው ውትድርና ውስጥ ጭምር በብቃት እየታየ ስለመሆኑ በተሳታፊ ሴት የሰራዊት አባላቱ ተገልጿል ።
አሸባሪውን የህወሀት ሀይል በመደምሰሡ ረገድ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሴቶች ከጠላት ጋር የጨበጣ ውጊያ በመግጠምና ቦንብ ሲጨርሡ በድንጋይ ምሽግ በማስለቀቅ ጭምር ጀግንነታቸውን እንዳሳዩም ነው የተነገረው ።
በግንባር የሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት የአውደ ውጊያ ጥንካሬ በአሁኑ ወቅት ለወንድ የሠራዊት አባላቱም ጭምር የተሻለ መነሳሳትን እየፈጠረ እንዳለም በውይይት መድረኩ ተነስቷል ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ሜጀር ጀነራል ጥሩዬ አሠፌ በበኩላቸው ፣ ጀግንነት ለኢትዮጵያውያን ሴቶች ቀድሞውንም መገለጫቸው እንደሆነ ጠቁመው ፣
እናንተም የሀገራችሁን ፍቅር በመስዋዕትነት ጭምር እየገለፃችሁና ይህንኑ ጀግንነት እያስቀጠላችሁ በመሆኑ ስራችሁ ምንጊዜም በታሪክ ሲነገር የሚኖር ነው ብለዋል ።
ነፃነት ሸዋንግዛው ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶ ግራፍ በሀይሉ ስለሺ