bacha debele
በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የሰራዊቱን ግዳጅ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበታተን በመፈለግ የትግራይ ህፃናትን በማሰለፍ በአማራ ክልል ወረራ ፈፅሟል፤ ስልጠና ያልወሰዱ ህፃናትን ወደ ጦርነት በመማገድ ላይም ይገኛል ነው ያሉት።
በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን በማሰለፍ በ4 አርሚ ራሱን በማደራጀት በአማራ ክልል የሚያደርገውን ወረራ ቀጥሎበት ይገኛል።
ከነዚህ አካባቢዎች በ4 አርሚዎች ካደራጃቸው በከሃዲው ጀነራል ምግበ የሚመራ አርሚ 1 ተብሎ የሚጠራ በሁመራ አካባቢ አደርቃይ እና ማይ ፀብሪ አካባቢ ደባርቅንና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን በመያዝ ከዚያ በኋላ ሁመራን ነፃ በማድረግ ከውጭ በጋለቧቸው ጌቶቻቸው የሚሰጧቸውን እርዳታ ማስገቢያ ቀዳዳ ሲፈልገ የነበረው ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ብለዋል።
አርሚ 1 የተባለው ይዟቸው የነበረው ከፍለ ጦሮች 1ኛ በስሩ 3 ኮሮች ያሉት ኮር 1 የሚባለው በከሃዲው ኮሎኔል ጉእሽ ገብረ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት።
2ኛው ኮር 2 የሚባለው በከሃዲው ኮሎኔል ብርጋዴር ጀነራል ዘነበ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት።
ኮር 3 የሚባለው በብርጋዴር ጄኔራል ወርቅ አይኑ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት ያሉት ጀነራል ባጫ በአጠቃላይ 9 ክፍለ ጦሮች ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን ነው የገለፁት።
በመሆኑም አሸባሪው ህወሓት ወደሱዳን ለመውጣት ያቀደው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
አርሚ ሁለት የሚባለው እና በከሃዲው ሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው ሃይል በጋሸና ከክምር ድንጋይ ጀምሮ በተደረገ ውጊያ ሁለቱ ክፍለጦሮች ተደምስሰውበታል፡፡
አርሚ ሦስት የሚባለው ደግሞ ከውጭ በብ/ጀነራል ፍስሃ የሚመራ እና የሰለጠነ በሽንፋ በኩል ከቅማንት ቅጥረኛ ቡድን ጋር በመተባባር ጥቃት ቢሰነዝርም ተደምስሷል የተረፈውም ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል፡፡
ይህ ሃይል በተለይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ስራ ለማስተጓጎል ቢያስብም እቅዱ በጀግናው ሃይላችን ተደምስሷል ብለዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ እየደረሰበት ያለው ኪሳራ በጣም ብዙ ነው ያሉት ጀነራል ባጫ በተለይ የትግራይ ወጣቶችን እያስጨረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
EBC