July 6, 2021
11 mins read

ቢያንስ ቢያንስ ቅርባችን ከሆነችው ከሩዋንዳ እንማር!!!!

መሰረት ተስፉ ([email protected])

ሩዋንዳ ህዝብ ውስጥ ብዙሃኑ ሁቱዎች፤ ጥቂቶቹ ደግሞ ቱትሲዎች እንደሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ሩዋንዳ በጀርመንና በቤልጅዬም ቅኝ በተገዛችበት ወቅት የመንግስት ስልጣኑን እንዲይዙ ተደርገው የነበሩት በህዝብ ብዛት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቱትሲዎች ናቸው። ይህ መሆኑ በብዙሃኑ ሁቶዎች ላይ ፈጥሮት የነበረው ቅሬታ ቀላል አልነበረም። በዚህ ምክንያትም በብዙሃኑ ሁቱዎችና በጥቂቶቹ ቱትሲዎች መካከል የተለያዩ ግጭቶች ይስተዋሉ ነበር።

ሩዋንዳ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር 1962 . ከቅኝ ግዛት ነፃ ከመውጣቷ አንድ አመት በፊት ተደርጎ በነበረው ምርጫ ግን ብዙሃኑ ሁቱዎች በቀላሉ አሸንፈው የመንግስት ስልጣንን ተቆጣጠሩ። ምርጫው ተደርጎ የሁቱዎች አሸናፊነት ቢረጋገጥም ከቱትሲዎች ጋር የነበራቸው ቁርቁስ ግን ቀጥሎ ነበር። በተለይ እንደፈረንጆች አቆጣጠር 1990 እስከ 1993 በነበሩት ሶስት አመታት ውስጥ የቱትሲን መብቶች አስከብራለሁ ብሎ ትጥቅ ትግል ያካሂድ በነበረው Rwandan Patriotic Front (PPF) በሁቱ መሩ መንግስት መካከል በርካታ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች ተካሂደው እንደነበር በታሪክ ተመዝግቦ አልፏል። በዚህ መልክ ሁኔታዎች እየተካረሩ በመሄዳቸው ምክንያት የሁቱ ፅንፈኞች ለሰላማችን ፀር ናቸው ብለው የፈረጇቸውን ቱትሲዎች ከምድረገፅ ለማጥፋት በማሰብ በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ በጣም አስቀያሚና አስከፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፀሙ። ይህ አስከፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቱትሲዎችን እጅግ አሳዝኖና አስቆጥቶ ስለነበር በስፋት የትጥቅ ትግሉን እንዲቀላቀሉና ሁቱ መር የሆነውን መንግስት እንዲፋለሙ አደረጋቸው። መጨረሻም Rwandan Patriotic Front ባካሄደው ትጥቅ ትግል ሁቱ መር የሆነው መንግስት ከስልጣን ተወግዶ በምትኩ በህዝብ ብዛት ከሁቱዎች በእጅጉ የሚያንሱት ቱትሲዎች የሚመሩት መንግስት ስልጣን ይዞ እስካሁን ሃገሪቷን እየመራ ይገኛል።

እዚህ ላይ አንድ መገንዘብ ያለብን ቁምነገር አለ ብየ አምናለሁ። በቁጥር ከታየ ቱትሲዎች ከአጠቃላዩ የሩዋንዳ ህዝብ ብዛት ወደ 14% ገደማ ናቸው ተብለው ይገመታሉ። በአንፃሩ ሁቱዎች ደግሞ ወደ 85 % ናቸው የሚል ግምት አለ። ነገር ግን በሃገሪቱ ታሪክ አሁን ያለውን ጨምሮ ለረጅም አመታት የመንግስትነቱን ስልጣን ይዞ የሚገኘው ቱትሲ መር የሆነ ሃይል ነው። በተለይ አሁን ያለው መንግስት ወደስልጣን የመጣበትን መንገድ በሚገባ መረዳት ኢትዮጵያ ላይ ተደቅኖ ያለውን አደጋ ለመቀልበስ እጅግ በጣም አድርጎ ይጠቅማል ብየ አስባለሁ። ምክንያቱም አንድ የትጥቅ ትግል የሚያደርግ ሃይል የወጣበት ማህበረሰብ በቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በውዴታም ሆነ በግዴታ ካለው ህዝብ ውስጥ አብዛኛውን በተዋጊነት ሌላውን ደግሞ በደጀንነት ከጎኑ አሰልፎ መንቀሳቀስ ከቻለ፤ በአንፃሩ ሌላው ወገን በህዝብ ቁጥር ብዙ ሆኖ በትግል ሜዳ ላይ ግን ከተቀናቃኙ ተመጣጣኝ ወይም የበለጠ ሃይል ማሰለፍ ካልቻለ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች የበላይነት ሊኖረው የሚችለው አንሰተኛ የህዝብ ብዛት ካለበት ማህበረሰብ የፈለቀ ቢሆንም በትግሉ ሜዳ ላይ ብዙ ሃይል ማሰለፍ የቻለው ወገን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አይከብድም።

ይህን የሩዋንዳ ታሪካዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገብተን ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣም ይዘቱ የተለያየ ይሁን እንጅ ሂደቱ ተመሳሳይነት እንዳለው ለመረዳት የሚከብድ አይመስለኝም። ሁላችንም እንደምናውቀው ሃገራችን 6 % ብቻ ከሚይዘው የትግራይ ህዝብ የወጡት ህወሃቶች ልክ ቱትሲዎች እንዳደረጉት የፌዴራል መንግስቱን ስልጣን በበላይነት ተቆጣጥረው ለሃያ ሰባት አመታት ገዝተዋል። አገዛዛቸው የሚመች ስላልነበረ ግን ብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ሃይል ተገፍተው ስልጣን እንዲለ ተደርገዋል ስለጣን ከለቀቁ በኋላ አንድም ተመልሰው ወደስልጣን ለመም ካልሆነም ኢትዮጵያን በታትነው ታላቋን ትግራይን ለመመስረት ብዙ ጥረቶች አድርገው እስካሁን አልተሳካላቸውም።

ህወሃቶች ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም ብቻ ሳይሆን አሁን ደግሞ እጅግ የመከበብ የመዋከብ ስሜት እንዳደረባቸው እያየን ነው ይህ የመከበብና የመዋከብ ስሜት የሚፈጥረው የፍርሃት መንፈስ ደግሞ ቀላል ሊሆን አይችልም። ከዚህ ስሜትና መንፈስ ለመውጣት ያሏቸው አማራጮች ሁለት ናቸው። አንደኛውና መሆን ያለበት አማራጫቸው ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ሰላማዊና ፍትሃዊ የሆነ ድርድር አድርገው ተፈፅመውብናል የሚሏቸውን በደሎች ህጋዊ በሆነ መንገድ መጨረስ ነው። ሁለተኛውና አግባብነት የሌለው መንገድ ደግሞ ያለ የሌለ ሃይላቸውን አሰባስበው ጥቃት በመፈጸም ጥሰው ለመውጣት መሞከር ይሆናል። አሁን እንደሚታየው ግን የመረጡት ሁለተኛውን መንገድ ይመስላል። ለዚህ ማሳያ ደግሞ የተኩስ አቁም ስምምነት ቅድመ ሁኔታዎች ብለው ያስቀመጧቸውን የማይታረቁ ሰባት ነጥቦች መጥቀስ ብቻ በቂ ይመስለኛል።

እንደተባለው ሁለተኛውን መንገድ ከመረጡ መጀመሪያ ሊያደርጉ የሚችሉት ጠመንጃ ሊሸከም የሚችልን ማንኛውም ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ጎልማሳ ምናልባትም ህፃናትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ የሽምቅ ውጊያው አካል አድርገው በተለይ ከሌላው አለም ጋር ሊያገናኘን ይችላል የሚሉትን መንገድ ለማስከፈት መጣራቸው አይቀርም። እንዲያውም አሁን ላይ ትግራይ ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆነ ገምት ብባል እስካሁን የነበራቸውን እንቅስቃሴዎች ገምግመው ወደፊት በምን አይነት መንገድ ጥቃት እንፈፅም የሚል ውይይት እያደረጉና፤ እዛው ሳሉም በጣም በርካታ የሆኑ ማሰልጠኛዎች ከፍተው ሰፋፊ የሆኑ ወታደራዊ ስልጠናዎች እየሰጡ ሊሆን ይችላል የሚል ነው የኔ መልስ የሚሆነው።

ለማንኛውም በዚህች አጭር ፅሁፍ ለማስተላለፍ የፈለኳቸው ጠቅለል ያሉ መልዕክቶች ሶስት ናቸው። አንደኛው መልዕክቴ የህዝብ ቁጥር በተለይ በወታደራዊ መስክ ወሳኝ የሚሆነው በተጨባጭ በትግሉ ሜዳ በሚሰለፈው የሃይል መጠን እንጅ ለበጀት ድልድል ወይም ለህዝብ ቆጠራ ተብሎ በሚጠናቀረው መጠን እንዳልሆነ ግንዛቤ እንዲወሰድበት ለማሳሰብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ሽምቅ ውጊያና መደበኛ ውጊያ የየራሳቸው የሆኑ ባህሪያት እንዳሏቸው ለማስታወስ ያህል ነው። ሶስተኛው ጥቃቱ/ሽብሩ ለፈፀም የሚችለው በማንኛውም የድንበር ወይም ሌላ አከባቢ ሊሆን እንደሚችል ያለኝን ግምት ለመጠቆም ነው።

ስለዚህ የፌዴራሉም ሆኑ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የመከላከያ አመራሮች የትኛውንም አይነት ጥቃት ለመቀልበስ በሚያደርጓቸው ዝግጅቶች ዙሪያ ከላይ የተጠቀሱትን መልዕክቶች ግምት ውስጥ ቢያስገቧቸው ሊጠቅሙ ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ።

ቸር እንሰንብት!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop