February 24, 2020
6 mins read

አዲስ አበባ ከምጧ “ፍቅርና ኢትዮጵያ” የተባሉ መንታ ልጆችን ተገላገለች፤ – ሰማነህ ጀመረ፤ ካናዳ

File Photo
አዲስ አበባ ከምጧ “ፍቅርና ኢትዮጵያ” የተባሉ መንታ ልጆችን ተገላገለች፤ - ሰማነህ ጀመረ፤ ካናዳ 1

የካቲት 9፣ 2012

እቴጌ ጠሐይቱ አዲስ አበባ የሚለውን ስያሜ እንደሰጧት የሚነገርላት ከተማ ሁልጊዜ እንዳበበች፤ መዓዛዋም  እንዳወደን ይገኛል። ሊአጠፏት ሴራ ሲሸረቡ፤ ሰላሟንና ፍቅሯን ሊነሷት ቢዶልቱባትም ታሪክ እየሰራች ከመጓዝ ግን አልቦዘነችም።

አዲስ አበባ የሁላችን ከተማ፤ የአፍሪካና የዓለም መዲና በመሆኗ በቀላሉ አትጠፋም። ከተማዋ የተቆረቆረችውና የተመሰረተችው በጠንካራ ኢትዮጵያዊ አርበኞች፤ ምሁራን፤ መሐንዲሶች፤ ሐኪሞች፤ አርቲስቶች፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ የእምነት አባቶች፤ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች ነው። መስራቾቿን ወልዳ፤ በየፈርጁ አስተምራና አሳድጋ አቋቁማለች፤ ለወግ ለመአረግ አብቅታለች። ልጆቿ ከአስራ አራቱም ክፍለ ሃገራት ወይም ጠቅላይ ግዛትና ከሌሎች ዓለማት ጭምር መጥተው የተማሩባት፤ የነገዱባት፤ የሰሩባት፤ የበለጸጉባት፤ ትዳር የመሰረቱባት የሁሉም ከተማ መሆኗ ሊታወቅ ይገባል።

መሐሙድ አሕመድ አዲስ አበባ ቤቴ ብሎ ያንጎራጎረላት፤ ቲወድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) የመሰለ አዲስ ትውልድ ከያኒ ያፈራች የግብረገብ ከተማ ነች። በዚህና መሰል በሐሪዋ አዲስ አበባ እንደ ኒዮርክ፤ ሎንዶን፤ ናይሮቢ፤ ቶሮንቶ፤ ዋሽንግቶን ወዘተ ሁለገብ ከተማነቷን (Cosmopolitan City) መካድ ከቶ አይቻልም።

አዲስ አበባ ፍቅር እንጂ ዘር፤ ጎሳ፤ ቀለምና ጎጥ አታውቅም። ከአብሮነት ውጪ የመነጣጠል ትርክት አይገባትም። ይህንም ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 በቴዲ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ነዋሪዎች በአንድ ድምፅ መስክረዋል። ነዋሪዎቿ የሚአውቁት ሶስት ቀለማትን ማለት አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሲሆን ዘሯም ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

በከተማዋ ተወልዶ ያደገው የኪነት ባለሙያ ቴዲ አፍሮ ታሪክ የተመራመረ፤ ለሕዝብና ለሃገር አንድነት የቆመ፤ የተሟገተ፤ የዘመረ የአዲስ አበባና የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅና ከያኔ ነው። ኢትዮጵያንና ታሪኳን ፤ፍቅርንና ሰላምን ሲአዜም ኖሯል። በመረዋ ድምጹ ኢትዮጵያን በፍቅር ይዞ ሊጓዛ የተነሳ የልጅ አዋቂ፤ አስተማሪና ሰባኪም ነው። የመልካም ስነምግባሩና የኪነት ውጤቱ የሆነውን ‘ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ’  የተሰኘውን የሙዚቃ ውጤቶች ለህዝብ ለማቅረብ ለአያሌ ዓመታት ሲባዝን ኖሯል።  ብዙ ጊዜ ሞክሮ ሳይሳካለት ቆይቷል።

የፍቅር ጉዞ መልዕክቱን ለሕዝብ እንዳያቀርብ ሲከለክሉ የቆዩ የኢሕአዴግና ሕወሃት ባለስልጣናት አንገላተውታል። ሕዝቡም ፍቀዱለት እያለ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሲጠይቅና ጫና ሲአደርግ ሃያ ዓመት በምጥ ኖሯል። ዛሬ ቴዲ ተከልክሎ የነበረው ተፈቅዶ የፍቅር ጉዞ ኮንሰርቱንና የሙዚቃ ቅኝቱን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 ለሕዝብ አሳይቷል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል እንዲሉ ትእግስትም ፍቅርን ወለደች። አዲስ አበባና ኢትዮጵያም እንኳን ደስያላችሁ። በኮንሰርቱ ኢትዮጵያዊነትና ሰባዊ ፍቅር ነግሰው አምሽተዋል።

የኢትዮጵያና የዓለም ማህበረሰብ ለዓመታት ሲአምጥ የኖረውን ከባድ ምጥ በኮንሰርቱ ተገላግሏል። ምጡ በቀዶ ጥገና ሳይሆን በተፈትሮ ሕግ ፆታ የሌለው፤ በልብ ቅርጽና በቀይ አበባ የሚመሰለው ሁሉን የሚአስማማ ፍቅርና ኢትዮጵያዊነት የተባሉ መንታ ልጆችን ወልደው ተገላግለዋል። መልካም ልደት።

በመጨረሻም 150, 000 ሕዝብ በመስቀል አደባባይ በፍቅር ሲታደም ያለኮሽታ፤ ሕይውት ሳይጠፋ፤ ንብረት ሳይወድም የቴዲ መርሃ ግብር በሰላም እንዲጠናቀቅ በማድረጋችሁ ለአዲስ አበባ ሕዝብና ወጣቶች አክብሮታችን የላቀ ነው። የፍቅርና የሰላም ከተማ መሆኗን ስላስመሰከራችሁ በድጋሜ እንኳን ደስያላችሁ፤ ደስያለን። ቴዲም በሕዝብ መወደድና በፍቅር መጓዝ ያለውን ጥቅም ስላሳየኸን እግዚአብሔር እደሜና ጤና ይስጥህ-ኑርልን።

የሁሉም ሙዚቃዎችህ ሱሰኛና የባህር ማዶ አድናቂህ፤

ሰማነህ ጀመረ፤ ካናዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop