November 12, 2019
10 mins read

አዲስ ለሚዋቀረው ለኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ አማራጭ ሀሳብ ጠቁዋሚ – ይድረስ ለሚመለከታችሁ ሁሉ

እንዲህ ነው ጉዳዩ። አካሄዳችን ስላላማረኝ ምናልባት አገራችንን ወደሰላም ያመጣል ብዬ መፍትሄ ሀሳብ ነውና እንደፈለጋችሁ እዩት። አንድ ጃንሆይ ካደረጉት ነገር ይቺን በብዙ ጎሳዎች የታጠረችን አገር በዘዴ ነበር ያስተዳድሩ የነበረው። ያለንበት ሁኔታ ዘዴን ይፈልጋል ይመስለኛል። አይተናት ያደግናት ኢትዮጵያ መልኳን ቀይራ ሁሉ ጫፍ ይዞ እርስበራሱ የሚጓተትበት ዘመን ላይ ስለሆን የአቢይ መንግስት ይህን ከግንዛቤ አስገብቶ አሁን የሚዋቀረውን ፓርቲ እንዲህ ቢያደርግ ጊዜያዊ መፍትሄ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
፩) ሙስጠፌን የአዲሱ ፓርቲ  ሊቀመንበር አድርጋችሁ እስከ ምርጫው ጠ/ሚር ሆነው እንዲሾሙ አመቻቹላቸው። ለምን? ከተቀራችሁ ኢሀዴጎች በሙሉ ልክ ሁሉን ግዛት እንደራሳቸው ሱማሌ ግዛት በማየት ፍጹም ኢትዮጵያዊነት ተመልሶ እንዲያብብ ተስፋ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ። ማለፍያ አለምአቀፍ ተሞክሮም አላቸው። የካድሬነት ባህሪ አልነካቸውም። የወያኔ ተንኮል ሰለባ ባለመሆናቸው በሀቅ ሁሉን ጎሳ በኩልነትና ፍትሃዊነት ይመራሉ ብዬ አስባለሁ። ሱማሌ ልጆቻችን ቃልኪዳናቸው አስደማሚ ነው። ቆራጥም ናቸው። የሙስጠፌ ጠ/ሚር መሆን የዖነግን ጎማ ያስተነፍሳል። የ አክራሪ አማሮቹንም ጫፍ ረገጥነት ልክ ያስገባል። የሌሎች በቁጥር ያልደመቁ ግን በኢትዮጵያዊነት የደመቁ  ብሄር ብሄረሰቦችም ተስፋ ይሆናሉ። ይህ ከሆነ ሊበጠስ የሳሳው የኢትዮጵያዊነት ገመድ ቀስ እያለ ይጠብቃል። ልብ በሉ ወገኖቼ። የዖነግና ወያኔ አላቻ ጋብቻ ለተንኮል ካልሆነ በቀር ለአገር ምንም የሚፈይደው የለም። አቢይና ደመቀ የሙስጠፌ ምክትል ሆነው ይስሩ። ሌላ ምክትል ካስፈለገ አንዱን የአረና ወይም ህወሃት ያልሆነ ተወካይ ጨምሩ። ያገራችን ችግር ከ 50 አመታት ወዲህ ከ ዖሮሞ፣ አማራና ትግራይ ከበቀሉ ምሁራን ተብዬ ነውና እስቲ ለለውጥ ያህል የሱማሌ ልጆቻችን አስተዳደሩን ይረከቡና ያስተዳድሩን። የህዝብን ቁጥር ያማከለ ውክልና ዴሞክራሲው ሲደራ ይደርሳል። ከ ፫ አመት በሁዋላ በትንሹ።
፪) የታቀደውን የቅርብ ምርጫ እንዲተላለፍ በአንድ ድምጽ ለፓርላማ አስቀርባችሁ አጸድቁ። የ28 አመታት ያለቁት ወገኖቻችን “ቢረሱ” እንኩዋ በቅርቡ ያለቁት ወገኖቻችን ከአይምሯችን እስቲ ከሰም ይበል። ደሞስ ዬትኛው የፖሊሲ ውይይት ተጀመረናስ ምርጫ ይታሰባል? ለመምረጥስ አድራሻ አያስፈልገውም  ነዋሪው? ሰው እየተፈናቀለ ከፊሉ ቤቱ እየፈረሰበት አስመራጩስ ማ ቤት ሄዶ ነው ተመራጩን የሚመዘግበው? ወይስ የደቦ ምርጫ ሊሆን ነው? ምርጫው ጭራሽ መተላለቂያ እንዳይሆን እሰጋለሁ። ምርጫ በ ፫ አመታት ውስጥም ከሆነም እሰየው። እናም ምርጫ አለመኖሩ በግልጽ ለህዝቡ ይነገረው። በየቤቱ እልል ቢል እንጂ የሚከፋው አይኖርም ብዬ አስባለሁ። የሚከፋቸው የታወቁት የጽልመት ሀይላት ናቸው። እነሱ ደሞ በቁጥር እጅግ አናሳ ናቸው። በየ ማስሚዲያው  ፊሽካ ስለነፉ ብዙ መስለውን ሊታዩ  ግን ይችላሉ። አይደሉም።
፫) እዚህ አዲሱ ሸንጎ የተዋቀራችሁ ፓርቲዎች በጥቂት ቀናት ልዩ ሀይሎቻችሁን አንድ እዝ ስር አድርጉና ወደር የማይገኝለት ጦር ሰራዊት ይመስረት። ታያላችሁ ይህ የአንድነት መንፈስ ሃያሉዋን ኢትዮጵያን እንዴት እንደሚመሰርት። በነ አክራሪያን ሰበካ አትሸወዱ። አንድነት ወጥነት አይደለም። ህብረብሄራዊነት እንጂ ። አማራ፣ ዖሮሞ፣ ትግሬ ሊውጠን ነው፣ አሃዳዊ ስርአት ሊመጣ ነው ለሚለው ሰበካ ሙስጠፌ አይመቹም። ለዚህም ነው የኝህ ሰውዬ ጠቅላይ አስተዳዳሪ መሆን የያንዳንዱዋን አክራሪ ጎማ አስተንፋሽ ወስፌ የሚሆነው። በአገራችን ብዙ ነገራችን ምስቅልቅሉ ለ ብዙ አስርተ አመታት ስለወጣ ይህ አስታራቂ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
፬) ክብርት ፕሬዚደንቱዋን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የተባበሩት መንግስታት ዋና ተጠሪ ማድረግ። እኒህን ሰው የይስሙላ እንደራሴ ማድረግ ክህሎታቸውን በትክክል አለመጠቀም ነው። በአለም አቀፍ ጉዳይ ጥርሳቸውን የነቀሉ ብርቱ ሴት ናቸውና ኢትዮጵያችንን ወደልዩ ከፍታ ያመጡልናል ብዬ አስባለሁ። ፕሬዚደንትነት እስከ ምርጫው ይቅር። በአንድ ፓርላማ ስብሰባ ማፍረስ ነው። ፕሮፌሽናል ስለሆኑም ቅር ይላቸው አይመስለኝም። አቶ ገዱን የ interregional affairs ሊቀመንበርና የአዲሱ ፓርቲ ልዩ አማካሪ አድርጎ መሾም።
፭) አምባሳደሮቻችንን በሙሉ እንዳሉ ብቃታቸውን መፈተሽ። ክብርት ፕሬዚደንቱዋ የውጭ ጉዳይ ከሆኑ ይህ በጣም ይቀላል። በብቃት ከሆነ አገራችን በማንም ካድሬ ብቃት መመዘኑዋ ይቀርና ወደ ቀድሞዋ ከፍታ ታመራለች። እነ ከተማ ይፍሩ፣ ይልማ ዴ’ሬሳ፣  አክሊሉን ያፈራች ኢትዮጵያ ፣ እንኩዋንስ ባገራቸው ጉዳይ ቀርቶ የአፍሪካ ሀገራትን አምባሳደሮች ሀሁ ያስተማሩ ልሂቃን ነበሩን። ቅንነቱ ካለና በደንብ ቢፈለጉ ዛሬም ይኖራሉ። ሙያውን ከባለሙያው ካዛመድን ይቺ አገር ከፍ ያለ ቦታ ትደርሳለች። ለምሳሌ የአዲሱ ኢሰመጉ ሊቀመንበር ወጣቱ ሰውዬ ምደባ ግሩም ድንቅ ነው።
ማሳሰብያ!
መፍትሄ የምትሉትን ከመጨመር ሌላ ጉዳይ ላይ ጊዜአችሁን አታጥፉ። የአገራችን ሁኔታ አደገኛ መስመር ላይ ነው። እስቲ ብሶታችሁን ብቻ ማመልከቻ የምትጽፉ ሰዋች መፍትሄ ውለዱ። መደማመጥ ቀርቶ መወነጃጀል ብቻ ከሆነ ዬትም አንደርስም። እንደ ህዝብ እንጠፋፋ ይሆናል እንጂ ኢትዮጵያ እንደአገር ትቀጥላለች። በኢትዮጵያችን ውስጥ ሌላ አገር እንፈለስፋለን የምትሉ እንኩዋ ከልባችሁ እንዳልሆነ  አጥታችሁ ሳይሆን በውስጣችሁ ያለው አምቃችሁ የያዛችሁት ሰልፊሽነት እየገነፈለባችሁ ተቸግራችሁ ነው። ተረጋጉ። ግራና ቀኙን የሚያለቅሰውን አቅመደካማ፣ የሚሳቀቀውን ታዳጊ አስተውሉ። ግፍ ሲበዛ በጎ አይደለም። ብዙ በሙያ የተራቀቁ አስደማሚ ልጆችና የልጅ ልጆች  በአለም ተበትነው አሉን። እነሱን እንዴት አርገን በፍቅር ሀርቨስት እናርግ ብለን እናስብ። ይህው ነው።
የበኩሌን ለግሻለሁ። እናንተስ?
ከምስጋና ጋር
አባዊርቱ

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop