November 13, 2019
16 mins read

በኢህአዴግ ውህደት የሚፈርሰው ህወሓት ወይስ ኢትዮጵያ? – ስዩም ተሾመ

images925252457

“የኢህአዴግ ውህደት እና የህወሓት አጥፍቶ መጥፋት” በሚለው ፅሁፍ ለመግለፅ እንደተሞከረው ህወሓት የህወሓት አጥፍቶ መጥፋት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ተግባራዊ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። ከመጋቢት 2011 ዓ.ም ጀምሮ የወሰዳቸውን ዝርዝር ተግባራት፣ እንዲሁም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መቀሌ ላይ እያደረገ ባለው ስብሰባ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች መመልከት ከመጀመራችን በፊት ባለፉት አራት አመታት የታዩትን ለውጦች በአጭሩ እንመልከት።

በጥቅሉ ከ2008 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ ተስፋፋ። ከ2009 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ ኦህዴድ እና ብአዴን በኦሮማራ ጥምረት አማካኝነት ራሳቸውን ከህወሐት አገልጋይነት ነፃ አወጡ። በ2010 አጋማሽ ላይ የህወሓት የስልጣን የበላይነት ተወግዶ አዲስ አመራር ወደ ስልጣን መጣ። አዲሱ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣበት ግዜ ጀምሮ እስከ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ አምስቱን አጋር ድርጅቶች እና ደህዴንን ከህወሓት ተፅዕኖ እና መገልገያነት ነፃ አወጣ። በዚህ ረገድ የአብዲ ኢሌ ከስልጣን መወገድ፣ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ግሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ፣ አፋርና ድሬዳዋ የተደረጉት የአመራር ለውጦች ይጠቀሳሉ።

images925252457ፎቶ፦ Tigrai Online

በአንፃሩ ህወሓት እስከ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶችን በመጠቀም እድሜውን የማራዘም ተስፋ ነበረው። ለዚህ ደግሞ የኦሮሞና አማራ ልሂቃን ከስልጣን ክፍፍል ጋር በተያያዘ በመካከላቸው አለመግባባት ይፈጠራል። በዚህም የህወሓትን አከርካሪ የሰበረው የኦሮማራ ጥምረት በራሱ ግዜ ይሰበራል የሚል ተስፋ ነበራቸው። በሌላ በኩል አጋር ድርጅቶች በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ የባለቤት ስሜት እና የመወሰን ስልጣን እስከሌላቸው ድረስ ከፌደራሉ መንግስት ጋር ተቀራርበው አይሰሩም የሚል እምነት ነበራቸው።

በዚህ መሰረት ኢህአዴግን እንደ አንድ መታገያ መድረክ በመጠቀም በተለይ በኦህዴድ/ኦዴፓ እና ብአዴን/አዴፓ መካከል ያለውን ልዩነትና ክፍተት ይበልጥ በማስፋት የኦሮማራን ጥምረት ለማዳከም ሞክሯል። ከዚህ በተጨማሪ የኦሮማራ ጥምረት ፍፁም ዘረኛ እና አግላይ እንደሆነ በመግለፅ ለደህዴንና አጋር ድርጅቶች ስጋት መሆኑን ለማሳየት ተደጋጋሚ ጥረት አድርጓል። በዚህ መልኩ ህወሓት በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል፣ እንዲሁም በኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች መካከል ያሉትን ክፍተቶች በማስፋትና በመጠቀም ወደ ስልጣን ለመመለስ አሊያም እድሜውን ለማራዘም ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት በኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች መካከል ልዩነት ለመፍጠር በሚያደርገው ጥረት ልክ የኢህአዴግ ውህደት እየተፋጠነ መምጣቱ ነው።

ህወሓት የግንባሩ መስራች እንደመሆኑ መጠን የኢህአዴግን ውህደት የሚቃወምበት ምክንያት ለብዙዎች ግልፅ አይደለም። አንዳንዶች ይህን የአጥፍቶ መጥፋት ባህሪ ጠንቅቀው የሚያውቁ ቢሆንም ህወሓት በፌደራሉ መንግስት ላይ የነበረውን የስልጣን የበላይነት በማጣቱ አደጋው የቀነሰ ወይም ያለፈ መስሏቸዋል። ሌሎች ደግሞ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የሚመራውን ህዝብና ሀገር አጥፍቶ የሚጠፋበት ምክንያት ሊታያቸው አይችልም። ስለዚህ “ኢህአዴግ ከተዋሃደ ህወሓት ህዝብና ሀገርን አጥፍቶ ይጠፋል” ሲባል ለአብዛኞቻችን እውነት ላይመስል ይችላል። ይሁን እንጂ ሁለቱም እሳቤ የህወሓትን ትክክለኛ ባህሪና እንቅስቃሴ ካለመገንዘብ የመነጨ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ህወሓት የፖለቲካ ቡድን ሳይሆን ጥገኛ የማፊያ ቡድን ነው። በመሆኑም እንደ ማንኛውም የፖለቲካ ቡድን ራሱን ችሎ መቆም፣ ለህዝብ ጥቅምና ተጠቃሚነት መስራት አይችልም። ከዚያ ይልቅ ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖችን በመጠቀም የፖለቲካ ስልጣን በበላይነት መቆጣጠርና ህዝብን አፍኖ ሀገርን የሚዘርፍ ነው። የመንግስትን ስልጣንና መዋቅርን ተጠቅሞ ህገወጥ አፈና እና ዘረፋ የሚፈጽም ቡድን የማፊያ መንግስት ይባላል። ይህ የማፊያ ቡድን የመንግስታዊ ስርዓቱ መስራችና ባለቤት ሲሆን የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የእሱ አገልጋይ፣ አጋር ድርጅቶች የህወሓት መገልገያዎች ነበሩ። የመንግስት ስልጣን የሌላቸው የፖለቲካ ቡድኖች ደግሞ የህወሓት ተላላኪና አጋሮች ነበሩ ማለት ይቻላል።

ከላይ በተገለፀው መሰረት ህወሓት ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎችነና እንቅስቃሴ በበላይነት መቆጣጠር መፈለጉ በራሱ የማፊያነት ሌላኛው መገለጫ ነው። ህዝብን በማፈን ሀገርን የመዝረፍ ዓላማና ተልዕኮ ያለው ቡድን ህዝባዊ መሰረትና ቅቡልነት የለውም። በመሆኑም ከሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ጋር በሃሳብ ተወዳድሮ ተመራጭ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ለህዝብ ጥቅምና መብት የቆሙ የፖለቲካ ቡድኖች በሀገር ውስጥ በነፃነት እንዳይደራጁና እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ ህዝቡን ምርጫና አማራጭ ማሳጣት አለበት። በእነዚህ ምትክ ደግሞ ከህዝብ ይልቅ ለእሱ አገልጋይና ተላላኪ የሆኑ የፖለቲካ ቡድኖችን ራሱ አደራጅቶ የፖለቲካ ስልጣን እንዲይዙ ያደርጋል።

ሆኖም ግን ይህ የማፍያ ቡድን በራሱ አደራጅቶ ስልጣንና ኃላፊነት የሰጣቸው ቡድኖች በድንገት ከቁጥጥር ውጪ ከወጡ የሚያስከትለው አደጋ ከባድ ነው። ምክንያቱም የዚህ ጥገኛ ቡድን ጥቅምና ህልውና የተመሰረተው ከራሱ ይልቅ በሌሎች አገልግሎትና ተገዢነት ላይ ነው። ከእነሱ አገልግሎትና ድጋፍ ውጪ በራሱ መቆምና መንቀሳቀስ አይችልም። በተመሳሳይ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እና አጋር ድርጅቶች ለህወሓት ተገዢና አገልጋይ ካልሆኑ ህልውናው ያከትማል። ስለዚህ ይህን ስጋትና አደጋ ለማስወገድ የራሱን ህልውና ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ከሆነ ነገር ጋር ማቆራኘት አለበት። ህወሓት “በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚመራ ኢህአዴግ ከሌለ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ትፈርሳለች፣ ህዝቦቿን በጦርነት ያልቃሉ” የሚል አቋም የሚያራምደው ጥገኛ ማፊያ ስለሆነ ነው። የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ሆነ በብሔር ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ አደረጃጀት መሰረታዊ ዓላማው “እኔ ከሌለሁ ሀገሪቱ የመበታተን አደጋ ይገጥማታል፣ ህዝቡም በጦርነት ለዕልቂት ይዳረጋል” በሚል የራሱን ህልውና ከህዝብና ሀገር ጋር ለማቆራኘት እንዲያስችለው ነው።

በእርግጥ የአንዱ መኖርና አለመኖር በሌላው ሕይወት ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። “እኔ ከሌለሁ አንተ አትኖርም” በሚለው እሳቤ ግን ከሁለት አንዳችን ወይም ሁለታችንም ጥገኛ መሆናችንን ያሳያል። የትግራይ ህዝብ ለሶስት ሺህ አመታት ያለና የነበረ ከሆነ የዛሬ 45 አመት የተፈጠረው ህወሓት በትግራይ ህዝብ ላይ የበቀለ ጥገኛ አረም እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበረች ሀገር እንደመሆኗ መጠን የዛሬ 30 አመት የመጣው ኢህአዴግ በሀገሪቱ ላይ የበቀለ ጥገኛ አረም ነው። ስለዚህ የህወሓት ሆነ ኢህአዴግ መወገድ ለትግራይና ኢትዮጵያ ህዝብ የህልውና አደጋ ሊሆን አይችልም።

ይሁን እንጂ ህወሓት መጋቢት 2011 ዓ.ም ወይን መፅሔት ላይ ያወጣው ባለ 43 ገፅ ፅሁፍ መነሻ ምክንያቱ የኢህአዴግ ውህደት እንደሆነ ይገልፃል። ፀኃፊው “አሁን በአገራችን ያጋጠመው ውስብስብ ፖለቲካ አንድ ውሁድ ፓርቲን በሚመለከት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ጥበብና ቆራጥነት ሊመራ ይገባል” በማለት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይገልፃል። አያይዞም “እየተቀበረ ያለውን ኢህአዴግ አልቅሰን እንሸኘው ወይስ ሙሉና የተጨበጠ አማራጫችንን ይዘን ቀርበን ትግላችንን እናጋግል?” በማለት ይጠይቃል። ከዚህ በተጨማሪ በተጠቀሰው የህወሓት ፅሁፍ ገፅ 29 ላይ እንዲህ ይላል፡-

“አሁን ኢህአዴግንና በርሱ የሚመራውን ልማታዊ ዴሞክራሲ መንግስት በመምራት ላይ ያለው ኢህአዴግና የገዥ መደብ ቡድን መለያው ፀረ- አብዮት፣ ፀረ- ልማትና ፀረ-ዴሞክራሲ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ሙስናና ብልሹ አሰራር ገዥ የሆነበት በውጤቱም አገር በመበታተን ጫፍ ላይ የደረሰበት ወቅት ላይ የሚቀነቀን “ውህደት” የሚባል ተረት ተረት ሊታለም አይችልም።”
ለህወሓት የኢህአዴግ ውህደት በአንድ በኩል ጣዕረ-ሞት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ተረት ተረት የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? በመሰረቱ የኢህአዴግ ውህደት ከሚያስከትላቸው ለውጦች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- በኦዴፓና አዴፓ መካከል የነበረውን ያለመተማመን ስሜት ያስወግዳል፣ በኦሮማራ ጥምረት እና ደህዴን መካከል የነበረውን ክፍተት ይደፍናል፣ በኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶች መካከል የነበረው ልዩነት ያስወግዳል፣ በሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የነበረውን ኢፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል ያስቀራል፣ በክልልና ብሔሮች መካከል የነበረውን የጠላትነትና ባላንጣነት ስሜት ያስቀራል፣ እንዲሁም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጥራዝ ነጠቅ መርህን ጨርሶ ለማስወገድ ያስችላል የሚሉት ናቸው።

ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ በኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ላይ የነበረውን ያልተገባ ስልጣንና የበላይነት የሚያስወግዱ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመበታተንና በህዝቦች መካከል ግጭትና ዕልቂት ለመፍጠር የሚጠቀምባቸውን ክፍተቶች የሚደፍኑ መሆናቸው እርግጥ ነው። በመሆኑም የኢህአዴግ ውህደት የህወሓትን የበላይነት እና ሀገሪቷን ለማፍረስና ለማተራመስ የነበረው አቅምና እድል ተመናምኖ ያልቃል። በዚህ ምክንያት ህወሓት ተመልሶ ወደ ስልጣን በመምጣት እንደ ቀድሞ ለእሱ አገልጋይና ተገዢ የሆኑ የፖለቲካ ቡድኖችን በማደራጀት የኢትዮጵያን ህዝብ ማፈንና መዝረፍ አይችልም። ስለዚህ በውህደቱ ምክንያት ሞቶ የሚቀበረው ኢህአዴግ ሳይሆን ራሱ ህወሓት ነው። በኢህአዴግ ውህደት ምክንያት የሚፈርሰው ሀገር ሳይሆን የህወሓት ማፊያ ቡድን ነው።

6 Comments

  1. ሕወአት አይፈርስም። የምትፈርሱት አንተና ኢትዮጵያ ናችሁ። የኢትዮጵያ መፍረስ የጀመረዉ ኤርትራ የሄደች ጊዜ ነበረ። እንዳልተደረገ አድርገህ ዝም አልክ። ወልቃይት፤ ፀገዴና ራያ ስሄዱም እንዳላየ ሁነህ ዝም አልክ፤ ከቡካትህ የተነሳ ማለት ነዉ። አሁን ፊትህን ወደ ኦሮሞ አዙረህ መሸለልና መፎከር ጀመርክ። ወያኔ መጣ ቢሉህ እመቤቴ ማርያምን እኔ ስለእነርሱ ምንም ክፉ ነገር አልተናገርኩም ትላለህ። ምክንያቱም እስቅምሰዉኋላ። ያንተ ድንፋታ እነርሱ እስኪመጡ ድረስ ነዉ። ያኔ ሸክምህም ትንሽ ይቀልልሃል።

  2. The reason why Muslims are after Addis Ababa , Dire Dawa , Harrari and also Oromia is solely economical reasons, same as why international Muslims attacked the world trade center on 9 11 was for economical reasons…

    List of Ethiopian regions by Human Development Index (HDI)
    From Wikipedia, the free encyclopedia

    This is a list of Ethiopian regions and the two chartered cities of Addis Ababa and Dire Dawa by Human Development Index as of 2017.

    . HDI (2017) Comparable country
    Medium human development
    1. City of Addis Ababa 0.698 South Africa
    2. Region of Harari Region 0.562 Pakistan

    Low human development
    3.City of Dire Dawa 0.544 Papua New Guinea
    4. Gambela Region 0.539 Tanzania
    5. Tigray Region 0.487 Ivory Coast
    6. SNNP Region 0.464 Gambia

    –COUNTRY OF Ethiopia- 0.463 Gambia

    7. Benishangul-Gumuz Region 0.453 Yemen
    8. Oromia Region 0.448 Yemen
    9. Amhara Region 0.443 Eritrea
    10. Somali Region 0.409 Chad
    11. Afar Region 0.405 Chad

    የአዲሰ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ የተሰረቁ ቼኮችንና ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ከመንግስትና ከግል ባንክ ደንበኞች ሊጭበረበር የነበረ 28 ሚሊዮን ብር ማዳን ተችሏል
    November 9, 2019 –.
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከመንግስትና ከግል ባንክ ደንበኞች ሊጭበረበር የነበረ 28 ሚሊዮን ብር ማዳኑን የአዲሰ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

    ኮሚሽኑ ለኢዜአ እንዳስታወቀው ከመንግስትና ከግል ባንኮች ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ያጭበረበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

    ተጠርጣሪዎቹ የተሰረቁ ቼኮችንና ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ነው ከመንግስትና ከግል ባንክ ደንበኞች ላይ ገንዘቡን ያጭበረበሩት ።

    ፖሊስ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ባንክ ደንበኞች ላይ ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል እየተፈፀመ ስለመሆኑ ከብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ነው ክትትል ያደረገው።

    በወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ከ70 በላይ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ባንክ ደንበኞች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 60 ሚሊዮን 843 ሺህ 601 ብር ወጪ ማድረጋቸውም ተረጋግጧል።

    በተመሳሳይ መንገድ ወጪ ተደርጎ ሊወሰድ በሂደት ላይ የነበረ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን እንደተቻለና ከተጠርጣሪዎቹ እጅም የተለያዩ የባንክ ቼኮችና ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች እንደተያዙም ነው የተገለፀው።

  3. It is time to get ready for the worst , the Ethiopian civil war is inevitable, what we can do from now on is figure out how to fight this civil war with little to minimal sufferings. The historical era of the Amercian USA Civil War is a good example of the stage where Ethiopia is now.

  4. ኤርትራን ውሰዱልኝ ብላ ያስረከበች ከምድር ፍጥረታት ሁሉ ተንኮለኛና ከሃዲ የሆነችው ወያኔ ናት።
    አሁን ግን የገዛ መርዟን እየተጋተችና በየቀኑ እየሞተች ያለች ምስኪን ጣእረሞት ሆና ፡ መያዣዋና መጨበጫዋ ጠፍቶ ለግነዛ ብታስቸግርም መጣያ አይጠፋላትም።
    እባብ ጭራው ቶሎ አይሞትም።

    • Eritrea with the people, sea,and land was sold to Italy by Emiye Menelick for 1 millionL Lira and 289000 guns. If you sell something it means is sold . You do not claim things after selling them. The reason Eritrean fought for 30 years is because you sold them already. They did not want you anymore. To begin with, Menelick sold the land, people and sea, because they did not belong to him. So from beginning the land and sea belonged to Tegarus, no to Nephetegneas

  5. የኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ የመሆን ጉምጉምታ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ይሰማል–ተገቢ ነውና ተገቢ አይደለም፤ ወይም ገንቢና ገንቢ አይደለም የሚሉ፡፡ በዚህ ሃሳብ አሰጣጥ ላይ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ የኦነግና ህወሃት ጥቂት ባለስልጣናትና ደጋፊዎች የሚያነሷቸው ሃሳቦች ግን ግራ የሚያጋባና የተምታታ ነው፡፡
    1. አንዳንዱ ውህደቱ አሃዳዊ ስርዓት ለማምጣት ያለመ ነው ይሉናል ምክንያታቸው ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ማጉላት አንድነት ያመጣል በሚል
    2. ሌሎች ደግሞ ኢህአዴግ ከተዋሃደ ህገመንግስቱ ተናደ ማለት ይሆናል ለዚህ ምክንያታቸው ደግም ህገመንግስቱ ብሄርን እንጂ ዜጋን ያማከለ አይደለም በሚል ማደናገሪያ
    3. አንዳንድ የወያኔ ስራአስፈጻሚና ምሁር ተብዬዎች ደግሞ ጊዜው አይደለም ይሉናል መለስና ስዩም መስፍን ጭምር ሲደሰኩሩት የነበረውን ሃቅ በመርሳትና ህዝቡን በመናቅ
    ግን ማንም መርሳት የሌለበት የኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ መሆን በዋናነት የድርጅቱ ጉዳይ እንጂ የምእላተ ህዝቡ ሊሆን አይችልም፡፡ አንድ ላይ ቢሰሩ ይሻላል ወይስ በተናጥል ከተባለ ህብረት ማን ሲጎዳ አይን ነው የምንለው፡፡ ውህድ ፓርቲ ከሆነ፣ ምርጫ ካልተካሄደ እነጠለላለው እያለ ወያኔ በልሳኑ ጭምር እያቅራራ ነው፡፡ አብረን እየኖርን ያለነው ሰጥቶ በመቀበል የጋራ ተጠቃሚነት መርህ እንጂ በአንደናው ወገን መልካም ፍቃድ አይደለም፡፡
    ህወሃት በልሳኑ መጽሄት ላይ ዲፋክቶ ስቴት እያለ የሚያስፈራራው ማንን እንደሆነ አይገባንም፡፡ ሲበዛ የልጅ ብሂል ነው፡፡ አገር እንዲህ በዋዛ ብጭቅጭቋ የሚወጣ ከሆነማ ምኑን አገር ሆነው ተራ የመንደር ማህበር ወይም እድር እንጂ፡፡ ህገመንግስት እነሱ ሲሉት ብቻ እውነት ይመስላቸዋል፡፡ በትግራይ ክልል ቀብር እንኳን ማስቀበር ሳይችሉ ታስረው የተባረሩትን እናስታውሳለን፡፡ ቀድሞ አገር ሲመሩ እንደነበርው አንጻራዊ ሰላም በትግራይ አለ ይሉናል፡፡ ሰላም ማለት ህዝቡን ሁላችንም ከሁለት አመታት በነበርንበት ሁኔታ ህዝብን ጸጥ ለጥ አድርገው በ1-ለ5 ጠርንፈው አንዱ ሌላውን እየሰለለ፤ ከተቃወመ ባንዳና ሌላም እየተባለ ያለበትን ምድር-ትግራይ፡፡

Comments are closed.

Previous Story

አዲስ ለሚዋቀረው ለኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ አማራጭ ሀሳብ ጠቁዋሚ – ይድረስ ለሚመለከታችሁ ሁሉ

Next Story

 ፖለቲካዊ መነጣጠቅ በእርግጥ አክትሟልን? ዛሬሥ በቢላዋ የሚቀልዱ የሉምን? ሥንቱስ ሰው ነው በፈጣሪ በየነ መረብ ውስጥ   እንዳለ የሚያውቀው? (መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop