ከእውነት የበለጠ እውነት ኢትዮጵያን ያሻግራል – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

ኢትዮጵያን እንበታትናለን ብሎ ሲሰራ የነበረው ዕብሪተኛ ሰው ባለጊዜ ሆነና፥ ራሱ ብቻውን መንግስት ሆኖ መላውን ኢትዮጵያ እንደ ጎልያድ በማን አለብኝነት ሲያስጨንቅ የሚታይባት ምድር ኢትዮጵያ ናት።

አንድ ቤተሰብ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በክልል እያጠሩ ባላንጣ መንግስታትን ፈጥረው፥ ጨለማውን ብርሃን እያሉ ሲጠሩ የማይታፈርበት ምድር ኢትዮጵያ ናት።

ከነገድ ከቋንቋ ዋጅቶ በክርስቶስ ፍቅር አንድ ስለመሆን የሚሰብከው ሃይማኖት ተከታይ ነኝ እያሉ፥ በወንድማማች መካከል ጠብ የሚዘሩ ጉደኞች የሞሉባት ምድር ኢትዮጵያ ናት።

በመርህ ላይ ሳይሆን በዘረኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የመንጋ አንድነት ያለው ፓርቲ፥ መላውን ኢትዮጵያ አንድ የሚያደርግበት ምሪት ይሰጣል ተብሎ ጉም የሚጨበጥበት ምድር ኢትዮጵያ ናት።

ወዶም ሆነ ተገዶ ሁሉም በየጎሳው ዙሪያ አንድነቱን አጠናክሮ እየተደራጀ ራሱን ለማዳን ሲዳክር፥ ራሱን ለእርስ በርስ ዕልቂት እያመቻቸ መሆኑ እየታወቀ፥ የ “ሰው” ነት ፖለቲካ ቦታ የማይሰጠው ምድር ኢትዮጵያ ናት።

እኩይ የሆነው ዘረኝነት ኢትዮጵያን ሊያሰጥም ጫፍ የደረሰበት ጊዜ ሆኖ ሳለ፥ ሩዋንዳ ልንሆን ነው ብሎ ከመፍራት ያለፈ፥ በማስተዋል ለመጠበቅ ምንም እርምጃ የማይወሰድባት ምድር ኢትዮጵያ ናት።

ይህ ሁሉ እውነት ነው። ግን ከዚህ እውነት የሚበልጥ ሌላ እውነት ደግሞ አለ።

የኢትዮጵያ መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው!

ዕድሜ ልካችንን በመከራ ውስጥ አልፈን ስናበቃ፥ የብርሃን ጭላንጭል አሳይቶ እንቁልጭልጭ የሚጫወትብን ጨካኝ አምላክ የለንም። እግዚአብሔር በምድራችን የጀመረውን መልካም ሥራ ዳር ሳያደርስ መንገድ ላይ አይጥለንም።

እግዚአብሔር ያያል።
እግዚአብሔር ይፈርዳል።
ፈጥኖ ይፈርዳል።
በቀናት ውስጥ ክብሩን ይገልጣል።

ዲያብሎስ የደገሰልን የዕልቂት እኩይ ሤራ ይገለበጣል። ኢትዮጵያ ወጀቡን አልፋ ትሻገራለች። ታበራለች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት ጁን 15 አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በሚገኝበት ይከበራል

መከራ ያየነው ከዓለም በኃጢአት አንደኛ ስለሆንን አይደለም። የቃል ኪዳን ሀገር የሆንነው ከዓለም በፅድቅ አንደኛ ስለሆንን አይደለም። ያለፈው መከራችንም ሆነ የሚመጣው ጉብኝታችን ምክንያቱ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር እንዲገለጥብን ብቻ ነው።

ጠላት ለኢትዮጵያ መበታተን ያጠመደው ክፉ ወጥመድ ለእኛ ጭንቀት ቢሆንብንም፥ ለፈጣሪ ክብሩን እንዲገልጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ምድር ሁሉ በኢትዮጵያ አምላክ አለ እስኪል ድረስ ሥራውን ሊሰራ ፈጣሪ ራሱ ይወርዳል።
ወጥመዱን ይሰብራል።
ኢትዮጵያንም ያስመልጣል።

ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡
• የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ
• አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
• ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

2 Comments

  1. ማስተካከያ፣
    ከቅዱስ ቃሉ የተወሰደ፡
    • የኩሽ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ
    • አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኩሽ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
    • ኩሽ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንማ የጠብመንጃ ማከማቻ፣ የሽፍቶች መሸሸግያ ሆናለች! የሃይማኖት አባቶችዋም ወታደር አሰልጥነው ጦርነት እያወጁ ነው። ቀጥታ ከፓትርያርኩ አፍ ስሙ!!

  2. በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ ዋናው ተጠያቂ አዝማሪና አዝማሪ ያሳደገው የሆያሆዬ ማህበረሰብ ነው።
    ጠጅቤትና አዝማሪ የሚበዛባቸው አካባቢዎች በውሸት ተረት የተሞሉ በመሆኑ ከመንደራቸውና ጎጣቸው ውጭ ማሰብ የተሳናቸውና ያንን ሌት ተቀን ሲያላዝኑ የሚኖሩ እራሳቸውን ያለአቅማቸና ያለስራቸው ያገዘፉ ጠባብ ትምክህተኞች ናቸው።መንደር መንደር መንደር እያሉ ሲያናፉ ይቆዩና እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያዊነት ይሉታል – ወዲያልኝ ወዲያ።
    የዚህ ውጤቱ ደግሞ አገርን አንድ ማድረግ ይቅርና አሁን እየታየ ላለው መገፋትና በተለያዬ የአገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ወገኖቻችንን የሰቆቃ ህይወት የጋበዘ ነገር ጥንሳሽ ትንኮሳ ሆኖ እያገለገለ ያለ ጉዳይ ነው።
    ድሮም የሚታወቀው አዝማሪ የሚያምርበት ማሲንቆ ሲያነግት እንጂ ከወንዶች ቦታ ማን ዶለው?
    አሁን ማንይሙት ጸጉር እያንጨበረሩና ክላሽ እያንዘለዘሉ ፎቶ በመነሳት ጀግና ነኝ ማለት ከጎደሎ ማንነት የመነጨ ፉለላ እንጂ ዝንጀሮስ ማስደንበር ይችላል?
    እውነተኛ የታሪክ ባለቤቶችኮ በየጠጅቤቱ፡በየድራፍት ቤቱ እንዲሁ ሲያናፉ አይሰሙም፡የእነሱ ማንነት የሚገኘው በታሪክ ድርሳናት እንጂ በየጠጅቤቱ አዝማሪ አፍ ስላልሆነ።
    የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች አዝማሪና የሴራ ፖለቲካ ናቸው!

Comments are closed.

Share