ዶክተር ዐቢይ እርምጃ እንዳይወስዱ ምን እየያዛቸው ይሆን? – ዋቅወያ ነመራ

እንቆቅልሽ እየሆነ  ያለ ጉዳይ

እኔ  የጠቅላይ  ሚኒስቴር  ዶክተር  ዐቢይ  ጭፍን  ደጋፍም  ተቀዋሚም  አይደለሁም፤ ኢትዮጵያን ግን ስለምወዳት ስላሟ፤ አንድነቷና ፤ ብልጽግኗዋ ግድ ይለኛል።  ሳየው ስውዬው (ማለትም ዶክተር ዐቢይ)  የዓለምንና የኢትዮጵያን ታረክ፤ የግፈኞችንና የወንጀለኞችን  ሥራና  ዓለማ፤    የሀገርን  ድህነትንና ብልፅግናን፤ በግል ማግኝትንም  ሆነ መጣትን ፤እንደ ግለስብም ሆነ እንደ ህገር መከበርንና መዋረድ ምን፤  የክተማን ኑሮ፤ የገጠርን ኑሮ፤ ወታደር መሆንን፤ ተራ ሰው መሆንን፤ የፖለቲከኝን ሕይወት፤ መንፈሳዊነትን፤ ሃይማኖተኛ አለመሆን ወይም አለመምሰልን፤  ባህልና ወግ ፤ አንድነት ወይም መደመር ለእድገትና ለብልጽግና ያለውን ፋይዳ፤  የሥልጣን ምንነት፤ እንዲሁም የዘረኝነትንና  የፅንፈኝነትን  መዘዝ  ጠንቅቆ የሚያዉቁ  ይመስላሉ። አንዳንዶቹ እንደሚሉ ደግሞ   ሥልጣንን የሚወዱና ሥልጣናቸውን ለመጠበቅ ሲሉ  ምንም የሚሆኑ ወይም የሚያደርጉ ፤ አማራ ጠል፤  በለ ተረኛ ወይም የኦሮሞ ዘረኞና ጽነፈኞን ሃሣብ  በስውር  የሚያስፈፅሙም  አይመስሉኝም። ታዲያ  ዶክተሩ እንዲህ  ዓይት  ስለሁሉም  ዕውቀት ካላቸው የተወሰኑ ግለስቦች  ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያጋጭ እውነት ያልሆነውን ነገር ፈጥረው  ሲያወሩ ለምን ዝም ይሏሉ?  ለምሳሌ ያህል አቶ በቀለ ገርባ  መቀሌ ንግግር አድርገው ሲመለሱ በኢትዮጵያ  ውስጥ  የግል  የትራንስፖርት ኃላፊዎች አልተደረም ያሉትን ጉዳይ ትግሬዎችን ለመጉዳት ወደ መቀሌ የሚሄድ  ትራንስፖርት ከቆመ  አንድ ዓመት  ሆነ  በማለት  ፈጥረው ሕዝን ክሕዝብ ጋር የሚያጋጭ ነገር ተናገሩ።  አንዳንድ ግለሰቦች እኛ ሌላ መንግሥት ነን ብለው ተናግረው ከአበቁ ብኃላ መንግሥት ለሕዝብ እንዳይሠራና ልማትንም እንደያካሄድ በጉልበት ሲከለክሉ  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን  ዝም ብለው  ያዩዋቸዋል? አንዳንዶቹ  በንግግርና በውይይት በማሳመንና በማማን ሳይሆን በጠመጃና በጉልበት የመንግሥትን ሥልጣን ካልያዝን ብለውን ሕዝብን ሲዘርፉና ሲገዲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ክልክ አለፋችው ብሎ ለምን አድብ አያስገዛቸውም?  ጠቅላይ ሚኒስትሩ  አአንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ ”ዱሪዬዎችን” በመንግሥት ላይ ሲያነሳሱና ዱሪዬዎቹ ሕዝብን  በመንግሥት ላይ ከማነሳሳት አልፈው ሕዝቡን  ሲዘርፉና ሲገድሉ  እንዲህ ዓይነት ሥራ እንዲሠራ በሚቀሰቅሱ  ላይ  እንዴት ምንም እርምጃ ሲወሰድ  አይታይም? አንዳንድ ግለሰቦች ደግመው የራሳቸውን መንግሥት መሥርተው ሲንቀሳቀሱ  ለምን ዝም  አሉ? እንዲሁም  በኢትዮጵያ ውስጥ በዶክትር ዐቢይ ዘመነ መንግሥት አንዳንድ የዜና አውታሮች  (ለምሳሌ ኦ አኤም ኤን [OMN] በመባል የሚታወቃው አውታር)   ያልተበረዘውን እውነተኛ ዜና  ለሕዝብ  እንደማቅረብ  ክላይ ለተጠቀሱት ግለሰቦች የማወናበጃ መድረክ ሆነው  ሲያገለግሉ ይስተውላሉ።

በኔ ግምት ለኢዮጵያ ደህንነትና ጥቅም ዶክተር ዐቢይ እላይ በተጠቀሱት ግለሰቦችና ድርጅት ላይ እርምጃ መውሰድ አለባቸው። እነኚህን  ግለሰቦች  መንካት በመንግሥት ላይ  ጊዜያዊ  መዘዝ ሊያመጣ ይችላል። አቶ ጀዋር ከተኛ የኦሮሞ ዲጋፍ እንዳለው አውቃለው፤ ይሁን እንጂ አብዘኛው ኦሮሞና ቄሮዎች  እንደ አቶ ጀዋር ወፍራም ገቢ በየወሩ አያገኙም፤ ልጆቻቸውን አሜሪካ እያስተማሩና  ሚስቶቻውን  አሜሪካ በቅንጦት እያኖሩ አይደሉም ና ይህ እውነት መታወቅ አለበት፤ ደጋግሞም መነገር ይገባል። ባንኮችን የዘረፋውን ኦነግን  እሹሩሩ እያሉ አቶ ጀዋርን ማስር ወይም ክሀገር ማባረር ወይም አቶ እስክንደርን መንካት ፍትህነቱ አጠያያቂ ሊሆን ይችላል፤ መታውቅና መነገርም  ያለበት እውነት  ግን ኦነግ በሰላም ብቻ እየታገለ  ሲሆን  አቶ ጀዋር፤ አቶ በቀለ እና  አቶ እስክንድር በሥራቸው ቀጥለዋል (ደግሞ ባለፈው ጊዜ ብዙዎች ጥፋት አጥፍተው ይቅር ተብለዋል)። ሌላው ነገር ደግሞ  እንደአነ  አቶ ጌታቸው አሰፋ ያሉቱ ወንጀለኛች መቀሌ መሽገው እያሉ በእነ ጁዋር ብቻ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ላይመስል ይችላል፤   ግን እኮ እውነቱ ነገር  ቀስብቀስ ሕግ ወደ  እነ አቶ ጌታቸው አሰፋና ግብረ አበሮች መምጣቱ አርቀሬ ነውና አሁን ግን አዲስ አበበ ውስጥ ባሉቱ ወንጀልኞ ላይ  እርምጃ ይወሰድ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤ.ል ሽልማት (Nobel Prize) ሕልም ይኖራቸው  ይሆን? ከሽልማቱ ኢትዮጵያ ትበልጥባቸዋለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገር አጥፍ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ ምን እየያዛቸው ይሆን? ይህም የኔና የብዙ ሰው እንቆቅልሽ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትህነግ የለየለት ጭራቅ በመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ለመደራደር አይቻለም – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

እውነት ይነገር ክተባለ እኔ ሆንኩ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር ዐቢይ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያዊያን  አሁን ያላቸውን ዕውቀት ማንም የለውም ብዬ እግምታለሁ። በአሁኑ ጊዜ እኔ ከውጭ ስመለከት ስለህግሪቱ የነገ ሁኔታ ፈፅሞ የማያዩና ስለነጋም የሕዝቡ እድል ፈንታ ፈጽሞ ደንታ የሌላቸው ጽንፈኞችና መቀሌ የተመሽጉ ወንጀለኞች  ወደ መንግሥት ሥልጣን ለመድረስ ሲንጠራሩ እያዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዴት ዝም ሊሉ  ቻሉ?  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገር አጥፍ ጽንፈኝ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ ምን እየያዛቸው ይሆን? ሕዝቡም ሆነ ህገሪቱ  ላይ ደስ የማይሉ ሁኔታዎች  ክደረሱ ወደ ኋላ መመለስ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገነዘባሉ ይሆን? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  እርስዎ  አንድ ጊዜ ከሥልጣንዎ  ከተውገዱ  በኋላ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ  አስበው ያውቃሉ?  የሚያውቁ ክሆነ ለፅንፈኛ ወንጀለኞችና  ወንጀለኞቹ የመንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ  እንደምንጠራሩ ተሳክቶላቸው  ተባብረው ሥልጠን ከያዙ ለብዙ ምስክን ሕዝብ የማይምቹ  ስለሚሆን አሁንኑ  ጠንከር ያለ እርምጃ ወይም መራራ እርምጃ  በመውስድው ሀገርንና ሕዝብን ማዳን አይሽልም (አይመረጥም)?

ከዚህ ቀጥሎ ስለአቶ ጀዋርና ስለ አቶ እስክንድር ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል።

እስክንድር ንጋ  የወያኔን መንግሥት በመቃወሙ አሥራ ስምንት (18) ዓመት ተፈርዶበት የታሰረ ጋዜጠኛ ፤ የስው መብት ተሟጋችና ብሎገር ነበር።  ከወጣም  በኋላ እነኝህን ሥራዎች መሥራት ይችላል። አሁን እያደረገ እንዳለ የቴሌቪቪን አውታር ባለቤትም  ሊሆን  ይችላል።  ከፈለገም   መንግሥትን   ለመቃወም የራሱን ተቋውሚ ፓርቲ መስርቶ መቃወም መብቱ ነው።  እነኚህን ሥራዎችን  ሲሠራ ከመንግሥት ሆነ ከሌላ ምንም ቢደርስበት ሁሉም ከጎኑ ኢትዮጵያውና የኢትዮጵያ ሊቆሙ ይግባል።  ይሁን እንጂ ‘ባለ አደራ ምክር ቤት ‘የሚባል የራስ ስውር መንግሥት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ሌላ ጉዳይ ነው። ብርገድየር ጄኔራል አሳምነው ዶክተር አምባቸውን በጥይት እንደገደለ ሁሉ አቶ እስክድር የዐቢይን  መንግሥት  በሥራቸውና በምላሳቸው በየቀኑ  በዲሞክራሲ ስም እየገዘገዙ ነው። ይህን በማድረጋቸውም   አቶ እስክንድር  ጸረ ለውጥ አቋም እየያዙ መጥቷል።አሁንማ የወያኔ ካድሬ የነበረ ኤርሚያስን  ምክትላቸውና የውጭ ሀገር. አፈ ቀላጤያቸው አድርገዋል። ይህ ለውጥ  አቶ እስክብድርንም  18 ዓምት  ተፈርዶባቸው ይማቅቁ ከነበሩበት የእስራት ዘመን ያዳናቸው ነው።   አቶ እስክንድር “በወያኔ ዘመን እንኳ እንዲህ ያለ ሕገ ወጥ ሥራ አልተሠራም” ብለው  ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡት  እርሳቸውን ያሠረው ስርአአት እሷቸውን  ከፈታው ስርአት ይሻላል ማለታቸው ይሆናል ። ይህ ደግሞ ሐገር ወዳድነትም ጀግንነትም ሳይሆን በአቋራጭ ዝነኛ ሆኖ ለቅረብ የሚደረግ ሩጫ ሊሆን ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለኦርቶዶክስ ስኖዶስ

በመሠረቱ  ሐገር ወዳድ ወይም ጀግና ለመባል ወይም ለመሆን  ለሕይወትና ለጥቅም ወይም ለሚቀርቡት ( ይህም አባት፤ እናት፤ ልጅ፤ሚስት ፤ ባል ወዘተ)ሕይወትና ጥቅም  ሳይሉ በጊዜው የሚያስፈልጋውን ለማድረግ መዘጋጀትን ያመለክታል። በዚህ ሚዛን አቶ እስክንድር ትናንት የአደረጉት ድርጊታቸው ሲመዘን ሐገር ወዳድና ጀግና ሲሆኑ ፤ ዛሬ ግን የትናትና ታሪካቸውን እያሳደፉ ናቸው። ሐገር ወዳድ ወይም ጀግና ለመባል ወይም ለመሆን  የራስ ሕይወትና ጥቅምን ሆነ የሌላውን ሕይውትና ጥቅም መስዋዕት ማድረግ ብቻ ሳይሆን መስዋዕትነቱ ለሐገርና ለሕዝቧ እውነተኛና ዘላቂ ጥቅም ሲሆን ብቻ ነው። እንደዚህ  ካልሆነማ  አንድ ስው  ስክሮም ሆነ አብዶ የራሱን  ሕይወት  ይሁን  የሌለውን ሕይወትና ጥቅም ሊስዋ ይችላል።   በአንድ ጊዜ ሁለት መንግሥት ሊኖር ስለማይችል በሐገሪቱ ያለው መንግሥት የባለ አደራውን ምክር ቤት ማፍረስ አለበት።

የባለ አደራው ምክር ቤት መሪ አቶ እስክንድር ዓይነት ስው  ያሐገሪቷን የትናንትናን የመጥፎ ግጽታ እየሳሉ  ዛሬ ያለውን ለውጥንና እውነትን አለመቀበል  የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሲሆን የሚያደርጉትም ሥራ  በዕውቅትና በእውነትም ላይ የተመሠረተ አይደለም።   በትናንት ዓለም የሚኖሩ ዘረኞች (ጎስኞች)  የአዲስ አበባ የከተማን  የማንነት ጥያቄ ያነሳሉ።  ተወደደም ተጠላ በዲሞክራሲ ቅራኔዎች የሚፈቱት በውይይትና በውውይት ብቻ ነው።፡ በዲሞክራሲ  ሕግ መሠረትም  በጣም የታወቁና የተከበሩ ግለስቦችና ቡድኖች  በስነሥርዓት ስለአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ  ተገቢውን መልስ እየስጡ ይገኛሉ። እዚህ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት በአንድ ወቅት ስለ አዲስ አበባ የማንነት ጉዳይ  የተናገሩትን ለምሳሌ  መጥቅሱ ተገቢ ይሆናል። ከተማይቷን  በወጉ የሚያስተዳድር  መንግሥት እያለ  “ባለ አደራ ምክር ቤት”ብሎ ሌላ መንግሥት የሚመስል ድርጅት  ማቋቋም  አስፈላጊም ተገቢም  አይደለም።  ይህንን  ድርጊት  አንድ  ያልስለጠነ  (uncilized or uncultured) ስው ቢያደርግ ድሮስ ተብሎ ይታለፍ ነበር ። ግን እኮ  የበለ አደራውን ምክር ቤትን የሚመራው  የቀድሞ የሕግ እስረኝና  የስው መብት ተሟጋች ስለሆነ  ድርጊቱ  ለምን የሚል ጥያቄ ያመጣል። ከዚህ በፊት የትነግ ካድሬና አክራሪው የእሳት ጋዜጠኛ ምክትሉ ሲሆን አያፅናናም።

 የባለ አዳራውን ምክር ቤት ጉደይ ካነሳን  ዘንዳ  መሪውን በእውነትና በዕውቀት ላይ ሳይመሠረት በጭፍን የመደገፍና  በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት  በስመ መንግሥትነት የመቃወም አዝማሚያ ይታያልና ይህንን ጉዳይ  አስመልክቶ  እቅጩን መናገር  ተገቢ ይሆናል።  የባለ አደራውን ምክር ቤት መሪን  በጭፍን መደገፍ ስውየው ከዚህ በፊት ደጋግሞ ስለታሠረ ለዚያ ውለታ ለመክፈል  ተብሎ  ይመስላል። እንደዚያ ከሆነ  ትነግ (TPLF)  ጫካ ገብቶ የደርግ መንግሥትን ጥሎ  ኢትዮጵያን በጎሣ ከፋፍሎ 27 ዓመት መግዛቱና መበዝበዙ ከዚያ በፊት 17 ዓመት ለታገለ  ትግል የሚገባው ወሮታና  መብቱ ነው እንደ ማለት ይሆናል። ማንም ስው ለሐገሩ ቢታሠር  በኋላ በሕይወት ዘመኑ  ለመካስ አስቦ  ሳይሆን  ለሐገሩ የተከፈለ  ነፃ ዋጋ ነው። በቀውጢ ጊዜ ለሐገር ነፃነትና ለሕዝቦች እኩልነት የታሰሩም ልጆችዋንም  ሐገር ታመስግናለች ታከብራቸውላች እንጂ ለማንኛውም ግለስብ ሆነ ቡድን ከዚህ በፊት ስለ ሠራው  ሥራ ሐገር የምትከፍለው  ዕዳ የለም።

“ኣክቲቪስት” ጁዋር ሙሐመድ   ስለወያኔ ብዙ እውነቶችን ስለተናገረ ወደ  ኢትዮጵያ መምጣትና ሐገሪቱንም ማየት የማይችል ሆኖ ሳለ ይህ መንግሥት ባመጣው ለውጥና በተገኝው ነፃነት ወደ ኢትዮጵያ መግባት የቻለ ሰው ነው። ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋለ ግን ዘረኝነትን አጥብቆ ያቀነቅናል፤ መንግሥቱ “እየተሽመደመደና”  “ማስተዳደርም እያቃተው ነው” እያለ ቃለ መጠየቅ ይሰጣል (በረከት ስም ኦንም በመቀሌ ዩኒቨሲቲ በአደረጉ ንግግር ይህንኑ ነበር የተነገረው)። ጀዋር  መንግሥቱን  የሚያየው ሐገርን ለማስተዳደር ኅላፊት እንዳለ አከል ሳይሆን “እንደ አህያ ከኋላ እተገረፈ የሚነዳ” ምንንም በራሱ አስቦ ማድረግ የማይችል እንደሆነ ነው። ቄሮዎች በሱ ትዛዝ ሥር የሚንቀሳ ቀሱ ስለሆኑ ተነሱ ብሎ በመንግሥት ላይ በፈለገ ጊዜ ሊያስነሳ እንደሚችል ሲናገር ይደመጣል። ጃዋር ኤሪቶዎችን (የሲዳማ ወጣቶችን) ለአመፅ  ያነሳሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንዳስቀመጧቸዉ  ስላሉ ነዉ ! - ማላጅ

ጃዋር የኦሮሞ ሕዝብ እንደሚያስበው አቃፊ፤ትሁትና ሰጪ ሳይሆን ዘረኛ፤ትብተኛና የራስ ጥቅም አሳዳጅ ነው። ለምሳሌ  ከዚህ በፊት ፓሊስ በግልጽ ያስተባበለውን አርባ ሶስት (43) አሮሞዎች  በአንድ የአዲስ አበባ ከተማ ቀበሌ  ውስጥ እንደተገደሉ አድርጎ  ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ የሀሰትና የፈጠራ ወሬ አውርተዋል።  ኮየፈቻ የምትባል ለአዲስ አበባ ከተማ ቅርብ ሆና ግን  በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  ውስጥ የምትገኝ መንደር ናት። ታዲያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮየፈቻ መንደር  ለአንዳንድ ነዋሪዎች ቤት ሠርቶ ዕጣ  ለደርሳቸው  ሰዎች  በቱን ሊያስረክብ ሲል ጃዋር  እነኚህ ሰዎች  ቤታችውን  መረክብ የሚችሉቱ  በሱ ሬስ ላይ ተረማምደው እንደሆነ ተናግሮ  ቃሉንም እንዴት  ማስከበር እንደፈለገ ሲያሳይ  ሚስማር የተመታበትን ዱላ የያዙ ጎረምሳዎችን አስለፈ።  ጃዋር በሕዝብ ንብረት ተቋቁሞ የሕዝብ ንብረት የሆነውን  ኦ ኤም ኤንን (OMN) የቦርድ አባሎቹን ከባረረ በኋላ  ድርጅቱን  የግሉ ንብረት አድርጎ እንደሚጠቀምበት ይነገራል።

እነዚህና የመስሉት ድርጊቶች ጃዋር ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ያደረጋውን ለውጥ አሁን ይደግፋል ወይ ብሎ ከመጠየቅም አልፎ ሰውዬው ወንጀልኛም ሊሆን እንድሚችል ይጠቁማልና መንግሥት ሁኔታውን አጣርቶ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ በጃዋር መሐመድ ላይ መውሰድ አለበት። በጃዋር ሙሐመድ ላይ ሕጋዊ እርምጃ ቢወሰድ “እንዴት” ብለው ድምፅ የሚያሰሙ ሊኖሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የትኛውም ግለሰብ ቢሆን ከሕግ በላይ አይደለምና እርምጃ መውሰዱ ተገቢ ነው።

የዶክተር ዐቢይ መንግሥት ቢቀበልም  ባይቀበልም  በኢትዮጵያ ውስጥ  አና በኢትዮጵያ ወዳጆች የሚወራ አንድ እውነት አለ። ይህም እውነት ከዚህ በፊት የነበሩ ገዢዎች ብዙ ቃል ገብተው ስለአልፈጸሙ አሁን የትኛውም ወደ ሥልጣን የሚመጣ መንግሥት አይታመንም። ለመታመንም መንግሥቱ የሚናገረውን በተግባር ማሳየት አለበት። የዶክተር ዐብይም መንግሥት “ኢትዮጵያ” “ ኢትዮጵያ” ሲል መጥቶ የሕዝቡን ቀልብ ስቦ ነበር።  ይሁን እንጂ ጁዋር ሙሐመድና በዳውድ ኢብሳ ይመራ የነበረው ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሐገርን  ሲያተራምሱ እያየ መንግሥት ዝም ብሎ ማየቱ ታማንነቱን ክፉኛ ጎድቶታል ። ብዙዎቹም የለውጡን መንግሥት ደጋፊዎች   መንግሥቱ በእነጁዋር ላይ በዚያን ጊዜ ምንም እርምጃ አለመወሰዱ ይሆናል አቶ እስክንድር ነጋ ተዳባይ መንግሥትን አቋቁሞ ሲንቀሳቀስ ጥቂትም ቢሆኑ ደጋፊዎችን እንድያግኝ ያደረገው ይላሉ። አሁንም ቢሆን ኦነግ አካሄዱን እያስተካከለ የመጣ ይመስላልና መንግሥቱ በጀዋር ሙሐመድ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት።

 

 

1 Comment

  1. “………ኮየፈቻ የምትባል ለአዲስ አበባ ከተማ ቅርብ ሆና ግን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የምትገኝ መንደር ናት። ታዲያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮየፈቻ መንደር ለአንዳንድ ነዋሪዎች ቤት ሠርቶ ዕጣ ለደርሳቸው ሰዎች በቱን ሊያስረክብ ሲል ጃዋር እነኚህ ሰዎች ቤታችውን መረክብ የሚችሉቱ በሱ ሬስ ላይ ተረማምደው እንደሆነ ተናግሮ ቃሉንም እንዴት ማስከበር እንደፈለገ ሲያሳይ ሚስማር የተመታበትን ዱላ የያዙ ጎረምሳዎችን አስለፈ።…….”

    ዋቅወያ ነመራ!!!!

    Yih yemizelabidew Oromoo lememsel new. Ayi nafxanyana shintochu. Ahunim Oromoon indetilantu ajaajilo yebelayinetachewun lemasqexel yasibalu. Monyooch, jiloch. Isuun tewuut ahun. Iwunet hager yemitiwedu kehone indet meqexel indalebin asibu. Ciraquu wayaneem siyaqitew ferexexe. Adiro qariyaa/kermooxijaawoch zim bilew yelefalu. Oromoo ymiserawun zim bileh temelket ahun. Atijaajaal.
    Koye Fache Oromiyaa killil wusxi kehone leeboochuu lemin hedewu iziyaa bet seru????? Camilaaqaa. Beetoochu fersew legeberew memeles neberebet maretu. Indawum Jaawaar godtoonaln. Mewused yeneberebinin irmijaa hulluu iyekelekelen techegerin. Isuum yenefxenyaa shint indayihon yasegal!!!!

Comments are closed.

Share