ሥውሩ (ገጽ አልባው) ሕወሐት – ኢኑሻ አየለ

የመቀሌው  የደጺ ግሩፕ በተለይ በአዲስ አበባ ያሰማራቸው ኤጀንቶቹ በሁለት ነገሮች ላይ በስኬት እየሠሩ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡

ከነዚህ ሰሞነኛ የሤራ ተግባሮቹ ውስጥ አንዱ ሙስና ሲሆን፣ ሙስናን ከሃያ ሰባቱ ዓመት የጨለማ ዘመን በባሰ ሁኔታና በረቀቀ መንገድ በአገሪቱ እንዲስፋፋ ማድረግ ዓላማው አድርጎ እየሠራበት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የጦር መሣሪያ ማዘዋወር ከባድ ነገር እየሆነ በመምጣቱ ሌሎች መሣሪያ የማይጠይቁ ፀረ ደኅንነት መሰናክሎችን ልክ እንደ ቲማቲም ማሣ ችካል እዚህም አዚያም መቸከል ሌላው ስትራቴጂክ እቅዱ ሆኖ እየተገበረው ነው፡፡ ይህ የደኅንነት ሥጋት ደግሞ በከተማው ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝርፊያዎችን መፈፀምና ነዋሪዎችን ማማረር ብሎም ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ ታዲያ ይህን እኩይ ተግባር ሲፈጽም እንደተለመደው እንደ ርኩስ መንፈስ ከእይታ ውጪ ሆኖ አሻራ ሳያስቀር ወንጀሎችን በታላቅ ጥንቃቄ መከወን ነው፡፡ የኦዴፓ ሰላዮች ዓይኖች ደግሞ እነ እስክንድር ነጋ እንቅስቃሴዎች ላይ ተቸክለው ስለቀሩ የሥውሩን የሕወሐትን እጆች ለማየት ገና አልታደሉም፡፡ ስለዚህም በከተማይቱ ውስጥ የሚታየው የዘረፋ እንቅስቃሴ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ ሕወሐትም ይህ ሤራው የታቀደለትን ግብ እየመታ መሆኑን ወደ መቀሌ የሚላኩት ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡

የነዚህ የሁለቱም ሤራዎች ዓላማዎች ግልጽ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ‹‹ሙስናው አሁንም አልቀነሰም !!! ጭራሹንም በባሰ ሁኔታ ተጧጡፎ ቀጥሏል!!!›› ስለሚያስብል ለነጌታቸው አሰፋም ሆነ ለሁሉም የሕወሐት አባላት ለጥፋት ማቅለያነት ብቻ ሳይሆን ኦዴፓንና አዴፓን ከደሙ ላለማንጻት ፍቱን መድኃኒቶች ናቸውና የመቀሌው ቡድን በሚገባ ይጠቅማቸዋል፡፡

ልክ እንደዚሁ የደኅንነት ሥጋቱን ማጦዝ ደግሞ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ‹‹ሰው ካልሄደና ካልሞተ አይመሰገንም›› እስኪሉ ድረስ ነዋሪዎቿን በከፍተኛ የሥጋት ቅርቃር  ውስጥ አስገብቶ ‹‹እነ ዐቢይ ማስተዳር አልቻሉም›› (ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም) የሚለውን ሕወሐታዊ ትርክት ማስረገጥ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰሜን ወሎን ወደ“ደቡብ ትግራይ” ደቡብ ወሎን ደግሞ ወደ “ሰሜን ኦርምያ” የማጠቃለሉ ቅዠት (እውነቱ ቢሆን)

በከተማችን በአዲስ አበባ ውስጥ የጦር መሣሪያ ሳያዘዋውርሩ በቀላሉ የሚያከናውናቸው እነዚህ ሁለቱ መስኮች በዚህች ቅጽበት ውስጥ በሰፊው እየተሠሩባቸው ለመሆኑ ማስረጃዎች አሉ፡፡

የዘረፋው ነገር በዚያን ሰሞን ታከለ ኡማ ሞተር ሳይክል በከተማዬ ውስጥ ማየት አልፈልግም ልክ ብሎ እንደ በረሮ በከተማይቱ መንገዶች ላይ ሲርመሰመሱ የነበሩትን ሞተር ሳይክሎችን በድነገት እገዳ ሲጥልባቸው  የቀን ዘረፋው በሚያስገርም ደረጃ የቀነሰ ቢመስልም አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ በአዲስ ስልት መጥቷል፡፡ ተሸከርካሪዎችን መሠወር፣ በተቀነባበረ መንገድ ሰዎችን እያገቱ መዝረፍ የመሳሰሉትን ፕሮፌሽናል በሚያስብል መልኩ አገሬውን ብቻ ሳይሆን፣ እንዲያውም በሚገራርሙ ስልቶች የውጭ ዜጎችን ዒላማ አድርገው እየተካሄዱ  ይገኛሉ፡፡

የሚገርመው ነገር ዘረፋዎቹ በተራ ሰዎች አይካሄዱም፡፡  የሚካሄዱትበጣም የዳበረ ዕውቀት ባላቸው ግለሰቦች ነው፡፡ ቻይናዎቹ በጣም ብዙ የሚባሉ ተሸከርካሪዎች ተሠውረውባቸዋል፡፡ አንዳንዴም ካቆሙባቸው ቦታዎች፣ አንዳንዴም እባክህን አሽከርክርልን ብለው በደመወዝ በቀጠሩአቸው ተቀጣሪ አሽከርካሪዎቻቸው አማካኝነት፡፡

በጣም በርካታ የኮንስትራክሽ መሣሪያዎችም እንዲሁ ተሠውረዋል፡፡ ወዴት ይወሰዳሉ የሚለውን ለጊዜው ባንመልሰውም ከሰሞኑ ግን ለተዘራፊዎችም ለመንግሥትም ግብአት የሚሆኑ ሚስጥሮችን ጀባ እንላቸኋለን፡፡

ለነደጺ የሚያስገኙት ጠቀሜታ ግን ከላይ እንደገለጽነው ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚያዊም መሆኑ አሌ “አይባልም፡፡ በዚህ ረቂቅ አሠራር ላይ ከሰሞኑ በተሸለና በበለጠ መረጃ ብቅ ለማለት ቃል እንገባለን፡፡

በሙስናው ረቂቅ ሥራ ላይ ግን የደረሱን ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚጠቁሙን ከሆነ የታከለ ኡማ የአዲስ አበባ መንግሥት በአዲሱ ዓመት ዕቅድ የያዘላቸውን ፕሮጅክቶችንና የልማት ሥራዎችን ማሰናከል ወይንም መጓተትን የሚፈጥሩ አሻጥሮችን መጫወት  ከዒላማዎቹ  ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡

ከሰሞኑ በአንዱ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ፕሮጅክት ላይ የተደረገውን አሻጥር እንደምሣሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አስፈሪው የውድቀት አዙሪት - ጠገናው ጎሹ

ኤጀንሲው ክረምቱ ሲወጣ በወርሃ መስከረም ላይ እሠራለሁ ብሎ ከያዛቸው ፕሮጅክቶች ውስጥ አንዱ የመንገድ ቅብ (ሮድ ማርኪንግ) ነው፡፡ ፕሮሰሱን የጀመረው ከስድስት ወር በፊት ሲሆን በዓለም አቀፍ ጨረታ  ተጫራቾችን አወዳድሮ ሥራውን ለአንድ የዓለም አቀፍና ለአንድ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ለመስጠት ዝግጅት በሂደት ላይ ሳለ በውድድር የተሸነፉና በዘመነ ሕወሐት ሥራውን በርስትነት ይዘው ቆይተው የነበሩ ድርጅቶች በግንባር በመሆን ከግዢ ሥርዓቱ በወጣ ሁኔታ በአዲስ አበባ ፋይናንስ ዲፓርትመንት ሥር ለሚገኘው የቅሬታ ሰሚ ክፍል ቅሬታ አለን በሚል በህገወጥ መንገድ ቅሬታቸው እስኪታይ ድረስ የጨረታው ሂደት እንዲቋረጥ ያስደርጋሉ፡፡

አካሄዱን ሕገወጥ የሚያደርገውም በቴክኒክ መመዘኛ የወደቁት እነዚህ ሰዎች በቴክኒክ ውጤቱ ላይ ቅሬታ አቅርበው ኤጀንሲውም ለቅሬታቸው በቂና አጥጋቢ መልስ ከሰጣቸው በኋላ በውሣኔው ባይስማሙ የቅሬታ ቅሬታ ማቅረብ እየቻሉ ያንን ሳያደርጉ ቆይተው ፋይናንስ መመዘኛው ውጤት ከተከፈተ በኋላ ውጤቱ ለተወዳዳሪዎች ተገልጾ አሸናፊዎች ከተለዩና ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ጉዳዩ ለማይመለከተው አካል ጊዜውን ያልጠበቀ ቅሬታ ማቅረባቸው ነው፡፡

በአጭር አገላለጽ የሰዎቹ ፍላጎት ጨረታውን በዚያም በዚህም ብለው (በእጅም በእግርም ብለው) እንዲሠረዝ ማድረግና ፕሮጅክቱን ማጓተት ስለሆነ ከውስጥ  ባሉአቸው የነሱ ሰዎችና በገንዘብ ኃይል ሕገወጥ የሆነ  ውሣኔ አስወስነው ሥራውን እያጓተቱት ይገኛል፡፡ ውሣኔውን ያልተቀበለው ኤጀንሲም አላስፈላጊ መጓተት ውስጥ ገብቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ገላጋዩ ታከለ ኡማ ስለሆነ የኡማ ልጅ ምን እንደሚያደርግ ከሰሞኑ የሚታይ ይሆናል፡፡

ለማጠቃለል፣ ‹‹ ባልበላውም ጭሬ እበትነዋለሁ›› እንዳለችው ዶሮ በእልህ ፖለቲካ ጨርቁን ጥሎ ሊሄድ የደረሰው ሕወሐት የዚህችን አገር ሰላም ማመስ መቀጠሉን ተያይዞታል፡፡ ስለዚህ መንግሥት ለነዚህ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተስፋ ሳይኖር ተስፋ መቁረጥ: የተስፋ ቢሶች ተስፋ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ሙስናውንም መከታተል በተለይ ደግሞ በከተማው ውስጥ እየተቀጣጠለ የሚገኘውን የደኅንነት ሥጋት ምንጭ የሆነውን ዘረፋ በውጭ አገር ባለሙያዎች በመታገዝ ባስቸኳይ ለጉዳዩ እልባት ቢያበጅለት ይሻለዋል፡፡ እግረ መንገዱንም የሕወሐትን ሤራ ኦዴፓ ብቻውን ሊቋቋመው እንደማይችል አምኖ መቀበልና ለዚህም ችግር መውጫ ፖለቲካዊ መፍትሔ ቢያፈላግለት ይበጀዋል፡፡

ኢኑሻ አየለ

4 Comments

  1. ገፅ አላቸው፣ የተዋቀሩም ናቸው፣ እንደየጠባያቸው በማጣራት ያዋቀራቸውም መለስ ዜናዊ ነው፣ ምንም እንዃን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ባለፉት ሁለት አመታት ላይ አንዳንድ ገመድ ቢበጠስባቸውም፣ በሰፊው ሲታይ ግን አሁንም intakt ናቸው

    እነዚህ ስብስቦች የትግራይ ህዝብ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ ሃብት ዘራፊዎች ሲሆኑ፣ ቁንጮዎቻቸውም እንደሚከተለው ናቸው:
    1. ኢሳያስ ኣፈወርቂ
    2. ስብሓት ነጋ
    3. መለስ ዜናዊ
    4. ተላላኪያቸው ስዩም መስፍን
    5. ከአራት እስከ አምስት የሚሆኑ በእናቶቻቸው ተጋሩ፣ ግን ተጋሩ ካልሆኑና ሃይለስላሴ መንግስት የትግራይን ህዝብ ያንገላቱ ዘንዳ ከላካቸው የተራ ወታደር ልጆች የተወለዱና ለትግራይ ህዝብ አንዳችም ቅንጣት ወገናዊነት የማይሰማቸው ሳዲስቶች
    6. ባንዶች መልምለው በዝቃጭ ተግባራት ዘንዳ ያሰማሩዋቸው አንድ ወደ 20 የሚሆኑ ዓንሰባዎች እንደ ኑግ ወቅጦው ሊወጣ በመይችል ኮምፕሌክስ ያላሸቋቸው የኣባሻውል ዓጋሜዎች
    7. ማሌሊት ስነ ህሊናቸው ዝቅተኛ ስለሆኑ ያልኳቸውን በማከናወን ለዝርፍያ ተግባራቶቼ ይጠቅሙኛል በማለት በጠቅላላው ኢትዮጵያ የበተነቻቸው ሆዳሞች

    ካለፈው አርባ አመታት ጀምሮ በትግራይ ህዝብ ላይ ለደረሰው በደልና፣ ባጠቃላይም በተለይ ባለፈው 27 አመታት ላይ ላይ ለደረሰውና እስከዚች ደቂቃ ድረስ ላለው ለዝርፍያ የሚያመቸውን “no war no peace” እና “ግርግር ለሌባ ያመቻል” አይነት ስርአቶች በኢትዮጵያ ምድር ላይ ስር መትከል ተጠያቂው ይሄ ብልሹ organ ነው!!

  2. የህወሀት እጅ የሌለበት ቦታ የለም፡፡ ይህ ሐቅ ነው፡፡
    በአዲስ አበባ እውነቱን ለመናገር ሙስና ጣሪያ በጥሶ ሄዷል፡፡ በዚህ ሰዓት የፖለቲካ ሥልጣኑን የተረከቡት ኦዴፓዎች ህወሀቶችን እያስናቁ ለመምጣታቸው አጠራጣሪነት የለውም፡፡ ገና ለገና ግን ህወሀት አኩርፎ የተንኮልና የጥፋ ሥራ ላይ ተጠመዷል በሚል ብቻ በዓለም ላይ ያለውን ኃጢአት በሙሉ እነርሱ ላይ ብቻ መለጠፉ የዋህነት ይመስለኛል፡፡
    ኦዴፓዎች ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ መልኩ መሬትን መቸብቸብ ብቻ አይደለም ነገር ግን የኦሮሞን ገበሬ በእጥፍ በእጥፉ እያፈናቀሉ ይገኛል፡፡ ጣታችንን ህወሀት ላይ ባቻ ስንቀስር ለኦዴፓዎች ጥሩ ማላከኪያ እያዘጋጀንላቸው መሆናችንን መዘንጋት የለብንም፡፡
    እርግጥ ነው ህወሀት በፖለቲካና በኤኮኖሚው ላይ የሚጫወተውን የረቀቀ አሻጥር የሚስተው የለም፡፡ በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ላይ እየተደረገ ያለው አሻጥር ግን ልክ ነው፡፡ የቅሬታ ሰሚ አባላትን አውቃለሁ፡፡ ስማቸውን መጥራት ግን ለጊዜው አልፈግም፡፡ ይህን ያህል ጊዜ ውሳኔውን ሲያጓትቱት የመሰለኝ በአዲሱ አደረጃጀት ምክንያት ነበር፡፡ ለካስ ድፍረት አጥተው ነበር ጊዜ ሲፈጁ የነበረው፡፡ ውጤቱም እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠረጠርኩም ነበር፡፡ ሙስናው ግልጽና ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም የታሪኩን (የቅሬታውን) ውስጡን አውቀዋለሁ፡፡ ስለዚህ ኮሚቴው ያንን ውሣኔ ባያሳልፍ ጥሩ ነበር፡፡ መረነረ ታደርጉታላችሁ!!!

  3. ‘It is about time the Tigrai government and the TPLF stop the nonsense policy of “we are Mother Teresa of Ethiopia”.’

    ይላል “ሃዘንተኛው” የማሌሊቱ Sklavenhalter (TOL) ድረገፅ ከሎንደን ሆኖ ሁለት የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት መገደልን አስመልክትሎ አማርሮ ሲያስማርርና አልቅሶም ስያስለቅስ::

    መቸም ጆሮ የማሰማው ነገር የለ፣ ደግሞ ማሌሊት “Mother Teresa” ሆነች? ለመሆኑ ይሄ ቅፅል ካሁን በፊትም በማሌሊት ላይ ተሰንዝሯል ወይንስ አሁን በ’Sklavenhalter’ሩ ተጀምሮ ለወደፊቱ ግን ቀስ በቀስ ለጠቅላላው ኢትዮጵያ ሊተላለፍና ሊለመድ ነው ማለት ይሆንን?

    ሁለት ሁለት እያለች ትግራይ/ኢትዮጵያ ግን ምርጥ ምርጥ ልጆችዋን ማጣት እየቀጠለ ነው ማለት ነው፣ ሁለት ሃገራቸውን በመጠበቅ ልምድ ያላቸው ጀነራሎች ልጆችዋ በገዛ ሳሎናቸው ውስጥ ሂይወታቸው አለፈ፣ ለምን እና እንዴትስ የመድረሱ ጉዳይ ግን እንደተድበሰበሰ ነው፣ አሁን ደግሞ ሁለት ወጣት ልጆችዋን የሆነ ሃይል ከሰብል ውስጥ ሆኖ ሂይወታቸውን አሳለፈ፣ ይሄኛው የልዩ ምርጥ ልጆቿ ሂይወት ማለፍ ደግሞ ለሁለት ቀናት ያህል ለጥላቻ ፕሮፓጋንዳነት ካገለገለ በኋላ ተንጠልጥሎ ሊቀመጥ ነው ማለት ነውን??
    ” Mother Teresa of Ethiopia” መባል የጀመረችው ማሌሊት ደግሞ፣ ነገሮችን ሙሉ ለሙሉ አጣርቶ ፍርድ መስጠትና ባጠቃላይም ነገሮችን መቋጠር፣ ውጥኖችን ከግብ ማድረስ፣ ግጭቶችን አብርዶ በሰዎችና በህዝቦች መሃከል ሰላምን ማስፈን ሳይሆን፣ ብቻ እንድያው ሁለመና ውጥንቅጥን አንጠልጥሎ ማሳደርና ለዘረፋ መሳርያ አድርጎ እየተጠቅመች፣ በጎን ግን የህዝብን ደም ስር ማጋል ልምዷ ከሆነ ይሄው አርባኛውን አመት ይዟል፣ እስካሁን የተጀመሩ ጉዳዮች እንጂ የተከናወኑ ተግባራት ታይተው አይታወቁም፣ የሚከናወኑ ነገሮች ቢኖሩ፣ ሃገሪቱን መበዝበዝና በኢትዮጵያ ስም ገንዘብ ከሃያላን መንግስታትም ሳይቀር እየተበደሩ፣ ይሄንኑ ኢትዮጵያ ላይ የተጫነውን እዳ በግል ስም ገንዘቡ ወደ መጣበት ሃገር መልሶ በንክ ውስጥ መክተትና ከዚያም በህዝቦች መሃከል ግርግር ለሌባ ያመቻል ሁናቴዎችን ማቀነባበርና የሌባ አይነደረቆችን ማስጨፈር! ይሄ ሁሉ ሂደት ታድያ ለትግራይ ሆነ አማራ እንዲሁም ወላይታ ወወዘተ ምን ሊያመጣለት??

    ሰዎች ልብ እንበል፣ ቆም ብለንና ሰከን ብለን ወደ Barbarism ውስጥ ገብተን ስናበቃ፣ ጭራሽኑ በመንፈሳችንና በ አካላችን ውስጥ Barbarism’ን እያሰረፅነው መሆናችንን ተገንዝበን ወደ ሰው ልጅነት የምንመለስበትን መንገድ እንሻ! በፍጥነት የራሳችንን ጉዳይ በገዛ ራሳችን የምናከናውንበትን መንገድ ካላገኘን፣ ኢትዮጵያ እየከበብዋት ባሉት ሃያላን መንግስታት የ’Barbarism ጦርነት አውደ ምድር ትሆንና ሁሉም ነገር ያልቅለታል! ይህ ከሆነ ደግሞ የውጭ ሃይል ጋባዦችም ብትሆኑ በሳዳም ወታደሮች ላይ የደረሰው አይነት ምህረት የሌለው ክትትል እደርስባችኋል! ኢትዮጵያ ታበፅህ እደውሃ ሃበ ህዝቦሽዋ!

Comments are closed.

Share