November 19, 2013
8 mins read

Health: ስትሮክ

በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም፣ ዲፓርትመንት ኦፍ ኸልዝ እና ዘ-ሐበሻ በመተባበር የቀረበ ትምህርታዊ ጽሁፍ

1. ለምን ስለ ስትሮክ ትምህርት መስጠት አስፈላጊ ሆነ ?
• ብዙ ሰዎች በስትሮክ ምክንያት ህይወታቸውን እያጡ ስለሆነ፡፡
• ብዙ ሰዎች በስትሮክ ምክንያት የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው አካለ ስንኩል እየሆኑ ስለሆነ፡፡
• ስትሮክ ዘር ፣ ሃይማኖት እና ፆታ ሳይለይ ሰው ስለሚጎዳ፡፡
• በዚህም ብዙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የሞትና የአካል አደጋ እየደረሰባቸው ስለሆነ፡፡
• አስፈላጊውን ትምህርት እና የጤና ክትትል ከተደረገ ስትሮክን መከላለክ ስለሚቻል፡፡
• 80 በመቶ ስትሮክን መከላከል ስለሚቻል፡፡
• በ ደ/ሰ/መ/ቤ/ክ ጤና ክሊኒክ በተሰበሰበው መረጃ አብዛኛው ምዕመን ቅድመ ከፍተኛ ደምግፊት (pre ypertension) እና ቅድመ ስኳር በሽታ (pre diabetes ) መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ ይህም ለስትሮክ የተጋለጡ መሆናቸውን ስለሚያመለክት
• የሰው ልጅ ጤነኛ ሆኖ በህይወት ለመኖር የእግዚአብሔርን ህግ መከተልና በመጠን መኖር እንደሚገባው መፅሐፍ ቅዱስ በሰፊው ስለሚያስተምር
2. ስትሮክ ምንድን ነው ?
• ስትሮክ ( stroke ) በሌላ አጠራር የአንጎል ደም ስር አደጋ በእንግሊዝኛው ደግሞ ( ሴሬብሮ ቫስኩላር አክሲደንት (CVA )
• ከ ኸርት አታክ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ወደ ልብ የሚሄደው የደም ዝውውር በድንገት ሲቋረጥ ኸርት አታክ ሲባል ወደ አንጎል የሚመላለሰው የደም ዝውውር በድንገት ሲቋረጥ ስትሮክ ይባላል፡፡
• ጊዜያዊ ኢስኬሚክ አታክ (TIA ) ወይም ትንሽ ስትሮክ (Ministroke) የሚከሰተው ጊዜያዊ የሆነ የደም ዝውውር ወደ አንጎል መዘዋወሩን ሲያቆም ነው፡፡ ይህ ሁኔታ (TIA) አስጊና ለወደፊት ስትሮክ ሊገጥመን እንደሚችል ስለሚጠቁመን አስፈላጊውን የሕክምና ክትትል በአስቸኳይ ያድርጉ፡፡
3. ስትሮክ እንዴት ይታከማል ?
• እንደ ስትሮኩ ዓይነትና ክብደት ብዙ የሕክምና ዓይነቶችና መድሃኒቶች አሉ፡፡ ስለዚህ በአቅራቢያዎ ያለ የጤና ማዕከል ( ሐኪም ቤት) በአስቸኳይ ይሂዱ፡፡
4. የስትሮክ ምልክቶችና የሚያስከትሉት ስሜቶች ምንድን ናቸው ?
በስትሮክ የተጠቃ ሰው ከሚከተሉት አንዱን ወይም ብዙዎቹን ስሜቶች ሊሰማው ይችላል፡፡
• ድንገተኛ የፊት እና የዕግር መደንዘዝ ወይም መዛል ( ብዙውን ጊዜ ስሜቱ በአንድ በኩል የግራ ወይም የቀኝ አካላችንን ያጠቃልላል)፡፡
• ድንገተኛ የመጭበርበር ( ግራ መጋባት ) ስሜት (confusion ) በድንገት የንግግር መሳን፡፡ድንገተኛ የማየት አለማቻል ( አንዱ ወይም ሁለቱም ዓይን ሊሆን ይችላል )
• ድንገተኛ መራመድ አለመቻል ማዞር መንገዳገድ፡፡
• ድንገተኛ ሃይለኛ የራስ ምታት ( ያለምንም ምክንያት)
5. ስትሮክ አለብኝ ብዬ ከገመትኩ ምን ማድረግ አለብኝ ?
• በራሶትም ላይ ሆነ በሌላ ሰው ላይ የስትሮክ ምልክት ካስተዋሉ እጅግ በጣም አጣዳፊ ነውና በአስቸኳይ 911 ይደውሉ ቶሎ ብለው አስፈላጊውን ሕክምና በማግኘት ሊደርስ የሚችለውን የሞትና እና ወይም የአካል ጉዳት እንዲቀንስ ያድርጉ፡፡
6. ልንቀይራቸው የማንችላቸው ለስትሮክ
የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
• የዕድሜ እየጨመረ መሄድ ( ከ 55 ዓመት በኋላ በየ 10 ዓመቱ አደጋው በሁለት እጥፍ እየጨመረ ይሄዳል)
• ከሴቶች ይልቅ ወንዶችን የበለጠ ያጠቃል፡፡
• አፍሪካን አሜሪካን ( ይህ የህብረተሰብ ክፍል በከፍተኛ የደም ግፊት በስኳር በሽታ ከመጠን ባለፈ ውፍረት የተጠቃ የህብረተሰብ ክፍል ነው ) ፡፡
• የቤተሰብ ታሪክ ( በቤተሰብ ውስጥ በስትሮክ የተጠቃ ካለ) ዘር ብቻ ሳይሆን ባህል የምግብ ዓይነትና ያኗኗር ዘይቤንም ያጠቃልላል፡፡
7. ሊቀየር ወይም ሊስተካከል
የሚችል ለስትሮክ
የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
እነማን ናቸው ?
• የደም ግፊት
•ትክክል ያልሆነ የልብ አመታት (አትሪያል ፊብሪሌሽን /AFIB)
•ሲጋራ ማጨስ
•አልኮሆል መጠጣት
•ከፍተኛ የሆነ የደም ውስጥ ስብ (cholesterol)
•በቂ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
•የሰውነት ክብደት ከሚፈለገው በላይ መጨመር (ውፍረት )
• የስኳር በሽታ
8. ስትሮክን ለመከላከል ምን ማድረግ አለብኝ ?
•ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት የደም ስብ(cholesterol) ስኳር ፣ የልብ ሕመምን መታከም አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ
•ሲጋራ ማጨስ ማቆም
•የአልኮል መጠጥ መቀነስ (በቀን ከ 1-2 መጠጥ ያልበለጠ )
•የተመጣጠነ ጤናማ የሆኑ ምግቦችን በልኩ መመገብ
•እንዳይወድቁና ወድቀው እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ማድረግ
9.ተጨማሪ መረጃ ከፈለኩ ከየት ማግኘት እችላለሁ ?
1. የ ደ/ሰ/መ/ ፓሪሽ ክሊኒክን መጠየቅ Email. health@debreselam.net
ክሊኒካችን የስኳር ኮሌስተሮል የደም ግፊት እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ዘወትር እሁድ ከ 10፡00-12፡00 ከቅዳሴ በኋላ በነፃ ስለሚሰጥ እየመጣችሁ መገልገል ትችላላችሁ፡፡
2. የግል ሃኪምዎን/ የጤና ጣቢያ ማነጋገር
3. የሚኒሶታ የጤና ዲፓርትመንት (MDH )
ስልክ 651 2015405 www.health.state.mn.us
4. National Stroke Association ስልክ
1-800-787-6537
Stroke helpline info@stroke.org
ምንጭ ፡- 1. የሚኒሶታ የጤና ዲፓርትመንት
( MDH) የልብ ሕመምና ስትሮክ መከላከያ ክፍል ስልከ 651.201.5405
አዘጋጅ ፡- የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤ/ክ
ፓሪሽ ክሊኒክ ሚኒያ ፖሊስ ሚኒሶታ
ስልክ፡- 612.721.1222
Email. health@debreselam.net

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop