የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አመጽ አነሳስተዋል ያላቸውን 27 ሠራተኞቹን ከሥራ አባረረ

4 Comments

 1. በለው! የፓለቲካ ሽርሙጥና ልብስ ማውለቅን አይጠይቅም። አሁን እስቲ መቼ መሽቶ ነጋ እና ነው ሰው ተሹሞ በተሰጠው ሃላፊነት ምንም ሥራ ሳይሰራ እንደገና ሌላ ስልጣን ላይ የሚወጣው? ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ ነው እንጂ ፋይዳ የለውም። አሁን ማን ይሙት አቶ ገድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነትን አሜን ብለው ተቀብሉት? የውጭ ነገር ጭልፊት መሆንን ይጠይቃል። አክሎም የቋንቋን ችሎታን ያማክላል። እንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን መንደሪን (የቻይናውን)ፈረንሳይኛ ቢቻል የሩስክ ቋንቋ አቀላጥፈው የሚናገሩና ሃገራችንን በየመድረኩ የሚያስጠራ ሰው ቢሆን ይመረጥ ነበር። እንደ እኔ እንደ እኔ አሁን በፕረዚደንትነት የሚያገለግሉት ሴትዮ ለውጭ ጉዳይ የሚመጥኑ ይመስለኛል። ገድ አንዳርጋቸው የረጋ ለፓለቲካ ሳይሆን ለንስሃ አባትነት የሚበጅ ሰው ነው። ለአስረሽ ምቺው የዓለም ፓለቲካ አይመጥንም።
  አቶ ለማ ለምን መከላከያ እንደመጡም አይገባኝም። ያው ጊዜው “ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ” ሆኖ እንጂ በሃገር አቀፍ ፓለቲካና በኦሮሚያ ክልሎች ያደረጉትና የሚያደርጉት አስተዋጾ ከፍ ያለ ነው። አዎን በቅርቡ የሃሳብ እንቅፋት መትቷቸው ማብራሪያ ሰጥተውናል። ተቀብያለሁ። እኔ አስቤ የነበረው ለመጪው ምርጫ ለመሪነት ወይም በአጋርነት ይሰለፋሉ ነበር። አሁን ደግሞ የመከላከያውን ዘርፍ እንዲመሩ መሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ ምን ሃገራዊ እድምታ ይኖረው ይሆን? መሰንበት የማያሰየን የለም። ቆይቶ ማየት ነው። በአጭር የሥራ ዘመን ከመከላከያ ስራቸው ወደ ምህንድስና ስራ የተመሱት ወ/ሮ ደግሞ ይመቻቸው። በሙያቸው ለውድ ሃገራችን የሚበጅ ያምጡልን እላለሁ።
  በማጠቃለያው ወያኔ በመቀሌ መሽጎና ወንጀለኞችን አቅፎ በከተማ ለጽዳት የወጡ ወጣቶችን ለድብደባና ለእስራት ሲዳርግ ዝም መባሉ የፓለቲካ ቁልጭ ቁልጭ መሆኑ ያሳያል። የያዘው ጥለፈው ፓለቲካ! በአንጻሩ ትጥቁን ፈቶ በሰላም ሃገር ውስጥ ገባ የተባለው የኦነግ ስብስብና በአሮሞ ህዝብ የሚነግዱ ጠበንጃና ሃሳብ አንጋች ወስላቶች ሃገር ሲያምሱ፤ በጠራራ ጸሃይ ቤ/ክርስቲያን ሲያቃጥሉ ዝም ብሎ የሚያይ መንግሥት የእለት ወሬው ሺ የካላሽን ጥይት የክላሺን ጠበንጃ ሽጉጥ ያዝኩ እያለ ይለፋል። ሰው እኮ ሰላሙ ከተከበረለት በሬውን እየሸጠ ለራሱና ለቤተሰብ መከላከያ መሳሪያ መግዛቱ አይቀርም። ግን ያው እንደ ወያኔ ዘመን ለአንድ እሳት በመስጠት ሌላው ለነፍሱ እንዲሮጥና ተሰዳጅ እንዲሆን የአሁን ኦሮሞዎችን ያማከለት ፓለቲካም የሚገድለው በዘርና በጎሳ በሃይማኖት በመሆኑ እረፍት የሌላት ይህች ሃገር እንደገና የእሳት ማገዶ መሆኗን ልብ ያለው ያስተውላል። የውስጥ፤ የቅርብና የውጭ ጠላቶቻችን እኛን ለማጫረስ ትጥቅና ስንቅ ማቅረባቸው አይቀሬ ነው። ህግ የሰፈነባት ሰው በሰላም ውሎ የሚገባባት ሃገር ከሆነች ግን እሳቱ ላይ ነዳጅ የሚያርከፈክፉት የውስጥ መሰሪዎችም ሆኑ የቅርብና የሩቅ ጠላቶቻችን ፍላጎት ሊጎለብት አይችልም። ጫካ ካቀፈው ተጋዳይ ህዝብ ያቀፈው ይበጃልና!የፓለቲካ ግልሙትና በሃሳብና በተግባር የሚገለጽ ነው። ለዛም ነው እርቃነ ስጋነትን የማይጠይቀው… የአእምሮ መራቆትን እንጂ! አይ ሃገሬ ቢል የከፋው ሰው። እንፋሎቱን የሰማው …ምነው ስንት ጊዜ ሆናት ከጠፋችብህ ቢለው… ገና ሳልፈጠር አለው ይባላል። ማለቂያ የሌለው የፓለቲካ ሽር ጉድ… ስብሰባ ያሰከረው፤ የጎጥ ቀረርቶ ያደነቆረው ሃገራዊነትን ያልተላበሰ እኔን ስሙ የሚል የቀበሌ ጥሩንባ …ለጀሮ ሲቀፍ። አድነኝ ፈጣሪ!!

 2. “Oromai”,ale Be’alu Girma! Abiy clearly off balance as a result of the punches from and squeezes of “Ehiopianists” vs. “Biheretegnoch” – “ke’hulet yata gomen”.

 3. በኢህአዴግ ውስጥ ሹመት መስጠትና ማቀያየር አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ግን በዚህ ወቅት የሚደረግ ማንኛውም ስልጣንና ሽግሽግ ከሌላው ጊዜ የሚለየው አገሪቷ አደጋና መስቀለኛ መንገድ ላይ ከመሆኗ አንፃር ነው፡፡ ስለዚህ የአቶ ለማም ምደባ ለኢትዮጵያ አንድነትና የጠንካረ አገር ለምፍጠር ታስቦ ከሆነ ከበድ ያለ ኃላፊነት ይሆናል፡፡
  ካልሆነ ግን በቀጣይ የጠነከረችና የተዋኃዳች አገር ግንበታ ላይ ፈተና የሚያስከትል መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

 4. I think there is no change. still now ethiopia is like game of thrones.
  no one is working for ethiopian people. every leaders are working for their life game. one leader kill inocent people for remainning in power.
  and the othe leader let inocent people killed by other fucking terriors (DR. ABY).

Comments are closed.

Share