ለምግብነት ሊውል የማይችል 55,000 ቶን የተበላሸ ስንዴ የጫነች መርከብ..

ለምግብነት ሊውል የማይችል 55,000 ቶን የተበላሸ ስንዴ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ላይ ቆማ ሶስት ወር ድርድር ከተደረገበት በሁዋላ ስንዴው ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው ሲሉ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ አጋለጡ::

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

‘አምባሳደሩ በፌስቡክ ገጾች እንዳሰፈሩት “ፕሮሚስንግ በተባለ አቅራቢ ድርጅት አማካይነት የቀረበው ይህ ስንዴ በስብሶ ለምግብነት ሊውል ስለማይችል ወደመጣበት እንዲመለስ የተወሰነ ቢሆንም የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከአስመጭው ድርጅት ጋር ባደረገው ድርድር ስንዴው ታክሞአል በሚል ምክንያት ተጭኖ ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ ተደርጎአል።” ያሉት አምባሳደሩ :ስንዴው የበሰበሰው አንሶ መታከሚያ ኬሚካል ተጨምሮበት ሊያስከትለው ስለሚችለው የጤና ጠንቅ የታሰበበት ነገር ይኖር ይሆን?

ታክሞ መግባት የሚችል ከሆነ ከመጀመሪያው ወደ መጣበት እንዲመለስ ለምን ተወሰነ?

የተወሰነው ውሳኔ እንዴት በድርድር ሊሻር ቻለ?” ሲሉ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው “እንደኔ እምነት ድሮ በነበረው አሰራር ውሳኔው ተሽሮ ስንዴው እንዲገባ የተደረገው ጉቦ ተበልቶበት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ስለዚህ ለምግብነት በሚውሉ ገቢ ምርቶች ጥራት ላይ መንግስት በቂ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል። ፕሮሚስንግ የተባለ የስንዴ አቅራቢ ድርጅት ከ20 ዓመታት በላይ ከጨረታ ውጭ በብቸኝነት ስንዴ አቅራቢ የነበረ ከባለሥልጣኖች ጋር ጥብቅ ትሥሥር የነበረው ድርጅት ነው። ” ብለዋል::

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ወደ ስቱዲዩ እስከገባንበት ጊዜ  የሰጠውን ምላሽ የለም::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነት በመንግስት ጥያቄ መሰረት የጎንደርን ሰላማዊ ሰልፍ ለሐምሌ ሰባት አዘዋውረናል አለ
Share