በኢትዮጵያ  ባለፉት ስድስት ወራት  የ15 ሃገራት ዜግነት ያላቸው 56 አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር  ዋሉ

በኢትዮጵያ  ባለፉት ስድስት ወራት  የ15 ሃገራት ዜግነት ያላቸው 56 አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን  የፌዴራል ፖሊስ የአደገኛ እጽ ቁጥጥር ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር መንግስተአብ በየነ ገለጹ::

https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY

ከተያዙት ውስጥ 19 የሚሆኑት ናይጄሪያውያን ሲሆኑ አስር ኢትዮጵያውያን በዝውውሩ ሲሳተፉ ተይዘዋል፡፡ ቀሪዎቹ የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው ናቸው ያልይት ኮማንደር መንግስተአብ  ከአዘዋዋሪዎች 95 ኪሎ ግራም ካናቢስ እና ከ141 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬን በፌደራል ፖሊስ መያዙን ጠቁመውላ::

በሃገር ውስጥም በአዲስ አበባ አንድ ሺህ ካሬ ሜትር፤ በሻሸመኔ ሰባት ሄክታር የበቀለ ካናቢስ የተባለ አደገኛ እጽ በፖሊስ እንዲነቀል አብቅለዋል የተባሉትም ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን ሃላፊው በመግለጫቸው ገልጸዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለ የፋሺሽት ኢጣልያ የጦር ወንጀልና ለአድዋ ድል በቀል ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ - ኪዳኔ ዓለማየሁ
Share