በኢትዮጵያ ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ ታወጀ

የሀይማኖት አባቶች በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየእምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንዲያደርጉ አወጁ፡፡ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች እና የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች አሁን በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው እለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤው ሁሉም ወገን ቅድሚያ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብአዊ ክብርና ሰላም በመትጋት የወገኖቻችን ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት በአፋጣኝ ማቆም ይገባዋል ሲል የተማጽዕኖ ጥሪም አቅርቧል፡፡ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ምንም አይነት ግጭት እና የሚተኮስ ጥይት ሊኖር እንደማይገባ አሳሰበው ጉባኤው ለመላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባለአስር ነጥብ የሰላም መልዕክት እና የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ግጭቱ ተወግዶ የታሰበው ሰላም እውን እንዲሆንም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየ ዕምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ጸሎትና ምሕላ ታውጇል ብሏል ጉባኤው፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=Pe4vPoSA5JM&t=223s

ተጨማሪ ያንብቡ:  የትግራይ ተወላጆች አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል
Share