ሲኤንኤን (CNN) ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካን ቀልብ መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው ሲል አሞካሸ

የአሜሪካው ትልቁ የሚዲያ ተቋም ሲኤን ኤን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የመላው አፍሪካን ቀልብ መሳብ ችለዋል ሲል አሞካሸ::

ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያ ከገባችበት የብሔር ግጭትና ውጥረት እንድትወጣና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ማድረግ መቻላቸውን የገለጸው ሲኤንኤን በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ብሎም በውጭ የሚኖሩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ጠቅሶላቸዋል::

“በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረው የረጅም ጊዜ ውጥረት ወጥተው ወደ ሰላም እንዲገቡ ማድረጋቸውን” የጠቀሰው ሲኤንኤን በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን ግጭት ለማስወገድ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲን ያካተተ የጋራ ውይይት በማድረግ የተጫወቱት ሚናም ቀላል የሚባል እንዳልሆነ አስረድቶ በዚህም፣ የአፍሪካ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ ያምኑባቸዋል ሲል ሲ ኤኤን ዘግቧል::

የዶ/ር አብይ የፈረንጆቹ 2019 ዓመት ዋና ስራም በኢትዮጵያ በ2020 የሚደረገው ምርጫ ነው ሲል ሲኤን ኤን ጠቅሷል::

https://www.youtube.com/watch?v=Pe4vPoSA5JM&t=223s

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ክልል የተፈራው ተፈጸመ ከ100 በላይ ተረሸኑ ቪዲዮ ተለቀቀ
Share