December 29, 2018
4 mins read

በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ300 የማያንሱ የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ወታደሮች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቀሉ

300

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱና በዳኡድ ኢብሳ ትዕዛዝ የሚንቀሳቀሱ ከ300 የማያንሱ የኦነግ ወታደሮች በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ትጥቁን በመጣል በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ለመቀጠል ተስማሙ::

የኦሮሞ ቄሮዎች ሕይወታቸውን ገብረው ላመጡት ለዚህ ለውጥ እንቅፋት አንሆንም:: እንደውም ይህን በትግል የመጣውን ለውጥ እንጠብቃለን በሚል ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉት እነዚሁ ወታደሮች ቄሮ ደሙን አፍሱ ያመጣውን ለውጡን ለማስቀጠል ሰላማዊ ትግሉን መቀላቀላቸውን አስታወቀዋል::

በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የመንግስት ሚዲያዎች በምዕራብ ወለጋ የነበሩ የኦነግ ወታደሮች በሰላም ለመታገል የወሰኑ መሆኑን አሳይተው የነበረ ሲሆን ከዚያም በኋላ በየቀኑ በርካታ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ ለመታገልና ትግሉን ለማስቀጠል የዳኡድ ኢብሳን እየጣሉ ወጥተዋል:: እስካሁንም በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወሰኑ ወታደሮች ቁጥር ወደ ሶስት መቶ እንደሚደርስ ምንጮች ገልጸዋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ሸኔ የባሌ አካባቢ ክንፍ መሪ ሞጎልቡስ ዲና አሊ ከአራት ተባባሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተዘገበ:: በባሌ አካባቢ በከፍተኛ ስርቆት እና የግድያ ወንጀል ላይ ሲሰማራ ነበር የተባለው ሞጎልቡስ ከታሰረ በኋላም ሌሎችን ለማደን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጸጥታ ቢሮ እየሰራ መሆኑን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

በጉዳዩ ላይ የዳኡድ ኢብሳ ኦነግ የሰጠው ማብራሪያ የለም::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የፊንጫአ ኃይል ማመንጫ እና ጌዶ ከተማ ላይ የሚገኝ የኃይል ማከማቻ ጠባቂዎች ነበሩ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ መነ ቤኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል::
የዞኑ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተረፈ ሁኔታውን ሲያሰረዱ ”መኪና ላይ ሆነው ወደ ፊንጫአ እየተጓዙ ሳሉ ተኩስ ተከፈተባቸው:: ጥቃቱን ማን እንደሰነዘረ አልታወቀል:: የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ከትናንት በስቲያ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ነው የተገደሉት”
በቅርቡ የኦዴፓ መአከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ ኦነግ የመንግሥት ባለስልጣናትን ይገድላል፣ የአስተዳደር ስርዓቱን ያፈራርሳል፣ ዘረፋ እና ሚሊሻዎችን ጦር ያስፈታል ሲሉ ኦነግን ከሰዋል።
በምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢዎች የጸጥታ መደፍረስ ካጋጠመ ሰነባብቷል::
https://www.youtube.com/watch?v=qn4xrU8Cer8&t=64s

93418
Previous Story

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ህግ ሊወጣ ነው

93437
Next Story

ጥብቅ መረጃ – በብሔራዊ መረጃና ደህንነት የተገኘው መርዝ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop