የጋዳፊ ልጅ በቦሌ ከአውሮፕላን አልወርድም ብሎ አስቸገረ ተባለ

የሊቢያው አምባገነን መሪ ሙሀመድ ጋዳፊ የጉዲፈቻ ልጅ የሆነው አብደላህ ሞኔ ሙሳ ሙማሬ በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ አስቸገረ፡፡ ይህን የዘገበው የዚምባቡዌው ሄራልድ ጋዜጣ ነው፡፡

የዚምባቡዌ ሴኔት ትላንት የተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ፣ የህግና የፓርላማ ጉዳዮች ሚኒስትሩን ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ሚኒስትሩ ዚያምቢ እንደተናገሩት የጋዳፊ ልጅ በአዲስ አበባ ከአውሮፕላን አልወርድም ብሎ አስቸግሮ ነበር፡፡ አባቱ በ2011 አ.ም ከተገደሉ ከሶስት አመታት በኋላ በ2014 የዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሀራሬ የደረሰው ሙማሬን ወደአገሩ ለመውሰድ በተሞከረበት ወቅት ይህ ድርጊት መፈፀሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በዚምባቡዌ ስደተኞችን ማስተዳደር እንደማይቻል የገለፁት ሚኒስትሩ ለተወሰነ ጊዜ አቆይተው ወደመጡበት አገር የመመለስ አሰራር እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ይህንን ልጅም ወደሊቢያ ለመመለስ በኢትዮጵያ በኩል ባለው ትራንዚት በረራ አዲስ አበባ ላይ ወደሊቢያ የሚጓዘው አውሮፕላን ላይ ሊያሳፍሩት ሲሉ ከአውሮፕላን አልወርድም ማለቱን ለሴኔቱ አስታውቀዋል፡፡ ወደሊቢያ ከሄደ እንደሚገደል በመናገሩም ወደዚምባብዌ ለመመለስ መገደዳቸውን አስታውቀዋል ሚኒስትሩ፡

https://www.youtube.com/watch?v=3DhpJfLazkE&t=397s

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደሴ እንደ ስታሊንግራድ (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

1 Comment

  1. የምህረት አዋጅ የተሰጠዉ ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ የቀናት ዕድሜ እንደቀሩት ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ

    December 19, 2018

    በተለያዩ ምክንያቶች የተከሰሱ ወይም እንጠየቃለን በሚል ስጋት ከሀገር ተሰደዉ የነበሩ ኢትዮጵዉያንና ትውልደ ኢትዮጲያዉያንም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሆኗል።”December 19, 2018 አቶ ዝናቡ ቱሉ የጠቅላይ አቃቢ ህግ ፅ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ገልፀዋል

    ብዙ ከሃገር ተሰደን ያለን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተነሳ በቀነ ገደቡ ወደ ሃገራችን ለመለስ ያልቻልን ብዛት ያለን ሰዎች ምህረት ቀነ ገደቡ እንዲራዘምልን እንፈልጋለን::
    በስደት ያለን ወደ ሃገር ለመሳፈር ያልቻልን እዚሁ በስደት ሃገር ባለንበት ሆነን የት ብለን አምባሳደሮቹ ጋር ይሁን ወይ ሌላ ቦታ ምህረት ለማን ምህረት እንደምናመልክት ግራ ገብቶናል::

Comments are closed.

Share