የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) በጎንደር ጭርቆና በምትባለ በርሃ ላይ ከወያኔ አንድ ሻምበል ጦር ጋር ባደረግኩት ውጊያ 25 ወታደሮችን መግደሉን እና 11 ማቁሰሉን አስታወቀ።
የነፃነት ኃይሉ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “ከፌብሩዋሪ 25 እስከ 27 2013 ዓ.ም በአካባቢው የመንግስት አጨብጫቢ ሚሊሻዎች እየተመራ ወደ ነፃ መሬታችን በመምጣት ጥቃት ሊያደርስብን የመጣነውን አንድ ሻምበል ጦር አሳፍረን መልሰነዋል” ብሏል።
በአርማጭሆና በአይከል መካከል በምትገኘው ጭርቆና በረሃ ለ3 ቀናት በተደረገው ውጊያ ከመንግስት ወታደሮች 25 ሰዎች መሞታቸውን፣ 11 መቁሰላቸውን እና 3 ወታደሮችን መማረኩን ያስታወቀው የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (EUFF) ከራሱ ሠራዊትም 5 ወታደሮች በዚህ ውጊያ መሞታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) ከወያኔ ጋር አትሥሩ በሚል ማስጠንቀቂያ ለሰጣቸውና ይህን ማስጠንቀቂያ አልሰማ አሉኝ ላለው ባለፈው ጃንዋሪ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በመተማ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የከተማው የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የከተማው የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ 18 ሰዎች በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ሕይወታቸው ወዲያዉኑ ሲያልፍ ሌሎች 4 ሰዎች መቁሰላቸውንና ለዚህም ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ይኸው ድርጅት “ከኢሕአዴግ ሥርዓት ጋር አትተባበሩ የሚል ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ላልሰሙ ደጋፊዎች ክምር ድንጋይ የሚባለው አካባቢ የነዳጅ ዘይት ማጠራቀሚያ ማጋየቱና፤ እንዲሁምጨጨሆ ላይ ላይ ደግሞ አውቶቡስ ማቃጠሉ መዘገቡ አይዘነጋም። አሁን የመንግስት አንድ ሻምበል ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ ይህን ኃይል ለማጥፋት ወደ ሠራዊቱ ነጻ መሬት (ጭርቆና በርሃ) በመሄድ ውጊያ የገጠመው ቢባልም፤ ከመንግስት ወገን በተለይም ወደ መከላከያ ሚ/ር ደውለን ይህንን ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይልና የኢሕአዴግ ጦር በጭርቆና በረሃ ውጊያ ገጠሙ ተባለ
Latest from Blog
በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና
ሰው ሆይ!
“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።” መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን
ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች
\በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ የቀድሞው መከላከያ አመራር ፋኖን ሸለመ || ሻ/ቃ ዝናቡ ስላወቅሁ ደስ ብሎኛል || ጥር 7 አዲስ ቪዲዮ
በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ
አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ
አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም
ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ
የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ
ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ
ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN