December 19, 2016
48 mins read

የጥንታዌት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  አጭር ታሪክና ሥርዓት

ታሪኩ ዉብነህ ገታነህ

ክፍል አራት

                                         ቤተክርሲቴያን

[ማሳሰቢያ፡ የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክ ማወቅና መመርመር አስፈላጊ ነው፤ ከሁሉ በላይ ሥነ መለኮትን በሚገባ መረዳት አለብን፤ ቤተ ክርስትያን መመላለስ ጥሩ ክርስቲያን አያደርገንም፤ የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ቤተ ክርስቲያን ስለ ሂድን ብቻ አያከብሩንም፤ አለማዋቃችንም ሲያዉቁ የቤተ ክርስቲያኑን ሥነ ሥርዓት በማን አለብኝነት ይገድፉታል፤ የፖለቲካ ካድሬዎች መነኮሳት፤ ካህናት፤ ዴያቆናት ነን እያሉ ቅድስት የሆነችዉን ቤተ መቅደስ እያረከሱት መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው።  ከሁሉ አስቀድመን ማወቅ ያለብን ጽንፈኝች ሥነ መለኮትን በሚገባ ሳይመረምሩ ራሳቸዉን እንደ አዋቂ በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችን ከመንግሥት አካል እንዳትላቀቅ በመዋጋት ላይ ይገኛሉ፤ አሁን በዚህ ስአት መስቀል ተሸክመው ከወንቤዲዎች ጋር አብረው ለነፃነቱ የሚዋጋዉን  ሕዘብ መሳሪያዉን ለማስፈታት እየተሯሯጡ ነው። ስለዚህ ምዕመን ይህንን ጉዳይ በአትኩሮት ተመልክቶ አስፈላጊዉን እርምጃ መውሰድ አለበት፤ የቤተ ክርስቲያንን ነፃነት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ዉስጥ አይገኝም፤ ምክንያቱም በአወዳሽነት ከፖለቲካው ሥርዓት ጋር ስለተዋሃደች ነፃነት የሚባል ክግንዛቤ ዉስጥ ስለሊለ ነው። መንግሥትና ሃይማኖት ፈጽሞ መለየት አለበት፤ መንግሥት ያለ አግባብ ሕዝብን ሲበድል ቤተ ክርስቲያን አቤቱታ ማሰማት ሃይማኖታዌ ግዲታ ነው፤ ይህ ከተባለ በኋላ አንባቢ በጥንቃቂ መመራመር ያለበት የታሪኩን ታሪካዌ ሂደት ከክፍል አንድ አስክ መጨርስሻው ድረስ ያለዉን ትንታኒ ከመረጃ ጋር እያመሳከረ መሆን አለበት፤ ከጽንፈኖችና ለታሪኩ ምንም ግንዛቤ የሊላቸው  ግለ ሰቦች የሚሰጠው አስተያየት ተራ ወሬ ስለሆነ ለሚያስፈልገው ለዉጥ እንቅፋት ከመሆን ሊላ ጥቅም የሚሰጠው ነገር የለም። አሁን መጠየቅ ያለብን ስለ ስለ ቤተ ክርስቲያን ነፃነት እንጂ ስለ ሲኖዶ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ ነፃነቱ ሲዋጋ ምዕመን ደግሞ ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ነፃነት መታገል አለበት፤ ቤተ ክርስቲያኗ ከፖለቲካ አካል መላቀቅ አለባት፤ ጎንደርና ጎጃም ቤተ ክርስቲያናቸዉን  ከፖለቲካ ነፃ አድርገዋል ይባላል? እዉነት ከሆነ ይህ በ 1600 ዓመት ዘመን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዉስጥ ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑ ነው። ግን እዉነቱን ማረጋገጥ አለብን፤ ከሆነ ጽንፈኞች ምን ይሉ ይሆን? ከአንድ ሲኖድ ክአንድ መንበር  ጋር የተያያዘ አይደለም፤ የነፃነት ጉዳይ ነው።  ይህ ውይይት ይህንን ጽሑፍ ካቀረበው ጋር መሆን የለበትም፤ ማነው የሚለው ቀርቶ ታሪኩን ሳይቻኮሉ ሥርዓተ ንባብን ተክትሎ ታሪካዌ  ሂደቱን መመርመር ነው፤ የተሰጡትን መረጃዎች አይቶ ከነባር “ሁኔታ” ጋር አገናዝቦ  የሚሰጠው አስተያየት ለዚህ ውይይት ጠቃሚ ነው ብዮ እገምታለሁ፤ ከሁሉ በላይ ለውይይቱ እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው በምን አይነት ዘዴ ቤተ ክርስቲያንችን ነፃ መውጣት ትችላለች የሚለው ጠቃሚ ስለሆነ ሰፋ ያለ አስተያየት ያስፈልጋል፤ እዚህ የቀረበው አጭር ታሪክ ስለሆነ አንባቢ  ሊያዳብረው ይችላል፤ መልካም ውይይት]።  

የጥንታዌት ኢትዮጵያን ቤተክርስቴያንን ጥንታዌት ያደረጓት ቤተመቅደሷ ነው፤ ከላይ እንደተጠቀሰው ለረጅም ዘመናት ቤተ መቅደስ ነበራት፤ ይህም የሜያመለክተው ከክርስትና በፌት ሃይማኖት እንድነበረ ነው፤ “ሥርዓተ ኦሪት” የሃይማኖቷ አቋም ስለነበር እስክ አሁን ድረስ “ከሥርዓተ ወንጌል” ጋር አዋሕዳ  “ቤተመቅደሷን” “ቤተክርስቴያን” ብላ በመሰየም ብልዩንና ሐዴስን አጣምራ ትገኛለች። እንግዴህ የመጀመሪያው ጥያቄ መሆን ያለበት “ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ መቼ ነው የገባው ነው?” ለዜህ ጥያቄ የምናገኝው መልስ ከዚህ የሚከተለው ነው፡

በቤተክርስቴያን መዛግብት ዉስጥ እንደተጻፈው  [as it was written by Rufimis in Ecclesistical History] ሩፌሙስ የተባለው ጸሐፊ ክርስትና ወደ ኢቶዮጵያ የገባው በሁለት ሶሪያን ወጣት ልጆች አማካይነት ነው፤ እነዘህ ልጆች በአንድ ንግድ መርከብ ላይ እየተጓዙ አዱሊስ  ላይ በሚገኝው የባሕር ወደብ ይደርሳሉ፤ እዚያም እንደደረሱ ሽፍታዎች የመርከቡን አዛዥ ገድለው  የንግዱን ዕቃዉን  ዘርፈው እነዚህን ሁለት ወጣቶች ማርከው ይዘው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን የአገሩ ዉስጥ ጸጥታ አስከባሬዎች ሁለቱን ወጣቶች ከሽፍቶቹ አድነው ወደ ቤተመንግሥት ወስደው ለንጉሡ ያስረክባሉ፤ ንጉሡም እነዚህን ሁለት ወጣቶች ተቀብሎ ፍሬሚናጦስን የቤተ መጻሕፍት ኃላፊ አድሲሱን  [Aedesius] የቤት መንግሥት ዋና ስራ አስኪያጅ  አድርጎ ይሾማችዋል፤ ከጥቂት ዘመን በኃሏ ንጉሡ ስለሞተ ፍሬሚናጦስ   [Frumentius] የወጣቱ አልጋወራሽ እንደራሴ በመሆን ስለተመረጠ እድል አግኝቶ ወጣቱን ንጉሥ ክርስትናን እንዲቀብል በማድረግ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ በ334 ዓ.ም ክርስትናን ተቀብላለች ይላል። [W. Yefru. The Nile Valley Civilization: A Histriographical Commentary on Ancient Africa. Pollouck Press, 2016 p. 232].

እንግዲህ  አንባቢ እስከ አሁን  ድረስ በአደረገው የውውይት ጉዞ በቂ የሆነ ታሪካዌ ግምገማና “ሁኔታን” መርማሪ [ሐታቲ] መላ ምት ስለ አዳበረ ከዚህ በላይ የተጻፈዉን “ሐተታ” [ምርምር] “ሐትቶ” [መርምሮ]  በዋቢነት የቀረበውን ጽሑፍ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ለመግባቱ መነሻ “ታሪክ” መሆኑንና ያለመሆኑን ሊመረምር [የሐትት] በቂ “ችሎታ” ይኖረዋል ብዮ እገምታለሁ፤ ይህ ግምት ነው፤ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ እዚህ ላይ ዉይይታችን ከፍ ባለ ደረጃ እንዲያድግ በማለት “ሐተተ” የሚለዉን የግዕዝ ቃል ግሥ  እርባታዉን ማሳየት ለአንባቢው ምርምር ይረደዋል፤ እንግዲህ  “ሐተተ” የሚለዉን አርእስት ወስደን የግሡን እርባታ [እርባ ግሥ] እንመልከት፤ “ሐተተ” [መረመረ] “የሐትት” [መረመረ] “ይሕትት” [ይመረምር] “ሐቲቶት” [መመርመር] “ሐታቲ” [የመረመረ] “ሐታቲያን” [የመረመሩ] “ሐታቲት” [የመረመረች]  “ሐታቲያት” [የመረመሩ] “ሕቱት” [የተመረመረ] “ሐታቲ” [መርማሪ] እያለና በገቢር በተግብሮ እያሰረ በአር ዕስት ተከፍሎ በአዕማድ ተጠቅሎ በዕቢይ በንዕስና በደቂቅ አንቀጽ እየገባ “ሁኔታን”  የሚመረምር የግሥ እርባታ ነው። ቋንቋው በሚገባ ዳብሯል፤ አገር ፤ መንግሥት ፤ ሕብረተሰብ  ትምህርት ቤት ፤ ቤኖር ከዚህ የበለጠ “ሁኔታን” መርማሪ መሳሪያ የለም። ከዚህ በላይ የተጻፉቱን “ቅድመ “ሁኔታዎች” አሉ ብለን በመጠኑ ምርምራችንን እንቀጥል፤ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ገባ በተባለብት ዓመት [334 ዓ.ም] ነበረ የተባለዉን በዕብይ አንቀጽ እንመዝግባቸው፤  “አገር” ፤ “ወደብ”  ፤ “ቤተመንግሥት” ፤ ቤተ መጻሕፍት” ነበሩ እንበል፤ በአንጻሩ ደግሞ በንዕስ አንቀጽ ደረጃ “ነጋዴ”  “ወጣቶች”  “ሽፍቶች” ነበሩ እንበል፤ እንግዲህ በዓብይና በንዕስ አንቀጽ ያሉትን ስንመረምር “በገቢርና”  “በተገብሮ” የተደረጉትን  ያለምንም ስህተት ማግኝት እንችላለን፤ ኢትዮጵያ የሚባል አገር አለ፤ ወደብ ከአለ የግድ የባሕር ኃይል አለ ማለት ነው፤ በወደቡ ላይ የሚተላለፍ ንግድ ከአለ ፅጥታ አስካባሪ አካል አለ፤ እንግዲህ በዋነኛነት የምናየው “ቤተመንግሥቱንና” ቤተ “መጻሕፍት” ነው፤ እዚህ ላይ ጥያቄው በምን አይነት “ሁኔታ” ነው እነዚህ ሆለት የሶርያን ወጣቶች የቤተመንግሥትና የቤተ “መጻሕፍት” ሃላፊ የሆኑት? በተለይ “መጽሐፍት” ቤቱ የሚነግረን በጽሑፍ የተጻፉ ጽሑፎችን የያዘና ታላቅ የሥነ ጽሑፍን ዕውቀት የተከማቸበት ቦታ መሆኑን ነው፤ ወጣቱ ፍሬሚናጦስ [Frementius] በምን ዕውቀቱ ነው ለዚህ ስራ የተመረጠው? ቋንቋዉን አይችልም ፤ ስለ ቤተ መጻሕፍት ቤትም የሚያቀው ነገር የለም ። በምን “ሁኔታ” ነው ፍሬሚናጦስ [Frumentius] አንድ የባሕር ኃይልና ወደብ ያለው አገር የቤተ መንግሥቱ ዋና አማካሪና ደግሞም የወጣቱ ንጉሥ እንደራሴ ሊሆን የቻለው? ይህንን “ሁኔታ” ሊፈጥር የሚችል ምክናያት አይኖርም፤ በተጨማሪ ለታሪኩ መጀመሪያ እንዲሆን የተሰጠው ቀን 334 ዓ.ም የተባለው ዘመን የፈጠራ እንጂ በዕውነት በዘያ ዘመን አንድ ሃይማኖት ተቀባይነት አግኝቶ  በአንድ ዘመን ወይም ዓመት ግዜ የነበረዉን ቤተ መቅደስ በከመ ቅስፈት ቤተ ክርስቴያን ብሎ ሊለዉጥ አይችልም፤ ስለዚህ በመረጃነት የቀረበው የልብ ወለድ “ታሪክ” እንጂ “ሁኔታ” ፈቅዶ በተግባር የሆነ “ታሪክ” አይድለም። ነባር ቅርስ እያለ ምን አልባት ሳይሆን  አይቀርም በሚል መላ ምት የተጻፈ ታሪክ ነው። እዚህ ላይ ክርስትና መግባቱንና ያለመግባቱን ሳይሆን በምን አይነት ሁኔታ እንደገባ ማወቅ አስፈላጊ ነው ምክናያቱም የሕብረተሰቡ ታሪክ ስለሆነ።

መነሻ ፤ መንደርደሪያ፤ መድረሻ የሊለው ታሪክ ሊሆን አይችልም፤ የሕበረተስቡንም ሕሊናዉነት ምን እንደሆነ አይገልጽም፤ ከክርስትና በፊት ለብዙ ዘመናት መቅደስ ያለው አገር፤ ሥነ  ጽሑፉ ዳብሮ በመጻሕፍት ቤት የተለያዩ ጽሑፎችን ያከማቸ ሕብረተሰብ በአንድ ሶርያን ወጣት አማካይነት ክርስትናን ተቀበለ ለማለት ያስቸግራል;፡ ከዚህ ሊላ ስለ ክርስትና መስፋፋት የተጻፈው ታሪክ  ነው፤ ታሪኩም በአጭሩ እንዲህ ይላል፡

በአራተኛው ክፈለ ዘመን አጋማሽ  ክርስትና በፍሬምናጦስ [ Frumenttius] ብዙም አልተስፋፋም ነበር፤ ስንክሳርና ሌላም የቤተ ክርስቴያን የታሪክ መጻሕፍት እንድሚያመለክቱት አዲሱ የክርስትና እምነት የተስፋፋው በተስዓቱ ቅዱሳን መነኮሳት ከሶርያ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ በአምስትኛው መቶ ክፍለ ዘመን  ከመጡ በኋሏ ነው። በአምስትኛውና በስድስትኛው መቶ ክፍለ ዘመን እነዚህ መነኮሳት ክርስትና በሰፌው እንዲስፋፋ አድርገዋል፤ የመንኮሳቱም አመጣጥ ከሶሬያ በደቡብ አረቤያ አድርገው ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት፤ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበትም ዋናው ምክናያት  ቻልሲዶን ላይ በተደረገውታላቅ ጉባኢ ላይ በተወስነው ሥነ መለኮትና በሚስጥረ ሥላሴ ላይ በታወጀው  ሥር ዓት ላይ ስምምነት ላይ ስለአልተደረስ ነው። እነዚህ መነኮሳት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋሏ ነው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያን የተስፋፉት፤ ከዚህም በላይ መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉመው ወንጌል በሰፌው እንዲሰበክ ያደረጉ ቅዱሳን መነኮሳት ነበሩ። [Ulllendorf : Ethiopia and the Bible].

ፕሮፌሰር ኡልንዶርፍ ታዋቂ የታሪክ መምሕር ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያም ብዙ መጻሕፍት ጽፈዋል፤ ይህም ሆኖ ስለክርስትና የጻፉት ጽሑፍ ከላይ እንደተጠቀሰው መነሻ፤ መንደርደሪያ፤ መድረሻ የሊለው  ሲሆን፤ ሳይሆን አይቀርም በሚል መላ ምት የተጻፈ ጽሑፍ መሆኑን ከመረጃ ጋር መቅረብ ይኖርበታል፤ ለኢትዮጵያ ክርስትና ታሪክ መነሻ የሆነው የሶሬያው ወጣት ፍሬሚናጦስ ነው፤ ይህም የሆነበት ምክንያት የነበረው ሕብረተስብ ክርስትናን የመቀበል ኃይል ስለሊለው ማለትም ሕሊናዉነቱ ስለአልዳበረ የግድ የዉጭ አስተማሪ ያስፈልገዋል ተብሎ የታሰበ ነው፤ ለዚህም በመረጃነት መቅረብ ያለበት የኢትዮጵያን ክርስትና በአንድ ሶሪያን ወጣት ተጀምሮ በዘጠኝ መነኮሳት [ተሳዓቱ ቅዱሳን] የክርስትናው ስራ ተከናወነ ማለት ነው፤ በአጠቃላይ “ታሪኩ” የኢትዮጵያ ሳይሆን የሶራውያን መሆኑን መረዳት አያዳግትም። ይህ የአንባቢዉን አንብቦ የመረዳት ጠለቅ ያለ ዕውቀት ይጠይቃል፤ ከነባር ቅርስ ጋር እያመሳከረ የዚህን ታሪካዌ ሂደት መመርመር ይኖርበታል፤ ከክርስትና በፊት ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመን ቤተ መቅደስ ሰርታ “ሕገ ኦሪትን” ተከትላ የነበረች አገር ነች፤ እንግዲህ ጥያቄው በምን አይነት “ሁኔታ” ነው አንድ ወጣት ለሺህ ዓመት ዘመን የነበረዉን በአንድ ዓመት [334] ግዜ ሊለዉጥ የቻለው? የዚህን ጥያቄ መልስ አንባቢ ፈልጎ ማግኝት ይኖርበታል፤ በምን አይነት “ሁኔታ” ነው ዘጠኝ ሽማግሌ መነኮሳት “ግዕዙንና” “ግሪኩን” አጥንተው መጽሐፍ ቅዱስን የተረጎሙትና ያስተማሩት? አሁንም አንባቢ የዚህን ጥያቄ መልስ ፈልጎ ማግኘት ይኖርበታል፤ እዚህ ላይ የሚያስፈልገው በተረጋጋ መንፈስ መወያየቱ ነው፤ የዚህ ውይይት አስፈላጊነት የታሪክን ጠቃሚነት ስለሚያስረዳን ነው። ታሪክ ከነባር ቅርስ ጋር እየተመሳከረ በግዜው የነብበረው “ሁኔታ” እየተመረመረ የተጻፈ እንድሆነ የመጭው ትውልድ ከአለፈው ትውልድ እየተማረ የተሰሩ ስሕተቶች እየታረሙ ሕሊናዉነቱን የሚያዳብርበት ታላቅ የሆነ የትምሕርት ክፍል ነው። እንግዲህ ተከታዩ ጥያቄ በምን አይነት ሁኔታ ነው ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ነው። ለዚህ መልሱ አንባቢን ፈልገህ አግኝ አይደለም፤ መረጃዎች ተሰብስቦ ከአልተሰጠው በጭፉን መላ ምት ሊያገኝው አይችልም፤ ስለዚህ መረጃው የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት “የአክሱም ስጦታ” ብለው በጻፉት መጽሐፍ ላይ ነው፤ በሁለተኛው ምዕራፍ ዉስጥ “የቤተ ክርስቴያን ምስረታ በአክሱም” ብለው የጻፉት ላይ የነበረዉን “ሁኔታ” በሚገባ ዘርዝረዉታል፤ ፕሮፈሰሩ ሲጽፉ እንዲህ ይላሉ፦

በአራተኛው መቶ ዓመት ክፍለ ዘመን አክሱም አሉ ከሚባሉት ገናና መንግሥታት አንዱ ነበረች፤ የነባራት ጦር ሰራዌት ኣባይ ሸለቆ አካባቢ ለነበሩት እንደ ሜሮ  ለሚባሉት ደካማ አገሮች እንደመፍትሒ ሆኖ ይጠብቃቸው እንደነበር ይታወቃል፤ ከዚህም በላይ በአካባቢው የነበሩቱን አገሮች በአንድ ላይ አጠቃላ ታስተዳድር ነበር። ከመቶ ዓመት  ላይ በአካባቢው  በተደረገው የበላይነት ትግል አክሱም  በአሸናፊነት ደቡብ አረብን  ጭምር በአንድነት አካታ ትቆጣጠር እንደነበር ይታወቃል፤ በአዱሊስና በቀይ ባሕር የነበራትን ወደብ በመቆጣጠር አለም አቀፉን ንግድ በቀጥታ በቁጥጥሯ ስር እንደነበር ይታወቃል፤ የሮማም መንግሥትም ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ የሆነ ግንኝነት እንደነበረው ታሪክ ዘግቦታል። ይህም የንግድና የባሕል ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ  እንደነበር መረጃ  የሚሆነው ዞስኬልስ የሚበለው የአክሱም ንጉሥ  የግሪክን ሥነ ጽሕፍና ባሕል በሚገባ ያውቅ እንደነበር “ፐሪፕላስ” የሚባለው የታሪክ መዝገብ መዝግቦታል፤ ይህም የሚያሳየው በአክሱም ከተማ ዉስጥ ግሪክና ላቲን ተናጋሪዎች በብዛት ይኖሩ እንደነበር ነው። በኋላም  ኢዛናም ክርስትና የተቀበለው በባሕሉ መተሳሰርና ከመቶ ዓመት በላይ የነበረው ግንኝነት መሆኑን ያስረዳል፤ ከዚህም በላይ ንጉሡ ክርስትናን ከመቀበሉ በፊት በአክሱምና በወደቡ አካባቢ ብዙ ከርስቴያን እንደነበሩ ይታወቃል፤ ከዚህም በላይ የሮማው ንግሥ ኮንስታንቲን [312-37] ክርስትናን ተቀብሎ የክርስትና ሃይማኖት እየተስፋፋ ስለሄደ ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ ገብታል።  [T.Tamrat. Church and State, pp. 21-22]

ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ስለክርስትና አመጣጥ በሚገባ ከበቂ መረጃ ጋር አቅርበዋል፤ እንግዲህ አንባቢ ከላይ የነበርውን ሁኔታ ከግንዛቢ አስገብቶ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደገባ ሊያውቅ ይገባል፤ አንድ ታላቅ የጦር ኃይልና ወደብ ያለው መንግሥት በአንድ ወጣት ሶርያን በአንድ ዓመት ውስጥ ለዉጦ መቅደሱን ቤተክርስቴያን አደረገ ማለት ልብ ወለድ ከመሆኑም በላይ የአገሪቱን ታሪክ እንዳልንበረ ማድረግ ነው፤ ከላይ ፕሮፌሰሩ እንደጻፉት ክርስትና የተስፋፋው ቀስ በቀስ ነው፤ ሮማ ውስጥም በጥብቅ ተክልክሎ ለበዙ ዘመን ታግቶ እንደነበር የታወቀ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥም ቀስ በቀስ ነው ሊገባ የቻለው፤ ምንም እንኳ በዙ ደም መፋሰስ ባይኖርም  “ሕገ ኦሪትን “ ተከታዮች ለብዙ ዘመናት ተክላክለዋል፤ ሄደቱም ከመቶ ዓመት በላይ እንደወሰደ ታሪክ ያስረዳል፤ እስክ ህያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ያወዛግብ የነበረው አንድ ሰንበት ሁለት ሰንበት የሚለው “ሕገ  ኦርትና ሕገ ወንጌል” ናቸው።  መጽሐፍ ቁድስ የተተረጎመው በአገረ ውስጥ በነበሩት ሊቃውንት እንጂ ጥግኝነትን ፈልገው በመጡ መነኮሳት [ተስዓቱ ቅዱሳን]  አይደለም፤ እነዚህን መነኮሳት ኢትዮጵያ በታላቅ ክብር ተቀብላ ጽላት በየስማቸው ቀርጻ አስተናግዳለች፤ ይህንን ውለታ ክግንዛቤ ሳያስገቡና የኢትዮጵያን ታላቅነት ዕውቅና ለመስጠት ስለአልፈለጉ ነው፤ እዚህ ላይ በታላቅ ጥንቃቄ አንባቢ ማስተዋል ያለበት ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ሌሎቹን የዘመናዌ ትምህርት የተማሩቱን ምሑራን ያጋጠማቸዉን ችግር ነው፤ ታላቅ እገታ ስለአለባቸው  ታሪክን ከነባር ሁኔታ ጋር እያመሳክሩ ሊጽፋ አልቻሉም፤ የውጭ ጸሐፊዎችን የግድ በዋቢነት ጠቅሰው ሚስተር ጆን ወይም ሚስተር ኮንቴ ሮስኒ እንደጽፉት ከአላሉ ጽሑፋቸው ተቀባይነት አይኖሮዉም፤ ራሳቸዉን ችለው ከነባር ቀስ ጋር አመሳክረው የመጻፉም ሆነ የመናገር መብት የላቸዉም፤ ምናልባት እንደ ኢትዮጵያን ምሁራን ጥግኛነትን እንደክብርና እንደ አዋቄነት አጥብቆ አለ ለማለት ያስቸግራል፤ ከዚህም በላይ የሚአስገርመው ደግግሞ እኛ ታሪካችንን አክብረን ራሳችንን አክባሪዎች ነን እያልን ራሳችንን እናታልላለን፤ የታርካችን አባት የምንላቸው ብዙ ናቸው፤ ታሪካችንን ሊላ ሰው ጽፎሉን እኛ የዚያ ታሪክ ልጆች መሆናችን በጣም የሚያስገርም ነው፤ ለዚህ ሁሉ መልሱ ምን ይሆን? ይህ ለአንባቢ የሚተው አይደለም፤ በቅጡ ተጠንቶ በታሪክ ጸሐፊዎች መገምገም ይኖርበታል።

ከላይ የተጠቀሰዉን የታሪክ ጸሐፊዎች በሚገባ መመርመር ግዲታቸው ነው፤ ከግዲታቸው አንዱ  ያለምንም ገደብ በነፃነት የሚጽፉበት ሁኔታ መኖር አለበት፤ ይህ ከአልሆነ የሚጻፈው ሁሉ ንግርት ይሆናል፤ በሊላ ጥናትና ክፍል ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው ይቀርባል። አሁን እዚህ ላይ ትኩረት የሚሰጠው ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተርስቲያን  የፖለቲካ ሥርዓ ቱ  እንዴት እንደተሳሰረ በአንክሮ መመልከት ተገቢ ነው። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኒታዎች መርምሮ ማወቅ አሁን በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለአለው መፍትሔ ያመጣል ብሎ መገመት ይቻላል። ዝርዙሩን በታላቅ ዝንጋቤ ይመልከቱት፤ ግንዛቤዎ በድርጊት በተደረጉት ታሪካዌ ሂደት ጋር መሆን አለበት።

አንደኛ፡ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የቤተክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂው የአገሩ መሪ ወይም ንጉሥ እንደነበረ ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ ይህም ማለት ቢተክርስቲያኑ ወይም ካህናቱ የመሪው አወዳሽ በመሆን የፖለቲካው አካል ሆኗል ማለት ነው፤ ከ1600 ዓመት ዘመናት ለአንድም ግዜ ቢሆን ከፖለቲካ አካል ከመሆን ዉጭ ሆና አታውቅም፤ ማለትም ነፃ [autocephalous] ሆና አታውቅም ማለት ነው፤ እንግሊዘኛው ያስፈለገው የምስራቅ ቤተ ክርስቲያን የሚጠቀሙበት ከግሪክ ቋንቋ የተወሰደ ቃል ስለሆነና በአጠቃላይ የምስራቁን ቢ ክርስቲያን ሁኒታ ስለሚገልጽ ነው፤ እዚህ ላይ የኢትዪኦጵያ ቤተ ክርስቲያን የፖለቲካ አካል መሆኑን የሚያከራክር መሆ አይገባዉም፤ አንባቢ ይህንን ጉዳይ በሚመራመርበት ወቅት አክራሪ ካድሬዎች በሃይማኖት ስም እንዳያወናብዱት ታቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል።

ሁለተኛ፡  የአንድ አገር ታሪክ ሊጻፍ የሚችለው ጸሐፊው ያለምንም ገደብ ያለፈውን ፤ በግዜው ያለዉንና ወደፊት የሚያስከትለዉን “ሁኒታ”  ነፃ ሆኖ ሲተነትን ነው።  ታሪክ –ይባላል፤ ሳይሆን አይቀርም፤  ሊሆን ይችላል እየተባለ መላ ምት በሊለው ትንታኔ ሊጻፍ አይችልም። ያለምንም መረጃ በተፈጠረ “ሁኒታ” እየተነዱ የሆነ ያልሆነዉን ነገር መጻፍ ከወሪ አልፎ ታሪክ ሊሆን አይችልም። አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት “ሁኒታ” ወሬ እንደታሪክ ሆኖ የሚነገርበት ነው። ወሬው እየተደጋገመ ሲነገር ታሬክ ይመስላል፤ ከጫካ የወጡ ግን ጫካው ከአእምሮቻቸው ያልወጣ አውሪዎች ኢትዮጵያን እያጠፉ አለማን የሚሉ፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር በሃይል የተፈጠረችው  የዛሬ መቶ ዓመት ነው፤ አንድ ብሔር ሌሎቹን ብሒረተሰብ ጨቁኗል የሚሉ፤ የብሔር ብሕረሰቦች እኩልነት እናመጣለን እያሉ የግለሰቡን መብት የማያከብሩ፤ ነፃነት ምን እንደሆነ የሚያውቁ አውሪዎች ናቸው። ታሪክ ጸሐፊ “ሁኔታው” ሲፈቅድለት ከላይ የተጠቀሰዉን ከመረጃ ጋር ሆኖ ሕበረተሰቡን የነበረበትን “ሁኔታ” ተቀነባብሮ ሲቀርብ ያለፈው ትውልድ ታሪክ ይሆናል። መጭዉም ትውልድ ከአለፈው ትውልድ ይማራል፤ ጥፋትም አይደጋገምም። ታሪክ የጥፋት ማረሚያ ክፍለ ትምሕርት ነው፤ በወሬ የሚታረም ነገር የለም፤ ወሬ የሚያመጣው ሊላ ወሬ ነው። ከዚህ አያልፍም። በዚህ አርዕሥት ላይ በሚቀጥለው ጽሑፍ ላይ ስለሚቀርብ አሁን ወደ ቤተክርስቲያኑ ማጠቃሊያ ታሪክ እንሂድ።

እዚህ ላይ ለማጠቃላያ በአጭሩ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዌ ሂደት ለምዕመን ይቀርባል፤  አንባቢ በታላቅ አትኩረት መመልከበት ያለበት የዚህ ታሪካዊ ሂደት መሆኑና ያለመሆኑን አረጋግጦ ስለቤተ ክርስቲያኑ ያለዉን ግንዛቤ ለማጎለመስ ነው፤ ይህም ማለት ለምን ሆነ ብሎ ለመጠየቅ  አይደለም፤ በሂደት ታሪኩ ስለተከናወነ ወደኋላ ተመልሶ ማረም አይቻልም፤ ነገር ግን አንባቢ ማድረግ የሚችለው ያለፈዉን ታሪክ ተመልክቶ አስተያየት ከሰጠበት በኋላ የተደረገ ስህተት ከአለ ወደፊት እንዳይደገም የማስተካካያ ሁኔታ ፈጥሮ ለማረም ነው፤ ለዚህ ነው ታሪክ የስህተት ማረሚያ ትምህርት ክፍል የሆነው፤  ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው አንድ አዋቂ ስለታሪክ ሲተርክ “ስህተትን ከታሪክ የማይማሩ ፍጻሚያቸው ሞት ነው” እንዳለው ይሆናል። ያለፈዉን ታሪክ ሳናወቀው ሊላ የታሪክ “ሁኔታ” ተፈጥሮ የጥፋቱ ሰለባ መሆን የተለመደ ነው። የሥነ ጹሑፍ ሥርዓት ያለበት አገር የማንበብ ባሕል የለም። የሰው ልጅ ደህንነት ከግንዛቢያችን ውጭ ስለሆነ ሃይማኖታችንን ትርጉም አሳጥቶታል፤ አካላችን ከፈጣሪያችን ጋር መወሐዱን ባለማወቅ እንደፈረዋለን፤ እናዋርዳወለን፤ እንገደልዋል፤ ፈጣሪያችን እንድንሰራበት የሰጠንን መክሊት ቀበረን ያልሰራንበትን ዋጋ እንዲሰጠን በመጮህ እንፈታተነዋለን፤ መስራት ሲገባን ቁጭ ብለን አምጣ እያልን እንፈታተነዋለን፤ የሆነ ያልሆነዉን ነገር በማሰብ ግዜያችችንን እናባክናለን፤ ብዙ የሕሊና ደግሞም የሥነ ልቦና ችግሮች ስለአሉ በአጭሩ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ሳይፈቱ ሥርዓተ አልባ ሆነን ቀርተናል። ይህንን ሁሉ ችግር መፍታት የምንችለው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም ነፃ [autocephalous] ስትሆን ብቻ ነው። ለ1600 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንችን ከመንግሥት ጋር ተጣምራ እንደቆየች ለካህናቱም ሆነ ለምዕመን ማስረዳቱ ቀላል ስራ አይደለም።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪካዌ ሂደት በጣም ረጅም ስለሆነ አንባቢ በጥንቃቄ ጉዞዉን መመልከት ይኖርበታል፤ በ 1600 ዓመታት ግዜ ዉስጥ ታሪካዌ ሂደቱን በዝርዝር እንመልከት።

  1. ክርስትና ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ገባ፤ ሂደቱ ቢያንስ ከመቶ ዓመት
    በላይ እንደሆነ የሚያሳየን መረጃ ሕገ ኦሪት ከክርስትና በፊት ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ በቢተመቅደሱ እንደነበረ የታሪክ ቅርሶች በመረጃነት ሊቀርቡ ይችላል፤
  2. ቤተክርስቲያናችን በመንግሥት ደረጃ ሆኖ ዕውቅና ያገኝው በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ነው፤ ስለዚህ ክርስትና የመንግሥት አካል በመሆን እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥትን እያገለገለች ትገኛለች፤
  3. የመንግሥትና የቤተክርስቲያንን ግንኙነት ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፤

ኮኒቲ ሮሲኒ ስለ ግብፁ ፓትሪያርክ አቡነ ዮሃንስ ታሪክ ሲጽፍ የዛጓዌን ዘመነ መንግሥት የተነሳበትን ዘመን [1147-67] መነሻ በማድረግ ነበር፤ በግዜው የሰሎሞናዉያን መንግሥትን ጥሎ የነገሰው ንጉሥ ለግብፅ ፓትርያርክ ለአቡነ ዮሃንስና ለአገሩ መንግሥት ገዥ ለነበረው ለአሊ ኢቭን ሳላር [1153] በግዜው የነበረዉን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሚካኢል የመንገሱን ዕውቅና አልሰጥም ስለአለ እሱን የሚተካ  ሊላ ጳጳስ እንዲላክለት ቢጠይቅ ፓትርያርኩ ሊቀጳጳሱን በመደገፍና ጳጳስ በሕይወት እስክ አለ ድረስ ሊላ ጳጳስ መሾም ከቤተክርስቲያኑ ሕግ [ቀኖና] ዉጭ ስለሆነ ስለከለከለ አገረ  ገዥው ፓትሪያርኩን አስሮ ሊላ ጳጳስ እንዲላክ አድርጓል። በአባ ሚካኢል ገድል እንደትጻፈው ጳጳሱ የሰሎሞንዉያንን በትረ መንግሥት የጣለዉን የዛጓውን መንግሥት አልቀበልም በማለታቸው መሆኑን ነው [see Taddesse Tamarat: Church and Sate in Ethiopia. Oxford Clarendon Press, 1972 P. 55]።

  1. እላይ እንደተጠቀሰው የዛጓዌን መንግሥት ተቀበላ በአወዳሽነት አገልግላላች
  2. በ1270 የሰለሞናዌ መንግሥት ከዛጓዌ ላይ መልሶ ሲወስድ ሲሶ መሪት ተቀባላ የሰለሞንን መንግሥት አወድሳ ተቀብላለች፤
  3. በዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ዉስጥ የየክፈለ አገሩን መስፍን በማወደስ የተክፋፈለ አገዛዝን አወድሻለች [see Bahru Zewede: A History Modern Ethiopian 1855-1974, Ohio Universit Press, 1991]፤
  4. በአድዋ ጦርነት ግዜ የአክሱም ካህናትና መነኮሳት በመቀሌ ላይ ተስብስበው የጄሪናል ቫራቴርን ድል ማድረግ ሲጠባባቁ የኢትዮጵያ ጦር ስለአሸነፈ የሚንልኪን ማሸነፍ በማህሊትና በወረብ በከረቦና በጽናጽን ደስታችውን በመግለጽ የኢትዮጵያን ድል አድራጊነት ተቀብለዋል [see Raymond Jonas: The Battle 0f Adwa: African Victory in Age of Empire, Harvard University Press, 2011, pp200-237]፤
  5. አፄ ሚንልክ የልጅ ልጃቸዉን አቤቶ እያሱን ሚካኢልን በአልጋ ወራሻነት ሲሾሙ ጃን ሜዳ ላይ ሊቀ ጳጳሱንና ካህናቱን ሰብስበው በኢትዮጵያው ሊቀ ጳጳሱ በአብነ ተክለ ሃይማኖት ቃለ አልጋወራሹን ልጅ አቤቶ እያሱን እንዲቀበሉ ቃለ መሐላ ተደርጎ ከተፈጸመ በኃሏ አፄ ምንሊክ ሲሞቱ በተደረገው የሥልጣን ስኩቻ ቀሳዉስቱና ካህናቱ በማበር ሊቀ ጳጳሱን ያለፈቃዳቸው ምሕላዉን እንዲያነሱ በማስገደድ ቃል ኪዳኑ እንዲፈርስ ትልቁን መስትዋጽኦ በማድረግ የቤተ ከርስቲያኑንን ቀኖና ተላልፈዋል [see W. Yefru. The Nile Valley Civilization: A Histriographical Commentary on Ancient Africa. Pollock Press, 2016, pp 285-350]፤
  6. ጣሊያን አገራችንን በወረረበት ወቅት ቤተክርስቲያናችን ከጠላት ጋር በመተባበር አቡና ጴጥሮስና አቡነ ሚካኢል ያደረጉትን ሰማዕታትንት ሳይቀበሉ የጠላት አወዳሽ በመሆን የኢትዮጵያ ሕዝብን መከራ ሳይካፈሉ ቀርተዋል [see John Spencer: Ethiopia at Bay, Tsehay Publisher];
  7. ደርግ ሁለተኛዉን ፓትሪያርክ አቡነ ተዎፍሎስን በጥይይት ደብድቦ ሲገደል ቀሳዉቱና ካህናቱ ሰልፍ በመዉጣት ለገዳዩ መንግሥት ድጋፋቸዉን በመስጠት አወድሰዋል፤
  8. ወያኔ ኢትዮጵያን በመውረር ሥልጣን ሲይዝ በመተባበርና በማወደስ ለሚያደርገው ፍጅት ድጋፍ ከመስጠታቸውም በላይ በካዴረነት እያገለግሉ ይገኛሉ፤
  9. አሁን ይህ ጽሑፍ በሚዘጋጅበት ወቅት ቀስውቱና ካህናቱ መስቀል ይዘው በማንነታችን ብቻ በጅምላ አንገደለም በማለት ራሳቸዉን በሚከላከሉ ወጎኖች ጋር በመሂድ ትጥቃቸዉን ለማስፈታት የካድሬ ስራቸዉን በመስራት ላይ ይገኛሉ፤ አሁን አንድ ሲኖድ አንድ መንበር እያሉ የሚጮሁ ካድሬዎች የወያኒን መንግሥት ቀጣይነት የሚፈልጉ ግለሰቦች ስለሆኑ ምዕመን ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ በአንክሮ ተመልክቶ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ ግዲታ ነው።

እንግዲህ አንባቢ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን 12 ነጥቦች ተመልክቶና አመዛዝኖ ሚዛናዌ ዳኝነቱን እንዲሰጥበት ነው። እዚህ ላይ በአንክሮ መመልከት ያለብን የቤተክርስቲያናችንን ሥነ መልኮትና ሥርዓት ነው፤ የተዋህዶ እምነታችን ምንም እንክን የለበትም፤ ይህንን ለይተን ማወቅ አለብን፤ ቀሳዉስቱና ካህናቱ እንደኛው ሰው ናቸው፤ ልዩነታችን እነሱ በቤተክርስቲያኑ ዉስጥ ሆነው እኝን እንዲያስተምሩና በግብረ ገብነት እንዲያጎሎሙሱን ነበር፤ ነገር ግን ይህንን የተስጣቸዉን ኃላፊነት አልተወጡም፤ የቤተክርስትያኑን ሥርዓት አጓድለው ምዕመንን አዋርደው የቤተክርስትያኑን  ሥራ ትተው አላማዊ ስራቸዉን የሚያክናዉነበት ቢት አድርገዉታል። እዚህ  ላይ ውይይቱ ይህንን ጥናት ከአደረገው ጸሐፊ ጋር መሆን የለብትም፤ ከላይ በዝርዝር ተደረጉ የተባሉት ነገሮች በርግጥ ሆነዋል ከተባለ አስፈላጊዉን እርምጃ ወስዶ ቤተ ክርስቲያንችንን ማስተካከል የምዕመኑ ኃላፊነት ነው፤ ግን እንደዚሁ በመታወር ለሃይማኖቲ እቆማለህ ማለት የትም አያደርሰነም፤ ምናልባትም የኛ የተዋህዶ እምነት ተከታዮች የመኖርና  ያለመኖር እድላችን የመነመነ እንደሚሆን መጠራጠር የለብንም፤ ተደርገዋል የተባሉትን ጥፋቶች ማረም ይኖርብናል ወይም ጥፋታችን መልሶ እንደሚያጠፋን ማወቅ አለብን፤ ትዕቢታችን፤ መጎደኞች መሆናችን፤ ያለመካባበር፤ ኃሳብ ለኃሳብ እንዲይሽራሽር ማድረግ፤ የአምባ ገነንት ጠባያችን የሚወስደን መንገድ የጥፋት መንገድ  ነው፤ ቤተ ክርስቲያናችንን እምንወድና እምናከብር ከሆነ በሰከነ ልብ የተዋህዶ እምነታችንን እንጠ ብቃት፤ ጥፋትም ሲኖር በቅን ልቦና እናርመው፤ በተቃና ልቦና ለመማር ሳንቸኩል ተደረጉ የተባሉትን አጥንተን ግዜ ወስደን እናስተካክል።

በመጨረሻ ግዚያችሁን ወስዳችሁ ይህንን አጭር ጥናት ስለተመለከታችሁሉኝ ምስጋንዮ እጅግ ከፍ ያለ ነው። በሊላ ጉዳይ ላይ አጋጣሚ አግንቺ ለመጻፍ ቸርነቱ የሚያልቅበት አምላክ ፈቃድ ይሁን፤  ወስብሐት ለእግዚአብሒር»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»

 

 

 

 

 

 

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop