(ተንሳይት በቃና)
ወልቃይትና ጠገዴ በፍጹም የትግራይ ክልል እንዳልነበሩ የሚያሳይ ነው።ይህም “The Book of Axum.. shows a traditional schematic map of Tigray with its city Axum at its Center Surrounded by the thirteen principalprovinces: Tembein, Shire, Seray Hamasen,
Bur,Sama, Agame, Amba Senait, Geralta, Enderta, Sahart andAbergele” የሚል ነው።ማጠቃለያ የወያኔ መንግስት ግፈኝነት፣ ዘረኝነት፣ ጠባብነት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አየፈጀ ያለበትና፣ በተመሳሳይ ከዚህ በፊት እንደለመደው የእውሸት ፕሮፓጋንዳ ወይም ቅስቀሳ የትግራይን ሕዝብ በመጠቀም በማካሄድ ያለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። እውሸትን ዛሬም የወያኔ ባለስልጣናት እንደ እንድ የትግል ዘዴ በመጠቀም አየዋሹ በመቀስቀስ ላይ እንዳሉ ነው።ይህንን በተለይ የትግራይ ሕዝብ ሃቁን በመከታተል የወያኔ ባለስልጣናት የእውሸት ቅስቀሳ ሰላባ ላለመሆን ድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል። በአገራችን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዜህ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ለማላቀቅና ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የምትመሰረትበትን፣
እንዲሁም የመገንጠል ጥያቄ የማይነሳባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁለት አማራጮች ይኖራሉ። አንደኛው አማራጭ፣ በአገርና በሕዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሲባል የወያኔ መንግስት እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት በሚፈጠረው የሽግግር መንግስት ሲጠቃለልና ሲቋቋም ነው።ይህም የወያኔ መንግስት የዴሞክራሲያዊ አሰራር መርሆችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሲቀበልና አሁን እንደ መንግስት የሚቆጣጠራቸውን የመንግስት መዋቅሮችን የስልጣን አውታሮች መሉ በሙሉ ራሱን ካገለለ፣ የመጨቆኛ መሳሪያዎቹ ፈርሰው ስልጣኑን ለሚቋቋመው የሽግግር መንግስት የሚያስረክብ ሲሆን ብቻ ነው። ሁለተኛው አማራጭ፣ የወያኔ መንግስት በአንደኛው አማራጭ መሰረት ሰላማዊ ሽግግሩን የማይቀበል ከሆነ፣ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች በሙሉ የጋራ የሽግግር መንግስት ፕሮግራም በጋራ ነድፈው፣ ለነደፉትና ለተስማሙበት የሽግግር መንግስት ፕሮግራም ትግላቸውን መቀጠል ይሆናል። የመጀመሪያው ዓላማቸው የዘረኛውን የወያኔ መንግስት ከስልጣን ማስወገድና ከዚያ የጋራ የሽግግር መንግስት ለማቋቋምና ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል። ተንሳይት በቃና
ሰፕቴምበር 19 ቀን 2016 ዓ.ም.