ጀዋር እና ኢስላማዊት ኦሮሚያ (ለያሬድ አይቼህ መልስ)

ከብሩክ ደሳለኝ
በህይወቴ ከመጠላው ነገር ቢኖር ከንቅልፌ ሚቀሰቅሰኝና በባዶ ሜዳ ሚንጅሰኝ ሰው ነው። አንድ አማራ ሲያልፈ የሰማውን ስም ወስዶ በብእር ስም የሚያደርቀን ያሬድ አይቼህ ሚባሉ ግለሰብ እንደ ትሪፓ ማይታኝክ ሃሳባቸውን እየነሰነሱብን ይገኛሉ። በየጠላቤቱ የተወራ ሁሉ ፖለቲካ ሚመስለው በዛብን። በተለይ እኛ ወጣቶች አበሳችንን ሚያበዛብን ብሽ ሆነብን። አማሪኛው ልክ ኦነጎች እንድሚጽፉት እንግሊዝኛ የሰዋሰው ውርጅብኝ ይበዛበታል። ማለትም ሁለት ነጥብ እና አራት ነጥብ በተነፈሰ ቁጥር ያስገባል። እነዛ ኢንግሊዝኛ ሲጽፉ ኮማና ኤክስክላሜሽን ያበዛሉ። ወደ መጣሁበት ሃሳቤ ስመጣ ፥ አዲስ የፖለቲካ አመለካከት ያምጡልን መስልዋቸው አቶ ያሬድ ድህረግጽን ጠጅ ቤት አድርገውብናል። 
አቶ ጀዋር አልጀዚራላይ የፖለቲካ መከረባበት ላደረጉት አስተያየት በሰጡበት “ጀዋር መሃመድ እና የአማራ ልሂቃን” በሚል ርእስ በጻፉት መጣጥፍ ላይ ፈላስፋው እንደነገሩን ከሆነ አማራ ምትባል ብሄር ብታርፍ ይሻላታል ብለውናል። ያ ሲገርመን ያማራ ቅቦች ለካስ ንቀው ሲተው የተፈሩ መስልዋችው አብዋራ ያስነሳሉ። ለንደዚ አይነቱ መልስ መስጠት መውረድ ነው ብዬ ባስብም ሊያርፍ ስላልቻለ ትንሽ የሃሳብ ኩርኩም የሚያስፈልገው ይመስላል። አስርደቂቃ እሱላይ ማትፋቴ ቢያበሳጨኝም የሚላቸው ነገሮች መርዝ ስለሆኑ ትንሽ ወደሱ ደረጃ መውረድ ያስፈልጋል። ምንን ምን ካላሉት ምን ላይ ይቀርባል ይላለ የሸገር ልጅ። እናም ከጽሁፋቸው ቆንጠብ አድርገን “….ዐማራዎች ሆይ! የድሮዋ እትዮዽያ ተመልሳ አትመጣም። አማርኛ ቇንቇ ሁሉም የሚናገርባት ….ወዘተ ይሉናል። እያንዳንዱን ብንነጋገርበት አመት ይፈጃል።
ግን ኢትዮዽያውስጥ ሌላ ብሄር አማሪኛ ባወራ ቁጥር በፊደል ለጎጃም ገበሬ ሚከፈለው መስሎት ይሆን? አላዋቂ ሳሚ አለ። ብቻ ሰብዬው በሞቅታ የጻፉትን አንቡትና ተገረሙ። ካመለካከቱና ጽሁፉላይ እንደሚያራምደው ስነልቦና ነኝ የሚለውን ብሄረሰብ ሳይሆን ምን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ያሳያል።  ደሞ ያ ሳያንሰን አንድ ጭስ ጭስ የሚል “ጃዋር እና ኢስላማዊት ኦሮሚያ” በሚል ርእስ ሌላ ጽሁፍ ድህረገጽ ላይ ደፉብን። አቶ ጀዋር በቃዡ ቁጥር የህልማቸው አስተርጉዋሚ ሆነው አቶ ያሬድ ከች ይላሉ። የባለፈው ጽሁፉ ላይ ከታች ብዙ አስተያየትና ምክር ቢለገስም ሰውየው ሊማሩ አልቻሉም። አዙረሽ ለበሽ ሲልዋት ገልብጣ ለበሰችው ይላል ያገሬ ሰው። እናም ባጭሩ እዚች ላይ ላብቃ። ትንሽ ከቆየሁ የኔንም ስም ይወስድና ስሙን ይቀይራል። ደሞም እንደ አቶ ያሬድ የማይታኝክ ስጋ ሳልሆንባቹ በዚቹ ላጥ ብል ይሻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወንጭፍና ድራጉኖፍ

13 Comments

  1. Forget Jawar, he is one bloody opportunist who is trying to give life to his dead and buried OLF by hijacking the Ethiopian Muslim’s struggle against forced imposition of Ahbash. He won’s succeed in attaining his fantasy except causing more pain to the Muslims backhome.

  2. Mr. Bruk,

    “Ye Onegoch Sewasew”, Calm down baby!

    You have way to go to even utter a word about “Onegoch”. Ask your masters about the writing styles and the English language skills of those “Onegoch”. I know that you don’t like them. Keep on disliking but you had no luck about the other part you wanted to criticize.

    Tortora!!

  3. Yared’s use of the words “Lihikan” and “Tsinfegna” indicates his intent to say that he is perfect in Geez. I realy hate these kinds of words which degrade the quality of Amharic. No doubt, he is a Tigre or he has served Tigres for several years or better they were his baby sitters.

  4. የሠው ልጅ በአስተሳሰቡ ፣በስራው፣የሚለካበት ሐገር ላይ እየኖሩ፣
    ዘላለም ስለዘር ጐሳ ፣ብሔር ፣ሀይማኖት፣የሚደሰኩሩ ጠባብ አስተሳሰብ
    ያላቸው ሰዎች ግርም ይሉኛል ።ምን አይነት የጭንቅላት መበደል ነው ፣?
    በሽተኞች ፣አምላክ ይቅር ይበላችሁ፣ሀገር ቤት ያለውን ወገን ግን
    እግዚአብሔር አምላክ ይታደገው።

  5. I am classical oromo and Shegerian but when I read all this mambo Jambo about Jewar, I started asking myself, was Meles after all right all the way when he talked about Ethiopian history ?

    We are talking human right issue but we don’t let people to express their idea. For God sake can we all keep quite.

    Why do we have to fight weyane, give me one good reason. I have never supported Weyane in my life but I am revisiting my political stand…..

  6. First ethnic politics and now relegion is being added to stir up oromo. jawar is becoming more and more controversial and he now says he looks at the oromo problem from islamic perspective. If relegion is the issue why should all people who have allegiance to that relegion be together and defend their faith. why should they be split on ethnic/tribal/regional/village lines.

    this approach wont help anybody.

    That is where ethnic or relegious politics fails. You have to fulfill certain criteria to be considered a member.

  7. አዎን ክብር ይድረስዎ ብሩክነትዎ ደስአለኝ! ዘወትር አማራ ለመሆን በትጋት የሚጥሩት አቶ ግርማ ካሳና ያሬድ ሰው ሆነህ አይቼህ… መርዝ እንደበላች ውሻ ከድረ ገፅ ድረገፅ ይቅበዘበዛሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መች ዋዛ ነው ‘መቅድስ’ እደገባች ውሻ በቅዝምዝም ያበራቸወል፡፤ አይ ቅሌት! ግለሰቡ አርስትና መልኩን እንደ እስስት እየቀያየረ ይቀሳፍታል። ማታ ማታ ያዋጡትን ጠዋት ዘ-አባሻ ላይ ይተፋዋል። አዎን ይህ ግለሰብ የመናገር መብት፤ሐሳብን መግለፅ መብት፣የግለሰብ መብት፣ የሚለውን ሠምቷል ግን “አፍ መክፈት” እደጃዋር ኦሮሞን መጀወር እንደሆነ አልገባውም!! አፌድን ኦብኮ ደለኮ ማላት የለም ሁላችሁም ሰማንያ ከመቶ የእስላማዊ ኦሮሚያን ለመመሥረት የምትታገሉና የምንታገል ሙስሊም ኦሮሞ ነን እኛ ነፃ ካልሠጣን ነፃ አትወጡም! ተብሎ፡፤ በሊቁ የኦሮሞኢስላማዊ መሪው ጃዋር ተፈርጃችኋል ነጂብም የሙስሊሙም መሪ ሁላችንም ኦሮሞ እስላም ነን ብለዋል አረጋግጠዋል። ስለዚህ ይህ ድምፃችን ይሰማ የማነው? የእስላማዊ ኦሮሚያ እንገንጠል ጥያቄ ወይንስ የመልካም አስተዳደርና ፍትህ የኢትዮጵያ አብሮ መኖር ሙስሊሞች ጥያቄ? ግርማ ካሳ፣ ጃዋር፣ ያሬድ፣ፋሲል አዳነ፣ተስፋዬ ገብረእባብም ቢሆን አርፋችሁ ተቀመጡ። ከፋፋይ፣ ዘረኛ፣ አስገንጣይ ወንበዴን፣ እንቃወማለን ህዝባችን ማናቸውም ብሔር ‘በሜንጫ’ አንገቱ እንዲቀላ አንፈልግም። እዚህ ላይ አስታራቂ ሐሳብ ማሻሻያ፣ ማስተባበያ፣ የሚያቀርቡና የሚያዘናጉ ሁሉ መፈተሽ አለባቸው የአቶ መስፍን ነጋሽም ጽሑፍ ሌባን ያባብላል። የአቶ ተድላ አስፋው ቆራጥ ውሳኔና ሐሳብ ግን ቀጥተኛ ነው።

    ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ፣ ይህ የሚሺኒረስት የፋፋና ወተት ዲቄት ትምህርት ይቁም! ደግመን በመሳሳት ረሀብተኝነታችንን ብቻ ሳይሆን መሐይምነታችንንም በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን አናንፀባርቅ የነጭ የሸቀጥ ማራገፊያ አንሁን ህዝባችን በሰላም፣ በደስታ፣ ይኑር! ልዩነታችንን በማጥበብ አወናባጅን በማጥራት፣ ሕዝብና ሀገር በባዕዳን ከመወረሱ በፊት እንድረስ! ኢትዮጵያን እናድን! አስመሳይ ሆድአደር፣ አድርባይ፣ ቀሳፋችን ግዜና ቦታ አትስጡ! ለዚያ የዋህ ድሃ አማራና ኦሮሞ ወይንም የደቡብ ህዘብ የአልቅት ውሃ ከመጠጣት ትኋንና ቅማል ከመበላት ያዳነው የለም!።አራት ነጥብ፡፡ ጃዋር የታሸገ ንፁህ ውሃ እየጠጣ፣ ጫት እየቃመ፣ሳንድዊች በኮካ ኮላ እየገመጠ፣ ‘ሜንጫ’ ይዞ ሚኒያፖሊስ ይፎልላል…. አተላ በለው! የብሔር ብሔረሰብ ጭፋሮና ሽለላ የልጅ ቆሎና ቂጣ አይሆንም! ሕዝባችን ገና ፸፭ ከመቶ ቂጡን በሥርዓት አልሸፈነምና!? ሌባ አስመሳይ ይውደም ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ለዘለዓለም ተከብረው ይኑሩ።የማናቸውም ዲያስፖራ ትምህርትና ሐሳብ ከጥቅሙ ጉዳቱ አመዝናልና የሀገሩ ህዝብ የራሱን ፍላጎትና የመኖር ሁኔታ በራሱ ታግሎ፣ሀገርና ባህሉን ለመያዝ ለድል ይብቃ አሜን በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

  8. Blame it on Amhara is the new trend . I am kind of disappointed Yared (Hagos) forgot to add the following calamities on “blame it on Amhara” list.

    —The Aids virus

    —The civil war in Syria

    —The first and second world wars

    —The bombings of Hiroshima and Nagasaki

    —Drought in Africa and Hurricanes in North America

    —The expected death of Nelson Mandela….etc.

    Dig this! Eritrea gained its so-called “independence” at Woyane’s watch. Unless Woyane is the new Amhara the accusation doesn’t hold water. Ethiopian Muslims extreme or not have become vocal during Woyane’s reign for obvious reasons. In fact, Woyane’s doctrine paved the way to all kinds of extremists. So, how on earth Amhara gets the blame? Even a school child knows Amhara is toothless at this moment to even lift a finger. Amhara is not on the drivers seat leading Ethiopia to the brink. Don’t get confused with the likes of fake Amhras such as Bereket Simone who is committing crimes against humanity in the name of Amhara. In Ethiopia today, what you see is not what you get. Amhara has nothing to do with the separation of Eritrea or the flourishing of Muslim extremists. Woyane and paid agents like Hagos aka Yared are responsible for the chaos Ethiopia finds itself today. Blatant lies is the requirement to paid agents of Woyane and Yared happens to be one of them. A dirty Woyane sewer rat masquerading as an Amhara. Stop bashing Amhara!

    FREE ALL POLITICAL PRISONERS IN ETHIOPIA!!!!

  9. ጃዋር ለፕሮፓጋንዳው እንዲጠቅመው አድርጎ ያነበበው ታሪክ ወንዝ የማያሻግር መሆኑን ለማየት ይቻላል። በብዙ ብሄርተኞች ላይ እንደሚታየው ጃዋር በታሪክ ላይ ተሳልቋል፣ ታሪክም በጃዋር ላይ ተሳልቋል። እንዳለመታደል ሆኖ የጥንትኦሮሞዎች የጽሁፍ ባህል አልነበራቸውም፣ ታሪካቸውንም ጽፈው አላስቀመጡም፤ ጃዋር የእነሱን ታሪክ ለማንበብ የግድ በግእዝ ወይም በአማርኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ማገላበጥ ሊኖርበት ነው፤ አማርኛን ደግሞ ይጠላል፣ አማርኛ ማንበብ በአማራ ባህል መወረር ነው ብሎ ያምናል፣ ስለዚህ ለጃዋር ያለው ምርጫ በአፈ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ተረቱን ታሪክ እያደረገ ጆሮ ለሰጠው ሁሉ ማቅረብ ነው፤ አፈ ታሪክ ደግሞ ረጅም ርቀት አይወስድም፣ ይኸው አሁን እንደምናየው መያዣ መጨበጫ የሌለው ነገር ያናግራል። ስለኦሮሞ ጥንተ-ታሪክ የተጻፉ የፈረንጅ መጽሀፍትም ቢሆኑ ብዙዎቹ በአባ ባህሬን መጽሀፍ ላይ ተንተርሰው ወይም በአፈ ታሪክ ላይ ተመስርተው የተጻፉ ናቸው። አንዳንዶቹ የፈረንጅ መጽሀፍትም ለጃዋርያውያን የሚመቹ አይደሉም፤ ለምሳሌ በጅ የተባለ የታሪክ ጸሀፊ ስለኦሮሞች ማንነት የጻፈው ጽሁፍ ብዙ ኦሮሞችን እንዳበሳጨ ለመመልከት የሚሻ ሰው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መጽሀፍት ቤት ገብቶ መጽሀፉን ተውሶ ማየት ይበቃዋል፤ መጽሀፉ በኦሮሞ ተማሪዎች ተሰርዞ ተደልዞ ታዩታላችሁ። እንደያውም በዩኒቨርስቲው የሚገኙ አብዛኞቹ የታሪክ መጽሀፎች ስርዝ ድልዝ አላቸው በተለይ ኦሮሞን የሚመለከቱ ክፍሎች። በጥንቶቹ የታሪክ መጽሀፍት ውስጥ The Oromo Migration ( ስደት) የሚለው ሀረግ The Oromo Expansion በሚለው እየተሰረዘ እንዲተካ ተድርጓል። ታሪክ አስተማሪዎችም ኦሮሞ ተስፋፋ እንጅ ተሰደደ ብለው እንዳያስተምሩ ታዘው ተግባራዊ እያደረጉት ነው። አንድ ጊዜ ፕ/ር መርእድ ወ/አረጋይን “ለምን?” ብየ ጠይቄአቸው ነበር። “ታሪክ ሰዎችን አብረው እንዲኖሩ እንጅ እንዲለያዩ አያበረታታም” ብለው መለሱልኝ። ልክ ነበሩ። ኦሮሞ ተስፋፋሁ እንጅ አልተሰደድኩም ቢል ኢትዮጵያዊነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ በመሆኑ እቀበለዋለሁ። የእኔም ክርክር ኦሮሞ መጤ ሳይሆን ተወላጅ ነው የሚል ነው። እነጀዋር ግን ሳያውቁት አንዴ ራሳቸውን መጤ ያደርጋሉ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተወላጆች ነን ይላሉ። ታሪክን ማዛባት እንዲህ ያወናብዳል።ጃዋር የታሪክ ግድፈት አንዱን እንመልከት። “ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ከፕሮቱጋሎች እርዳታ በመቀበል ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ወግተዋል” ይለናል። ጃዋር ታሪኩን አዛብቶ ለራሱ በሚመች መልኩ አቅርቦታል። ክርስቲያኖች ፖርቱጋሎችን እርዳታ ከመጠየቃቸው በፊት ፣ ኦቶማን ቱርኮች ለግራኝ ሙሀመድ እርዳታ በመስጠት ልብነድንግልን እንዲወጋ አድርገውታል፣ ለዚህም ነው ግራኝ ያሸነፈው። ፖርቱጋሎች ገላውዲዮስን ለመርዳት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ክርስትናን ለማስፋፋት አስበው አልነበረም፤ (ፖርቱጋሎች ካቶሊኮች የኢትዮጵያ ንጉስ ደግሞ ኦርቶዶክስ እንደነበሩ አንርሳ)። ኦቶማን ቱርኮችም ግራኝን ሲደግፉ እስልምናን ያስፋፋልናል ብለው በማሰብ አልነበረም። ሁለቱም የዘመኑ ሀያሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ወይም እስልምናን የማስፋፋት አላማ አልነበራቸውም፤ የሁለቱም አላማ ቀይ ባህርን በመቆጣጠር ንግዳቸውን ማስፋፋት፣ ግዛታቸውን ማስፋፋት ነው። ለሁለቱም አገሮች ሀይማኖት እንደ መሳሪያ እንጅ እንደግብ ሆኖ አላገለገለም።

Comments are closed.

Share