ጎንደር ለሪፈር አንልክም የተባለች ወልቃይቴ ህይወቷ አለፈ

ሙሉቀን ተስፋው

የወልቃይት ነዋሪ የሆነችው የ30 ዓመቷ ወላድ እናት በኹመራ ሆስፒታል በ19/07/08 የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላት በሰላም ከተገላገለች በኋላ ተጨማሪ ህክምና የሚያስፈልጋት በመሆኑ የሆስፒታሉ ሐኪሞች የተሻለ ህክምና እንድታገኝ ወደ መቀሌ እንድትሄድ ሪፈር ሊጽፉላት ይዘጋጃሉ፡፡

በኹመራ ሆስፒታል የነበሩ የእንኩየውሽ ገሌ ቤተሰቦች ወደ መቀሌ ሳይሆን ወደ ጎንደር ሆስፒታል መውሰድ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶክተሮቹን ለጎንደር ሆስፒታል ይጽፉላቸው ዘንድ ይማጸናሉ፡፡ነገር ግን የካህሳይ አበራ ሆስፒታል ዶክተሮች የተጠየቁትን ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሶስት ቀናትን ‹‹ለጎንደር ሆስፒታል አንጽፍም ››በማለት ያባክናሉ፡፡

ከሶስት ቀናት ጭካኔ በኋላ ህመምተኛዋ እየተዳከመች መምጣቷን የተመለከቱት ዶክተሮች ለጎንደር ሆስፒታል ሪፈር ይጽፋሉ፡፡እንኩየውሽ ጎንደር ሆስፒታል በደረሰች በሁለት ሰዓታት ልዩነት ውስጥም ህይወቷ በማለፉ ይህችን አለም ተሰናብታለች፡፡

ሙሉቀን ተስፋው

ተጨማሪ ያንብቡ:  'ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ F ሰጥቼአለሁ" ጋዜጠኛና የህግ ባለሙያ አበበ ገላው

3 Comments

  1. እነዚህን ባለሙያዎች ማለት ኣይቻልም : ከጠበንጃ አንጋቾችም ኣይሻሉም
    ይሕ ኣይነት የወረደ ጠባብነትና ዘረኝነት ከሙያቸው የሚበልጥባቸው ከሆነ:: ጎንደር ሆስፒታል የሚሰሩትን የወያኒ አባላት እንዴት አምኖ መታከም ይቻላል?

Comments are closed.

Share