በኦሮሚያ በየቦታው የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ ነው – ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራን” አሉ

(ፎቶ ከፋይል)
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሥፍራዎች ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ:: ታክስ ሰብሳቢዎችም እንዲሁ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ግብር ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ሥራ መስራት እንደተቸገሩም ለማወቅ ተቻለ::

የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንዳመለከቱት በ አርሲ በባሌ በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ, በምስራቅ ሸዋ; በ ም ዕራብ ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ የአጋዚ ጦር አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ በየጫካው ሥር እንደሚገኙ ታውቋል””

በም ዕራብ ሸዋ አምቦ; አመያና ግንደበረት ባለፉት 3 ሳምንታት ብቻ ከ6 በላይ የአጋዚ ጦር አባላት ተገድለው ተገኝተዋል:: እንደ አይን እማኞች ገለጻ በግንደበረት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የአጋዚ ጦር አባላት ላይ ህዝቡ እርምጃ እንደወሰደም ታውቋል::
ከግንደበረት አካባቢ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም ህዝቡ ተፈትሮዋዊ ያልሆኑ ገደሎችን በመሥራት የአጋዚ ጦር መኪኖች ሲሄዱ እንዲገለበጡ በማድረግ ላይ እንዳለም ታውቋል::

በአሪሲ ሮቤ; መርቲ; ገደብ; እና ኮፈሌም እንዲሁ የአጋዚ ጦር አባላት እየሞቱ እየተገኙ ሲሆን መንግስት ግን ይህን ደብቆ እንደሚገኝ ታውቋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች ግብር ለመሰብሰብ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት አካላት ላይ ሕዝቡ ጥቃት በማድረሱ የተነሳ ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራነው ስለዚህ ሄደን ግብር ክፈሉ ማለት አንችልም” በማለት ሥራ እንዳቆሙ ለመረዳት ተችሏል:: ግብር ክፍሉ እያሉ በም ዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ የተንቀሳቀሱ የመንግስት አካላትን ሕዝቡ በቆመጥ ቀጥቅጦ እንዳባረረም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

ከም ዕራብ ወለጋ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም በተለይም በነጆ; በጃርሶና ጊምቢ አካባቢም ህዝቡ አድብቶ በመጠበቅ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የእስክንድር ጥሪና የቀጠለው የኢትዮጵያ ቢቲኒ ግስጋሴ | Hiber Radio Special program

3 Comments

  1. መበረታታት ያለበት የትግል ዘዴ ነው፥
    ሰው ባገሩ በሰላም እንዳይኖር ከተደረገና ከተገፋ፥ ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ጠላቱን ለማጥቃትና ለማሸማቀቅ ይገደዳል፥ በጠላት ዘመን መጀመሪያ ወራሪውን የኢጣሊያ ጦር፥ በኋላም ለጥበቃ ገብቶ ተጣብቄ ልቅር ያለውን የእንግሊዝ ጦር በምሽት ተደብቀው እንገቱን በሽቦ እየሸመቀቁ ይገድሉት እንደነበር ዓባቴ ዓጫውቶኛል፥

  2. At least I know for sure the people in central Oromia/Ethiopia gave hard time even for Italien with less support from outside let alone the banada clan. Therefore, TPLF will be buried in Shewa and Ethiopia will be free at last from banada who made us without port. A crime on 90 million people. Noone did this crime except TPL.

Comments are closed.

Share