በምስራቅ ጎጃም ደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ቀጣዩ እንደወረደ የቀረበው ዘገባ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ነው::

‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› ተማሪዎች

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ምንጮቹ ዛሬ ጥር 30/2008 ዓ.ም እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የሰሚስተሩን አጋማሽ ረፍት ጨርሰው ተማሪዎች ወደትምህርት ቤቱ ቢመጡት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ተማሪዎቹ ‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› በማለት መፈክር እያሰሙ ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ከርሟል ያሉት ምንጮቹ በዋናነት ከመመሪያ ውጭ በርዕሰ መምህርነት የሚሾሙት አካላትና የወረዳው የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ አላቸው ተብሏል፡፡

‹‹በክልሉ የሌለ አሰራር በመከተል በት/ቤቱ 4 ምክትል ርዕሰ መምህራን ተሹመውብን ቆይተዋል፤ ይህ መመሪያ ይጥሳል ብለን ታግለን አስወረድናቸው፡፡ ነገር ግን ከወረዱት መካከል አንዱን ርዕሰ መምህር አድርገው እንደገና ሾሙት፡፡ በዚህም ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ፤ እኛም ድርጊቱ ትምህርትን ይጎዳል ብለን ከዛሬ ጀምሮ አድማ ልናደርግ ችለናል›› ብሏል አድማ ከመቱ መምህራን አንዱ፡፡

በት/ቤቱ 141 መምህራን እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ከእነዚህ መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት የአድመውን ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡ የትምህርት ቤቱ አስተዳደርና የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት መምህራኑን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን እንጂ ኢህአዴግን አትቀበሉም›› እያለ ችግሩን ለመግፋት እየሞከረ እንደሆነም ምንጮቹ አክለው ግልጸዋል፡፡

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/12564#sthash.DNnywcVH.dpuf

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማን ሆነና ጠብ አስተናባሪው! - አሁንገና ዓለማየሁ

1 Comment

  1. በምስራቅ ጎጃም ደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ የሚለው ዜና እንደ ተጠበቀ ሆኖ በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉት ትምህርት ቤቶች ሳይውሉ ሳያድሩ ወደ ተቆዋሞ መቀላቀል ወሳኝ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው::
    “አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
    ያበላይ የልጅ ልጅ አይደለህሞይ
    ተነስ ተነስ” በማለት የወያኔን መንግስት ለህዝብ እንዲገዛና ወደ ሃገራዊ እርቅ እንዲመጣ ያስፈልጋል ይህን እድል ተጠቅሞ ወደ እርቅ የማይመጣ ከሆነ አያቶቻችን እንደሚሉት ” ምከረው ምከረው እምቢ ካለ …..” የአሁ ትውልድ ወጣት ደሞ እንዲህ ይበል መከርነው መከርነው አልሰማ ካለ በሰላማዊ ትግል አውርደን እንጣለው ተነስ ተነስ ማለት ያስፈልጋል:: ይህ ዓይነቱ በቃ አልገዛም ባይነት በምስራቅ; በምእርብ; በሰሜን በደቡብ መቀጣጠል አለበት::

    ታምራት

Comments are closed.

Share