ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መስከረም 2 ቀን 2008 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

<...በአገር ቤት የበዓል ሰሞን በዓል በዓል አይመስልም ። የበዓሉ ድባብ የለም። የሸቀጦች ዋጋ በጣም ጨምሯል። ድሮ ጤፍ በሀይለስላሴ ዘመን በደርግ ይባል ነበር ይሄ ትውልድ ከ97 በሁዋላ እንኳ ብዙ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪዎችን አይቷል...ውጥረት አለ የታፈነ ነገር ነው ብሶት አለ ይሄ በማንኛውን ወቅት ሊፈነዳ የሚችል ስርዓቱም ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ታሪኮች መረዳት እንደሚቻለው ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነው። በዚህ አገር ለውጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግሽግ ያስፈልጋል ቀውስ ከመምጣቱ በፊት ...> ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ከአገር ቤት የበዓሉን አከባበርን የብዙሃኑን ሕይወት በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<...የማህበራዊ ሚዲያው ፌስቡክም ሆነ ሌሎቹ ለለውጥ አስተዋጽዎ ማድረግ እንደሚችሉ የሰሞኑ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ብለን ያቀረብነው ጥሪና የተገኘው ሰፊ የሕዝብ ምላሽና ድጋፍ ማሳያ ነው ...አሁን ከዚህ በሁዋላ የማይከለከል ትውልድ እየመጣ መሆኑን ማሳያ ነው። እምቢ የማለትና መንገድ የመፈለግን ነገር አይተናል ወደፊትም በጋራ ለሚያቆሙን ጉዳዮች ማህበራዊ ሚዲአውን እንጠቀምበታለን። የኢትዮጵያውያን ፌስቡከሮች ባህሪ ከሌላው የተለየ ነው።ይሄም የሆነው ...> የትነበርክ ታደለ የቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት ዋና አስተባባሪ ስለ ስለ <<ኮንሰርቱ>> ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

የታጋይ ሞላን መክዳትና የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

የኢትዮጵያ ቀን በላስ ቬጋስ አከባበር(ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሞላ አስገዶም ከትህዴን ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን ተከታዮቻቸውን ይዘው በስምንት ላንድ ክሩዘር መክዳታቸው ተገለጸ

ከወያኔ ጋር ቀድመው ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ስርዓቱ ሞራሉን ለመገንባት የፈጠረው ነው ተባለ

የህወሓት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ በደህንነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማሳደድ ተሸጋገረ

በአገር ቤት ዘንድሮም በኑሮ ውድነቱ መባባስ ሳቢያ ለብዙሃኑ በዓሉ በዓል እንዳልመሰለ ተገለጸ

በአገሪቱ በሕዝቡ ውስጥ የታፈነው ውጥረት ፈጥኖ ሰላማዊ ሽግግር ካልተደረገ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተገለጸ

የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ የውጭ አገር ሰዎች ማስጠንቀቂያ አወጣ

ካይሮ ደቡብ ሱዳን ላይ ሰፊ የግብርና መሬት ወሰደች

የሆላንዱ ኩባንያ ራሱን ከአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ ጥናት ማግለሉነረ አስታወቀ

የመብረቅ አደጋ ኢትዮጵያ ውስጥ በተጠለሉ የደ/ሱዳን ስደተኞች ላይ የህይወት እና የአካል ጉዳት አደረሰ

በሑመራ በበረከት ከተማ በበዓሉ ዋዜማ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መካሄዱን ነዋሪዎች ገለጹ

የኡጋንዳው ፕ/ት ዩኤሪ ሙሴቬኒ ሰሞኑን ሶማሊያ ውስጥ ለሞቱት ወታደሮቻቸው ተጠያቂዎቹ <<እንቅልፋም>> መኮንኖች ናቸው አሉ

ሶማሊያዊው የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ሞሕ ፋራህ የተከለከለ እጽ ይጠቀም እንደነበር አመነ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቻልነው አቅም ሁሉ ከህዝባችን ጎን ነን - ወርቁ አይተነው
Share